ዘሌዋውያን 7:11-38

ዘሌዋውያን 7:11-38 አዲሱ መደበኛ ትርጒም (NASV)

“ ‘አንድ ሰው ለእግዚአብሔር የኅብረት መሥዋዕት በሚያቀርብበት ጊዜ፣ ሊከተለው የሚገባው ሥርዐት ይህ ነው፤ “ ‘መሥዋዕቱን የሚያቀርበው ለምስጋና መግለጫ ከሆነ፣ ከምስጋና መሥዋዕቱ ጋራ ያለ እርሾ የተጋገረና በዘይት የተለወሰ ኅብስት እርሾ ሳይገባበት፣ በሥሡ ተጋግሮ፣ ዘይት የተቀባ ቂጣ በሚገባ ታሽቶ፣ በዘይት የተለወሰም የላመ ዱቄት ኅብስት ዐብሮ ያቅርብ። ለምስጋና ከሚሆነው የኅብረት መሥዋዕት ጋራ፣ በእርሾ የተጋገረ ኅብስት ያቅርብ። ከእያንዳንዱም ዐይነት አንዳንድ አንሥቶ ለእግዚአብሔር የተለየ ቍርባን በማድረግ ያቅርብ፤ ይህም የኅብረት መሥዋዕቱን ደም ለሚረጨው ካህን ይሰጥ። ለምስጋና የሚሆነው የኅብረት መሥዋዕት ሥጋ፣ በቀረበበት ዕለት ይበላ እንጂ አንዳች አይደር። “ ‘መሥዋዕቱ ስእለት በመፈጸሙ ወይም የበጎ ፈቃድ ስጦታ ከሆነ፣ በቀረበበት ዕለት ይበላ፤ የተረፈውም ሁሉ በማግስቱም ይበላ። እስከ ሦስት ቀን የቈየ ማንኛውም የመሥዋዕቱ ሥጋ ይቃጠል። ማንኛውም የኅብረት መሥዋዕት ሥጋ በሦስተኛው ቀን ከተበላ ተቀባይነት የለውም፤ ርኩስ በመሆኑ ላቀረበው ሰው ዋጋ አይኖረውም፤ ከዚያም የበላ ሰው የበደል ዕዳ ይሆንበታል። “ ‘ርኩስ ከሆነ ነገር ጋራ የተነካካ ሥጋ ይቃጠል እንጂ አይበላ። ሌላውን ሥጋ ግን በሥርዐቱ መሠረት ንጹሕ የሆነ ማንኛውም ሰው ይብላ፤ ነገር ግን ንጹሕ ያልሆነ ማንኛውም ሰው ለእግዚአብሔር የቀረበውን የትኛውንም የኅብረት መሥዋዕት ሥጋ ቢበላ፣ ከሕዝቡ ፈጽሞ ይወገድ። ማንኛውም ሰው የሰውን ርኩሰት ወይም ርኩስ እንስሳን ወይም ማንኛውንም ርኩስ ነገር ቢነካና ለእግዚአብሔር ከቀረበው የኅብረት መሥዋዕት ሥጋ ቢበላ፣ ያ ሰው ፈጽሞ ከሕዝቡ ይወገድ።’ ” እግዚአብሔር ሙሴን እንዲህ አለው፤ “ለእስራኤላውያን እንዲህ በላቸው፤ ‘የበሬ ወይም የላም፣ የበግ ወይም የፍየል ሥብ አትብሉ። ሞቶ የተገኘ ወይም አውሬ የገደለው ከብት ሥብ ለሌላ ተግባር ይዋል እንጂ አይበላ። ለእግዚአብሔር በእሳት ከሚቀርብ እንስሳ ሥብ የሚበላ ማንኛውም ሰው ከሕዝቡ ይወገድ። በየትኛውም ቦታ ብትኖሩ የማንኛውንም የወፍ ዘር ወይም የእንስሳ ደም አትብሉ። ማንኛውም ሰው ደም ቢበላ፣ ያ ሰው ከሕዝቡ ይወገድ።’ ” እግዚአብሔር ሙሴን እንዲህ አለው፤ “ለእስራኤላውያን እንዲህ በላቸው፤ ‘የኅብረት መሥዋዕት ለእግዚአብሔር የሚያቀርብ ማንኛውም ሰው ስለ ራሱ መሥዋዕት አድርጎ ከዚሁ ላይ ለእግዚአብሔር ያቅርብ። በእሳት ለእግዚአብሔር የሚቀርበውን መሥዋዕት በራሱ እጅ ያቅርበው፤ ሥቡን ከፍርምባው ጋራ ያቅርብ፤ ፍርምባውን መሥዋዕት አድርጎ በእግዚአብሔር ፊት ይወዝውዘው። ካህኑ ሥቡን በመሠዊያው ላይ ያቃጥል፤ ፍርምባው ግን ለአሮንና ለልጆቹ ይሰጥ። የኅብረት መሥዋዕታችሁን የቀኝ ወርች ለካህኑ የተለየ አድርጋችሁ ስጡት። የኅብረት መሥዋዕቱን ደምና ሥብ የሚያቀርበው የአሮን ልጅ ቀኝ ወርቹን የራሱ ድርሻ አድርጎ ይውሰድ። ከእስራኤላውያን የኅብረት መሥዋዕት ላይ የተወዘወዘውን ፍርምባና የቀረበውን ወርች ወስጃለሁ፤ ለካህኑ ለአሮንና ለልጆቹም ከእስራኤላውያን የሚያገኙት መደበኛ ድርሻቸው እንዲሆን ሰጥቻቸዋለሁ።’ ” ካህናት ሆነው እግዚአብሔርን እንዲያገለግሉ በቀረቡ ቀን፣ በእሳት ለእግዚአብሔር ከቀረበው መሥዋዕት ላይ ለአሮንና ለልጆቹ የተመደበላቸው ድርሻ ይህ ነው። ካህናቱ በተቀቡበት ቀን፣ እስራኤላውያን መደበኛ ድርሻ አድርገው ከትውልድ እስከ ትውልድ ይህን እንዲሰጧቸው እግዚአብሔር አዘዘ። እንግዲህ የሚቃጠል መሥዋዕት፣ የእህል ቍርባን፣ የኀጢአት መሥዋዕት፣ የበደል መሥዋዕት፣ የክህነት ሹመት መሥዋዕትና የኅብረት መሥዋዕት ሥርዐት ይህ ነው፤ ይህም፣ በሲና ምድረ በዳ እስራኤላውያን መሥዋዕታቸውን ለእግዚአብሔር እንዲያቀርቡ ባዘዛቸው ቀን በሲና ተራራ ላይ ለሙሴ የሰጠው ሥርዐት ነው።

ዘሌዋውያን 7:11-38 የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) (አማ2000)

“ለእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር የሚ​ያ​ቀ​ር​ቡት የደ​ኅ​ን​ነት መሥ​ዋ​ዕት ሕግ ይህ ነው። ለም​ስ​ጋና ቢያ​ቀ​ር​በው፥ ከም​ስ​ጋ​ናው መሥ​ዋ​ዕት ጋር በዘ​ይት የተ​ለ​ወሰ የቂጣ እን​ጎቻ፥ በዘ​ይ​ትም የተ​ቀባ ስስ ቂጣ፥ በዘ​ይ​ትም የተ​ለ​ወሰ መል​ካም የስ​ንዴ ዱቄት ያቀ​ር​ባል። ለም​ስ​ጋና የሚ​ሆ​ነ​ውን የደ​ኅ​ን​ነት መሥ​ዋ​ዕት በአ​ቀ​ረበ ጊዜ እርሾ ያለ​በ​ትን ኅብ​ስት ያቀ​ር​ባል። ከቍ​ር​ባ​ኑም ሁሉ የእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርን ድርሻ ከእ​ነ​ርሱ አን​ዱን ያነ​ሣል። እር​ሱም የደ​ኅ​ን​ነ​ትን መሥ​ዋ​ዕት ደም ለሚ​ረ​ጨው ካህን ይሆ​ናል። “ለም​ስ​ጋና የሚ​ሆ​ነው የደ​ኅ​ን​ነት መሥ​ዋ​ዕት ሥጋም ለእ​ርሱ ነው፤ በሚ​ቀ​ር​ብ​በ​ትም ቀን ይበ​ሉ​ታል፤ ከእ​ርሱ እስከ ነገ ምንም አያ​ተ​ር​ፉም። የቍ​ር​ባ​ኑም መሥ​ዋ​ዕት የስ​እ​ለት ወይም የፈ​ቃድ ቢሆን፥ መሥ​ዋ​ዕቱ በሚ​ቀ​ር​ብ​በት ቀን ይብ​ሉት፤ ከእ​ር​ሱም የቀ​ረ​ውን በነ​ጋው ይብ​ሉት፤ ከመ​ሥ​ዋ​ዕ​ቱም ሥጋ እስከ ሦስ​ተ​ኛው ቀን የሚ​ቈ​የ​ውን በእ​ሳት ያቃ​ጥ​ሉ​ታል። በሦ​ስ​ተ​ኛው ቀን ከደ​ኅ​ን​ነት መሥ​ዋ​ዕት ሥጋ ቢበላ፥ አይ​ሠ​ም​ርም፤ ላቀ​ረ​በው ሰው የተ​ጠላ ይሆ​ን​በ​ታል እንጂ ቍር​ባን ሆኖ አይ​ቈ​ጠ​ር​ለ​ትም፤ ከእ​ር​ሱም የበላ ሰው ኀጢ​አ​ቱን ይሸ​ከ​ማል። “ርኩስ ነገር የሚ​ነ​ካ​ውን ሥጋ አይ​ብ​ሉት፤ በእ​ሳት ያቃ​ጥ​ሉት እንጂ። ንጹሕ የሆነ ሰው ሁሉ ግን ከሥ​ጋው ይብላ። ኀጢ​አት ሳለ​ባት፥ ለእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ከሆ​ነው ከደ​ኅ​ን​ነት መሥ​ዋ​ዕት ሥጋ የበ​ላች ሰው​ነት፥ ያች ሰው​ነት ከሕ​ዝ​ብዋ ተለ​ይታ ትጥፋ። ከር​ኩስ ሁሉ፥ ወይም ከረ​ከ​ሰው ሰው፥ ወይም ንጹሕ ካል​ሆ​ነው እን​ስሳ የነ​ካች ሰው​ነት፥ ለእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ከሆ​ነው ከደ​ኅ​ን​ነት መሥ​ዋ​ዕት ሥጋ ብት​በላ፥ ያች ሰው​ነት ከሕ​ዝ​ብዋ ተለ​ይታ ትጥፋ።” እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርም