የYouVersion አርማ
የፍለጋ አዶ

ዘሌዋውያን 26:40-45

ዘሌዋውያን 26:40-45 የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) (አማ2000)

“እንደ ከዱኝ፥ ቸልም እን​ዳ​ሉኝ፥ በፊ​ቴም አግ​ድ​መው እንደ ሄዱ፥ ኀጢ​አ​ታ​ቸ​ው​ንና፥ የአ​ባ​ቶ​ቻ​ቸ​ውን ኀጢ​አት ይና​ዘ​ዛሉ። እኔም ደግሞ አግ​ድሜ ከእ​ነ​ርሱ ጋር በቍጣ ሄድሁ፤ በጠ​ላ​ቶ​ቻ​ቸ​ውም ምድር አጠ​ፋ​ቸ​ዋ​ለሁ። ነገር ግን በዚ​ያን ጊዜ ያል​ተ​ገ​ረ​ዘው ልባ​ቸው ያፍ​ራል፤ ስለ ኀጢ​አ​ታ​ቸ​ውም ይና​ዘ​ዛሉ፤ ያን ጊዜ እኔ ከያ​ዕ​ቆብ ጋር የገ​ባ​ሁ​ትን ቃል ኪዳ​ኔን አስ​ባ​ለሁ፤ ደግ​ሞም ከይ​ስ​ሐቅ ጋር የገ​ባ​ሁ​ትን ቃል ኪዳ​ኔን፥ ከአ​ብ​ር​ሃ​ምም ጋር የገ​ባ​ሁ​ትን ቃል ኪዳ​ኔን አስ​ባ​ለሁ፤ ምድ​ሪ​ቱ​ንም አስ​ባ​ለሁ። ምድ​ርም ከእ​ነ​ርሱ መጥ​ፋት የተ​ነሣ ባዶ ትቀ​ራ​ለች፤ እነ​ር​ሱም ሳይ​ኖሩ በተ​ፈ​ታ​ች​በት ዘመን ዕረ​ፍት ታደ​ር​ጋ​ለች፤ ፍር​ዴ​ንም ስለ ናቁ፥ ነፍ​ሳ​ቸ​ውም ሥር​ዐ​ቴን ስለ ተጸ​የ​ፈች የኀ​ጢ​አ​ታ​ቸ​ውን ቅጣት ይሸ​ከ​ማሉ። ነገር ግን እኔ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር አም​ላ​ካ​ቸው ነኝና እነ​ርሱ በጠ​ላ​ቶ​ቻ​ቸው ምድር ሳሉ፥ እስ​ካ​ጠ​ፋ​ቸው ድረስ ከእ​ነ​ር​ሱም ጋር ያለ​ኝን ቃል ኪዳን እስ​ካ​ፈ​ርስ ድረስ አል​ጥ​ላ​ቸ​ውም፤ አል​ጸ​የ​ፋ​ቸ​ው​ምም። እኔ አም​ላ​ካ​ቸው እሆን ዘንድ አሕ​ዛብ እያዩ ከግ​ብፅ ምድር ከግ​ዞት ቤት እን​ዳ​ወ​ጣ​ኋ​ቸው የቀ​ድሞ ቃል ኪዳ​ና​ቸ​ውን ስለ እነ​ርሱ አስ​ባ​ለሁ፤ እኔ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ነኝና።”

ዘሌዋውያን 26:40-45 አዲሱ መደበኛ ትርጒም (NASV)

