የYouVersion አርማ
የፍለጋ አዶ

ዘሌዋውያን 25:23-38

ዘሌዋውያን 25:23-38 የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) (አማ2000)

“ምድ​ርም ለእኔ ናትና፥ እና​ን​ተም በእኔ ፊት እን​ግ​ዶ​ችና መጻ​ተ​ኞች ናች​ሁና ምድ​ርን ለዘ​ለ​ዓ​ለም አት​ሽጡ። በር​ስ​ታ​ች​ሁም ምድር ሁሉ መቤ​ዠ​ትን ለም​ድ​ሪቱ አድ​ርጉ። ወን​ድ​ም​ህም ቢደ​ኸይ፥ ከር​ስ​ቱም ቢሸጥ፥ ለእ​ርሱ የቀ​ረበ ዘመዱ መጥቶ ወን​ድሙ የሸ​ጠ​ውን ይቤ​ዠ​ዋል። የሚ​ቤ​ዠ​ውም ሰው ቢያጣ፥ እር​ሱም እጁ ቢረ​ጥብ፥ ለመ​ቤ​ዠ​ትም የሚ​በቃ ቢያ​ገኝ፥ የሽ​ያ​ጩን ዘመን ቈጥሮ የቀ​ረ​ውን ወደ ገዛው ሰው ይመ​ልስ፤ እር​ሱም ወደ ርስቱ ይመ​ለስ። ለራ​ሱም ዕዳ​ውን መክ​ፈል ባይ​ችል፥ ሽያጩ በገ​ዛው ሰው እጅ እስከ ኢዮ​ቤ​ልዩ ዓመት ድረስ ይቀ​መጥ፤ በኢ​ዮ​ቤ​ል​ዩም ዓመት ይውጣ፤ እር​ሱም ወደ ርስቱ ይመ​ለስ። “ሰውም ቅጥር ባለ​በት ከተማ መኖ​ርያ ቤትን ቢሸጥ፥ ከተ​ሸጠ በኋላ አንድ ዓመት እስ​ኪ​ፈ​ጸም ድረስ ለመ​ቤ​ዠት ይች​ላል፤ ለአ​ንድ ሙሉ ዓመት መቤ​ዠት ይች​ላል። አንድ ዓመት እስ​ኪ​ጨ​ረስ ባይ​ቤ​ዠው ቤቱ ለገዡ ይሆ​ናል፤ ቅጥር ባለ​በት ከተማ ያለ​ውን ያን ቤት ይመ​ረ​ም​ሩ​ለ​ታል፤ ለገ​ዛው ሰው ለልጅ ልጁ ለዘ​ለ​ዓ​ለም ይጸ​ና​ለ​ታል፤ በኢ​ዮ​ቤ​ልዩ ዓመ​ትም አይ​ወ​ስ​ዱ​በ​ትም። ቅጥር በሌ​ለ​በት መን​ደር ያሉ ቤቶች ግን እንደ እርሻ ይቈ​ጠ​ራሉ፤ ይቤ​ዣሉ፤ በኢ​ዮ​ቤ​ልዩ ዓመ​ትም ይመ​ለ​ሳሉ። የሌ​ዋ​ው​ያ​ንን ከተ​ሞች፥ በከ​ተ​ሞ​ቻ​ቸ​ውም ያሉ ቤቶ​ቻ​ቸ​ውን ሌዋ​ው​ያን ለዘ​ለ​ዓ​ለም መቤ​ዠት ይች​ላሉ። ማና​ቸ​ውም ሰው ከሌ​ዋ​ው​ያን ቢገዛ፥ በእ​ስ​ራ​ኤል ልጆች መካ​ከል የሌ​ዋ​ው​ያን ከተ​ሞች ቤቶች ርስ​ቶ​ቻ​ቸው ናቸ​ውና በር​ስቱ ከተማ ያለ የተ​ሸ​ጠው ቤት በኢ​ዮ​ቤ​ልዩ ዓመት ይመ​ለ​ሳል። በከ​ተ​ማ​ዎ​ቻ​ቸው ዙሪያ ያሉ እር​ሻ​ዎ​ቻ​ቸ​ውም የዘ​ለ​ዓ​ለም ርስ​ቶ​ቻ​ቸው ናቸ​ውና አይ​ሸ​ጡም። “ከአ​ንተ ጋር ያለው ወን​ድ​ምህ ቢደ​ኸይ፥ እጁም በአ​ንተ ዘንድ ቢደ​ክም እንደ እን​ግ​ዳና እንደ መጻ​ተኛ ትረ​ዳ​ዋ​ለህ፤ ከአ​ን​ተም ጋር ይኑር። ወን​ድ​ምህ ከአ​ንተ ጋር ይኖር ዘንድ ከእ​ርሱ ምንም ወለድ ወይም ትርፍ አት​ው​ሰድ፤ ነገር ግን አም​ላ​ክ​ህን ፍራ፤ እኔ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ነኝና። ብር​ህን በወ​ለድ አታ​በ​ድ​ረው፤ እህ​ል​ህ​ንም በት​ርፍ አት​ስ​ጠው። የከ​ነ​ዓ​ንን ምድር እሰ​ጥህ ዘንድ፥ አም​ላ​ክም እሆ​ንህ ዘንድ ከግ​ብፅ ምድር ያወ​ጣ​ሁህ እኔ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር አም​ላ​ክህ ነኝና።

