ኢዮብ 16:1-21
ኢዮብ 16:1-21 አዲሱ መደበኛ ትርጒም (NASV)
ኢዮብም እንዲህ ሲል መለሰ፤ “ይህን የሚመስል ብዙ ነገር ሰምቻለሁ፤ እናንተ ሁላችሁ የምታስጨንቁ አጽናኞች ናችሁ። ይህ ከንቱ ንግግር አያልቅምን? ትለፈልፍ ዘንድ የሚገፋፋህ ምንድን ነው? እናንተ በእኔ ስፍራ ብትሆኑ ኖሮ፣ እኔም እንደ እናንተ መናገር እችል ነበር፤ ቃላት አሳክቼ በመናገር፣ በእናንተ ላይ ራሴን መነቅነቅ በቻልሁ ነበር። ይልቁንም አንደበቴ ባበረታታችሁ፣ የከንፈሬም ማጽናናት ባሳረፋችሁ ነበር። “ብናገር ሕመሜ አይሻለኝም፤ ዝም ብልም አይተወኝም። እግዚአብሔር ሆይ አሁንስ አድክመኸኛል፤ ወገኖቼንም ሁሉ አጥፍተሃል። ጭምትርትር ያደረግኸኝ ምስክር ሆኖብኛል፣ ዐጥንቴን ያወጣው ክሳቴም ያጋልጠኛል። በቍጣው ሰነጠቀኝ፤ በጥላቻው አስጨነቀኝ፣ ጥርሱን ነከሰብኝ፤ ባላጋራዬ ክፉ ዐይኑን ተከለብኝ። ሰዎች በፌዝ አፋቸውን ከፈቱብኝ፤ በንቀት ጕንጬን ጠፈጠፉኝ፤ በአንድነትም በላዬ ተሰበሰቡ። እግዚአብሔር ለክፉዎች አሳልፎ ሰጠኝ፤ በጠማሞችም እጅ ጣለኝ። በሰላም እኖር ነበር፤ እርሱ ግን ሰባበረኝ፤ ዐንገቴን ይዞ አደቀቀኝ፤ ማነጣጠሪያ ዒላማው አደረገኝ፤ የርሱ ቀስተኞች ከበቡኝ፤ ያለ ርኅራኄ ኵላሊቴን ይበጣጥሳል፤ ሐሞቴን መሬት ላይ ያፈስሳል። ደጋግሞ ይቀጠቅጠኛል፤ እንደ ጦረኛም ተንደርድሮ ይመጣብኛል። “በቈዳዬ ላይ ማቅ ሰፍቻለሁ፤ ቀንዴን በዐፈር ውስጥ ቀብሬአለሁ። ፊቴ ከልቅሶ የተነሣ ቀልቷል፤ ጨለማም በዐይኖቼ ቆብ ላይ ዐርፏል፤ ነገር ግን በእጄ ዐመፅ አይገኝም፤ ጸሎቴም ንጹሕ ነው። “ምድር ሆይ፤ ደሜን አትሸፍኚ፤ ጩኸቴም ማረፊያ አያግኝ! አሁን እንኳ ምስክሬ በሰማይ አለ፤ ጠበቃዬም በላይ በአርያም ይገኛል። ወዳጆቼ በንቀት ቢመለከቱኝም፣ ዐይኔ ወደ እግዚአብሔር ያነባል። ሰው ለወዳጁ እንደሚማልድ፣ በእግዚአብሔር ፊት የሚማልድ ሰው ምነው በተገኘ!
