የYouVersion አርማ
የፍለጋ አዶ

መጽሐፈ ኢዮብ 14

14
1 # ጥበ. 2፥1፤ ሲራ. 40፥1-11፤ 41፥1-4። “ከሴት የተወለደ ሰው#14፥1 የሰው ልጅን ደካማነት ለማመልከት ነው።
የሕይወቱ ዘመን ጥቂት ቀን ነው፥ በመከራም የተሞላ ነው።
2እንደ አበባ ይፈካል፥ ይረግፋልም፥
እንደ ጥላም ይሸሻል፥ እርሱም አይጸናም።
3እንደዚህስ ባለ ሰው ላይ ዐይኖችህን ትተክላለህን?
ከአንተስ ጋር እኔን ወደ ፍርድ ታገባለህን?
4ከርኩስ ነገር ንጹሕን ማን ሊያወጣ ይችላል?
አንድ እንኳን የሚችል የለም።
5የሰው ዕድሜ የተወሰነ ነው፥
የወሩም ቍጥር በአንተ ዘንድ ነው፥
እርሱም ሊተላለፈው የማይችለውን ዳርቻ አደረግህለት።
6እንደ ምንደኛ ዕድሜው እስኪፈጸም ድረስ
ያርፍ ዘንድ ከእርሱ ጥቂት ዘወር በል።”
7“ዛፍ እንኳን ተሰፋ አለው፥ ቢቈረጥ የማቈጠቁጥ፥
ቅርንጫፉም የማደግ እድል አለው።
8ሥሩም በምድር ውስጥ ቢያረጅ፥
ግንዱም በመሬት ውስጥ ቢሞት፥
9በውኃ ሽታ ያቈጠቁጣል፥
እንደ አትክልት ቅርንጫፍ ያወጣል።
10ሰው ግን ይሞትና ይጋደማል፥
ሰውም ነፍሱ ትወጣለች፥ እርሱስ ወዴት አለ?
11ውኃ ከባሕር ውስጥ ያልቃል፥
ወንዙም ያንሳል ይደርቅማል።
12ሰውም እንዲሁ ተኝቶ አይነሣም፥
ሰማይ እስኪያልፍ ድረስ አይነቃም፥
ከእንቅልፉም አይነሣም።
13በሲኦል ውስጥ ምነው በሰወርኸኝ ኖሮ!
ቁጣህ እስኪያልፍ ድረስ በሸሸግኸኝ ኖሮ!
ቀጠሮም አድርገህ ምነው ባሰብኸኝ ኖሮ!
14በውኑ ሰው ከሞተ ተመልሶ ሕያው ይሆናልን?
ዕረፍቴ እስኪመጣ ድረስ፥
የአገልግሎቴን ዘመን ሁሉ በትዕግሥት በተጠባበቅሁ ነበር።
15በጠራኸኝና በመለስሁልህ ነበር፥
የእጅህንም ሥራ በተመኘኸው ነበር።
16አሁን ግን እርምጃዬን ቈጥረኸዋል፥
ይልቁንም ኃጢአቴን ባልተጠባበቅህ።
17መተላላፌን በከረጢት ውስጥ ታትሞ፥
ኃጢአቴንም በለበጥህበት ነበር።”
18“ተራራ ሲወድቅ ይጠፋል፥
ዓለቱም ከስፍራው ይፈልሳል፥
19ውኆች ድንጋዮቹን ይፍቃሉ፥
ፈሳሾቹም የምድሩን አፈር ይወስዳሉ፥
እንዲሁም የሰውን ተስፋ ታጠፋዋለህ።
20ለዘለዓለም ታሸንፈዋለህ፥ እርሱም ያልፋል፥
ፊቱን ትለውጣለህ፥ እርሱንም ትሰድደዋለህ።
21ልጆቹ ቢከብሩ አያውቅም፥
ቢዋረዱም አያይም።
22ነገር ግን የገዛ ሥጋው ሕመም ብቻ ይሰማዋል፥
ለራሱም ብቻ ያለቅሳል።”

ማድመቅ

Share

Copy

None

ያደመቋቸው ምንባቦች በሁሉም መሣሪያዎችዎ ላይ እንዲቀመጡ ይፈልጋሉ? ይመዝገቡ ወይም ይግቡ