ዘሌዋውያን 25:23-38 አዲሱ መደበኛ ትርጒም (NASV)

“ ‘መሬት ለዘለቄታ አይሸጥ፤ ምክንያቱም ምድሪቱ የእኔ ናት፤ እናንተም መጻተኞችና እንግዶች ናችሁ። ርስት አድርጋችሁ በምትይዙት ምድር ሁሉ መሬት የሚዋጅበት ሁኔታ እንዲኖር አድርጉ። “ ‘ከወገንህ አንዱ ደኽይቶ ርስቱን ቢሸጥ፣ የቅርብ ዘመዱ መጥቶ ወገኑ የሸጠውን ይዋጅለት። ነገር ግን ሰውየው ርስቱን የሚዋጅለት ምንም ዘመድ ባይኖረውና እርሱ ራሱ መዋጀት የሚችልበትን ሀብት ቢያገኝ፣ ርስቱን ከሸጠበት ጊዜ ጀምሮ ያለውን የሽያጭ ዘመን በመቍጠር የዋጋውን ልዩነት ለገዛው ሰው ይመልስ፤ እርሱም ወደ ገዛ ርስቱ ይመለስ። ነገር ግን ዋጋውን መመለስ ካልቻለ፣ የሸጠው ርስት እስከ ኢዮቤልዩ ዓመት ድረስ የገዥው ንብረት ሆኖ ይቈያል፤ በኢዮቤልዩ ዓመት ለባለቤቱ ይመለሳል፤ ሰውየውም ወደ ርስቱ ይመለሳል። “ ‘ማንኛውም ሰው ቅጥር በተሠራለት ከተማ ውስጥ የሚገኝ መኖሪያ ቤቱን ቢሸጥ ከሸጠበት ጊዜ ጀምሮ እስከ አንድ ዓመት ሊዋጀው ይችላል፤ የመዋጀት መብቱ እስከ አንድ ዓመት ድረስ ነው። አንዱ ዓመት ከማለቁ በፊት መዋጀት ካልቻለ ግን፣ ቅጥር በተሠራለት ከተማ ውስጥ ያለው ቤት የገዢውና የልጅ ልጆቹ ንብረት ሆኖ ይቀራል፤ በኢዮቤልዩ አይመለስለትም። ቅጥር በዙሪያው ባልተሠራለት መንደር ውስጥ የሚገኙ ቤቶች ግን እንደ ዕርሻ መሬት ተቈጥረው ሊዋጁ ይችላሉ፤ በኢዮቤልዩም ይመለሳሉ። “ ‘ነገር ግን ሌዋውያን የራሳቸው በሆኑት ከተሞች ውስጥ የሚገኙትን ቤቶቻቸውን ምንጊዜም የመዋጀት መብት አላቸው። ሌዋውያን በከተማቸው ያለውን ቤታቸውን ቢሸጡና መዋጀት ባይችሉ፣ በኢዮቤልዩ ይመለሳል፤ በሌዋውያን ከተሞች የሚገኙ ቤቶች በእስራኤላውያን መካከል የሌዋውያን ንብረት ናቸውና። በከተሞቻቸው ዙሪያ ያለው የግጦሽ መሬት ግን አይሸጥ፤ ለዘላለም ቋሚ ንብረታቸው ነውና። “ ‘በመካከልህ ከወገንህ አንዱ ቢደኸይ፣ ራሱንም መርዳት ባይችል፣ በመካከልህ ይኖር ዘንድ መጻተኛውን ወይም እንግዳውን እንደምትረዳ እርዳው። ወገንህ በመካከልህ ይኖር ዘንድ ምንም ዐይነት ወለድ አትቀበለው፤ አምላክህን (ኤሎሂም) ፍራው። ገንዘብህን በዐራጣ አታበድረው፤ ምግብህንም በትርፍ አትሽጥለት። የከነዓንን ምድር ልሰጥህና አምላክህ (ኤሎሂም) ልሆን፣ ከግብፅ ያወጣሁህ እኔ እግዚአብሔር አምላክህ (ያህዌ ኤሎሂም) ነኝ።