ኢዮብ 16:1-21 አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም (አማ05)
ኢዮብም እንዲህ ሲል መለሰ፦ “ይህን የመሰለ ንግግር ብዙ ጊዜ ሰምቼአለሁ፤ እናንተ አሰልቺ አጽናኞች ናችሁ። ይህ ከንቱ ንግግራችሁ መጨረሻ የለውምን? ከእኔ ጋር ይህን ያኽል ለመከራከር ያነሣሣችሁ ምክንያት ምንድን ነው? እናንተ በእኔ ቦታ ሆናችሁ እኔ በእናንተ ቦታ ብሆን ኖሮ በንቀት ራሴን እየነቀነቅሁ አሁን እናንተ የምትሉትን ሁሉ በእናንተ ላይ አሳምሬ መናገር በቻልኩ ነበር። እንዲሁም በአንደበቴ ባበረታታኋችሁና እናንተንም ለማጽናናት ብዙ መናገር በቻልኩ ነበር። “ነገር ግን ብዙ ብናገርም ሕመሜ አይቀነስልኝም፤ ዝም ብዬ ብታገሠውም ሥቃዬ ከእኔ አይወገድም። አምላክ ሆይ! ከሰውነት ውጪ አደረግኸኝ፤ ቤተሰቤንም ሁሉ አጠፋህብኝ። የሰውነቴ መጨማደድ ማስረጃ ሆኖብኛል፤ ክሳቴም በእኔ ላይ ተነሥቶ ኃጢአተኛ ነህ ብሎ ይመሰክርብኛል። እግዚአብሔር ተቈጥቶ ሰውነቴን ቈራረጠ፤ በጥላቻም ጥርሱን አፋጨብኝ፤ ጠላቴም ዐይኑን አፈጠጠብኝ። ሰዎች በዙሪያዬ ተሰብስበው ተዘባበቱብኝ፤ እያፌዙም በጥፊ መቱኝ። እግዚአብሔር ለክፉ ሰዎች አሳልፎ ሰጠኝ፤ በዐመፀኞች እጅ ላይ ጣለኝ። በሰላም እኖር ነበር፤ ነገር ግን እግዚአብሔር በቊጣው ሰባበረኝ፤ አንገቴንም አንቆ ፈጠፈጠኝ፤ ለዒላማውም አደረገኝ። ቀስተኞቹ ከበቡኝ ያለ ርኅራኄ ኲላሊቶቼን ቈራረጡ፤ ሐሞቴንም በምድር ላይ አፈሰሱ፤ እየደጋገመ አቈሰለኝ፤ እንደ ብርቱ ጦረኛም ተንደርድሮ መታኝ። ስለ ሐዘኔም ማቅ ሰፍቼ ለበስኩ፤ በትቢያ ውስጥም ተደፋሁ። ፊቴ በልቅሶ ቀላ ድቅድቅ ጨለማም ቅንድቦቼን ሸፈናቸው። ይህ ሁሉ ሲሆን የፈጸምኩት በደል የለም፤ ጸሎቴንም ወደ እግዚአብሔር የማቀርበው በንጹሕ ልብ ነው። “ምድር ሆይ! የደረሰብኝን በደል አትሸፍኚ! ስለ ፍትሕ የማቀርበው አቤቱታ ተሸፍኖ እንዲቀር አታድርጊ! እነሆ፥ ለእኔ የሚመሰክርልኝና ጥብቅናም የሚቆምልኝ በሰማይ አለ። ወዳጆቼ በንቀት ይመለከቱኛል፤ እኔ ግን ወደ እግዚአብሔር አለቅሳለሁ። ሰውና ሰውን አወቃቅሶ የሚያስታርቅ እንዳለ ሁሉ፥ ምነው ሰውንና እግዚአብሔርን አወቃቅሶ የሚያስታርቅ በኖረ፤
ኢዮብ 16:1-21 የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) (አማ2000)
