ዘሌዋውያን 8:10-12
ዘሌዋውያን 8:10-12 የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) (አማ2000)
ሙሴም የቅብዐቱን ዘይት ወሰደ፤ ከእርሱም በመሠዊያው ላይ ሰባት ጊዜ ረጨ፤ ይቀድሳቸውም ዘንድ መሠዊያውንና ዕቃውን ሁሉ፥ የመታጠቢያውን ሰንና መቀመጫውን ቀባ፤ ድንኳኒቱንና ዕቃዋን ሁሉ ቀብቶ ቀደሳቸው። ከቅብዐቱም ዘይት በአሮን ራስ ላይ አፈሰሰ፤ ቀባው፤ ቀደሰውም።
ዘሌዋውያን 8:10-12 አዲሱ መደበኛ ትርጒም (NASV)
ሙሴም መቅቢያ ዘይቱን ወሰደ፤ ማደሪያ ድንኳኑንና በውስጡ የሚገኘውን ሁሉ ቀብቶ ቀደሰ። ከዘይቱም ጥቂት ወስዶ በመሠዊያው ላይ ሰባት ጊዜ ረጨ፤ ይቀድሳቸውም ዘንድ መሠዊያውን ከነመገልገያ ዕቃው ሁሉ እንዲሁም የመታጠቢያ ሳሕኑን ከነማስቀመጫው በዘይት ቀባ። ከመቅቢያ ዘይቱም በአሮን ራስ ላይ አፈሰሰ፤ የተቀደሰ እንዲሆንም ቀባው።
ዘሌዋውያን 8:10-12 መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) (አማ54)
ሙሴም የቅብዓቱን ዘይት ወሰደ፥ ማደሪያውንና በውስጡ ያለውን ሁሉ ቀብቶ ቀደሳቸው። ከእርሱም በመሠዊያው ላይ ሰባት ጊዜ ረጨ፤ ይቀድሳቸውም ዘንድ መሠዊያውንና ዕቃውን ሁሉ፥ የመታጠቢያውን ሰንና መቀመጫውን ቀባ። ከቅብዓቱም ዘይት በአሮን ራስ ላይ አፈሰሰ፥ ይቀድሰውም ዘንድ ቀባው።
ዘሌዋውያን 8:10-12 አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም (አማ05)
ከዚህም ቀጥሎ ሙሴ የቅባቱን ዘይት ወስዶ የተቀደሰውን ድንኳንና በውስጡ ያሉትንም ነገሮች ቀባ፤ በዚህ ዐይነት ሁሉንም ለእግዚአብሔር አገልግሎት የተለየ እንዲሆን አደረገው፤ ከዘይቱም ጥቂት ወስዶ በመሠዊያው ላይ ሰባት ጊዜ ረጨ፤ በዚሁ ዐይነት ለእግዚአብሔር አገልግሎት የተለዩ ይሆኑ ዘንድ በመሠዊያውና ለእርሱ መገልገያ በተሠሩት ዕቃዎች ሁሉ ላይ እንዲሁም በመታጠቢያው ሳሕንና በሳሕኑ ማስቀመጫ ላይ ረጨ። የቅባቱንም ዘይት በአሮን ራስ ላይ በማፍሰስ ቀብቶ ለእግዚአብሔር አገልግሎት የተለየ በማድረግ የክህነት ሹመት ሰጠው፤