ሙሴን እን​ዲህ ብሎ ተና​ገ​ረው፦ “የእ​ስ​ራ​ኤ​ልን ልጆች እን​ዲህ ብለህ ተና​ገ​ራ​ቸው፦ የበሬ ወይም የበግ ወይም የፍ​የል ስብ ከቶ አት​ብሉ። የሞ​ተ​ውን ስብ፥ አውሬ የሰ​በ​ረ​ው​ንም ስብ ለሌላ ተግ​ባር አድ​ር​ጉት፤ እና​ንተ ግን አት​ብ​ሉት፤ ለእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር በእ​ሳት ከሚ​ቀ​ር​በው ከእ​ን​ስሳ ስብ የሚ​በላ ሁሉ ያች የበ​ላች ሰው​ነት ከሕ​ዝ​ብዋ ተለ​ይታ ትጥፋ። በመ​ኖ​ሪ​ያ​ዎ​ቻ​ችሁ ሁሉ የወፍ ወይም የእ​ን​ስሳ ደም ቢሆን አት​ብሉ። ደም የም​ት​በላ ሰው​ነት ሁሉ ያች ሰው​ነት ከሕ​ዝ​ብዋ ተለ​ይታ ትጥፋ።” እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርም ሙሴን እን​ዲህ ብሎ ተና​ገ​ረው፦ “የእ​ስ​ራ​ኤ​ልን ልጆች እን​ዲህ ብለህ ተና​ገ​ራ​ቸው፦ ለእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር የደ​ኅ​ን​ነት መሥ​ዋ​ዕት የሚ​ያ​ቀ​ርብ ሰው ቍር​ባ​ኑን ለእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ከደ​ኅ​ን​ነቱ መሥ​ዋ​ዕት ያመ​ጣል። የእ​ርሱ እጆች ለእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር የእ​ሳ​ቱን ቍር​ባን ያመ​ጣሉ፤ ፍር​ም​ባ​ውን በእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ፊት ቍር​ባን ያቀ​ርብ ዘንድ በጉ​በቱ ላይ ያለ​ውን መረ​ብና የፍ​ር​ም​ባ​ውን ስብ ያመ​ጣል። ካህ​ኑም ስቡን በመ​ሠ​ዊ​ያው ላይ ይጨ​ም​ረው፤ ፍር​ም​ባ​ውም ለአ​ሮ​ንና ለል​ጆቹ ይሁን። ከደ​ኅ​ን​ነት መሥ​ዋ​ዕ​ታ​ችሁ ቀኝ ወር​ቹን ለማ​ን​ሣት ቍር​ባን እን​ዲ​ሆን ለካ​ህኑ ትሰ​ጡ​ታ​ላ​ቸሁ። ከአ​ሮ​ንም ልጆች የደ​ኅ​ን​ነ​ትን መሥ​ዋ​ዕት ደሙ​ንና ስቡን ለሚ​ያ​ቀ​ርብ ለእ​ርሱ ቀኝ ወርቹ እድል ፈን​ታው ይሆ​ናል። ፍር​ም​ባ​ው​ንና የቀኝ ወር​ቹን ከእ​ስ​ራ​ኤል ልጆች ከደ​ኅ​ን​ነት መሥ​ዋ​ዕ​ታ​ቸው ወስ​ጄ​አ​ለሁ፤ ለካ​ህኑ ለአ​ሮ​ንና ለል​ጆ​ቹም ለዘ​ለ​ዓ​ለም ሕግ እን​ዲ​ሆን ከእ​ስ​ራ​ኤል ልጆች ዘንድ ሰጥ​ቼ​አ​ቸ​ዋ​ለሁ።” እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርን በክ​ህ​ነት ያገ​ለ​ግ​ሉት ዘንድ በተ​ቀ​ቡ​በት ቀን ለእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ከሆነ ከእ​ሳት ቍር​ባን የአ​ሮ​ንና የል​ጆቹ ሕግ ይህ ነው። ለልጅ ልጃ​ቸው ለዘ​ለ​ዓ​ለም ሕግ እን​ዲ​ሆን በቀ​ባ​ቸው ቀን የእ​ስ​ራ​ኤል ልጆች ይሰ​ጡ​አ​ቸው ዘንድ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ያዘ​ዘው ይህ ነው። የሚ​ቃ​ጠል መሥ​ዋ​ዕ​ትና የእ​ህል ቍር​ባን፥ የኀ​ጢ​አ​ትና የበ​ደል መሥ​ዋ​ዕት፥ የቅ​ድ​ስ​ናና የደ​ኅ​ን​ነት መሥ​ዋ​ዕት ሕግ ይህ ነው። እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር በሲና ምድረ በዳ ቍር​ባ​ና​ቸ​ውን በእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ፊት ያቀ​ርቡ ዘንድ ለእ​ስ​ራ​ኤል ልጆች ባዘዘ ጊዜ በሲና ተራራ ለሙሴ ያዘ​ዘው ይህ ነው።

