ኢዮብ 13:13-16
ኢዮብ 13:13-16 የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) (አማ2000)
ዝም በሉ፤ እናገርም ዘንድ ተዉኝ፤ ከቍጣዬም ልረፍ። ሥጋዬን በጥርሴ እይዛለሁ፤ ሕይወቴንም በእጄ አጥብቄ አኖራታለሁ። እነሆ፥ ኀያሉ እጁን በእኔ ላይ ቢጭን፥ እርሱ እንደ ጀመረ እናገራለሁ፥ በፊቱም እዋቀሳለሁ። ዝንጉ ሰው በፊቱ አይገባምና እርሱ መድኀኒት ይሆንልኛል።
Share
ኢዮብ 13 ያንብቡኢዮብ 13:13-16 አዲሱ መደበኛ ትርጒም (NASV)
“ዝም በሉ፤ እኔ ልናገር፤ የመጣው ይምጣብኝ። ሥጋዬን በጥርሴ፣ ሕይወቴንም በእጄ ለምን እይዛለሁ? ቢገድለኝም እንኳ በእርሱ ተስፋ አደርጋለሁ፤ ስለ መንገዴም ፊት ለፊት እከራከረዋለሁ። ኀጢአተኛ በእርሱ ፊት መቅረብ ስለማይችል፣ ይህ ድፍረቴ ለመዳኔ ይሆናል።
Share
ኢዮብ 13 ያንብቡኢዮብ 13:13-16 መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) (አማ54)
ዝም በሉ፥ እናገርም ዘንድ ተዉኝ፥ የሆነው ነገር ይምጣብኝ። ሥጋዬን በጥርሴ እይዛለሁ፥ ሕይወቴንም በእጄ አኖራለሁ። እነሆ፥ ቢገድለኝ ስንኳ እርሱን በትዕግሥት እጠባበቃለሁ፥ ነገር ግን መንገዴን በፊቱ አጸናለሁ። ዝንጉ ሰው በፊቱ አይገባምና እርሱ መድኃኒት ይሆንልኛል።
Share
ኢዮብ 13 ያንብቡ