“ ‘ነገር ግን ለእኔ ያልታመኑበትንና በእኔም ላይ ያመፁበትን የራሳቸውን ኀጢአትና የአባቶቻቸውን ኀጢአት ቢናዘዙ፣ ይኸውም፣ እኔ ጠላት እንድሆንባቸውና ወደ ጠላቶቻቸው ምድር እንድሰድዳቸው ያደረገኝን ኀጢአት ቢናዘዙ፣ ያልተገረዘው ልባቸው ቢዋረድና ስለ ኀጢአታቸው የሚገባውን ቅጣት ቢቀበሉ፣ በዚያ ጊዜ ከያዕቆብ ጋር የገባሁትን ኪዳኔን፣ ከይስሐቅም ጋር የገባሁትን ኪዳኔን፣ ደግሞም ከአብርሃም ጋር የገባሁትን ኪዳኔን ዐስባለሁ፤ ምድሪቱንም አስባታለሁ። ምድሪቱ እነርሱ ለቅቀዋት ስለ ሄዱ ባዶ ትቀራለች፤ እነርሱ በሌሉበት ጊዜም ባድማ ሆና በሰንበቷ ትደሰታለች፤ ሕጌን በማቃለላቸውና ሥርዐቴን በመናቃቸው፣ የኀጢአታቸውን ቅጣት ይቀበላሉ። በዚህ ሁሉ ግን ከእነርሱ ጋር የገባሁትን ኪዳኔን በማፍረስ፣ በጠላቶቻቸው ምድር ሳሉ ፈጽሜ እስካጠፋቸው ድረስ አልተዋቸውም፤ አልጸየፋቸውምም፤ እኔ እግዚአብሔር አምላካቸው (ያህዌ ኤሎሂም) ነኝ። ስለ እነርሱም ስል፣ አምላካቸው (ኤሎሂም) እሆን ዘንድ አሕዛብ እያዩ ከግብፅ ምድር ካወጣኋቸው አባቶቻቸው ጋር የገባሁትን ኪዳን ዐስባለሁ፤ እኔ እግዚአብሔር (ያህዌ) ነኝ።’ ”

ዘሌዋውያን 26:40-45 መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) (አማ54)

በእኔም ላይ በእንቢተኝነት ስለ ሄዱብኝ የበደሉኝን በደል፥ ኃጢአታቸውንም፥ የአባቶቻቸውንም ኃጢአት ይናዘዛሉ። እኔም ደግሞ በእንቢተኝነት ሄድሁባቸው፤ ወደ ጠላቶቻቸውም ምድር አገባኋቸው፤ ነገር ግን በዚያን ጊዜ ያልተገረዘው ልባቸው ቢዋረድ፥ የኃጢአታቸውንም ቅጣት ቢቀበሉ፥ እኔ ለያዕቆብ የማልሁትን ቃል ኪዳኔን አስባለሁ፤ ደግሞ ለይስሐቅና ለአብርሃም የማልሁትን ቃል ኪዳኔን አስባለሁ፤ ምድሪቱንም አስባለሁ። ምድርም ከእነርሱ መጥፋት የተነሣ ባዶ ትቀራለች፤ እነርሱም ሳይኖሩ በተፈታችበት ዘመን ሰንበት በማድረግዋ ትደሰታለች፤ ፍርዴንም ስለ ናቁ፥ ነፍሳቸውም ሥርዓቴን ስለ ተጸየፈች የኃጢአታቸውን ቅጣት ይሸከማሉ። ነገር ግን እኔ እግዚአብሔር አምላካቸው ነኝና እነርሱ በጠላቶቻቸው ምድር ሳሉ፥ እስካጠፋቸው ድረስ ከእነርሱም ጋር ያለኝን ቃል ኪዳን እስካፈርስ ድረስ አልጥላቸውም አልጸየፋቸውምም። እኔ አምላካቸው እሆን ዘንድ አሕዛብ እያዩ ከግብፅ ምድር ያወጣኋቸውን የአባቶቻቸውን ቃል ኪዳን ስለ እነርሱ አስባለሁ፤ እኔ እግዚአብሔር ነኝ።

ዘሌዋውያን 26:40-45 አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም (አማ05)

