መሳፍንት 3:1-27

መሳፍንት 3:1-27 መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) (አማ54)

ከከነዓናውያንም ጋር መዋጋት ያላወቁትን እስራኤልን በእነርሱ ይፈትናቸው ዘንድ፥ በፊትም ሰልፍን ያልለመዱ የእስራኤል ልጆች ትውልድ መዋጋትን ያውቁና ይማሩ ዘንድ እግዚአብሔር ያስቀራቸው አሕዛብ እነዚህ ናቸው፥ አምስቱ የፍልስጥኤማውያን መኳንንት፥ ከነዓናውያንም ሁሉ፥ ሲዶናውያንም፥ ከበኣልአርሞንዔም ተራራ ጀምሮ እስከ ሐማት መግቢያ ድረስ በሊባኖስ ተራራ የሚኖሩትም ኤዊያውያን። እግዚአብሔር በሙሴ እጅ ለአባቶቻቸው ያዘዘውን ትእዛዝ መስማታቸው እንዲታወቅ እስራኤል ይፈተኑባቸው ዘንድ እነዚህ ቀሩ። የእስራኤልም ልጆች በከነዓናውያን በኬጢያውያንም በአሞራውያንም በፌርዛውያንም በኤዊያውያንም በኢያቡሳውያንም መካከል ተቀመጡ። ሴት ልጆቻቸውንም አገቡአቸው፥ እነርሱም ሴቶች ልጆቻቸውን ለወንዶች ልጆቻቸው ሰጡ፥ አማልክቶቻቸውንም አመለኩ። የእስራኤልም ልጆች በእግዚአብሔር ፊት ክፉ የሆነውን ነገር አደረጉ፥ አምላካቸውንም እግዚአብሔርን ረስተው በኣሊምንና አስታሮትን አመለኩ። ስለዚህ የእግዚአብሔር ቁጣ በእስራኤል ላይ ነደደ፥ በመስጴጦምያ ንጉሥ በኩሰርሰቴም እጅ አሳልፎ ሰጣቸው፥ የእስራኤልም ልጆች ለኩሰርሰቴም ስምንት ዓመት ተገዙለት። የእስራኤልም ልጆች ወደ እግዚአብሔር ጮኹ፥ እግዚአብሔርም የሚያድናቸውን አዳኝ የካሌብን የታናሽ ውንድሙን የቄኔዝን ልጅ ጎቶንያልን አስነሣላቸው። የእግዚአብሔርም መንፈስ በእርሱ ላይ መጣ፥ በእስራኤልም ላይ ይፈርድ ነበር፥ ለሰልፍ ወጣ፥ እግዚአብሔርም የመሰጴጦምያን ንጉሥ ኩሰርሰቴምን በእጁ አሳልፎ ሰጠው፥ እጁም በኩሰርሰቴም ላይ አሸነፈች። ምድሪቱም አርባ ዓመት ዐረፈች፥ የቄኔዝም ልጅ ጎቶንያል ሞተ። የእስራኤልም ልጆች በእግዚአብሔር ፊት እንደ ገና ክፉ ሥራ ሠሩ፥ በእግዚአብሔርም ፊት ክፉ ስለ ሠሩ እግዚአብሔር የሞዓብን ንጉሥ ዔግሎምን በእስራኤል ላይ አበረታባቸው። የአሞንን ልጆችና አማሌቅን ወደ እርሱ ሰበሰበ፥ ሄዶም እስራኤልን መታ፥ ዘንባባም ያለባትን ከተማ ያዙአት። የእስራኤልም ልጆች ለሞዓብ ንጉሥ ለዔግሎም አሥራ ስምንት ዓመት ተገዙለት። የእስራኤልም ልጆች ወደ እግዚአብሔር ጮኹ፥ እግዚአብሔርም ብንያማዊውን የጌራን ልጅ ናዖድን ግራኙን ሰው አዳኝ አስነሣላቸው፥ የእስራኤልም ልጆች በእርሱ እጅ ወደ ሞዓብ ንጉሥ ወደ ዔግሎም ግብር ላኩ። ናዖድም ሁለት አፍ ያለው ርዝመቱ አንድ ክንድ የሆነ ሰይፍ አበጀ፥ ከልብሱም በታች በቀኝ ጭኑ በኩል አደረገው። ለሞዓብም ንጉሥ ለዔግሎም ግብሩን አቀረበ፥ ዔግሎምም እጅግ ወፍራም ሰው ነበረ። ግብሩንም ማቅረብ በጨረሰ ጊዜ፥ ግብር የተሸከሙትን