የYouVersion አርማ
የፍለጋ አዶ

መጽሐፈ ኢዮብ 5

5
1“አሁንም ተጣራ፥ የሚመልስልህ አለን?
ከቅዱሳንስ ወደማናቸው ትዞራለህ?
2አላዋቂውን ሰው ቁጣ ይገድለዋል፥
ሞኙንም ቅንዓት ያጠፋዋል።
3አላዋቂውን ሰው ሥር ሰድዶ አየሁት፥
ድንገትም መኖሪያውን ረገምሁ።
4ልጆቹም ከደኅንነት ርቀዋል፥
በበርም ውስጥ ተረግጠዋል፥
የሚደርስላቸውም የለም።
5የሰበሰበውንም የተራበ ይበላዋል፥
ከእሾህም ውስጥ እንኳ ያወጣዋል፥
የተጠማ ሀብታቸውን ዋጠ።
6ችግር ከትቢያ አይመጣም፥
መከራም ከመሬት አይበቅልም፥
7ሰው ለመከራ ተወልዶአል
የአሞራ ግልገሎች ወደ ላይ እየበረሩ ከፍ እንደሚሉ።
8እኔ ግን እግዚአብሔርን እለምን ነበር፥
ነገሬንም ወደ እግዚአብሔር አቀርብ ነበር።
9 # ሲራ. 43፥32። የማይመረመረውን ታላቅ ነገርና
የማይቈጠረውን ተአምራት ያደርጋል።
10በምድር ላይ ዝናብን ይሰጣል፥
በእርሻም ላይ ውኃ ይልካል።
11የተዋረዱትን ወደ ላይ ያወጣል፥
ያዘኑትን ለደኅንነት ከፍ ያደርጋቸዋል።
12 # 1ቆሮ. 3፥19። የተንኰለኞችን አሳብ ከንቱ ያደርገዋል፥
እጃቸውም ደባቸውን ከግብ እንዳያደርስ።
13ጠቢባንን በተንኰላቸው ይይዛቸዋል፥
የጠማሞችንም ምክር ያጠፋል።
14በቀን ጨለማን ያገኛሉ፥
በቀትርም ጊዜ በሌሊት እንዳሉ ይርመሰመሳሉ።
15ድሀውን ከአፋቸው ሰይፍ
አንዲሁም ከኃያላን እጅ ያድነዋል።
16ለምስኪኑም ተስፋ አለው፥
ግፍ ግን አፍዋን ትዘጋለች።
17 # ምሳ. 3፥11፤12፤ ዕብ. 12፥5፤6። እነሆ፥ እግዚአብሔር የሚገሥጸው ሰው ብፁዕ ነው፥
ስለዚህ ሁሉን የሚችለውን የአምላክን ተግሣጽ አትናቅ።
18 # ሆሴዕ 6፥1። እርሱ ቢያቈስልም ይጠግናልና፥
ቢሰብርም፥ እጆቹ ይፈውሳሉና።
19ከስድስት ችግሮች ያድንሃል፥
በሰባተኛውም ውስጥ ክፋት አትነካህም።
20በራብ ጊዜ ከሞት፥
በሰልፍም ጊዜ ከሰይፍ እጅ ያድንሃል።
21ከምላስ ጅራፍ ትሰወራለህ፥
የጥፋት አደጋ ሲመጣም አትፈራም።
22በጥፋት አደጋና በራብ ላይ ትስቃለህ፥
የምድረ በዳ አራዊትንም አትፈራም፥
23ቃል ኪዳንህ ከምድረበዳ ድንጋይ ጋር ይሆናልና#5፥23 ይህ ጥቅስ ብዙ አመራምሯል። የድንጋይ ብዛት እርሻን እንዳያሰናክል ስምምነት ይኖርሃል ለማለት ይቻላል። ወይንም በድንጋይ የተከለለው የእርሻ ወሰን አይደፈርም ለማለት ይሆናል።
የምድረ በዳም አራዊት ከአንተ ጋር ይስማማሉና።
24ድንኳንህ ሰላምን እንደሚያገኝም ታውቃለህ፥
በረትህን ትጐበኛለህ፥ አንዳችም አይጐድልብህም።
25ዘርህም እንደሚበዛ፥
ትውልድህም እንደ ምድር ሣር ብዙ እንደሚሆን ታውቃለህ።
26የእህሉ ነዶ ወራቱ ሲደርስ ወደ አውድማ እንደሚገባ፥
ዕድሜ ጠግበህ ወደ መቃብር ትገባለህ።
27እነሆ፥ ይህችን መረመርን፥ የሰማነውም ይህ ነው፥
አንተም ለራስህ እወቀው።”

ማድመቅ

Share

Copy

None

ያደመቋቸው ምንባቦች በሁሉም መሣሪያዎችዎ ላይ እንዲቀመጡ ይፈልጋሉ? ይመዝገቡ ወይም ይግቡ