ኢዮብ 33:14-16
ኢዮብ 33:14-16 የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) (አማ2000)
እግዚአብሔር በሕልም ወይም በሌሊት ራእይ፥ አንድ ጊዜ ወይም ሁለት ጊዜ የተናገረ እንደሆነ፥ በአልጋ ላይ ተኝተው ሳሉ፥ በሰዎች ላይ ታላቅ ድንጋጤን ያመጣል። በዚያን ጊዜ የሰዎችን ማስተዋል ይከፍታል፥ ግርማ ባለው ራእይም ያስደነግጣቸዋል፤
Share
ኢዮብ 33 ያንብቡኢዮብ 33:14-16 አዲሱ መደበኛ ትርጒም (NASV)
ሰው ባያስተውለውም፣ እግዚአብሔር በተለያየ መንገድ ይናገራል፤ ሰዎች ዐልጋቸው ላይ ተኝተው ሳሉ፣ ከባድ እንቅልፍ ሲወድቅባቸው፣ በሕልም፣ በሌሊትም ራእይ ይናገራል። በጆሯቸው ይናገራል፤ በማስጠንቀቂያም ያስደነግጣቸዋል፤
Share
ኢዮብ 33 ያንብቡኢዮብ 33:14-16 መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) (አማ54)
እግዚአብሔር በአንድ መንገድ በሌላም ይናገራል፥ ሰው ግን አያስተውለውም። በሕልም፥ በሌሊት ራእይ፥ አፍላ እንቅልፍ በሰዎች ላይ ሲወድቅ፥ በአልጋ ላይ ተኝተው ሳሉ፥ በዚያን ጊዜ የሰዎችን ጆሮ ይከፍታል፥ በተግሣጹም ያስደነግጣቸዋል፥
Share
ኢዮብ 33 ያንብቡ