ዘሌዋውያን 25:23-38 መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) (አማ54)

ምድርም ለእኔ ናትና፥ እናንተም ከእኔ ጋር እንግዶችና መጻተኞች ናችሁና ምድርን ለዘላለም አትሽጡ። በርስታችሁም ምድር ሁሉ መቤዠትን ለምድሪቱ አድርጉ። ወንድምህም ቢደኸይ ከርስቱም ቢሸጥ፥ ለእርሱ የቀረበ ዘመዱ መጥቶ ወንድሙ የሸጠውን ይቤዠዋል። የሚቤዠውም ሰው ቢያጣ፥ እርሱም እጁ ቢረጥብ፥ ለመቤዠትም የሚበቃ ቢያገኝ፥ የሽያጩን ዘመን ቈጥሮ የቀረውን ወደ ገዛው ሰው ይመልስ፤ እርሱም ወደ ርስቱ ይመለስ። ለራሱም ዕዳውን መክፈል ባይችል፥ ሽያጩ በገዛው ሰው እጅ እስከ ኢዮቤልዩ ዓመት ድረስ ይቀመጥ፤ በኢዮቤልዩ ዓመት ይውጣ፥ እርሱም ወደ ርስቱ ይመለስ። ሰውም ቅጥር ባለበት ከተማ መኖሪያ ቤትን ቢሸጥ፥ ከተሸጠ በኋላ አንድ ዓመት እስኪፈጸም ድረስ ለመቤዠት ይችላል፤ ለአንድ ሙሉ ዓመት መቤዠት ይችላል። አንድ ዓመትም እስኪጨረስ ባይቤዠው፥ ቅጥር ባለበት ከተማ የሚሆን ቤት ለገዛው ለልጅ ልጁ ለዘላለም ይጸናለታል፤ በኢዮቤልዩም ከእርሱ አይወጣም። ቅጥር በሌለበት መንደር ያሉ ቤቶች ግን እንደ እርሻ ይቈጠራሉ፤ ይቤዣሉ፥ በኢዮቤልዩም ይወጣሉ። በእነርሱ ከተማ ያለ የሌዋውያን ቤት ግን ሌዋውያን ለዘላለም መቤዠት ይችላሉ። ማናቸውም ሰው ከሌዋውያን ቤት ቢገዛ፥ በእስራኤል ልጆች መካከል የሌዋውያን ከተማ ቤቶች ርስቶቻቸው ናቸውና በርስቱ ከተማ ያለ የተሸጠው ቤት በኢዮቤልዩ ይመለሳል። በከተማቸውም ዙሪያ ያለችው መሰምርያ የዘላለም ርስታቸው ናትና አትሸጥም። ወንድምህ ቢደኸይ እጁም በአንተ ዘንድ ቢደክም፥ አጽናው፤ እንደ እንግዳና እንደ መጻተኛም ከአንተ ጋር ይኑር። ወንድምህ ከአንተ ጋር ይኖር ዘንድ ከእርሱ ምንም ወለድ ወይም ትርፍ አትውሰድ፤ ነገር ግን አምላክህን ፍራ። ብርህን በወለድ አታበድረው፤ መኖህንም በትርፍ አትስጠው። የከነዓንን ምድር እሰጣችሁ ዘንድ፥ አምላክም እሆናችሁ ዘንድ ከግብፅ ምድር ያወጣኋችሁ እኔ እግዚአብሔር አምላካችሁ ነኝ።

