መጽሐፈ ኢዮብ 16
16
1ኢዮብም መለሰ፤ እንዲህም አለ፦
2“እንደዚህ ያለ ነገር አብዝቼ ሰማሁ፥
እናንተ ሁላችሁ የምታደክሙ አጽናኞች ናችሁ።
3በውኑ ከንቱ ቃል መጨረሻ የለውምን?
ወይስ ትመልስ ዘንድ ያነሣሣህ ምንድነው?
4እኔ ደግሞ እንደ እናንተ እናገር ዘንድ ይቻለኝ ነበር፥
ነፍሳችሁ በነፍሴ ፋንታ ቢሆን ኖሮ፥
እኔ በእናንተ ላይ ቃል ማሳካት፥
ራሴንም በእናንተ ላይ መነቅነቅ በተቻለኝ ነበር።
5በአፌም ነገር ባበረታኋችሁ ነበር፥
የከንፈሬን ማጽናናት ባልከለከልሁም ነበር።”
6“እኔ ብናገር ሕማሜ አይቀነስም፥
ዝምም ብል ከእኔ አይወገድም።
7አሁን ግን አድክሞኛል፥
ወገኔንም ሁሉ አፍርሰሃል።
8መጨማተሬ ይመሰክርብኛል፥
ክሳቴም ተነሥቶብኛል፥
በፊቴም ይመሰክርብኛል።
9በቁጣው ቆራረጠኝ፥ እርሱም ጠላኝ፥
ጥርሶቹንም አፋጨብኝ፥
ጠላቴ ዓይኑን አፈጠጠብኝ፥
10እነርሱም አፋቸውን ከፈቱብኝ፥
እያላገጡ ጉንጬን ጠፈጠፉኝ፥
በአንድነትም ተሰበሰቡብኝ።
11እግዚአብሔር ለጠማማ ሰው አሳልፎ ሰጠኝ፥
በክፋዎችም እጅ ጣለኝ።
12በርጋታ ተቀምጬ ነበር፥ እርሱም ሰበረኝ፥
አንገቴንም ይዞ ቀጠቀጠኝ፥
እንደ ዒላማ አድርጎ አቆመኝ።
13ቀስተኞቹ ከበቡኝ፥
ኩላሊቴንም ቈራረጠ፥ እርሱም አልራራም፥
ሐሞቴን በምድር ላይ አፈሰሰ።
14በቁስል ላይ ቁስል ጨመረብኝ፥
እንደ ኃያል እየሠገገ ይሮጥብኛል።
15በቆዳዬ ላይ ማቅ ሰፋሁ፥
ቀንዴንም#16፥15 ኃይሌንም። በመሬት ላይ አኖርሁ።
16ፊቴ ከልቅሶ የተነሣ ቀላ፥
የሞት ጥላ በዐይኖቼ ቆብ ላይ አለ፥
17ነገር ግን በእጄ ዓመጽ የለም፥
ጸሎቴም ንጹሕ ነው።”
18“ምድር ሆይ፥ ደሜን አትክደኚ፥
ለጩኸቴም ማረፊያ አይኑር።
19 #
ኢዮብ 19፥25። አሁንም፥ እነሆ፥ ምስክሬ በሰማይ አለ፥
የሚመሰክርልኝም በአርያም ነው።
20ወዳጆቼ ናቁኝ፥
ዓይኔም በእግዚአብሔር ፊት እንባ ታፈሳለች።
21የሰው ልጅ ከባልንጀራው ጋር እንደሚምዋገት፥
ሰው በእግዚአብሔር ፊት ለመምዋገት ምነው በቻለ!
22ጥቂት ዓመታት ካለፉ በኋላ
እኔ ወደማልመለስበት መንገድ እሄዳለሁ።”
Currently Selected:
መጽሐፈ ኢዮብ 16: መቅካእኤ
ማድመቅ
Share
Copy
ያደመቋቸው ምንባቦች በሁሉም መሣሪያዎችዎ ላይ እንዲቀመጡ ይፈልጋሉ? ይመዝገቡ ወይም ይግቡ