የYouVersion አርማ
የፍለጋ አዶ

መጽሐፈ ኢዮብ 13

13
1“እነሆ፥ ይህን ሁሉ ዓይኔ አየች፥
ጆሮዬም ሰምታ አስተዋለችው።
2እናንተ የምታውቁትን እኔ ደግሞ አውቃለሁ፥
ከእናንተ የማንስ አይደለሁም።
3ነገር ግን ሁሉን ለሚችል አምላክ መናገር እፈልጋለሁ፥
ከእግዚአብሔርም ጋር ለመዋቀስ እሻለሁ።
4እናንተ ግን በሐሰት ለባጮች#13፥4 እውነትን በሐሰት ትሸፍናላችሁ ለማለት ነው። መዝሙር 119፥ 69ን ይመልከቱ። ናችሁ፥
ሁላችሁም የማትጠቅሙ ሐኪሞች ናችሁ።
5ምነው ዝም ብላችሁ ብትኖሩ!
ይህ ጥበብ በሆነላችሁ ነበር።
6አሁንም ክርክሬን ስሙ፥
የከንፈሬንም ሙግት አድምጡ።
7በውኑ ስለ እግዚአብሔር ሐሰትን ትናገራላችሁን?
ስለ እርሱም ሽንገላን ታወራላችሁን?
8ለእርሱ እያዳላችሁ ነውን#13፥8 የዕብራይስጡ ንባብ “ፊቱን ታነሣላችሁን?” ይላል፤ የዕዮብ አነጋገር እዚህ ላይ ምፀታዊ ነው። የወዳጆቹ ንግግር ለእግዚአብሔር የሚቆረቆሩ ሰዎች ንግግር ይመስላል። ዕዮብ ግን እውነቱና ምሥጢሩ የተለየ መሆኑን ለመግለጥ ይሞክራል።?
ስለ እግዚአብሔርስ ትከራከራላችሁን?
9ቢመረምራችሁስ መልካም ይሆንልችኋልን?
ወይስ በሰውን እንደምታታልሉ ልታታልሉት ትፈልጋላችሁን?
10በስውር ብታዳሉ
በጥብቅ ይገሥጻችኋል።
11ክብሩስ አያስፈራችሁምን?
ግርማውስ አይወድቅባችሁምን?
12ምስሌዎቻችሁ#13፥12 የጥንት ተረቶችን፥ ወጎችን፥ ፈሊጦችን ያካትታል። የአመድ ምሳሌዎች ናቸው፥
ምሽጎቻችሁ የጭቃ ምሽጎች ናቸው።”
13“ዝም በሉ፥ እናገርም ዘንድ ተዉኝ፥
የፈለገ ነገር ይምጣብኝ።
14ሥጋዬን በጥርሴ እይዛለሁ፥
ሕይወቴንም በእጄ አኖራለሁ።
15እነሆ፥ ሊገድለኝ ይችላል፥ ተስፋም ባይኖረኝ፥
ነገር ግን ስለ መንገዴ በፊቱ እሟገታለሁ።
16ክፉ ሰው በፊቱ አይቀርብምና፥
እርሱ መድኃኒት ይሆንልኛል።
17ነገሬን ተግታችሁ ስሙ፥
ምስክርነቴንም በጆሮአችሁ አድምጡ።
18እነሆ፥ ሙግቴን አዘጋጅቻለሁ።
ጽድቄም እንደሚገለጽ አውቃለሁ።
19ከእኔስ ጋር የሚፋረድ ማን ነው?
አሁን እኔ ዝም ብል እሞታለሁ።
20ነገር ግን ሁለት ነገሮችን አድርግልኝና፥
የዚያን ጊዜ ከፊትህ አልሰወርም፥
21እጅህን ከእኔ አርቅ፥
ግርማህም አታስደንግጠኝ።
22ከዚያም በኋላ ጥራኝ፥ እኔም እመልስልሃለሁ።
ወይም እኔ ልናገር፥ አንተም መልስልኝ።
23ያለብኝስ በደልና ኃጢአት ምን ያህል ነው?
መተላለፌንና ኃጢአቴን አስታውቀኝ።
24ፊትህን ለምን ትሰውራለህ?
እንደ ጠላትህም የቈጠርኸኝ ለምንድነው?
25የረገፈውን ቅጠል ታስደነግጣለህን?
ወይስ የደረቀውን ገለባ ታሳድዳለህን?
26የመረረ ነገር ጽፈሕብኛልና፥
የልጅነቴንም ኃጢአት ታወርሰኛለህ።
27 # ኢዮብ 33፥11። እግሬንም በእግር ግንድ አግብተሃል፥
መንገዴንም ሁሉ ተቆጣጥረሃል፥
የእግሬንም ዱካ ወስነሃል።
28እኔ እንደሚበሰብስ የተበላሸ ነገር፥
ብልም እንደሚበላው ልብስ ነኝ።”

ማድመቅ

Share

Copy

None

ያደመቋቸው ምንባቦች በሁሉም መሣሪያዎችዎ ላይ እንዲቀመጡ ይፈልጋሉ? ይመዝገቡ ወይም ይግቡ