ሰዎች ሰደደ። ናዖድ ግን በጌልገላ ከነበሩት ትክል ድንጋዮች ዘንድ ተመልሶ፦ ንጉሥ ሆይ፥ የምሥጢር ነገር አለኝ አለ፥ ንጉሡም፦ ዝም በል አለ፥ በዙሪያውም የቆሙት ሁሉ ወጡ። ናዖድም ወደ እርሱ ቀረበ፥ እርሱም በሰገነት ቤት ለብቻው ተቀምጦ ነበር። ናዖድም፦ የእግዚአብሔር መልእክት ለአንተ አለኝ አለ። ከዙፋኑም ተነሣ። ናዖድም ግራ እጁን ዘርግቶ ከቀኝ ጭኑ ሰይፉን ወሰደ፥ ሆዱንም ወጋው፥ የሰይፉም እጀታው ደግሞ ከስለቱ በኋላ ገባ፥ ስቡም ስለቱን ከደነው፥ ሰይፉንም ከሆዱ መልሶ አላወጣውም፥ በኋላውም ወጣ። ናዖድም ወደ ደርቡ ወጣ፥ የሰገነቱንም ደጅ ዘግቶ ቈለፈው። ናዖድም ከሄደ በኋላ ባሪያዎቹ መጡ፥ የሰገነቱም ደጅ ተቈልፎ ባዩ ጊዜ፦ ማናልባት በሰገነቱ ውስጥ ወገቡን ይሞክር ይሆናል አሉ። እስኪያፍሩም ድረስ እጅግ ዘገዩ፥ የሰገነቱንም ደጅ እንዳልከፈተ ባዩ ጊዜ መክፈቻውን ወስደው ከፈቱ፥ እነሆም፥ ጌታቸው በምድር ወድቆ ሞቶም አገኙት። በዘገዩበትም ጊዜያት ናዖድ ሸሸ፥ ትክል ድንጋዮቹንም አለፈ፥ ወደ ሴይሮታም አመለጠ። በመጣም ጊዜ በተራራማው በኤፍሬም አገር ቀንደ መለከት ነፋ፥ የእስራኤልም ልጆች ከእርሱ ጋር ከተራራማው አገር ወረዱ፥ እርሱም በፊታቸው ሄደ።

መሳፍንት 3:1-27 አዲሱ መደበኛ ትርጒም (NASV)

በዚህ ጊዜ በከነዓን ላይ በተደረጉት ጦርነቶች ተሳትፈው የማያውቁትን እስራኤላውያን ለመፈተን፣ እግዚአብሔር ባሉበት የተዋቸው ሕዝቦች እነዚህ ናቸው፤ ይህን ማድረጉ ቀደም ሲል በጦር ሜዳ ውለው የማያውቁትን የእስራኤል ልጆች የጦርነት ልምድ እንዲያገኙ ለማድረግ ብቻ ነው፤ እነዚህም አሕዛብ ዐምስቱ የፍልስጥኤም ገዦች፣ ከነዓናውያን በሙሉ፣ ሲዶናውያንና ከበኣል አርሞንዔም ተራራ እስከ ሐማት መግቢያ ባሉት የሊባኖስ ተራሮች የሚኖሩ ኤዊያውያን ነበሩ። እነዚህ፣ እግዚአብሔር በሙሴ በኩል ለቀደሙ አባቶቻቸው የሰጠውን ትእዛዞች ማክበር አለማክበራቸውን ለማወቅ ለእስራኤል መፈተኛ እንዲሆኑ እዚያው የቀሩ ነበሩ። ስለዚህ እስራኤላውያን ከከነዓናውያን፣ ከኬጢያውያን፣ ከአሞራውያን፣ ከፌርዛውያን፣ ከኤዊያውያንና ከኢያቡሳውያን ጋራ ዐብረው ኖሩ። እስራኤላውያን የእነዚህን ሴቶች ልጆች አገቡ፤ የራሳቸውንም ሴቶች ልጆች ለእነርሱ ወንዶች ልጆች ዳሩ፤ አማልክታቸውንም አመለኩ። እስራኤላውያን በእግዚአብሔር ፊት ክፉ ድርጊት ፈጸሙ፤ እግዚአብሔር አምላካቸውንም ረሱ፤ የበኣልንና የአስታሮትን አማልክት አመለኩ። እግዚአብሔር በእስራኤላውያን ላይ እጅግ ተቈጣ፤ ስለዚህ ለመስጴጦምያ ንጉሥ ለኵስርስቴም አሳልፎ ሰጣቸው፤ እስራኤላውያንም ስምንት ዓመት በባርነት ተገዙለት። እስራኤላውያን ወደ እግዚአብሔር በጮኹ ጊዜ ግን የካሌብን ታናሽ ወንድም የቄኔዝን ልጅ ጎቶንያልን