ኢዮብም መለሰ እንዲህም አለ፦ “እንደዚህ ያለ ብዙ ነገር ሰማሁ፤ እናንተ ሁላችሁ የምታደክሙ አጽናኞች ናችሁ። የመጣላችሁን ሁሉ ያለ ልክ ትናገራላችሁ፦ ትከራከሩኝ ዘንድስ ምን አስቸገርኋችሁ? እኔ ደግሞ እናንተ እንደምትናገሩ እናገር ነበር፤ ነፍሳችሁ በነፍሴ ፋንታ ብትሆን ኖሮ፥ እኔም ነገርን እነግራችሁ ነበር፤ ራሴንም በእናንተ ላይ እነቀንቅ ነበር። ባፌም ኀይል ቢኖረኝ ኖሮ፥ ከንፈሬን ባልገታሁም ነበር፥ የምናገረውንም ባሻሻልሁ ነበር፤ እኔ ብናገር ቍስሌ አይድንም፤ ዝም ብልም ሕማሜ ይብስብኛል። አሁን ግን የዕብድ ቍርጥራጭና ብጥስጣሽ አደረግኸኝ፤ እኔንም መያዝህ ምስክር ሆነችብኝ፤ ሐሰቴም በእኔ ላይ ተነሣች፤ በፊቴም ተከራከረችብኝ። በቍጣው ጣለኝ፤ ጥርሶቹንም አፋጨብኝ፤ ፍላጻዎቹንም በእኔ ላይ ፈተነ። ዐይኖችን አፍዝዞ ጋረደኝ፤ በተሳለ ጦርም ጕልበቴን ወግቶ ጣለኝ። በአንድነትም ከበቡኝ። እግዚአብሔር ለጠማማ ሰው አሳልፎ ሰጠኝ፤ በክፉዎችም እጅ ጣለኝ። ተዘልዬ ስኖርም ጣለኝ፤ የራስ ጠጕሬን ይዞ ነጨው፤ እንደ ዓላማም አድርጎ አቆመኝ፤ እንደ ጉበኛም ተመለከተኝ። በጦር ከበቡኝ፤ ኵላሊቴንም ወጉኝ፤ እነርሱም አልራሩልኝም፤ ሐሞቴንም በምድር ላይ አፈሰሱ። በውድቀት ላይ ውድቀትን አደረሱብኝ፤ ኀያላኑ እየሠገጉ ሮጡብኝ። በቍርበቴ ላይ ማቅ ሰፉ፤ መከራዬ በመሬት ላይ በዛች። ሆዴ በልቅሶ ተቃጠለ፤ የሞት ጥላን በቅንድቦች ላይ አያለሁ፤ ነገር ግን በእጄ ዐመፅ የለም፤ ጸሎቴም ንጹሕ ነው። መሬት ሥጋዬን ይሸፍነው ይሆን? ደሜስ ይፈስስ ይሆን? የምጮህበትስ ቦታ አላገኝ ይሆን? “አሁንም፥ እነሆ፥ ምስክሬ በሰማይ አለ፤ የሚያውቅልኝም በአርያም ነው። ጸሎቴ ወደ እግዚአብሔር ትድረስ፥ ዐይኔም በፊቱ እንባ ታፍስስ።
መጽሐፈ ኢዮብ 16 ያንብቡ
ያጋሩ
ሁሉንም ሥሪቶች ያነጻጽሩ: መጽሐፈ ኢዮብ 16:1-21
ጥቅሶችን ያስቀምጡ፣ ያለበይነመረብ ያንብቡ፣ አጫጭር የትምህርት ቪዲዮዎችን ይመልከቱ እና ሌሎችም!
ቤት
መጽሐፍ ቅዱስ
እቅዶች
ቪዲዮዎች