ዘሌዋውያን 25:23-38 አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም (አማ05)

“ምድሪቱ ለዘለቄታ መሸጥ አይገባትም፤ እርስዋ የእኔ እንጂ የእናንተ አይደለችም፤ እናንተ እንደ መጻተኛ ሆናችሁ እንድትጠቀሙባት ብቻ ፈቅጃለሁ። “መሬት በሚሸጥበት ጊዜ የቀድሞ ባለቤቱ መልሶ ለመዋጀት መብት ያለው መሆኑ መታወቅ አለበት። አንድ እስራኤላዊ ድኻ ሆኖ መሬቱን ለመሸጥ ቢገደድ የቅርብ ዘመዱ የሆነ ሰው ሊዋጅለት ይገባዋል። ሊዋጅለት የሚችል የቅርብ ዘመድ ባይኖረው ግን ዘግየት ብሎ ሀብት በሚያገኝበት ጊዜ እርሱ ራሱ መዋጀት ይችላል። ይህንንም ማድረግ በሚችልበት ጊዜ እስከ ተከታዩ የንብረት መመለስ ዓመት ያለውን ዘመን ቈጥሮ ቀሪውን ገንዘብ ለገዛው ሰው ከመለሰለት በኋላ ወደ ርስቱ ይመለስ። ነገር ግን ለመዋጀት የሚያስችል በቂ ገንዘብ ባይኖረው ርስቱ እስከ ተከታዩ የኢዩቤልዩ ዓመት ድረስ በዚያው በገዛው ሰው እጅ ሊቆይለት ይችላል። በዚያም ዓመት ርስቱ ለባለቤቱ ይመለሳል። “አንድ ሰው ቅጽር በተሠራላት ከተማ ውስጥ ቤት ቢሸጥ ከተሸጠበት ዕለት ጀምሮ በአንድ ዓመት ውስጥ መልሶ የመዋጀት መብት አለው። ነገር ግን በዓመቱ ውስጥ መልሶ መዋጀት ባይችል፥ መልሶ የመዋጀት መብቱን ያጣል፤ ቤቱም ለገዛው ሰው ወይም ለዘሮቹ ቀዋሚ ንብረት ሆኖ ይቀራል፤ በኢዮቤልዩ ዓመት እንኳ ለሻጩ አይመለስለትም። ቅጽር ባልተሠራላቸው መንደሮች ውስጥ የሚገኙ ቤቶችን መሸጥ የሚችሉት ግን የእርሻ መሬቶች በሚሸጡበት ዐይነት ይሆናል፤ ባለ ንብረቱ እንደገና የመዋጀት መብት አለው፤ በኢዮቤልዩ ዓመት ንብረቱን መመለስ አለበት። ይሁን እንጂ ሌዋውያን ለእነርሱ በተመደቡላቸው ከተሞች የሚገኘውን ንብረት በማንኛውም ጊዜ መልሶ የመዋጀት መብት ይኖራቸዋል። ሌዋውያን በገዛ ከተሞቻቸው የሚሠሩአቸው ቤቶች በእስራኤላውያን መካከል የእነርሱ ቀዋሚ ንብረቶች ናቸው። በእነዚህ ከተሞች ውስጥ አንድ ሌዋዊ ቤት ቢሸጥና መልሶ ለመዋጀት ባይችል በኢዮቤልዩ ዓመት ይመለስለታል፤ ነገር ግን በሌዋውያን ከተሞች ዙሪያ የሚገኝ የግጦሽ ሣር መሬት ፈጽሞ አይሸጥም፤ እርሱ ለዘለዓለም ቀዋሚ ንብረታቸው ነው። “በአቅራቢያህ የሚኖር እስራኤላዊ ወገንህ ደኽይቶ ራሱን መርዳት የማይችል ቢሆን በአጠገብህ መኖር ይችል ዘንድ ላስጠጋኸው መጻተኛ በምታደርገው ዐይነት የሚያስፈልገውን ሁሉ በፈቃድህ አድርግለት። ወለድ እንዲከፍል አታድርገው፤ እግዚአብሔርን በመፍራት እስራኤላዊ ወገንህ በአጠገብህ እንዲኖር ፍቀድለት። በምታበድረውም ገንዘብ ወለድ አትጠይቀው፤ በምትሸጥለትም ምግብ ትርፍ አትጠይቀው። የከነዓንን ምድር እንድሰጣችሁና አምላካችሁ እንድሆን ከግብጽ ምድር ያወጣኋችሁ እኔ አምላካችሁ እግዚአብሔር ነኝ።

