የYouVersion አርማ
የፍለጋ አዶ

ኦሪት ዘሌዋውያን 7

7
1 # ዘሌ. 5፥14-19። “የበደል መሥዋዕት ሕግ ይህ ነው፤ እርሱም እጅግ የተቀደሰ ነው። 2#ዘሌ. 6፥18።የሚቃጠለውን መሥዋዕት በሚያርዱበት ስፍራ የበደሉን መሥዋዕት ያርዱታል፤ ደሙንም በመሠዊያው ላይ በዙሪያው ይረጨዋል። 3#ዘሌ. 3፥4።ስቡንም ሁሉ፥ ላቱንም፥ የሆድ ዕቃውንም የሚሸፍነውን ስብ ያቀርበዋል። 4ሁለቱንም ኩላሊቶች፥ በእነርሱም ላይና በጎድኑ አጠገብ ያለውን ስብ፥ በጉበቱም ላይ ያለውን መረብ ከኩላሊቶቹ ጋር ይወስዳል። 5ካህኑም ለጌታ በእሳት የሚቀርብ ቁርባን አድርጎ በመሠዊያው ላይ ያቃጥለዋል፤ እርሱ የበደል መሥዋዕት ነው። 6#ዘሌ. 6፥9።ከካህናት ወገን የሆነ ወንድ ሁሉ ይበላዋል፤ በተቀደሰ ስፍራ ይበላል፤ እርሱም እጅግ የተቀደሰ ነው።#ዘሌ. 2፥3። 7የበደል መሥዋዕት እንደ ኃጢአት መሥዋዕት ነው፤ ለሁለቱ አንድ ሕግ አለ፤ ያም በእነርሱ የሚያስተሰርይ ካህን ከእነርሱ ላይ ለራሱ ስለ ሚወስድ ነው። 8እንዲሁም የማናቸውንም ሰው የሚቃጠል መሥዋዕት የሚያቀርብ ካህን፥ ያቀረበው የሚቃጠለው መሥዋዕት ቆዳ ለዚያው ካህን ይሆናል። 9#ዘሌ. 2፥3-10፤ ዘኍ. 18፥9፤ ሕዝ. 44፥29።በምድጃ ላይ የተጋገረው፥ በመጥበሻም ወይም በምጣድ ላይ የተዘጋጀው የእህል ቁርባን ሁሉ ለሚያቀርበው ካህን ይሆናል። 10#ዘሌ. 2፥14-15።በዘይትም የተለወሰው ወይም የደረቀው የእህል ቁርባን በጠቅላላ ለአሮን ልጆች ሁሉ ይሆናል፤ እያንዳንዱም እንደሌላው ወንድሙ ይደርሰዋል።
ተጨማሪ ትእዛዛት
11 # ዘሌ. 3። “ሰው ለጌታ የሚያቀርበው የአንድነት መሥዋዕት ሕግ ይህ ነው። 12የሚያቀርውም ለምስጋና ቢሆን፥ ከምስጋናው መሥዋዕት ጋር እርሾ ያልገባበት በዘይት የተለወሰ የቂጣ እንጎቻ፥ እርሾ ያልነካው በዘይትም የተቀባ ስስ ቂጣ፥ በዘይትም የተለወሰ መልካም ዱቄት ያቀርባል። 13ለምስጋና የሚሆነውን የአንድነት መሥዋዕቱን ባቀረበ ጊዜ እርሾ ያለበትን ኅብስት ያቀርባል። 14ለጌታ እንደ ስጦታ አድርጎ አንድ ኅብስት ከእያንዳንዱ ቁርባን ያቀርባል። ከእርሱም የቀረው የአንድነትን መሥዋዕት ደም ለሚረጨው ካህን ይሆናል።
15 # ዘሌ. 19፥6-7። “ለምስጋና የሚሆነውን የአንድነት መሥዋዕቱን ሥጋ በሚያቀርብበት ቀን ይበላ፤ ከእርሱ እስከ ነገ ምንም አያሳድር።#ዘሌ. 22፥29-30። 16#ዘሌ. 19፥5-8።የቁርባኑም መሥዋዕት የስእለት ወይም የፈቃድ ቢሆን፥ መሥዋዕቱን በሚያቀርብበት ቀን ይበላ፤ ከእርሱም የቀረውን በማግስቱ ይበላ፤ 17ነገር ግን በሦስተኛው ቀን ከመሥዋዕቱ የተረፈው ሥጋ በእሳት ይቃጠል። 18በሦስተኛው ቀን ከአንድነቱ መሥዋዕት ከቶ ሥጋ ቢበላ፥ አይሠምርለትም ላቀረበው ሰው የተጠላ ይሆንበታል እንጂ ቁርባን ሆኖ አይቈጠርለትም፤ ሰውም ከእርሱ ቢበላ ኃጢአቱን ይሸከማል።
