የYouVersion አርማ
የፍለጋ አዶ

መጽ​ሐፈ ኢዮብ 5

5
1“አሁ​ንም የሚ​መ​ል​ስ​ልህ ካለ ጥራ፥
ከቅ​ዱ​ሳን መላ​እ​ክ​ትም የም​ታ​የው ካለ?
2ሰነ​ፉን ሰው ቍጣ ይገ​ድ​ለ​ዋ​ልና፥
ቅን​ዓ​ትም ሰነ​ፉን ያጠ​ፋ​ዋል።
3ሰነ​ፎ​ችን ሥር ሰድ​ደው አየ​ኋ​ቸው፥
በድ​ን​ገ​ትም መኖ​ሪ​ያ​ቸው ጠፋች።
4ልጆ​ቻ​ቸው ከደ​ኅ​ን​ነት ርቀ​ዋል፥
በበ​ርም ውስጥ ይቀ​ጠ​ቅ​ጡ​አ​ቸ​ዋል፤ መከ​ራም ያጸ​ኑ​ባ​ቸ​ዋል፥
የሚ​ታ​ደ​ጋ​ቸ​ውም የለም።
5እነ​ርሱ የሰ​በ​ሰ​ቡ​ት​ንም ጻድ​ቃን ይበ​ሉ​ታል።
እነ​ር​ሱን ግን ክፋት ቷጋ​ቸ​ዋ​ለች፥
ኀይ​ላ​ቸ​ውም ይደ​ክ​ማል።
6ችግር ከም​ድር አይ​ወ​ጣ​ምና፥
መከ​ራም ከተ​ራ​ሮች አይ​በ​ቅ​ል​ምና፤
7የአ​ሞራ ግል​ገ​ሎች ግን ወደ ላይ እየ​በ​ረሩ ከፍ እን​ዲሉ፥
ሰው እን​ዲሁ ለድ​ካም ተወ​ል​ዶ​አል።
8“እኔ ግን እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርን እለ​ም​ነው ነበር፥
የሁሉ ጌታ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ር​ንም እጠ​ራው ነበር።
9እርሱ የማ​ይ​መ​ረ​መ​ረ​ውን ታላቅ ነገ​ርና
የማ​ይ​ቈ​ጠ​ረ​ውን የከ​በ​ረና ድንቅ ነገር ያደ​ር​ጋል።
10በም​ድር ላይ ዝና​ብን ይሰ​ጣል፥
ከሰ​ማ​ይም በታች ውኃን ይል​ካል።
11የተ​ዋ​ረ​ዱ​ትን ከፍ ያደ​ር​ጋ​ቸ​ዋል፥
የወ​ደ​ቁ​ት​ንም ያነ​ሣ​ቸ​ዋል።
12የተ​ን​ኰ​ለ​ኞ​ችን ምክር ይለ​ው​ጣል፥
እጆ​ቻ​ቸ​ውም ቅን አይ​ሠ​ሩም።
13ጠቢ​ባ​ን​ንም በተ​ን​ኰ​ላ​ቸው ይይ​ዛ​ቸ​ዋል፤
ምክ​ርን የሚ​ጐ​ነ​ጉኑ ሰዎ​ችን አሳብ ያጠ​ፋል።
14በቀን ጨለማ ያገ​ኛ​ቸ​ዋል፥
በቀ​ት​ርም ጊዜ በሌ​ሊት እን​ዳሉ ይር​መ​ሰ​መ​ሳሉ።
15በጦ​ር​ነት ይጠ​ፋሉ፤
ደካ​ማ​ውም ከኀ​ያሉ እጅ ያመ​ል​ጣል።
16ለም​ስ​ኪ​ኑ ተስፋ አለ​ውና፤
የዐ​መ​ጸ​ኛም አፍ ይዘ​ጋ​ልና።
17“ነገር ግን እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር የሚ​ገ​ሥ​ጸው ሰው ብፁዕ ነው፤
ስለ​ዚህ ሁሉን የሚ​ች​ለ​ውን የአ​ም​ላ​ክን ተግ​ሣጽ አት​ናቅ።
18እርሱ ይሰ​ብ​ራል፥ ዳግ​መ​ኛም ይጠ​ግ​ናል፤
ይቀ​ሥ​ፋል፥ እጆ​ቹም ይፈ​ው​ሳሉ።
19ስድ​ስት ጊዜ ከክፉ ነገር ያድ​ን​ሃል፥
በሰ​ባ​ተ​ኛ​ውም ጊዜ ክፋት አት​ነ​ካ​ህም።
20በራብ ጊዜ ከሞት ያድ​ን​ሃል፥
በጦ​ር​ነ​ትም ጊዜ ከሰ​ይፍ እጅ ያድ​ን​ሃል።
21ከም​ላስ ጅራፍ ይሰ​ው​ር​ሃል፥
ከም​ት​መ​ጣ​ብ​ህም ክፋት አት​ፈ​ራም።
22በኃ​ጥ​ኣ​ንና በዐ​መ​ጸ​ኞች ላይ ትስ​ቅ​ባ​ቸ​ዋ​ለህ፤
ከም​ድረ በዳ አራ​ዊ​ትም አት​ፈ​ራም፤
23የም​ድረ በዳ አራ​ዊ​ትም ከአ​ንተ ጋር ይስ​ማ​ማሉ።
24ያን​ጊዜ ቤትህ በሰ​ላም እን​ዲ​ሆን ታው​ቃ​ለህ፤
ከን​ብ​ረ​ት​ህም አን​ዳች አይ​ጐ​ድ​ልም።
25ዘር​ህም ብዙ እን​ዲ​ሆን፥
ልጆ​ች​ህም እንደ አማረ መስክ ሣር እን​ዲ​ሆኑ ታው​ቃ​ለህ።
26በወ​ራቱ የደ​ረሰ አዝ​መራ እን​ዲ​ሰ​በ​ሰብ፥
የእ​ህሉ ነዶም በወ​ቅቱ ወደ አው​ድማ እን​ዲ​ገባ፥
በረ​ዥም ዕድሜ ወደ መቃ​ብር ትገ​ባ​ለህ።
27እነሆ፥ ይህን ዐው​ቀን መረ​መ​ርን፥ የሰ​ማ​ነ​ውም ይህ ነው፤
አንተ ግን አን​ዳች ሠር​ተህ እንደ ሆነ ለራ​ስህ ዕወቅ።”

ማድመቅ

Share

Copy

None

ያደመቋቸው ምንባቦች በሁሉም መሣሪያዎችዎ ላይ እንዲቀመጡ ይፈልጋሉ? ይመዝገቡ ወይም ይግቡ