ኢዮብም መለሰ እንዲህም አለ፦ “እንደዚህ ያለ ብዙ ነገር ሰማሁ፤ እናንተ ሁላችሁ የምታደክሙ አጽናኞች ናችሁ። የመጣላችሁን ሁሉ ያለ ልክ ትናገራላችሁ፦ ትከራከሩኝ ዘንድስ ምን አስቸገርኋችሁ? እኔ ደግሞ እናንተ እንደምትናገሩ እናገር ነበር፤ ነፍሳችሁ በነፍሴ ፋንታ ብትሆን ኖሮ፥ እኔም ነገርን እነግራችሁ ነበር፤ ራሴንም በእናንተ ላይ እነቀንቅ ነበር። ባፌም ኀይል ቢኖረኝ ኖሮ፥ ከንፈሬን ባልገታሁም ነበር፥ የምናገረውንም ባሻሻልሁ ነበር፤ እኔ ብናገር ቍስሌ አይድንም፤ ዝም ብልም ሕማሜ ይብስብኛል። አሁን ግን የዕብድ ቍርጥራጭና ብጥስጣሽ አደረግኸኝ፤ እኔንም መያዝህ ምስክር ሆነችብኝ፤ ሐሰቴም በእኔ ላይ ተነሣች፤ በፊቴም ተከራከረችብኝ። በቍጣው ጣለኝ፤ ጥርሶቹንም አፋጨብኝ፤ ፍላጻዎቹንም በእኔ ላይ ፈተነ። ዐይኖችን አፍዝዞ ጋረደኝ፤ በተሳለ ጦርም ጕልበቴን ወግቶ ጣለኝ። በአንድነትም ከበቡኝ። እግዚአብሔር ለጠማማ ሰው አሳልፎ ሰጠኝ፤ በክፉዎችም እጅ ጣለኝ። ተዘልዬ ስኖርም ጣለኝ፤ የራስ ጠጕሬን ይዞ ነጨው፤ እንደ ዓላማም አድርጎ አቆመኝ፤ እንደ ጉበኛም ተመለከተኝ። በጦር ከበቡኝ፤ ኵላሊቴንም ወጉኝ፤ እነርሱም አልራሩልኝም፤ ሐሞቴንም በምድር ላይ አፈሰሱ። በውድቀት ላይ ውድቀትን አደረሱብኝ፤ ኀያላኑ እየሠገጉ ሮጡብኝ። በቍርበቴ ላይ ማቅ ሰፉ፤ መከራዬ በመሬት ላይ በዛች። ሆዴ በልቅሶ ተቃጠለ፤ የሞት ጥላን በቅንድቦች ላይ አያለሁ፤ ነገር ግን በእጄ ዐመፅ የለም፤ ጸሎቴም ንጹሕ ነው። መሬት ሥጋዬን ይሸፍነው ይሆን? ደሜስ ይፈስስ ይሆን? የምጮህበትስ ቦታ አላገኝ ይሆን? “አሁንም፥ እነሆ፥ ምስክሬ በሰማይ አለ፤ የሚያውቅልኝም በአርያም ነው። ጸሎቴ ወደ እግዚአብሔር ትድረስ፥ ዐይኔም በፊቱ እንባ ታፍስስ።
ኢዮብ 16:1-21 አዲሱ መደበኛ ትርጒም (NASV)
ኢዮብም እንዲህ ሲል መለሰ፤ “ይህን የሚመስል ብዙ ነገር ሰምቻለሁ፤ እናንተ ሁላችሁ የምታስጨንቁ አጽናኞች ናችሁ። ይህ ከንቱ ንግግር አያልቅምን? ትለፈልፍ ዘንድ የሚገፋፋህ ምንድን ነው? እናንተ በእኔ ስፍራ ብትሆኑ ኖሮ፣ እኔም እንደ እናንተ መናገር እችል ነበር፤ ቃላት አሳክቼ በመናገር፣ በእናንተ ላይ ራሴን መነቅነቅ በቻልሁ ነበር። ይልቁንም አንደበቴ ባበረታታችሁ፣ የከንፈሬም ማጽናናት ባሳረፋችሁ ነበር። “ብናገር ሕመሜ አይሻለኝም፤ ዝም ብልም አይተወኝም። እግዚአብሔር ሆይ አሁንስ አድክመኸኛል፤ ወገኖቼንም ሁሉ አጥፍተሃል። ጭምትርትር ያደረግኸኝ ምስክር ሆኖብኛል፣ ዐጥንቴን ያወጣው ክሳቴም ያጋልጠኛል። በቍጣው ሰነጠቀኝ፤ በጥላቻው አስጨነቀኝ፣ ጥርሱን ነከሰብኝ፤ ባላጋራዬ ክፉ ዐይኑን ተከለብኝ። ሰዎች በፌዝ አፋቸውን ከፈቱብኝ፤ በንቀት ጕንጬን ጠፈጠፉኝ፤ በአንድነትም በላዬ ተሰበሰቡ። እግዚአብሔር ለክፉዎች አሳልፎ ሰጠኝ፤ በጠማሞችም እጅ ጣለኝ። በሰላም እኖር ነበር፤ እርሱ ግን ሰባበረኝ፤ ዐንገቴን ይዞ አደቀቀኝ፤ ማነጣጠሪያ ዒላማው አደረገኝ፤ የርሱ ቀስተኞች