ዘሌዋውያን 7:11-38 አዲሱ መደበኛ ትርጒም (NASV)

“ ‘አንድ ሰው ለእግዚአብሔር የኅብረት መሥዋዕት በሚያቀርብበት ጊዜ፣ ሊከተለው የሚገባው ሥርዐት ይህ ነው፤ “ ‘መሥዋዕቱን የሚያቀርበው ለምስጋና መግለጫ ከሆነ፣ ከምስጋና መሥዋዕቱ ጋራ ያለ እርሾ የተጋገረና በዘይት የተለወሰ ኅብስት እርሾ ሳይገባበት፣ በሥሡ ተጋግሮ፣ ዘይት የተቀባ ቂጣ በሚገባ ታሽቶ፣ በዘይት የተለወሰም የላመ ዱቄት ኅብስት ዐብሮ ያቅርብ። ለምስጋና ከሚሆነው የኅብረት መሥዋዕት ጋራ፣ በእርሾ የተጋገረ ኅብስት ያቅርብ። ከእያንዳንዱም ዐይነት አንዳንድ አንሥቶ ለእግዚአብሔር የተለየ ቍርባን በማድረግ ያቅርብ፤ ይህም የኅብረት መሥዋዕቱን ደም ለሚረጨው ካህን ይሰጥ። ለምስጋና የሚሆነው የኅብረት መሥዋዕት ሥጋ፣ በቀረበበት ዕለት ይበላ እንጂ አንዳች አይደር። “ ‘መሥዋዕቱ ስእለት በመፈጸሙ ወይም የበጎ ፈቃድ ስጦታ ከሆነ፣ በቀረበበት ዕለት ይበላ፤ የተረፈውም ሁሉ በማግስቱም ይበላ። እስከ ሦስት ቀን የቈየ ማንኛውም የመሥዋዕቱ ሥጋ ይቃጠል። ማንኛውም የኅብረት መሥዋዕት ሥጋ በሦስተኛው ቀን ከተበላ ተቀባይነት የለውም፤ ርኩስ በመሆኑ ላቀረበው ሰው ዋጋ አይኖረውም፤ ከዚያም የበላ ሰው የበደል ዕዳ ይሆንበታል። “ ‘ርኩስ ከሆነ ነገር ጋራ የተነካካ ሥጋ ይቃጠል እንጂ አይበላ። ሌላውን ሥጋ ግን በሥርዐቱ መሠረት ንጹሕ የሆነ ማንኛውም ሰው ይብላ፤ ነገር ግን ንጹሕ ያልሆነ ማንኛውም ሰው ለእግዚአብሔር የቀረበውን የትኛውንም የኅብረት መሥዋዕት ሥጋ ቢበላ፣ ከሕዝቡ ፈጽሞ ይወገድ። ማንኛውም ሰው የሰውን ርኩሰት ወይም ርኩስ እንስሳን ወይም ማንኛውንም ርኩስ ነገር ቢነካና ለእግዚአብሔር ከቀረበው የኅብረት መሥዋዕት ሥጋ ቢበላ፣ ያ ሰው ፈጽሞ ከሕዝቡ ይወገድ።’ ” እግዚአብሔር ሙሴን እንዲህ አለው፤ “ለእስራኤላውያን እንዲህ በላቸው፤ ‘የበሬ ወይም የላም፣ የበግ ወይም የፍየል ሥብ አትብሉ። ሞቶ የተገኘ ወይም አውሬ የገደለው ከብት ሥብ ለሌላ ተግባር ይዋል እንጂ አይበላ። ለእግዚአብሔር በእሳት ከሚቀርብ እንስሳ ሥብ የሚበላ ማንኛውም ሰው ከሕዝቡ ይወገድ። በየትኛውም ቦታ ብትኖሩ የማንኛውንም የወፍ ዘር ወይም የእንስሳ ደም አትብሉ። ማንኛውም ሰው ደም ቢበላ፣ ያ ሰው ከሕዝቡ ይወገድ።’ ” እግዚአብሔር ሙሴን እንዲህ አለው፤ “ለእስራኤላውያን እንዲህ በላቸው፤ ‘የኅብረት መሥዋዕት ለእግዚአብሔር የሚያቀርብ ማንኛውም ሰው ስለ ራሱ መሥዋዕት አድርጎ ከዚሁ ላይ ለእግዚአብሔር ያቅርብ። በእሳት ለእግዚአብሔር የሚቀርበውን መሥዋዕት በራሱ እጅ ያቅርበው፤ ሥቡን ከፍርምባው ጋራ ያቅርብ፤ ፍርምባውን መሥዋዕት አድርጎ በእግዚአብሔር ፊት ይወዝውዘው። ካህኑ ሥቡን በመሠዊያው ላይ ያቃጥል፤ ፍርምባው ግን ለአሮንና ለልጆቹ ይሰጥ። የኅብረት መሥዋዕታችሁን የቀኝ ወርች ለካህኑ የተለየ አድርጋችሁ ስጡት። የኅብረት መሥዋዕቱን ደምና ሥብ የሚያቀርበው የአሮን ልጅ ቀኝ ወርቹን የራሱ ድርሻ አድርጎ ይውሰድ። ከእስራኤላውያን የኅብረት መሥዋዕት ላይ የተወዘወዘውን ፍርምባና የቀረበውን ወርች ወስጃለሁ፤ ለካህኑ ለአሮንና ለልጆቹም ከእስራኤላውያን የሚያገኙት መደበኛ ድርሻቸው እንዲሆን ሰጥቻቸዋለሁ።’ ” ካህናት ሆነው እግዚአብሔርን እንዲያገለግሉ በቀረቡ ቀን፣ በእሳት ለእግዚአብሔር ከቀረበው መሥዋዕት ላይ ለአሮንና ለልጆቹ የተመደበላቸው ድርሻ ይህ ነው። ካህናቱ በተቀቡበት ቀን፣ እስራኤላውያን መደበኛ ድርሻ አድርገው ከትውልድ እስከ ትውልድ ይህን እንዲሰጧቸው እግዚአብሔር አዘዘ። እንግዲህ የሚቃጠል መሥዋዕት፣ የእህል ቍርባን፣ የኀጢአት መሥዋዕት፣ የበደል መሥዋዕት፣ የክህነት ሹመት መሥዋዕትና የኅብረት መሥዋዕት ሥርዐት ይህ ነው፤ ይህም፣ በሲና ምድረ በዳ እስራኤላውያን መሥዋዕታቸውን ለእግዚአብሔር እንዲያቀርቡ ባዘዛቸው ቀን በሲና ተራራ ላይ ለሙሴ የሰጠው ሥርዐት ነው።

ዘሌዋውያን 7:11-38 መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) (አማ54)

ሰው ለእግዚአብሔር የሚያቀርበው የደኅንነት መሥዋዕት ሕግ ነው። ለምስጋና ቢያቀርበው፥ ከምስጋናው መሥዋዕት ጋር በዘይት የተለወሰ የቂጣ እንጎቻ፥ በዘይትም የተቀባ ስስ ቂጣ፥ በዘይትም የተለወሰ መልካም ዱቄት ያቀርባል። ለምስጋና የሚሆነውን የደኅንነት መሥዋዕት ባቀረበ ጊዜ እርሾ ያለበትን ኅብስት ያቀርባል። ከቍርባኑም ሁሉ ለእግዚአብሔር የማንሣት ቍርባን እንዲሆን ከእነርሱ አንዱን ያነሣል። እርሱም የደኅንነትን መሥዋዕት ደም ለሚረጨው ካህን ይሆናል። ለምስጋና የሚሆነው የደኅንነት መሥዋዕት ሥጋ በሚቀርብበት ቀን ይበሉታል፤ ከእርሱ እስከ ነገ ምንም አያድርም። የቁርባኑም መሥዋዕት የስእለት ወይም የፈቃድ ቢሆን፥ መሥዋዕቱ በሚቀርብበት ቀን ይብሉት፤ ከእርሱም የቀረውን በነጋው ይብሉት፤ ከመሥዋዕቱም ሥጋ እስከ ሦስተኛው ቀን የሚቆየው በእሳት ይቃጠላል። በሦስተኛው ቀን ከደኅንነት መሥዋዕት ሥጋ ቢበላ፥ አይሠምርም ላቀረበው ሰው የተጠላ ይሆንበታል እንጂ ቁርባን ሆኖ አይቈጠርለትም፤ ከእርሱም ቢበላ ኃጢአቱን ይሸከማል። ርኩስ ነገር የሚነካውን ሥጋ አይብሉት፤ በእሳት ይቃጠል። ንጹሕ የሆነ ሰው ሁሉ ግን ከሥጋው ይብላ። ሰውም የረከሰ ቢሆን፥ ለእግዚአብሔርም ከሆነው ከደኅንነት መሥዋዕት ሥጋ ቢበላ፥ ያ ሰው ከሕዝቡ ተለይቶ ይጥፋ። ማናቸውንም ርኩስ ነገር ቢነካ፥ የሰውን ወይም የረከሰን እንስሳ ወይም ሌላውን የተጠላ ርኩስን ቢነካ፥ ለእግዚአብሔርም ከሆነው ከደኅንነት መሥዋዕት ሥጋ ቢበላ፥ ያ ሰው ከሕዝቡ ተለይቶ ይጥፋ። እግዚአብሔርም ሙሴን እንዲህ ብሎ ተናገረው፦ የእስራኤልን ልጆች እንዲህ ብለህ ተናገራቸው፦ የበሬ ወይም የበግ ወይም የፍየል ስብ ከቶ አትብሉ። የሞተውን ስብ፥ አውሬ የሰበረውንም ስብ ለሌላ ተግባር አድርጉት፤ ነገር ግን ከእርሱ ምንም አትብሉ፤ ለእግዚአብሔር በእሳት ከሚቀርበው ከእንስሳ ስብ የሚበላ ሁሉ፥ ያ የበላ ሰው ከሕዝቡ መካከል ተለይቶ ይጠፋልና። በማደሪያዎቻችሁም ሁሉ የወፍ ወይም የእንስሳ ደም ቢሆን አትብሉ። ደም የሚበላ ሰው ሁሉ ያ ሰው ከሕዝቡ መካከል ተለይቶ ይጥፋ። እግዚአብሔርም ሙሴን