መጽሐፈ ኢዮብ 13
13
1“እነሆ፥ ይህን ሁሉ ዐይኔ አየች፤
ጆሮየም ሰማች።
2እናንተ የምታውቁትን እኔ ደግሞ አውቃለሁ፤
ከእናንተም የምሰንፍ አይደለሁም።
3ነገር ግን ለእግዚአብሔር እናገራለሁ፤
ከፈቀደም በፊቱ እዋቀሳለሁ።
4እናንተ ግን የዐመፅ ባለ መድኀኒቶች፥
ሁላችሁም የክፋት ፈዋሾች ናችሁ።
5ላዳምጣችሁ አይገባኝም፥
ጥበብ ከእናንተ ጠፍታለችና።#ግሪክ ሰባ. ሊ. እና ዕብ. “ምነው ዝም ብላችሁ ብትኖሩ! ይህ ጥበብ በሆነላችሁ ነበር” ይላል።
6“አሁን የአፌን ክርክር ስሙ፥
የከንፈሬንም ፍርድ አድምጡ።
7በውኑ በእግዚአብሔር ፊት የምትናገሩ አይደላችሁምን?
በፊቱ ሽንገላን ታወራላችሁን?
8ከእርሱ ወደ ኋላ ትመለሳላችሁን?
እስኪ ራሳችሁ ፍረዱ።
9እርሱ ቢመረምራችሁ መልካም ነው፥
ይህን ሁሉ በኀይላችሁ ስታደርጉ ራሳችሁን ከእርሱ ጋር አንድ ታደርጋላችሁና።
10በስውር ለሰው ፊት ብታደሉ
ዘለፋ ይዘልፋችኋል።#ግሪክ ሰባ. ሊ. “አይዘልፋችሁም” ይላል።
11ጥንቱን ኀይሉ አያስፈራችሁምን?
ግርማስ ከእርሱ ዘንድ አይወድቅባችሁምን?
12ምሳሌያችሁ እንደ አመድ ዐላፊ ነው፤
ሥጋችሁም እንደ ትቢያ ነው።
13ዝም በሉ፤ እናገርም ዘንድ ተዉኝ፤
ከቍጣዬም ልረፍ።
14ሥጋዬን በጥርሴ እይዛለሁ፤
ሕይወቴንም በእጄ አጥብቄ አኖራታለሁ።
15እነሆ፥ ኀያሉ እጁን በእኔ ላይ ቢጭን፥
እርሱ እንደ ጀመረ እናገራለሁ፥
በፊቱም እዋቀሳለሁ።
16ዝንጉ ሰው በፊቱ አይገባምና
እርሱ መድኀኒት ይሆንልኛል።
17ነገሬን ስሙ ስሙ፥
እኔ በጆሮአችሁ እነግራችኋለሁና።
18እነሆ፥ ወደ ፍርዴ ቀርቤአለሁ።
ጽድቄም እንደምትገለጥ አውቃለሁ።
19አሁን ፈጽሜ ዝም እል ዘንድ፥
ከእኔ ጋር የሚፋረድ ማን ነው?
20“ነገር ግን ሁለት ነገርን ስጠኝ፤#ዕብ. “አታድርግብኝ” ይላል።
የዚያን ጊዜ ከፊትህ አልሰወርም፤#ግእዙ በምዕ. 13 ቍ. 20 ልዩነት አለው።
21እጅህን ከእኔ አርቅ፤
ግርማህም አታስደንግጠኝ።
22ከዚህም በኋላ ትጠራኛለህ፥ እኔም እመልስልሃለሁ።
ወይም አንተ ተናገር፥ አኔም እመልስልሃለሁ።
23ኀጢአቶችና በደሌ ምን ያህል ናቸው?
ምን ያህል እንደ ሆኑ አስታውቀኝ።
24“ፊትህን ከእኔ የሰወርህ፥
እንደ ጠላትህም የቈጠርኸኝ ስለምን ነው?
25በነፋስ እንደ ረገፈ ቅጠል ታፍሰኛለህን?
ወይስ ነፋስ እንደሚወስደው ዕብቅ ታሳድደኛለህን?
26ክፉ ነገርን ጽፈህብኛልና፤
የልጅነቴንም ኀጢአት ተቈጣጥረህ አስታጥቀኸኛልና።
27እግሮችንም በድጥ አሰነካከልህ፥
ሥራዬንም ሁሉ መርምረሃል፤
እግሬም በቆመች ጊዜ ተውኸኝ።#ዕብ. “የእግሬን ፍለጋ ወስነሃል” ይላል።
28እኔ እንደ አረጀ ረዋት፥
ብልም እንደሚበላው ልብስ ነኝ።
Currently Selected:
መጽሐፈ ኢዮብ 13: አማ2000
ማድመቅ
Share
Copy
ያደመቋቸው ምንባቦች በሁሉም መሣሪያዎችዎ ላይ እንዲቀመጡ ይፈልጋሉ? ይመዝገቡ ወይም ይግቡ