መጽሐፈ ኢዮብ 8
8
የበልዳዶስ ንግግር
1አውኬናዊው#ዕብ. “ሱሐዊው” ይላል። በልዳዶስ መለሰ፥ እንዲህም አለ፦
2“እስከ መቼ ይህን ነገር ትናገራለህ?
ወይስ ነገርን የማብዛት መንፈስ በአፍህ አለን?
3በውኑ እግዚአብሔር በዐመፅ ይፈርዳልን?
ሁሉን የፈጠረ አምላክስ ጽድቅን ያጣምማልን?
4ልጆችህ በፊቱ በድለው እንደ ሆነ፥
እርሱ በበደላቸው እጅ ጥሎአቸዋል።
5“አንተ ግን ወደ እግዚአብሔር ገሥግሥ፥
ሁሉን ወደሚችለው አምላክም ጸልይ፥
6ንጹሕና ጻድቅ ብትሆን፥
ልመናህን ፈጥኖ ይሰማሃል፥
የጽድቅህንም ብድራት ፈጽሞ ይሰጥሃል።
7ጅማሬህም ታናሽ ቢሆንም እንኳ
ፍጻሜህ ቍጥር አይኖረውም።
8 # ግእዙ “ኢዮብ እንዲህ ይላል ወደ ሰማይ ወጥቼ መዛግብቱን እሰርቅ ዘንድ ወደ ምድሩም ወርጄ እንደዚሁ አደርግ ዘንድ እችላለሁን” የሚል ይጨምራል። ስለዚህ የቀደመውን ትውልድ ጠይቅ፥ አባቶችንም በየወገናቸው በትጋት መርምር፥
9እኛ የትናንት ብቻ ነን ምንም አናውቅም፤
ሕይወታችን በምድር ላይ እንደ ጥላ ነውና
10እነርሱ የሚያስተምሩህና የሚነግሩህ፥
ቃልንም ከልባቸው የሚያወጡ አይደሉምን?
11“በውኑ ደንገል ረግረግ በሌለበት መሬት ይበቅላልን?
ወይስ ቄጠማ ውኃ በሌለበት ቦታ ይለመልማልን?
12ገና በሥሩ ሳለ፥ ሳይቈረጥም፥
ውኃ የማይጠጣ ተክል ሁሉ ይደርቃል።
13እግዚአብሔርን የሚረሱ ሁሉ ፍጻሜአቸው እንዲሁ ነው፤
የዝንጉ ሰውም ተስፋ ትጠፋለች፤
14ቤቱም ያለ ነዋሪ ይቀራል፥
ማደሪያውም የሸረሪት ድር ይሆናል።
15ቤቱን ቢደግፈውም አይቆምለትም፤
የጀመረውንም አይፈጽምም።
16ከፀሐይ በታች ይሻግታል፤#ዕብ. “ፀሐይ ሳይተኩስ ይለመልማል” ይላል።
ጫፉም በአትክልት ቦታ ይወጣል።
17በድንጋይ ክምር ላይ ያድራል፤
በድንጋዮቹም መካከል ይኖራል።
18ቦታው ቢውጠው፦
እንደዚህ ያለ አላየሁም ብሎ ይክደዋል።
19ኀጢአተኞች እንዲሁ ይጠፋሉና፤
ሌሎችም ከመሬት ይበቅላሉ።
20እነሆ፥ እግዚአብሔር የዋሁን ሰው አይጥለውም፥
የኀጢኣተኞችንም እጅ አያበረታም።#“የኀጢኣተኞችንም እጅ አያበረታም” የሚለው በግሪክ ሰባ. ሊ. የለም።
የዝንጉዎችንም መባ አይቀበልም።
21የቅኖችን አፍ ሳቅ ይሞላል፥
ከንፈሮቻቸውንም ምስጋና ይሞላል።
22ጠላቶቻቸውም ኀፍረትን ይለብሳሉ፤
የኀጢኣተኞችም ቤት ይጠፋል።”
Currently Selected:
መጽሐፈ ኢዮብ 8: አማ2000
ማድመቅ
Share
Copy
ያደመቋቸው ምንባቦች በሁሉም መሣሪያዎችዎ ላይ እንዲቀመጡ ይፈልጋሉ? ይመዝገቡ ወይም ይግቡ