የYouVersion አርማ
የፍለጋ አዶ

መጽሐፈ ኢዮብ 16:1-21

መጽሐፈ ኢዮብ 16:1-21 አማ05

ኢዮብም እንዲህ ሲል መለሰ፦ “ይህን የመሰለ ንግግር ብዙ ጊዜ ሰምቼአለሁ፤ እናንተ አሰልቺ አጽናኞች ናችሁ። ይህ ከንቱ ንግግራችሁ መጨረሻ የለውምን? ከእኔ ጋር ይህን ያኽል ለመከራከር ያነሣሣችሁ ምክንያት ምንድን ነው? እናንተ በእኔ ቦታ ሆናችሁ እኔ በእናንተ ቦታ ብሆን ኖሮ በንቀት ራሴን እየነቀነቅሁ አሁን እናንተ የምትሉትን ሁሉ በእናንተ ላይ አሳምሬ መናገር በቻልኩ ነበር። እንዲሁም በአንደበቴ ባበረታታኋችሁና እናንተንም ለማጽናናት ብዙ መናገር በቻልኩ ነበር። “ነገር ግን ብዙ ብናገርም ሕመሜ አይቀነስልኝም፤ ዝም ብዬ ብታገሠውም ሥቃዬ ከእኔ አይወገድም። አምላክ ሆይ! ከሰውነት ውጪ አደረግኸኝ፤ ቤተሰቤንም ሁሉ አጠፋህብኝ። የሰውነቴ መጨማደድ ማስረጃ ሆኖብኛል፤ ክሳቴም በእኔ ላይ ተነሥቶ ኃጢአተኛ ነህ ብሎ ይመሰክርብኛል። እግዚአብሔር ተቈጥቶ ሰውነቴን ቈራረጠ፤ በጥላቻም ጥርሱን አፋጨብኝ፤ ጠላቴም ዐይኑን አፈጠጠብኝ። ሰዎች በዙሪያዬ ተሰብስበው ተዘባበቱብኝ፤ እያፌዙም በጥፊ መቱኝ። እግዚአብሔር ለክፉ ሰዎች አሳልፎ ሰጠኝ፤ በዐመፀኞች እጅ ላይ ጣለኝ። በሰላም እኖር ነበር፤ ነገር ግን እግዚአብሔር በቊጣው ሰባበረኝ፤ አንገቴንም አንቆ ፈጠፈጠኝ፤ ለዒላማውም አደረገኝ። ቀስተኞቹ ከበቡኝ ያለ ርኅራኄ ኲላሊቶቼን ቈራረጡ፤ ሐሞቴንም በምድር ላይ አፈሰሱ፤ እየደጋገመ አቈሰለኝ፤ እንደ ብርቱ ጦረኛም ተንደርድሮ መታኝ። ስለ ሐዘኔም ማቅ ሰፍቼ ለበስኩ፤ በትቢያ ውስጥም ተደፋሁ። ፊቴ በልቅሶ ቀላ ድቅድቅ ጨለማም ቅንድቦቼን ሸፈናቸው። ይህ ሁሉ ሲሆን የፈጸምኩት በደል የለም፤ ጸሎቴንም ወደ እግዚአብሔር የማቀርበው በንጹሕ ልብ ነው። “ምድር ሆይ! የደረሰብኝን በደል አትሸፍኚ! ስለ ፍትሕ የማቀርበው አቤቱታ ተሸፍኖ እንዲቀር አታድርጊ! እነሆ፥ ለእኔ የሚመሰክርልኝና ጥብቅናም የሚቆምልኝ በሰማይ አለ። ወዳጆቼ በንቀት ይመለከቱኛል፤ እኔ ግን ወደ እግዚአብሔር አለቅሳለሁ። ሰውና ሰውን አወቃቅሶ የሚያስታርቅ እንዳለ ሁሉ፥ ምነው ሰውንና እግዚአብሔርን አወቃቅሶ የሚያስታርቅ በኖረ፤