ኢዮብ 5:9-16
ኢዮብ 5:9-16 የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) (አማ2000)
እርሱ የማይመረመረውን ታላቅ ነገርና የማይቈጠረውን የከበረና ድንቅ ነገር ያደርጋል። በምድር ላይ ዝናብን ይሰጣል፥ ከሰማይም በታች ውኃን ይልካል። የተዋረዱትን ከፍ ያደርጋቸዋል፥ የወደቁትንም ያነሣቸዋል። የተንኰለኞችን ምክር ይለውጣል፥ እጆቻቸውም ቅን አይሠሩም። ጠቢባንንም በተንኰላቸው ይይዛቸዋል፤ ምክርን የሚጐነጉኑ ሰዎችን አሳብ ያጠፋል። በቀን ጨለማ ያገኛቸዋል፥ በቀትርም ጊዜ በሌሊት እንዳሉ ይርመሰመሳሉ። በጦርነት ይጠፋሉ፤ ደካማውም ከኀያሉ እጅ ያመልጣል። ለምስኪኑ ተስፋ አለውና፤ የዐመጸኛም አፍ ይዘጋልና።
ኢዮብ 5:9-16 አዲሱ መደበኛ ትርጒም (NASV)
እርሱ፣ የማይመረመሩ ድንቅ ነገሮች፣ የማይቈጠሩም ታምራት ያደርጋል። ምድሪቱን በዝናብ ያረሰርሳል፤ ሜዳውንም ውሃ ያጠጣል። የተዋረዱትን በከፍታ ቦታ ያስቀምጣል፤ ያዘኑትንም ወደ አስተማማኝ ስፍራ ያወጣቸዋል። እጃቸው ያሰቡትን እንዳይፈጽም፣ የተንኰለኞችን ዕቅድ ያከሽፋል። ጠቢባንን በጥበባቸው ይይዛል፤ የተንኰለኞችንም ሤራ ያጠፋል። ቀኑ ጨለማ ይሆንባቸዋል፤ በቀትርም ጊዜ በሌሊት እንዳለ ሰው በዳበሳ ይሄዳሉ። ችግረኛውን ከአፋቸው ሰይፍ፣ ከኀይለኛውም እጅ ያድነዋል። ስለዚህ ድኻ ተስፋ አለው፤ ዐመፅም አፏን ትዘጋለች።
ኢዮብ 5:9-16 መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) (አማ54)
የማይመረመረውን ታላቅ ነገርና የማይቈጠረውን ተአምራት ያደርጋል። በምድር ላይ ዝናብን ይሰጣል፥ በእርሻም ላይ ውኃ ይልካል። የተዋረዱትን ወደ ላይ ያወጣል፥ ኀዘንተኞችንም ለደኅንነት ከፍ ከፍ ያደርጋቸዋል። እጃቸውም ምክራቸውን እንዳይፈጽም የተንኰለኞችን አሳብ ከንቱ ያደርገዋል። ጠቢባንን በተንኰላቸው ይይዛቸዋል፥ የጠማሞችንም ምክር ይዘረዝራል። በቀን ጨለማን ያገኛሉ፥ በቀትርም ጊዜ በሌሊት እንዳሉ ይርመሰመሳሉ። ድሀውንም ከአፋቸው ሰይፍ ከኃያሉም እጅ ያድነዋል። ለምስኪኑም ተስፋ አለው፥ ክፋት ግን አፍዋን ትዘጋለች።
ኢዮብ 5:9-16 አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም (አማ05)
እርሱ የማይቈጠረውን ተአምራት፦ የማይመረመረውን ታላቅ ነገር ያደርጋል። በምድር ላይ ዝናብን ያዘንባል፤ እርሻዎችንም በውሃ ያረሰርሳል። የተዋረዱትን በክብር ከፍ ያደርጋቸዋል፤ ያዘኑትንም በማጽናናት ደስ ያሰኛቸዋል። ሥራቸው እንዳይሳካ የተንኰለኞችን ዕቅድ ከንቱ ያደርጋል። ጥበበኞችን የራሳቸው ተንኰል ወጥመድ ሆኖ እንዲይዛቸው ያደርጋል የተንኰለኞችም ዕቅድ በፍጥነት ይጠፋል። ቀኑ ጨለማ ይሆንባቸዋል፤ ገና በእኩለ ቀን፥ በሌሊት ጨለማ ውስጥ እንዳሉ ሆነው ይደናበሩ። ድኾችን ከጠላቶቻቸው ሰይፍ ያድናቸዋል፤ ችግረኞችንም ከጨቋኞች እጅ ነጻ ያወጣቸዋል። ለድኾች ተስፋ ይሰጣል፤ ዐመፅንም ከምድረ ገጽ ያጠፋል።
ኢዮብ 5:9-16 መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) (መቅካእኤ)
የማይመረመረውን ታላቅ ነገርና የማይቈጠረውን ተአምራት ያደርጋል። በምድር ላይ ዝናብን ይሰጣል፥ በእርሻም ላይ ውኃ ይልካል። የተዋረዱትን ወደ ላይ ያወጣል፥ ያዘኑትን ለደኅንነት ከፍ ያደርጋቸዋል። የተንኰለኞችን አሳብ ከንቱ ያደርገዋል፥ እጃቸውም ደባቸውን ከግብ እንዳያደርስ። ጠቢባንን በተንኰላቸው ይይዛቸዋል፥ የጠማሞችንም ምክር ያጠፋል። በቀን ጨለማን ያገኛሉ፥ በቀትርም ጊዜ በሌሊት እንዳሉ ይርመሰመሳሉ። ድሀውን ከአፋቸው ሰይፍ አንዲሁም ከኃያላን እጅ ያድነዋል። ለምስኪኑም ተስፋ አለው፥ ግፍ ግን አፍዋን ትዘጋለች።