የYouVersion አርማ
የፍለጋ አዶ

መጽ​ሐፈ ኢዮብ 33

33
ኤል​ዩስ ኢዮ​ብን እንደ ገሠ​ጸው
1“ነገር ግን፥ ኢዮብ ሆይ፥ ቃሌን ስማ፥
ነገ​ሬ​ንም አድ​ምጥ።
2እነሆ፥ አፌን ከፍ​ቻ​ለሁ፥
አን​ደ​በ​ቴም ይና​ገ​ራል።
3ልቤም ንጹሕ ነገ​ርን ያስ​ባል፥
የከ​ን​ፈ​ሮ​ችም ማስ​ተ​ዋል ንጹሕ ነገ​ርን ይመ​ረ​ም​ራል።
4የእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር መን​ፈስ ፈጠ​ረኝ፥
ሁሉ​ንም የሚ​ችል የአ​ም​ላክ እስ​ት​ን​ፋስ ያስ​ተ​ም​ረ​ኛል።
5በዚህ ነገር ልት​መ​ል​ስ​ልኝ ትችል እንደ ሆነ ታገ​ሠኝ፥
እኔም እነ​ግ​ር​ሃ​ለሁ፤ አን​ተም መል​ስ​ልኝ።
6አንተ እንደ እኔ ከጭቃ የተ​ፈ​ጠ​ርህ ነህ፥
የሁ​ላ​ች​ንም ተፈ​ጥሮ ከዚ​ያው ነው።#በዕ​ብ​ራ​ይ​ስጥ ልዩ​ነት አለው።
7እነሆ፥ ግር​ማዬ አታ​ስ​ፈ​ራ​ህም፥
እጄም አት​ከ​ብ​ድ​ብ​ህም።
8ግፍ​ህን ተና​ግ​ረ​ሃል፥
የቃ​ል​ህ​ንም ድምፅ ሰም​ቻ​ለሁ፥ እን​ዲ​ህም ብለ​ሃል፦
9እኔ ንጹሕ ነኝ፥ አል​በ​ደ​ል​ሁ​ምና፤
እኔ ጻድቅ ነኝ፥ ኀጢ​አ​ት​ንም አል​ሠ​ራ​ሁም።
10እነሆ፥ ምክ​ን​ያት አግ​ኝ​ቶ​ብ​ኛል፥
እንደ ጠላ​ትም ቈጥ​ሮ​ኛል፤
11እግ​ሬን በግ​ንድ አጣ​በቀ፥
መን​ገ​ዴ​ንም ሁሉ ጠበቀ።
12እነሆ፥ እኔ ጻድቅ ነኝ፥ ቃሌ​ንም አይ​ሰ​ማ​ኝም እን​ዴት ትላ​ለህ?
ከሟች ሰው በላይ ያለ እርሱ ዘለ​ዓ​ለ​ማዊ ነውና።
13አንተ፦ ‘ቃሌን ሁሉ ለምን አይ​ሰ​ማ​ኝም?’ ትላ​ለህ።
14እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር በሕ​ልም ወይም በሌ​ሊት ራእይ፥
አንድ ጊዜ ወይም ሁለት ጊዜ የተ​ና​ገረ እን​ደ​ሆነ፥
15በአ​ልጋ ላይ ተኝ​ተው ሳሉ፥
በሰ​ዎች ላይ ታላቅ ድን​ጋ​ጤን ያመ​ጣል።
16በዚ​ያን ጊዜ የሰ​ዎ​ችን ማስ​ተ​ዋል ይከ​ፍ​ታል፥
ግርማ ባለው ራእ​ይም ያስ​ደ​ነ​ግ​ጣ​ቸ​ዋል፤
17ሰውን ከኀ​ጢ​አቱ ይመ​ል​ሰው ዘንድ፥
ሥጋ​ው​ንም ከው​ድ​ቀት ያድ​ነው ዘንድ፥
18ነፍ​ሱን ከሞት ያድ​ና​ታል፤
በሰ​ይ​ፍም እን​ዳ​ይ​ጠፋ ይጠ​ብ​ቀ​ዋል።
