የYouVersion አርማ
የፍለጋ አዶ

መጽ​ሐፈ ኢዮብ 8

8
የበ​ል​ዳ​ዶስ ንግ​ግር
1አው​ኬ​ና​ዊው#ዕብ. “ሱሐ​ዊው” ይላል። በል​ዳ​ዶስ መለሰ፥ እን​ዲ​ህም አለ፦
2“እስከ መቼ ይህን ነገር ትና​ገ​ራ​ለህ?
ወይስ ነገ​ርን የማ​ብ​ዛት መን​ፈስ በአ​ፍህ አለን?
3በውኑ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር በዐ​መፅ ይፈ​ር​ዳ​ልን?
ሁሉን የፈ​ጠረ አም​ላ​ክስ ጽድ​ቅን ያጣ​ም​ማ​ልን?
4ልጆ​ችህ በፊቱ በድ​ለው እንደ ሆነ፥
እርሱ በበ​ደ​ላ​ቸው እጅ ጥሎ​አ​ቸ​ዋል።
5“አንተ ግን ወደ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ገሥ​ግሥ፥
ሁሉን ወደ​ሚ​ች​ለው አም​ላ​ክም ጸልይ፥
6ንጹ​ሕና ጻድቅ ብት​ሆን፥
ልመ​ና​ህን ፈጥኖ ይሰ​ማ​ሃል፥
የጽ​ድ​ቅ​ህ​ንም ብድ​ራት ፈጽሞ ይሰ​ጥ​ሃል።
7ጅማ​ሬ​ህም ታናሽ ቢሆ​ንም እንኳ
ፍጻ​ሜህ ቍጥር አይ​ኖ​ረ​ውም።
8 # ግእዙ “ኢዮብ እን​ዲህ ይላል ወደ ሰማይ ወጥቼ መዛ​ግ​ብ​ቱን እሰ​ርቅ ዘንድ ወደ ምድ​ሩም ወርጄ እን​ደ​ዚሁ አደ​ርግ ዘንድ እች​ላ​ለ​ሁን” የሚል ይጨ​ም​ራል። ስለ​ዚህ የቀ​ደ​መ​ውን ትው​ልድ ጠይቅ፥ አባ​ቶ​ች​ንም በየ​ወ​ገ​ና​ቸው በት​ጋት መር​ምር፥
9እኛ የት​ና​ንት ብቻ ነን ምንም አና​ው​ቅም፤
ሕይ​ወ​ታ​ችን በም​ድር ላይ እንደ ጥላ ነውና
10እነ​ርሱ የሚ​ያ​ስ​ተ​ም​ሩ​ህና የሚ​ነ​ግ​ሩህ፥
ቃል​ንም ከል​ባ​ቸው የሚ​ያ​ወጡ አይ​ደ​ሉ​ምን?
11“በውኑ ደን​ገል ረግ​ረግ በሌ​ለ​በት መሬት ይበ​ቅ​ላ​ልን?
ወይስ ቄጠማ ውኃ በሌ​ለ​በት ቦታ ይለ​መ​ል​ማ​ልን?
12ገና በሥሩ ሳለ፥ ሳይ​ቈ​ረ​ጥም፥
ውኃ የማ​ይ​ጠጣ ተክል ሁሉ ይደ​ር​ቃል።
13እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርን የሚ​ረሱ ሁሉ ፍጻ​ሜ​አ​ቸው እን​ዲሁ ነው፤
የዝ​ንጉ ሰውም ተስፋ ትጠ​ፋ​ለች፤
14ቤቱም ያለ ነዋሪ ይቀ​ራል፥
ማደ​ሪ​ያ​ውም የሸ​ረ​ሪት ድር ይሆ​ናል።
15ቤቱን ቢደ​ግ​ፈ​ውም አይ​ቆ​ም​ለ​ትም፤
የጀ​መ​ረ​ው​ንም አይ​ፈ​ጽ​ምም።
16ከፀ​ሐይ በታች ይሻ​ግ​ታል፤#ዕብ. “ፀሐይ ሳይ​ተ​ኩስ ይለ​መ​ል​ማል” ይላል።
ጫፉም በአ​ት​ክ​ልት ቦታ ይወ​ጣል።
17በድ​ን​ጋይ ክምር ላይ ያድ​ራል፤
በድ​ን​ጋ​ዮ​ቹም መካ​ከል ይኖ​ራል።
18ቦታው ቢው​ጠው፦
እን​ደ​ዚህ ያለ አላ​የ​ሁም ብሎ ይክ​ደ​ዋል።
19ኀጢ​አ​ተ​ኞች እን​ዲሁ ይጠ​ፋ​ሉና፤
ሌሎ​ችም ከመ​ሬት ይበ​ቅ​ላሉ።
20እነሆ፥ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር የዋ​ሁን ሰው አይ​ጥ​ለ​ውም፥
የኀ​ጢ​ኣ​ተ​ኞ​ች​ንም እጅ አያ​በ​ረ​ታም።#“የኀ​ጢ​ኣ​ተ​ኞ​ች​ንም እጅ አያ​በ​ረ​ታም” የሚ​ለው በግ​ሪክ ሰባ. ሊ. የለም።
የዝ​ን​ጉ​ዎ​ች​ንም መባ አይ​ቀ​በ​ልም።
21የቅ​ኖ​ችን አፍ ሳቅ ይሞ​ላል፥
ከን​ፈ​ሮ​ቻ​ቸ​ው​ንም ምስ​ጋና ይሞ​ላል።
22ጠላ​ቶ​ቻ​ቸ​ውም ኀፍ​ረ​ትን ይለ​ብ​ሳሉ፤
የኀ​ጢ​ኣ​ተ​ኞ​ችም ቤት ይጠ​ፋል።”

ማድመቅ

Share

Copy

None

ያደመቋቸው ምንባቦች በሁሉም መሣሪያዎችዎ ላይ እንዲቀመጡ ይፈልጋሉ? ይመዝገቡ ወይም ይግቡ