ከበቡኝ፤ ያለ ርኅራኄ ኵላሊቴን ይበጣጥሳል፤ ሐሞቴን መሬት ላይ ያፈስሳል። ደጋግሞ ይቀጠቅጠኛል፤ እንደ ጦረኛም ተንደርድሮ ይመጣብኛል። “በቈዳዬ ላይ ማቅ ሰፍቻለሁ፤ ቀንዴን በዐፈር ውስጥ ቀብሬአለሁ። ፊቴ ከልቅሶ የተነሣ ቀልቷል፤ ጨለማም በዐይኖቼ ቆብ ላይ ዐርፏል፤ ነገር ግን በእጄ ዐመፅ አይገኝም፤ ጸሎቴም ንጹሕ ነው። “ምድር ሆይ፤ ደሜን አትሸፍኚ፤ ጩኸቴም ማረፊያ አያግኝ! አሁን እንኳ ምስክሬ በሰማይ አለ፤ ጠበቃዬም በላይ በአርያም ይገኛል። ወዳጆቼ በንቀት ቢመለከቱኝም፣ ዐይኔ ወደ እግዚአብሔር ያነባል። ሰው ለወዳጁ እንደሚማልድ፣ በእግዚአብሔር ፊት የሚማልድ ሰው ምነው በተገኘ!
ኢዮብ 16:1-21 መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) (አማ54)
ኢዮብም መለሰ እንዲህም አለ፦ እንደዚህ ያለ ዓይነት ነገር እጅግ ሰማሁ፥ እናንተ ሁላችሁ የምታደክሙ አጽናኞች ናችሁ። በውኑ ከንቱ ቃል ይፈጸማልን? ወይስ ትመልስ ዘንድ ያነሣሣህ ምንድር ነው? እኔ ደግሞ እንደ እናንተ እናገር ዘንድ ይቻለኝ ነበር፥ ነፍሳችሁ በነፍሴ ፋንታ ቢሆን ኖሮ፥ እኔ በእናንተ ላይ ቃል ማሳካት፥ ራሴንም በእናንተ ላይ መነቅነቅ በተቻለኝ ነበር። በአፌም ነገር ባበረታኋችሁ ነበር፥ የከንፈሬን ማጽናናት ባልከለከልሁም ነበር። እኔ ብናገር ሕማሜ አይቀነስም፥ ዝምም ብል ከእኔ አይወገድም። አሁን ግን አድክሞኛል፥ ወገኔንም ሁሉ አፍርሰሃል። መጨማተሬ ይመሰክርብኛል፥ ክሳቴም ተነሥቶብኛል፥ በፊቴም ይመሰክርብኛል። በቍጣው ቀደደኝ፥ እርሱም ጠላኝ፥ ጥርሶቹንም አፋጨብኝ፥ ጠላቴ ዓይኑን አፈጠጠብኝ፥ እነርሱም አፋቸውን ከፈቱብኝ፥ እያላገጡ ጕንጬን ጠፈጠፉኝ፥ በአንድነትም ተሰበሰቡብኝ። እግዚአብሔር ለጠማማ ሰው አሳልፎ ሰጠኝ፥ በክፋዎችም እጅ ጣለኝ። ተዘልዬ ተቀምጬ ነበር፥ እርሱም ሰበረኝ፥ አንገቴንም ይዞ ቀጠቀጠኝ፥ እንደ ዓላማ አድርጎ አቆመኝ። ቀስተኞቹ ከበቡኝ፥ ኵላሊቴንም ቈራረጠ፥ እርሱም አልራራም፥ ሐሞቴን በምድር ላይ አፈሰሰ። በቍስል ላይ ቍስል ጨመረብኝ፥ እንደ ኃያል እየሠገገ ይሮጥብኛል። በቁርበቴ ላይ ማቅ ሰፋሁ፥ ቀንዴንም በመሬት ላይ አኖርሁ። ፊቴ ከልቅሶ የተነሣ ቀላ፥ የሞት ጥላ በዓይኖቼ ቆብ ላይ አለ፥ ነገር ግን በእጄ ዓመፅ የለም፥ ጸሎቴም ንጹሕ ነው። ምድር ሆይ፥ ደሜን አትክደኚ፥ ለጩኸቴም ማረፊያ አይሁን። አሁንም፥ እነሆ፥ ምስክሬ በሰማይ አለ፥ የሚመሰክርልኝም በአርያም ነው። ጸሎቴ ወደ እግዚአብሔር ይድረስ፥ ዓይኔም በፊቱ እንባ ታፍስስ። የሰው ልጅ ከባልንጀራው ጋር እንደሚምዋገት፥ ሰው በእግዚአብሔር ፊት ለመምዋገት ምነው በቻለ!
