መጽሐፈ ኢዮብ 4
4
1ቴማናዊውም ኤልፋዝ መለሰ፤ እንዲህም አለ፦
2“አንድ ሰው ከአንተ ጋር ለመናገር ቢሞክር ትቀየማለህን?
ቃልንስ ከመናገር ማን ሊቀር ይችላል?
3እነሆ፥ አንተ ብዙዎችን ታስተምር ነበር፥
የደከሙትንም እጆች ታበረታ ነበር፥
4ቃልህ የሚሰናከለውን ያስነሣ ነበር፥
አንተም የሚብረከረከውን ጉልበት ታጸና ነበር።
5አሁን ግን በአንተ ላይ መጥቷል፥ አንተም ደከምህ፥
ደርሶብሃል፥ አንተም ተረበሽህ።
6አምላክህን መፍራትህ መጽናናትህ፥
የቅንነትህም መንገድ ተስፋህ አይደለምን?
7እባክህ አስብ፥ ንጹሕ ሆኖ የጠፋ ማን ነው?
ከልበ ቅንስ የተደመሰሰ ማን ነው?
8እኔ እንዳየሁት፥ ኃጢአትን የሚያርሱ፥
መከራንም የሚዘሩ ይህንኑ ያጭዳሉ።
9በእግዚአብሔር እስትንፋስ ይጠፋሉ፥
በቁጣውም መንፈስ ያልቃሉ።
10የአንበሳ ጩኸት፥ የጩዋኺ አንበሳ ድምፅ፥
የአንበሳ ደቦል ጥርስ ተሰባበረ።
11አንበሳ አደን በማጣት ይሞታል፥
የአንበሳይቱም ግልገሎች ይበተናሉ።
12ለእኔም በምሥጢር ቃል መጣልኝ፥
ጆሮዬም ሹክሹክታውን ሰማች።
13 #
ኢዮብ 33፥15። በሌሊት ሕልም አሳብ ሲነሣ፥
የከበደም እንቅልፍ በሰው ላይ ሲወድቅ፥
14ድንጋጤ ወደቀብኝ፥ እንዲሁም መንቀጥቀጥ
አጥንቶቼን ሁሉ ተነዋወጡ።
15መንፈስም በፊቴ አለፈ፥
የሥጋዬ ጠጉር ቆመ።
16እርሱም ቆመ፥ መልኩን ግን ለመለየት አልቻልሁም፥
ምሳሌም በዓይኔ ፊት ነበረ፥
ዝምታም ነበር፥ ድምፅም ሰማሁ፦
17‘በውኑ ሰው በእግዚአብሔር ፊት ጻድቅ ሊሆን፥
ወይስ ሰው በፈጣሪው ፊት ሊነጻ ይችላልን?
18እነሆ፥ በአገልጋዮቹ እንኳን አይተማመንም፥
በመላእክቱንም ላይ ስሕተት ያገኛል፥
19ይልቁንስ በጭቃ ቤት የሚኖሩ፥
መሠረታቸው በትቢያ ውስጥ የሆነ፥
ከብል በፊት የሚጨፈለቁ እንዴት ይሆኑ?
20በጥዋትና በማታ መካከል ይሰባበራሉ፥
ማንም ሳያስብ ለዘለዓለም ይጠፋሉ።
21ገመዳቸው የተነቀለ አይደለምን?#4፥21 ሰው ሲሞት ሀብቱን በሙሉ ጥሎ ያልፋል።
አለጥበብም ይሞታሉ።’”
Currently Selected:
መጽሐፈ ኢዮብ 4: መቅካእኤ
ማድመቅ
ያጋሩ
ኮፒ

ያደመቋቸው ምንባቦች በሁሉም መሣሪያዎችዎ ላይ እንዲቀመጡ ይፈልጋሉ? ይመዝገቡ ወይም ይግቡ