የሉቃስ ወንጌል 12:51-53

የሉቃስ ወንጌል 12:51-53 መቅካእኤ

በምድር ላይ ሰላምንም ለመስጠት የመጣሁ ይመስላችኋልን? እላችኋለሁ፤ አይደለም፥ መለያየትን እንጂ። ከአሁን ጀምሮ በአንዲት ቤት አምስት ሰዎች ይኖራሉና፤ ሦስቱም በሁለቱ ላይ ሁለቱም በሦስቱ ላይ ተነሥተው ይለያያሉ። አባት በልጁ ላይ ልጅም በአባቱ ላይ፥ እናት በልጇ ላይ ልጇም በእናትዋ ላይ፥ አማት በምራትዋ ላይ ምራትም በአማትዋ ላይ ተነሥተው ይለያያሉ።”