19 # ዘሌ. 12፥4። “ሥጋው ማናቸውንም ርኩስ ነገር ከነካ አይበላ፤ በእሳት ይቃጠል። ሌላውን ሥጋ ግን ንጹሕ የሆነ ሰው ሁሉ ከሥጋው ይብላ። 20#ዘሌ. 17፥4፤ 9—10፤ 14፤ 18፥29፤ 20፥3፤ 5—6፤ 17—18፤ ዘፍ. 17፥14፤ ዘፀ. 30፥33፤ ዘኍ. 15፥31፤ መዝ. 37፥9፤ 28፤ 34፤ 109፥13።ነገር ግን የረከሰ ሰው ሆኖ ሳለ፥ ለጌታ ከሆነው ከአንድነት መሥዋዕት ሥጋ የበላ እንደሆነ፥ ያ ሰው ከሕዝቡ ተለይቶ ይጥፋ። 21ማንም ሰው የሰውን ርኩሰት ወይም የረከሰን እንስሳ ወይም ምንም ዓይነት ርኩስ ሆኖ የተጠላን ማናቸውንም ርኩስ ነገር ነክቶ፥ ለጌታ ከሆነው ከአንድነት መሥዋዕት ሥጋ ቢበላ፥ ያ ሰው ከሕዝቡ ተለይቶ ይጥፋ።”
22ጌታም ሙሴን እንዲህ ብሎ ተናገረው፦ 23#ዘሌ. 3፥17።“ለእስራኤል ልጆች እንዲህ ብለህ ተናገር፦ የበሬ ወይም የበግ ወይም የፍየል ስብ ከቶ አትብሉ። 24#ዘሌ. 22፥8።ሞቶ የተገኘን የእንስሳ ስብ፥ እንዲሁም አውሬ የገደለውን የእንስሳ ስብ ለማናቸውም ለሌላ ተግባር አድርጉት እንጂ ከእርሱ ፈጽሞ ምንም አትብሉ፤ 25ለጌታ በእሳት ከሚያቀርበው ከእንስሳ ስብ የሚበላ ሰው ሁሉ፥ ከሕዝቡ መካከል ተለይቶ ይጠፋ። 26#ዘሌ. 17፥10።በማደሪያዎቻችሁም ሁሉ የወፍ ወይም የእንስሳ ደም ቢሆን ፈጽሞ አትብሉ። 27ማንም ሰው ደም የሚበላ ያ ሰው ከሕዝቡ መካከል ተለይቶ ይጥፋ።”
28ጌታም ሙሴን እንዲህ ብሎ ተናገረው፦ 29“ለእስራኤል ልጆች እንዲህ ብለህ ተናገር፦ ለጌታ የአንድነትን መሥዋዕት የሚያቀርብ ሰው ቁርባኑን ለጌታ ከሰላሙ መሥዋዕት ያመጣል። 30#ዘሌ. 8፥27፤ 9፥21፤ 10፥15፤ 14፥12፤ 21፤ 24፤ 23፥17፤ 20፤ ዘኍ. 6፥20፤ 8፥13፤ 18፥18።የእርሱ እጆች ለጌታ በእሳት የሚቀርበውን ቁርባን ያመጣሉ፤ እርሱም ፍርምባው በጌታ ፊት ለመወዝወዝ ቁርባን እንዲወዘወዝ ፍርምባውን ከስቡ ጋር ያመጣዋል። 31#ዘሌ. 3፥11፤ 16።ካህኑም ስቡን በመሠዊያው ላይ ያቃጥላል፤ ፍርምባው ግን ለአሮንና ለልጆቹ ይሆናል። 32ከሰላም መሥዋዕታችሁ ቀኝ ወርቹን እንደ ቁርባን አድርጋችሁ ለካህኑ ትሰጡታላችሁ። 33ከአሮንም ልጆች መካከል የአንድነትን መሥዋዕት ደሙንና ስቡን ለሚያቀርበው ለእርሱ ቀኝ ወርቹ ድርሻው ይሆናል። 34#ዘፀ. 29፥27-28።የሚወዘወዘውን ፍርምባና እንደ ቁርባን የሚቀርበውን ወርች ከእስራኤል ልጆች ከሰላም መሥዋዕታቸው ወስጄ፥ ለካህኑ ለአሮንና ለልጆቹም ለዘለዓለም ድርሻ እንዲሆን ከእስራኤል ልጆች ዘንድ እነርሱን ሰጥቼአቸዋለሁ።
35“ጌታን በክህነት እንዲያገለግሉት እነርሱን ባቀረባቸው ቀን ለጌታ በእሳት ከሚቀርበው ቁርባን የአሮንና የልጆቹ ድርሻ ይህ ነው። 36ለልጅ ልጃቸው ለዘለዓለም ድርሻቸው እንዲሆን በቀባቸው ቀን ከእስራኤል ልጆች እንዲሰጣቸው ጌታ ያዘዘው ይህ ነው። 37#ዘሌ. 8፥22።የሚቃጠል መሥዋዕትና የእህል ቁርባን፥ የኃጢአትና የበደል መሥዋዕት፥ የቅድስናና የአንድነት መሥዋዕት ሕግ ይህ ነው። 38#ዘሌ. 26፥46፤ 27፥34።ጌታ በሲና ምድረ በዳ ቁርባናቸውን ለጌታ እንዲያቀርቡ ለእስራኤል ልጆች ባዘዘ ጊዜ በሲና ተራራ ለሙሴ ያዘዘው ይህ ነው።”

ማድመቅ

Share

Copy

None

ያደመቋቸው ምንባቦች በሁሉም መሣሪያዎችዎ ላይ እንዲቀመጡ ይፈልጋሉ? ይመዝገቡ ወይም ይግቡ