የYouVersion አርማ
የፍለጋ አዶ

መጽ​ሐፈ ኢዮብ 6

6
የኢ​ዮብ መልስ
1ኢዮ​ብም መለሰ፥ እን​ዲ​ህም አለ፦
2“ከእ​ና​ንተ አንዱ መቅ​ሠ​ፍ​ቴን ምነው በመ​ዘነ ኖሮ!
መከ​ራ​ዬ​ንም በአ​ን​ድ​ነት ምነው በሚ​ዛን ላይ ባኖ​ረው ኖሮ!
3ከባ​ሕር አሸዋ ይልቅ ይከ​ብድ ነበ​ርና፤
ነገር ግን ቃሌ ሐሰ​ትን ይመ​ስ​ላል።
4እነሆ፥ የእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር#ዕብ. “ሁሉን የሚ​ችል” ይላል። ፍላጻ በሥ​ጋዬ ላይ ነው፤
መር​ዙም ደሜን ይመ​ጥ​ጣል።
ለመ​ና​ገር ስጀ​ም​ርም ይወ​ጋ​ኛል።
5በውኑ የሜዳ አህያ ሣር እያ​ለው በከ​ንቱ ይጮ​ኻ​ልን? የሚ​በ​ላ​ውን ፈልጎ አይ​ደ​ለ​ምን?
ወይስ በሬ በበ​ረት ውስጥ ገለባ ሳለው ይጮ​ኻ​ልን?
6ምግብ ያለ ጨው ይበ​ላ​ልን?
የጎ​መን ዘር ጭማ​ቂስ ይጣ​ፍ​ጣ​ልን?#ግሪክ ሰባ. ሊ. “የጎ​መን ዘርዕ ጭማ​ቂስ ይጣ​ፍ​ጣ​ልን” አይ​ልም።
ወይስ ለከ​ንቱ ጣዕም አለ​ውን?
7ሰው​ነቴ ማረፍ አል​ቻ​ለ​ችም፤#ግሪክ ሰባ. ሊ. “ቍጣዬ ሊገታ” ይላል
የሥ​ጋ​ዬን ክር​ፋት#ግሪክ ሰባ. ሊ. “የም​ግ​ቤን ክር​ፋት” ይላል። እንደ አን​በሳ ክር​ፋት እመ​ለ​ከ​ተ​ዋ​ለ​ሁና።
8ልመ​ናዬ ምነው በደ​ረ​ሰ​ልኝ!
እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርም ተስ​ፋ​ዬን ምነው በሰ​ጠኝ!
9እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርም ያቈ​ስ​ለኝ ዘንድ ጀመረ፥
ነገር ግን እስከ መጨ​ረ​ሻው አላ​ጠ​ፋ​ኝም።
10መቃ​ብሬ በግ​ንቡ የም​መ​ላ​ለ​ስ​በት ከተ​ማዬ ይሁን፥
ከእ​ር​ሱም ፈቀቅ አል​ልም
የአ​ም​ላ​ኬን ቅዱስ ቃል አል​ካ​ድ​ሁ​ምና።
11እታ​ገሥ ዘንድ ጕል​በቴ ምን​ድን ነው?
ነፍ​ሴም ትጽ​ናና ዘንድ ዘመኔ ምን​ድን ነው?
12ጕል​በቴ የድ​ን​ጋይ ጉል​በት ነውን?
በውኑ ሥጋ​ዬስ እንደ ናስ ነውን?
13በእ​ርሱ የታ​መ​ንሁ አይ​ደ​ለ​ሁ​ምን?
ረድ​ኤቱ ከእኔ ለምን ራቀ?
14ምሕ​ረቱ ቸል አለኝ፥
እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር አል​ጐ​በ​ኘ​ኝም አል​ተ​መ​ለ​ከ​ተ​ኝም።
15“ወን​ድ​ሞ​ቼም እንደ ደረቅ ወንዝ፥
እንደ አለፈ ማዕ​በ​ልም አላ​ወ​ቁ​ኝም።
16ያከ​ብ​ሩኝ የነ​በሩ እነ​ዚያ፥
አሁን እንደ በረ​ዶና እንደ ረጋ አመ​ዳይ ሆኑ​ብኝ፤
17ወደ ሙቀት ሲቀ​ርብ በቀ​ለጠ ጊዜ
ምን እንደ ነበረ አይ​ታ​ወ​ቅም።
18እን​ደ​ዚ​ሁም እኔ ከሁሉ ተለ​ይቼ ጠፋሁ፥
ከቤ​ቴም ወጥቼ የተ​ጣ​ልሁ ሆንሁ።
19የቴ​ማ​ና​ው​ያ​ንን መን​ገ​ዶች፥
የሳ​ባ​ው​ያ​ንን ክፋ​ትና ቸል​ተ​ኝ​ነት ተመ​ል​ከቱ።
20በከ​ተ​ሞ​ችና በገ​ን​ዘ​ቦች የሚ​ታ​መኑ ያፍ​ራሉ።
21አሁ​ንም እና​ንተ ያለ ምሕ​ረት መጣ​ችሁ፤
ቍስ​ሌ​ንም አይ​ታ​ችሁ ፈራ​ችሁ።
22ለምን? በውኑ፦ ከእ​ና​ንተ አን​ዳች ነገር ጠየ​ቅ​ሁን?
ወይስ፦ ከእ​ና​ንተ ኀይ​ልን ተመ​ኘ​ሁን?
23ወይስ ከጠ​ላ​ቶች እጅ ታስ​ጥ​ሉኝ ዘንድ
ከኀ​ይ​ለ​ኞ​ችም እጅ ታድ​ኑኝ ዘንድ።
24“አስ​ተ​ም​ሩኝ፥ እኔም አዳ​ም​ጣ​ች​ኋ​ለሁ፤
የተ​ሳ​ሳ​ት​ሁ​ትም ካለ አስ​ረ​ዱኝ።
25የእ​ው​ነ​ተኛ ሰው ቃል ሐሰ​ትን ይመ​ስ​ላል፥
ከእ​ና​ንተ ዘንድ ኀይ​ልን የም​ጠ​ይቅ አይ​ደ​ለ​ምና።
26የን​ግ​ግ​ራ​ች​ሁም ማጽ​ና​ናት ዕረ​ፍ​ትን አይ​ሰ​ጠ​ኝም፤
የአ​ን​ደ​በ​ታ​ች​ሁም ቅል​ጥ​ፍና ደስ አያ​ሰ​ኘ​ኝም።
27በድሃ አደጉ ላይ ትስ​ቃ​ላ​ች​ሁና፥
ወዳ​ጃ​ች​ሁ​ንም ትሰ​ድ​ባ​ላ​ች​ሁና።
28አሁ​ንም፥ ፊታ​ች​ሁን አይቼ#ዕብ. “ወደ እኔ ተመ​ል​ከቱ” ይላል።
ሐሰት አል​ና​ገ​ርም።
29አሁ​ንም ተቀ​መጡ፤ በደ​ልም አይ​ኑር፤
ዳግ​መ​ኛም ከጻ​ድቁ ጋር አንድ ሁኑ።
30በአ​ን​ደ​በቴ በደል የለ​ምና
አፌ ጕሮ​ሮ​ዬም ጥበ​ብን ይና​ገ​ራል።

ማድመቅ

Share

Copy

None

ያደመቋቸው ምንባቦች በሁሉም መሣሪያዎችዎ ላይ እንዲቀመጡ ይፈልጋሉ? ይመዝገቡ ወይም ይግቡ