የYouVersion አርማ
የፍለጋ አዶ

መጽሐፈ ኢዮብ 13:13-16

መጽሐፈ ኢዮብ 13:13-16 አማ05

እስቲ ዝም በሉ እኔም እንድናገር ዕድል ስጡኝ ከዚያ በኋላ የፈለገው ነገር ይሁን። “ጥርሴን ነክሼ ስጨነቅ የምኖረው ለምንድን ነው? ሕይወቴም በእጄ ላይ ነች። ስለዚህ እግዚአብሔር ሊገድለኝ ቢፈልግ ምንም የሚቀርብኝ ነገር የለም፤ ሆኖም ሁኔታዬን ለእርሱ አስረዳለሁ። ኃጢአተኛ ሰው በእግዚአብሔር ፊት መቅረብ ስለማይችል ምናልባት ይህ ድፍረቴ የመዳን ምክንያት ሊሆን ይችላል።