19“ደግሞ በአ​ልጋ ላይ በደዌ ይገ​ሥ​ጸ​ዋል፥
አጥ​ን​ቱም ሁሉ ይን​ቋ​ቋል።
20ማን​ኛ​ው​ንም መብል መቅ​መስ አይ​ች​ልም።
ሰው​ነቱ ግን መብ​ልን ትበላ ዘንድ ትመ​ኛ​ለች።
21ሥጋው እስ​ከ​ሚ​ያ​ልቅ ድረስ፥
አጥ​ን​ቱም ባዶ​ውን እስ​ከ​ሚ​ታይ ድረስ፥
22ሰው​ነቱ ለሞት፥
ሕይ​ወ​ቱም ወደ ሲኦል ቀር​ባ​ለች።
23የሞት መላ​እ​ክት ምንም ሺህ ቢሆኑ፥#በዕ​ብ​ራ​ይ​ስጥ ልዩ​ነት አለው።
በልቡ ወደ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ሊመ​ለስ ቢያ​ስብ፥
ኀጢ​አ​ቱን ለሰው ቢና​ገር፥
በደ​ሉ​ንም ቢገ​ልጥ፥
ከእ​ነ​ርሱ አንዱ እንኳ አይ​ገ​ድ​ለ​ውም፤
24በሞት እን​ዳ​ይ​ጠፋ ይጠ​ብ​ቀ​ዋል፥
ሰው​ነ​ቱ​ንም እንደ ግድ​ግዳ ምርግ ያድ​ሳ​ታል።
አጥ​ን​ቶ​ቹ​ንም በመ​ቅን ይሞ​ላል።
25ሥጋ​ውን እንደ ሕፃን ሥጋ ያለ​መ​ል​ማል፤
ከሰ​ዎ​ችም ይልቅ ወደ ጕብ​ዝ​ናው ዘመን ይመ​ል​ሰ​ዋል።
26ወደ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ይጸ​ል​ያል፥
ጸሎ​ቱም ተቀ​ባ​ይ​ነ​ትን ያገ​ኛል።
በደ​ስ​ተ​ኛም ፊት እያ​መ​ሰ​ገነ ይገ​ባል፥
ለሰ​ውም ጽድ​ቁን ይመ​ል​ስ​ለ​ታል።
27ያን​ጊ​ዜም ሰው ራሱን ይነ​ቅ​ፋል፤ እን​ዲ​ህም ይላል፦
‘እኔ ምን አድ​ር​ጌ​አ​ለሁ?
እንደ ኀጢ​አ​ቶ​ችም መጠን አል​ቀ​ጣ​ኝም፤
28ነፍሴ ወደ ጥፋት እን​ዳ​ት​ወ​ርድ አድ​ኖ​አ​ታል፥
ሕይ​ወ​ቴም ብር​ሃ​ንን ታያ​ለች።’
29“እነሆ፦ ሁሉን የሚ​ችል እርሱ፥
ይህን ሁሉ ሦስት ጊዜ ከሰው ጋር ያደ​ር​ጋል፤
30ሕይ​ወ​ቴም በብ​ር​ሃን ውስጥ ታመ​ሰ​ግን ዘንድ፥
እርሱ ነፍ​ሴን ከሞት አድ​ኖ​አ​ታል።
31ኢዮብ ሆይ፥ አድ​ምጥ፥ እኔ​ንም ስማ፤
ዝም በል፥ እኔም እና​ገ​ራ​ለሁ።
32ነገር ቢኖ​ርህ ተና​ገር፤
ትጸ​ድቅ ዘንድ እወ​ድ​ዳ​ለ​ሁና ተና​ገር።
33ያለ​ዚ​ያም እኔን ስማ፤
ዝም በል፥ እኔም ጥበ​ብን አስ​ተ​ም​ር​ሃ​ለሁ።”

ማድመቅ

Share

Copy

None

ያደመቋቸው ምንባቦች በሁሉም መሣሪያዎችዎ ላይ እንዲቀመጡ ይፈልጋሉ? ይመዝገቡ ወይም ይግቡ