እንዲህ ብሎ ተናገረው፦ የእስራኤልን ልጆች እንዲህ ብለህ ተናገራቸው፦ ለእግዚአብሔር የደኅንነት መሥዋዕት የሚያቀርብ ሰው ቁርባኑን ለእግዚአብሔር ከደኅንነቱ መሥዋዕት ያመጣል። የእርሱ እጆች ለእግዚአብሔር የእሳቱን ቁርባን ያመጣሉ፤ ፍርምባው በእግዚአብሔር ፊት ለመወዝወዝ ቁርባን ይወዘውዝ ዘንድ ስቡንና ፍርምባውን ያመጣል። ካህኑም ስቡን በመሠዊያው ላይ ያቃጥላል፤ ፍርምባውም ለአሮንና ለልጆቹ ይሁን። ከደኅንነት መሥዋዕታችሁ ቀኝ ወርቹን ለማንሣት ቁርባን እንዲሆን ለካህኑ ትሰጡታላችሁ። ከአሮንም ልጆች የደኅንነትን መሥዋዕት ደሙንና ስቡን ለሚያቀርብ ለእርሱ ቀኝ ወርቹ እድል ፈንታው ይሆናል። የሚወዘወዘውን ፍርምባና የሚነሣውን ወርች ከእስራኤል ልጆች ከደኅንነት መሥዋዕታቸው ወስጄአለሁ፥ ለካህኑ ለአሮንና ለልጆቹም ለዘላለም እድል ፈንታ እንዲሆን ከእስራኤል ልጆች ዘንድ ሰጥቼአቸዋለሁ። እግዚአብሔርን በክህነት ያገለግሉት ዘንድ ባቀረባቸው ቀን ለእግዚአብሔር ከሆነ ከእሳት ቁርባን የአሮንና የልጆቹ እድል ፈንታ ይህ ነው። ለልጅ ልጃቸው ለዘላለም እድል ፈንታቸው እንዲሆን በቀባቸው ቀን የእስራኤል ልጆች ይሰጡአቸው ዘንድ እግዚአብሔር ያዘዘው ይህ ነው። የሚቃጠል መሥዋዕትና የእህል ቁርባን፥ የኃጢአትና የበደል መሥዋዕት፥ የቅድስናና የደኅንነት መሥዋዕት ሕግ ይህ ነው። እግዚአብሔር በሲና ምድረ በዳ ቁርባናቸውን ለእግዚአብሔር ያቀርቡ ዘንድ ለእስራኤል ልጆች ባዘዘ ጊዜ በሲና ተራራ ለሙሴ ያዘዘው ይህ ነው።

ዘሌዋውያን 7:11-38 አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም (አማ05)

“ለእግዚአብሔር ስለሚቀርበው የአንድነት መሥዋዕት ሕግ ይህ ነው፤ አንድ ሰው ይህን መባ ለእግዚአብሔር የምስጋና መሥዋዕት አድርጎ ለማቅረብ ቢፈልግ፥ ከሚሠዋው እንስሳ ጋር እርሾ ያልነካው በዘይት ተለውሶ የተጋገረ ዳቦ፥ እርሾ ያልገባበት በስሱ ተጋግሮ ዘይት የተቀባ ዳቦ፥ በላመ ዱቄት በዘይት ተለውሶ የተጋገረ ዳቦ ያቅርብ። ከአንድነት መሥዋዕት በተጨማሪ ለመባ የሚሆን በእርሾ ተቦክቶ የተጋገረ ኅብስት ያቅርብ። ከእያንዳንዱ የኅብስት ዐይነት አንዱን ክፍል ለእግዚአብሔር የተለየ መባ አድርጎ ያቀርባል፤ ያም መባ የእንስሳውን ደም ወስዶ በመሠዊያው ጐን የኅብረት መሥዋዕት አድርጎ ለረጨው ካህን ድርሻ ይሁን፤ የእንስሳውም ሥጋ በዚያው በተሠዋበት ቀን መበላት አለበት፤ ከዚያ ተርፎ የሚያድር ምንም ነገር አይኑር። “አንድ ሰው የሚያቀርበው የአንድነት መሥዋዕት ስእለት ስለ ተፈጸመለት ወይም የበጎ ፈቃድ ስጦታ ቢሆን ሁሉም በዚያው በቀረበበት ዕለት ይበላ፤ ከዚያም የተረፈ ቢኖር በማግስቱ ይበላ። ከመሥዋዕቱ ተርፎ እስከ ሦስት ቀን የቈየው ሥጋ ግን በእሳት ይቃጠል፤ ከተረፈው ሥጋ ምንም ያኽል በሦስተኛው ቀን ቢበላ የዚያን ሰው መሥዋዕት እግዚአብሔር አይቀበልለትም፤ መሥዋዕቱም እንደ ቀረበ ሆኖ አይቈጠርለትም፤ እንዲያውም እንደ ረከሰ ሆኖ ይቈጠራል፤ እርሱንም የበላ ሰው የበደሉን ፍዳ ይቀበላል። ንጹሕ የሆነውን ሥጋ ማንኛውም የረከሰ ነገር ቢነካው መቃጠል እንጂ መበላት የለበትም፤ “ንጹሕ የሆነ ሰው ይህን ንጹሕ የሆነውን ሥጋ ይብላ፤ ነገር ግን አንድ ሰው ንጹሕ ሳይሆን የአንድነቱን መሥዋዕት ሥጋ ቢበላ ከእግዚአብሔር ሕዝብ መለየት አለበት፤ ማንም ሰው ንጹሕ ያልሆነው ከሰው ወይም ከእንስሶች የሚወጣ ማንኛውንም ርኩስ ነገር ነክቶ ይህን የአንድነት መሥዋዕት ሥጋ ቢበላ ያ ሰው ከእግዚአብሔር ሕዝብ ይለይ። ” እግዚአብሔር ሙሴን እንዲህ አለው፦ “ለእስራኤላውያን እንዲህ ብለህ ንገራቸው፦ የቀንድ ከብት፥ የበግና፥ የፍየልን ስብ የሚበላ አይኑር፤ ሞቶ የተገኘ እንስሳ ወይም አውሬ የገደለው እንስሳ ስቡ ለሌላ አገልግሎት ይዋል እንጂ ማንም ሰው አይብላው። የሚቃጠል መሥዋዕት ሆኖ ለእግዚአብሔር የቀረበውን እንስሳ ስብ የሚበላ ሰው ከእግዚአብሔር ሕዝብ ይለይ፤ እንዲሁም እስራኤላውያን የትም ቦታ ቢኖሩ በሚኖሩበት ስፍራ ሁሉ የወፍም ሆነ የእንስሳ ደም አይብሉ፤ ማንኛውንም ደም የሚበላ ሰው ሁሉ ከእግዚአብሔር ሕዝብ ይለይ።” እግዚአብሔር ሙሴን እንዲህ አለው፦ “ለእስራኤል ሕዝብ እንዲህ በላቸው፤ ማንም ሰው የአንድነት መሥዋዕት ቢያቀርብ ከእርሱ ከፍሎ ለእግዚአብሔር የተለየ መባ ያምጣ፤ እርሱንም የሚቃጠል መሥዋዕት አድርጎ ለእግዚአብሔር ያቅርብ፤ የእንስሳውንም ስብ ከፍርምባው ጋር በመወዝወዝ ለእግዚአብሔር ልዩ መባ አድርጎ ያቅርብ። ካህኑ ስቡን በመሠዊያው ላይ ያቃጥለው፤ ፍርምባው ግን ለካህናቱ ይሰጥ፤ ከአንድነቱ መሥዋዕት በቀኝ በኩል ያለው ወርች ድርሻው ሆኖ ለካህኑ ይሰጥ፤ የቀኙ ወርች የአንድነቱን መሥዋዕት ደምና ስብ ለሚያቀርበው ካህን ድርሻ ይሁን፤ ከእስራኤላውያን የአንድነት መሥዋዕት መካከል የተወዘወዘውን ፍርንባና የሚቀርበውን ወርች ከእስራኤላውያን እንደሚቀርብላቸው ቋሚ ድርሻ አድርጌ ለካህኑ ለአሮንና ለልጆቹ ሰጥቻቸዋለሁ። ይህም እግዚአብሔር አሮንንና ልጆቹን ካህናት አድርጎ በሾመበት ቀን ለእግዚአብሔር ከቀረበው ከሚቃጠል መሥዋዕት ለካህናት ድርሻ ሆኖ የተለየ ነው፤ በዚያን ቀን እግዚአብሔር ይህን የመሥዋዕት ክፍል ለካህናቱ እንዲሰጡአቸው የእስራኤልን ሕዝብ አዘዘ፤ ይህም በሚመጡት ዘመናት ሁሉ የካህናቱ ድርሻ እንዲሆን ቋሚ ሥርዓት አደረገው።” እንግዲህ ስለሚቃጠል መሥዋዕት፥ ስለ እህል መባ፥ ስለ ኃጢአት ስርየት መሥዋዕት፥ ስለ በደል ማስተስረያ መሥዋዕት ስለ ክህነት ሹመት መሥዋዕትና የአንድነት መሥዋዕት የሚፈጸሙትም የሥርዓት መመሪያዎች እነዚሁ ናቸው። በዚያም በረሓ በሆነው በሲና ተራራ እስራኤላውያን መሥዋዕት እንዲያቀርቡ ባዘዛቸው በዚያ ቀን እግዚአብሔር ለሙሴ እነዚህን ትእዛዞች ሰጠው።

ዘሌዋውያን 7:11-38 መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) (መቅካእኤ)

“ሰው ለጌታ የሚያቀርበው የአንድነት መሥዋዕት ሕግ ይህ ነው። የሚያቀርውም ለምስጋና ቢሆን፥ ከምስጋናው መሥዋዕት ጋር እርሾ ያልገባበት በዘይት የተለወሰ የቂጣ እንጎቻ፥ እርሾ ያልነካው በዘይትም የተቀባ ስስ ቂጣ፥ በዘይትም የተለወሰ መልካም ዱቄት ያቀርባል። ለምስጋና የሚሆነውን የአንድነት መሥዋዕቱን ባቀረበ ጊዜ እርሾ ያለበትን ኅብስት ያቀርባል። ለጌታ እንደ ስጦታ አድርጎ አንድ ኅብስት ከእያንዳንዱ ቁርባን ያቀርባል። ከእርሱም የቀረው የአንድነትን