“ነገር ግን የእናንተ ዘሮች የራሳቸውን ኃጢአት፥ እንዲሁም በእኔ ላይ ያመፁትንና የተቃወሙኝን የቀድሞ አባቶቻቸውን ኃጢአት ይናዘዛሉ፤ እነርሱን ተቃውሜ ወደ ጠላቶቻቸው አገር እንዲሰደዱ አደረግሁ፤ ሆኖም እልኸኛ ልባቸው በትሕትና ተሰብሮ ከኃጢአታቸው ቢታረሙ፥ ከያዕቆብ፥ ከይስሐቅና ከአብርሃም ጋር የገባሁትን ቃል ኪዳን አስባለሁ፤ ምድሪቱንም ለሕዝቤ ለመስጠት የሰጠሁትን የተስፋ ቃል አድሳለሁ። ከሕዝብዋ ባዶ የሆነችው ምድር ውድማ ሆና ሰንበቶችን ታከብራለች፤ እነርሱም ሥርዓቴን ስላልተቀበሉና ሕጌን ስላላከበሩ፥ በኃጢአታቸው ምክንያት ቅጣቱን በሙሉ ይቀበላሉ። ይሁን እንጂ በጠላቶቻቸው አገር ሳሉ እንኳ እስከ መጨረሻ አልተዋቸውም ወይም አልደመስሳቸውም፤ ይህማ ቢሆን ኖሮ ከእነርሱ ጋር የገባሁትን ቃል ኪዳን እስከ መጨረሻ ባልጠበቅሁም ነበር፤ እኔ እግዚአብሔር አምላካቸው ነኝ። ነገር ግን አምላካቸው እሆን ዘንድ ከግብጽ ምድር ካወጣኋቸው ከአባቶቻቸው ጋር የገባሁትን ቃል ኪዳን ስለ እነርሱ አስታውሳለሁ፤ እኔ እግዚአብሔር ነኝ።”

ዘሌዋውያን 26:40-45 መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) (መቅካእኤ)

“ነገር ግን እኔን በመቃወም ሄደዋልና፥ በእኔ ላይ ፈጽሞ በከዳተኝነት ያደረጉትን በደላቸውንና የአባቶቻቸውን በደል ይናዘዛሉ። እኔም ደግሞ እነርሱን በመቃወም እሄዳለሁ፤ ወደ ጠላቶቻቸውም ምድር አመጣቸዋለሁ፤ ነገር ግን በዚያን ጊዜ ያልተገረዘው ልባቸው ቢዋረድ፥ የበደላቸውንም ቅጣት ቢቀበሉ፥ እኔም ለያዕቆብ የማልሁትን ቃል ኪዳኔን አስታውሳለሁ፤ እንዲሁም ለይስሐቅና ለአብርሃም የማልሁትንም ቃል ኪዳኔን አስታውሳለሁ፤ ምድሪቱንም አስታውሳለሁ። ምድርሪቱም በእነርሱ ትተዋለች፤ ያለ እነርሱም ባድማ ሆና እስከተቀመጠችበት ጊዜ ድረስ ሰንበታትን በማድረግዋ ትደሰታለች፤ ፍርዴንም ስላልተቀበሉ፥ ነፍሳቸውም ሥርዓቴን ስለ ተጸየፈች የበደላቸውን ቅጣት ይቀበላሉ። በዚህ ነገር ሁሉ ግን እኔ ጌታ አምላካቸው ነኝና እነርሱ በጠላቶቻቸው ምድር ሳሉ፥ ፈጽሞ እስካጠፋቸው ድረስ ከእነርሱም ጋር ያለኝን ቃል ኪዳን እስካፈርስ ድረስ አልጥላቸውም አልጸየፋቸውምም። እኔ አምላክ እንድሆናቸው አሕዛብ እያዩ ከግብጽ ምድር ካወጣኋቸው ከአባቶቻቸው ጋር ያለኝን ቃል ኪዳን ስለ እነርሱ አስታውሳለሁ፤ እኔ ጌታ ነኝ።”