ዘሌዋውያን 25:23-38 መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) (መቅካእኤ)

ምድሪቱም የእኔ ናትና፥ እናንተም ከእኔ ዘንድ እንግዶችና መጻተኞች ናችሁና ምድሪቱን ለዘለዓለም አትሽጧት። በርስት በያዛችሁት ምድር ሁሉ መቤዠትን ለምድሪቱ ታደርጋላችሁ። “ወንድምህም ቢደኸይ ከርስቱም ቢሸጥ፥ የቅርብ ዘመዱ የሆነ ሰው መጥቶ ወንድሙ የሸጠውን ይቤዠዋል። የሚቤዠውም ሰው ባይኖረው፥ እርሱም ቢበለጥግ፥ ለመቤዠትም የሚበቃ ቢያገኝ፥ እርሱም እስከ ሸጠበት ጊዜ ያሉትን ዓመታት ያሰላል፥ ከዚያም የቀረውን ወደ ገዛው ሰው ይመልሳል፤ እርሱም ወደ ርስቱ ይመለሳል። ለማስመለስ ግን በቂ ገንዘብ ባያገኝ፥ ሽያጩ እስከ ኢዮቤልዩ ዓመት ድረስ በገዛው ሰው እጅ ይሆናል፤ በኢዮቤልዩ ዓመት ነፃ ይወጣል፥ እርሱም ወደ ርስቱ ይመለሳል። “ማናቸውም ሰው ቅጥር ባለው ከተማ ውስጥ ያለ መኖሪያ ቤትን ቢሸጥ፥ ከተሸጠ በኋላ አንድ ዓመት እስኪፈጸም ድረስ ለመቤዠት ይችላል፤ ለአንድ ሙሉ ዓመት የመቤዠት መብት አለውና። አንድ ዓመትም እስከሚፈጸም ባለው ጊዜ ሁሉ ባይቤዠው፥ ቅጥር ባለው ከተማ ውስጥ ያለው ቤት ለገዛው ሰው ለልጅ ልጁ ለዘለዓለም ይጸናለታል፤ በኢዮቤልዩም ከእርሱ ነፃ አይወጣም። ነገር ግን በዙሪያቸው ቅጥሮች በሌላቸው መንደሮች ያሉ ቤቶች እንደ እርሻ መሬቶች ይቈጠራሉ፤ ይቤዣሉ፥ በኢዮቤልዩም ነፃ ይወጣሉ። ነገር ግን ለሌዋውያን ርስታቸው በሆኑት በሌዋውያን ከተሞች ውስጥ ያሉትን ቤቶች ለዘለዓለም የመቤዠት መብት አላቸው። ማናቸውም ሰው ከሌዋውያን ቤት ቢገዛ፥ በእስራኤል ልጆች መካከል በሌዋውያን ከተሞች ያሉ ቤቶች ለሌዋውያን ርስቶቻቸው ናቸውና በርስታቸው ከተማ ውስጥ የተሸጠው ቤት በኢዮቤልዩ ይመለሳል። በከተማቸውም ዙሪያ ያለው መሰማሪያ የዘለዓለም ርስታቸው ነውና አይሸጥም። “ወንድምህ ቢደኸይ፥ እርሱም በአንተ ዘንድ ራሱን መቻል ቢያቅተው፥ አጽናው፤ እንደ እንግዳና እንደ መጻተኛም ከአንተ ጋር ይኑር። ወንድምህ ከአንተ ጋር እንዲኖር ከእርሱ ምንም ወለድ ወይም ትርፍ አትውሰድ፤ ነገር ግን አምላክህን ፍራ። ብርህን በወለድ አታበድረው፤ ምግብህንም በትርፍ አትሽጥለት። የከነዓንን ምድር እንድሰጣችሁ፥ አምላክም እንድሆናችሁ ከግብጽ ምድር ያወጣኋችሁ እኔ ጌታ አምላካችሁ ነኝ።