መሥዋዕት ደም ለሚረጨው ካህን ይሆናል። “ለምስጋና የሚሆነውን የአንድነት መሥዋዕቱን ሥጋ በሚያቀርብበት ቀን ይበላ፤ ከእርሱ እስከ ነገ ምንም አያሳድር። የቁርባኑም መሥዋዕት የስእለት ወይም የፈቃድ ቢሆን፥ መሥዋዕቱን በሚያቀርብበት ቀን ይበላ፤ ከእርሱም የቀረውን በማግስቱ ይበላ፤ ነገር ግን በሦስተኛው ቀን ከመሥዋዕቱ የተረፈው ሥጋ በእሳት ይቃጠል። በሦስተኛው ቀን ከአንድነቱ መሥዋዕት ከቶ ሥጋ ቢበላ፥ አይሠምርለትም ላቀረበው ሰው የተጠላ ይሆንበታል እንጂ ቁርባን ሆኖ አይቈጠርለትም፤ ሰውም ከእርሱ ቢበላ ኃጢአቱን ይሸከማል። “ሥጋው ማናቸውንም ርኩስ ነገር ከነካ አይበላ፤ በእሳት ይቃጠል። ሌላውን ሥጋ ግን ንጹሕ የሆነ ሰው ሁሉ ከሥጋው ይብላ። ነገር ግን የረከሰ ሰው ሆኖ ሳለ፥ ለጌታ ከሆነው ከአንድነት መሥዋዕት ሥጋ የበላ እንደሆነ፥ ያ ሰው ከሕዝቡ ተለይቶ ይጥፋ። ማንም ሰው የሰውን ርኩሰት ወይም የረከሰን እንስሳ ወይም ምንም ዓይነት ርኩስ ሆኖ የተጠላን ማናቸውንም ርኩስ ነገር ነክቶ፥ ለጌታ ከሆነው ከአንድነት መሥዋዕት ሥጋ ቢበላ፥ ያ ሰው ከሕዝቡ ተለይቶ ይጥፋ።” ጌታም ሙሴን እንዲህ ብሎ ተናገረው፦ “ለእስራኤል ልጆች እንዲህ ብለህ ተናገር፦ የበሬ ወይም የበግ ወይም የፍየል ስብ ከቶ አትብሉ። ሞቶ የተገኘን የእንስሳ ስብ፥ እንዲሁም አውሬ የገደለውን የእንስሳ ስብ ለማናቸውም ለሌላ ተግባር አድርጉት እንጂ ከእርሱ ፈጽሞ ምንም አትብሉ፤ ለጌታ በእሳት ከሚያቀርበው ከእንስሳ ስብ የሚበላ ሰው ሁሉ፥ ከሕዝቡ መካከል ተለይቶ ይጠፋ። በማደሪያዎቻችሁም ሁሉ የወፍ ወይም የእንስሳ ደም ቢሆን ፈጽሞ አትብሉ። ማንም ሰው ደም የሚበላ ያ ሰው ከሕዝቡ መካከል ተለይቶ ይጥፋ።” ጌታም ሙሴን እንዲህ ብሎ ተናገረው፦ “ለእስራኤል ልጆች እንዲህ ብለህ ተናገር፦ ለጌታ የአንድነትን መሥዋዕት የሚያቀርብ ሰው ቁርባኑን ለጌታ ከሰላሙ መሥዋዕት ያመጣል። የእርሱ እጆች ለጌታ በእሳት የሚቀርበውን ቁርባን ያመጣሉ፤ እርሱም ፍርምባው በጌታ ፊት ለመወዝወዝ ቁርባን እንዲወዘወዝ ፍርምባውን ከስቡ ጋር ያመጣዋል። ካህኑም ስቡን በመሠዊያው ላይ ያቃጥላል፤ ፍርምባው ግን ለአሮንና ለልጆቹ ይሆናል። ከሰላም መሥዋዕታችሁ ቀኝ ወርቹን እንደ ቁርባን አድርጋችሁ ለካህኑ ትሰጡታላችሁ። ከአሮንም ልጆች መካከል የአንድነትን መሥዋዕት ደሙንና ስቡን ለሚያቀርበው ለእርሱ ቀኝ ወርቹ ድርሻው ይሆናል። የሚወዘወዘውን ፍርምባና እንደ ቁርባን የሚቀርበውን ወርች ከእስራኤል ልጆች ከሰላም መሥዋዕታቸው ወስጄ፥ ለካህኑ ለአሮንና ለልጆቹም ለዘለዓለም ድርሻ እንዲሆን ከእስራኤል ልጆች ዘንድ እነርሱን ሰጥቼአቸዋለሁ። “ጌታን በክህነት እንዲያገለግሉት እነርሱን ባቀረባቸው ቀን ለጌታ በእሳት ከሚቀርበው ቁርባን የአሮንና የልጆቹ ድርሻ ይህ ነው። ለልጅ ልጃቸው ለዘለዓለም ድርሻቸው እንዲሆን በቀባቸው ቀን ከእስራኤል ልጆች እንዲሰጣቸው ጌታ ያዘዘው ይህ ነው። የሚቃጠል መሥዋዕትና የእህል ቁርባን፥ የኃጢአትና የበደል መሥዋዕት፥ የቅድስናና የአንድነት መሥዋዕት ሕግ ይህ ነው። ጌታ በሲና ምድረ በዳ ቁርባናቸውን ለጌታ እንዲያቀርቡ ለእስራኤል ልጆች ባዘዘ ጊዜ በሲና ተራራ ለሙሴ ያዘዘው ይህ ነው።”