ኢዮብ 16:1-21 አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም (አማ05)
ኢዮብም እንዲህ ሲል መለሰ፦ “ይህን የመሰለ ንግግር ብዙ ጊዜ ሰምቼአለሁ፤ እናንተ አሰልቺ አጽናኞች ናችሁ። ይህ ከንቱ ንግግራችሁ መጨረሻ የለውምን? ከእኔ ጋር ይህን ያኽል ለመከራከር ያነሣሣችሁ ምክንያት ምንድን ነው? እናንተ በእኔ ቦታ ሆናችሁ እኔ በእናንተ ቦታ ብሆን ኖሮ በንቀት ራሴን እየነቀነቅሁ አሁን እናንተ የምትሉትን ሁሉ በእናንተ ላይ አሳምሬ መናገር በቻልኩ ነበር። እንዲሁም በአንደበቴ ባበረታታኋችሁና እናንተንም ለማጽናናት ብዙ መናገር በቻልኩ ነበር። “ነገር ግን ብዙ ብናገርም ሕመሜ አይቀነስልኝም፤ ዝም ብዬ ብታገሠውም ሥቃዬ ከእኔ አይወገድም። አምላክ ሆይ! ከሰውነት ውጪ አደረግኸኝ፤ ቤተሰቤንም ሁሉ አጠፋህብኝ። የሰውነቴ መጨማደድ ማስረጃ ሆኖብኛል፤ ክሳቴም በእኔ ላይ ተነሥቶ ኃጢአተኛ ነህ ብሎ ይመሰክርብኛል። እግዚአብሔር ተቈጥቶ ሰውነቴን ቈራረጠ፤ በጥላቻም ጥርሱን አፋጨብኝ፤ ጠላቴም ዐይኑን አፈጠጠብኝ። ሰዎች በዙሪያዬ ተሰብስበው ተዘባበቱብኝ፤ እያፌዙም በጥፊ መቱኝ። እግዚአብሔር ለክፉ ሰዎች አሳልፎ ሰጠኝ፤ በዐመፀኞች እጅ ላይ ጣለኝ። በሰላም እኖር ነበር፤ ነገር ግን እግዚአብሔር በቊጣው ሰባበረኝ፤ አንገቴንም አንቆ ፈጠፈጠኝ፤ ለዒላማውም አደረገኝ። ቀስተኞቹ ከበቡኝ ያለ ርኅራኄ ኲላሊቶቼን ቈራረጡ፤ ሐሞቴንም በምድር ላይ አፈሰሱ፤ እየደጋገመ አቈሰለኝ፤ እንደ ብርቱ ጦረኛም ተንደርድሮ መታኝ። ስለ ሐዘኔም ማቅ ሰፍቼ ለበስኩ፤ በትቢያ ውስጥም ተደፋሁ። ፊቴ በልቅሶ ቀላ ድቅድቅ ጨለማም ቅንድቦቼን ሸፈናቸው። ይህ ሁሉ ሲሆን የፈጸምኩት በደል የለም፤ ጸሎቴንም ወደ እግዚአብሔር የማቀርበው በንጹሕ ልብ ነው። “ምድር ሆይ! የደረሰብኝን በደል አትሸፍኚ! ስለ ፍትሕ የማቀርበው አቤቱታ ተሸፍኖ እንዲቀር አታድርጊ! እነሆ፥ ለእኔ የሚመሰክርልኝና ጥብቅናም የሚቆምልኝ በሰማይ አለ። ወዳጆቼ በንቀት ይመለከቱኛል፤ እኔ ግን ወደ እግዚአብሔር አለቅሳለሁ። ሰውና ሰውን አወቃቅሶ የሚያስታርቅ እንዳለ ሁሉ፥ ምነው ሰውንና እግዚአብሔርን አወቃቅሶ የሚያስታርቅ በኖረ፤
