የYouVersion አርማ
የፍለጋ አዶ

መጽ​ሐፈ ኢዮብ 7

7
1“ጥን​ቱን በም​ድር ላይ የሰው ሕይ​ወት ጥላ አይ​ደ​ለ​ምን?#ግሪክ ሰባ. ሊ. “ፈተና አይ​ደ​ለ​ምን” ይላል።
ኑሮ​ውስ እንደ ቀን ምን​ደኛ አይ​ደ​ለ​ምን?
2ወይም ጌታ​ውን እን​ደ​ሚ​ፈራ አገ​ል​ጋይ ጥላ​ው​ንም እን​ደ​ሚ​መኝ፥
ወይም ደመ​ወ​ዙን እን​ደ​ሚ​ጠ​ብቅ ምን​ደኛ አይ​ደ​ለ​ምን?
3እን​ዲሁ እኔ የከ​ንቱ ወራ​ትን ታገ​ሥሁ፥
የፃ​ዕ​ርም ሌሊት ተወ​ሰ​ነ​ች​ልኝ።
4በተ​ኛ​ሁም ጊዜ፦ መቼ ይነ​ጋል? እላ​ለሁ፤
በተ​ነ​ሣ​ሁም ጊዜ ዳግ​መኛ መቼ ይመ​ሻል? እላ​ለሁ፤
ከማታ እስከ ጥዋት ድረስ መከ​ራን ጠገ​ብሁ።
5ሥጋዬ በት​ልና በመ​ግል በስ​ብ​ሶ​አል፥
ቍስ​ሌን በገል እያ​ከ​ክሁ አለ​ቅሁ። ዐመ​ድም ሆንሁ።
6ሕይ​ወቴ እንደ ሸማኔ መወ​ር​ወ​ርያ፥ ቀላል ሆነች#ግሪክ ሰባ. ሊ. “ከቃል ይልቅ ቀላል ሆነች” ይላል።
በከ​ንቱ ተስ​ፋም ጠፋሁ።
7ሕይ​ወቴ እስ​ት​ን​ፋስ እንደ ሆነች አስብ፤
ዐይ​ኔም መል​ካም ነገ​ርን ከእ​ን​ግ​ዲህ ወዲህ ዳግ​መኛ አታ​ይም።
8የሚ​ያ​የኝ ሰው ዐይን ከእ​ን​ግ​ዲህ ወዲህ አያ​የ​ኝም፤
ዐይ​ንህ በእኔ ላይ ይሆ​ናል፤ እኔም አል​ገ​ኝም።
9ደመና ከሰ​ማይ ተበ​ትኖ እን​ደ​ሚ​ጠፋ፥
እን​ዲሁ ወደ መቃ​ብር የሚ​ወ​ርድ ሰው ዳግ​መኛ አይ​ወ​ጣም።
10ወደ ቤቱም ዳግ​መኛ አይ​መ​ለ​ስም፥
ስፍ​ራ​ውም ዳግ​መኛ እር​ሱን አያ​ው​ቀ​ውም።
11ስለ​ዚ​ህም እኔ አፌን አል​ከ​ለ​ክ​ልም፤
በመ​ን​ፈሴ ጭን​ቀ​ትን እና​ገ​ራ​ለሁ፤
የነ​ፍ​ሴ​ንም ምሬት በኀ​ዘን እገ​ል​ጣ​ለሁ።
12ጠባቂ አዝ​ዘ​ህ​ብ​ኛ​ልና፥
እኔ ባሕር ወይስ አን​በሪ#ግእዙ “ቀላይ” ይላል። ነኝን?
13እኔም፦ አል​ጋዬ ያጽ​ና​ናኝ ይሆን?
መኝ​ታ​ዬስ ደስ ያሰ​ኘኝ ይሆን? እላ​ለሁ።
14አን​ተም በሕ​ልም ታስ​ፈ​ራ​ራ​ኛ​ለህ፥
በራ​እ​ይም ታስ​ደ​ነ​ግ​ጠ​ኛ​ለህ፤
15ሕይ​ወ​ትን ከመ​ን​ፈሴ ትለ​ያ​ለህ።
አጥ​ን​ቶ​ቼ​ንም ከሞት ትጠ​ብ​ቃ​ለህ።
16እን​ድ​ታ​ገሥ ለዘ​ለ​ዓ​ለም እኖ​ራ​ለ​ሁን?
ሕይ​ወቴ ከንቱ ነውና ከእኔ ራቅ።
17ሰው ምን​ድን ነው? ከፍ ከፍ ታደ​ር​ገው ዘንድ፥
ልቡ​ና​ው​ንም ትጐ​በ​ኘው ዘንድ፥
18ማለዳ ማለ​ዳስ ትጐ​በ​ኘው ዘንድ፥
በዕ​ረ​ፍ​ቱም ትፈ​ር​ድ​ለት ዘንድ፥
19የማ​ታ​ሳ​ር​ፈኝ እስከ መቼ ነው?
ምራ​ቄ​ንስ እስ​ክ​ውጥ ድረስ የማ​ት​ለ​ቅ​ቀኝ እስከ መቼ ነው?
20የሰ​ውን ልብ፦ የም​ታ​ውቅ ሆይ፥
በድ​ዬስ እንደ ሆነ እን​ግ​ዲህ ምን ላደ​ር​ግ​ልህ እች​ላ​ለሁ?
ስለ​ምን እኔን ለመ​ከራ አደ​ረ​ግ​ኸኝ? #ግእ​ዝና ዕብ​ራ​ይ​ስጥ ብቻ
ስለ ምን በአ​ንተ ላይ እን​ድ​ና​ገር በአ​ም​ሳ​ልህ ፈጠ​ር​ኸኝ?
ስለ ምንስ እኔ ሸክም ሆን​ሁ​ብህ?
21ስለ ምን መተ​ላ​ለ​ፌን ይቅር አት​ልም?
ኀጢ​አ​ቴ​ንስ ስለ ምን አታ​ነ​ጻም?
አሁን በም​ድር ውስጥ እተ​ኛ​ለሁ፤
በማ​ለ​ዳም አል​ነ​ቃም።”

ማድመቅ

Share

Copy

None

ያደመቋቸው ምንባቦች በሁሉም መሣሪያዎችዎ ላይ እንዲቀመጡ ይፈልጋሉ? ይመዝገቡ ወይም ይግቡ