ኢዮብ 16:1-21 መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) (መቅካእኤ)
ኢዮብም መለሰ፤ እንዲህም አለ፦ “እንደዚህ ያለ ነገር አብዝቼ ሰማሁ፥ እናንተ ሁላችሁ የምታደክሙ አጽናኞች ናችሁ። በውኑ ከንቱ ቃል መጨረሻ የለውምን? ወይስ ትመልስ ዘንድ ያነሣሣህ ምንድነው? እኔ ደግሞ እንደ እናንተ እናገር ዘንድ ይቻለኝ ነበር፥ ነፍሳችሁ በነፍሴ ፋንታ ቢሆን ኖሮ፥ እኔ በእናንተ ላይ ቃል ማሳካት፥ ራሴንም በእናንተ ላይ መነቅነቅ በተቻለኝ ነበር። በአፌም ነገር ባበረታኋችሁ ነበር፥ የከንፈሬን ማጽናናት ባልከለከልሁም ነበር።” “እኔ ብናገር ሕማሜ አይቀነስም፥ ዝምም ብል ከእኔ አይወገድም። አሁን ግን አድክሞኛል፥ ወገኔንም ሁሉ አፍርሰሃል። መጨማተሬ ይመሰክርብኛል፥ ክሳቴም ተነሥቶብኛል፥ በፊቴም ይመሰክርብኛል። በቁጣው ቆራረጠኝ፥ እርሱም ጠላኝ፥ ጥርሶቹንም አፋጨብኝ፥ ጠላቴ ዓይኑን አፈጠጠብኝ፥ እነርሱም አፋቸውን ከፈቱብኝ፥ እያላገጡ ጉንጬን ጠፈጠፉኝ፥ በአንድነትም ተሰበሰቡብኝ። እግዚአብሔር ለጠማማ ሰው አሳልፎ ሰጠኝ፥ በክፋዎችም እጅ ጣለኝ። በርጋታ ተቀምጬ ነበር፥ እርሱም ሰበረኝ፥ አንገቴንም ይዞ ቀጠቀጠኝ፥ እንደ ዒላማ አድርጎ አቆመኝ። ቀስተኞቹ ከበቡኝ፥ ኩላሊቴንም ቈራረጠ፥ እርሱም አልራራም፥ ሐሞቴን በምድር ላይ አፈሰሰ። በቁስል ላይ ቁስል ጨመረብኝ፥ እንደ ኃያል እየሠገገ ይሮጥብኛል። በቆዳዬ ላይ ማቅ ሰፋሁ፥ ቀንዴንም በመሬት ላይ አኖርሁ። ፊቴ ከልቅሶ የተነሣ ቀላ፥ የሞት ጥላ በዐይኖቼ ቆብ ላይ አለ፥ ነገር ግን በእጄ ዓመጽ የለም፥ ጸሎቴም ንጹሕ ነው።” “ምድር ሆይ፥ ደሜን አትክደኚ፥ ለጩኸቴም ማረፊያ አይኑር። አሁንም፥ እነሆ፥ ምስክሬ በሰማይ አለ፥ የሚመሰክርልኝም በአርያም ነው። ወዳጆቼ ናቁኝ፥ ዓይኔም በእግዚአብሔር ፊት እንባ ታፈሳለች። የሰው ልጅ ከባልንጀራው ጋር እንደሚምዋገት፥ ሰው በእግዚአብሔር ፊት ለመምዋገት ምነው በቻለ!