ታዳጊ አድርጎ አስነሣላቸው። የእግዚአብሔር መንፈስ በርሱ ላይ ወረደ፤ የእስራኤል መስፍን ሆኖ ወደ ጦርነትም ወጣ። እግዚአብሔር የአራም ንጉሥ ኵስርስቴምን አሳልፎ ስለ ሰጠው ድል አደረገ። የቄኔዝ ልጅ ጎቶንያል እስከ ሞተበት ጊዜ ድረስ ምድሪቱ ለአርባ ዓመት ሰላም አገኘች። እስራኤላውያን እንደ ገና በእግዚአብሔር ፊት ክፉ ድርጊት ፈጸሙ፤ ይህን በማድረጋቸውም እግዚአብሔር የሞዓብ ንጉሥ ዔግሎን በእስራኤል ላይ እንዲበረታባቸው አደረገ። እርሱም አሞናውያንንና አማሌቃውያንን ካስተባበረ በኋላ እስራኤልን ወግቶ የዘንባባ ዛፎች ከተማ የሆነችውን ኢያሪኮን ያዙ። እስራኤላውያንም ለሞዓብ ንጉሥ ለዔግሎን ዐሥራ ስምንት ዓመት ተገዘሉት። እስራኤላውያን እንደ ገና ወደ እግዚአብሔር ጮኹ፤ እግዚአብሔርም ብንያማዊውን የጌራን ልጅ ግራኙን ናዖድን ነጻ እንዲያወጣቸው አስነሣው። እስራኤላውያን ናዖድን ግብር አስይዘው ወደ ሞዓብ ንጉሥ ወደ ዔግሎን ላኩት። እርሱም በሁለት በኩል ስለታም የሆነና አንድ ክንድ ተኩል ርዝመት ያለው ሰይፍ አዘጋጅቶ በልብሱ ውስጥ በቀኝ ጭኑ ላይ አሰረው። ግብሩንም ወፍራም ለነበረው ለሞዓብ ንጉሥ ለዔግሎን አቀረበ፤ ናዖድም ግብሩን ካቀረበ በኋላ፣ ግብር ተሸክመው የመጡት ሰዎች ተመልሰው እንዲሄዱ አደረገ። እርሱ ራሱ ግን ጌልገላ አጠገብ ድንጋዮች ተጠርበው ከሚወጡበት አካባቢ ሲደርስ ወደ ኋላ በመመለስ ወደ ንጉሡ ሄዶ፣ “ንጉሥ ሆይ፤ በምስጢር የምነግርህ ነገር አለኝ” አለው። ንጉሡም፣ “ጸጥታ” ሲል፤ አጠገቡ የነበሩት አገልጋዮች በሙሉ ትተዉት ወጡ። ንጉሡ ሰገነት ላይ ባለው ነፋሻ ዕልፍኝ ውስጥ ብቻውን ተቀምጦ ሳለ ናዖድ ቀረብ ብሎ፣ “ከእግዚአብሔር ዘንድ ለአንተ ያመጣሁት መልእክት አለኝ” አለው፤ ንጉሡም ከዙፋኑ ተነሣ። ናዖድ ግራ እጁን ሰደድ በማድረግ ሰይፉን ከደበቀበት ከቀኝ ጭኑ መዝዞ በንጉሡ ሆድ ሻጠው። እጀታው ሳይቀር ሰይፉ እንዳለ ሆዱ ውስጥ ገባ፤ ስለቱም በጀርባው ወጣ፤ ሞራም ስለቱን ሸፈነው፤ ናዖድ ሰይፉን ስላልነቀለው አንጀቱ ተዘረገፈ። ከዚያም በኋላ ናዖድ በዕልፍኙ መግቢያ ወጣ፤ የዕልፍኙንም በር በንጉሡ ላይ ዘግቶ ቈለፈው። ናዖድ ከሄደ በኋላ፣ የንጉሡ አገልጋዮች ሲመጡ፣ የዕልፍኙ በር ተቈልፎ አገኙት፤ እነርሱም፣ “በውስጠኛው ክፍል እየተጸዳዳ ይሆናል” አሉ፤ እስኪደክማቸውም ድረስ ጠበቁ፤ ነገር ግን ንጉሡ የዕልፍኙን በሮች ባለመክፈቱ ቍልፍ ወስደው ከፈቱ፤ በዚያም ጌታቸው ሞቶ፣ በወለሉም ላይ ተዘርግቶ አገኙት። የንጉሡ አገልጋዮች በዕልፍኙ በር ላይ ቆመው ሲጠባበቁ ናዖድ ርቆ ሄደ፤ ድንጋዮች ተጠርበው በሚወጡበት በኩል ወደ ሴርታይም አመለጠ። እዚያም እንደ ደረሰ፣ በኰረብታማው በኤፍሬም ምድር ቀንደ መለከቱን ነፋ፤ እስራኤላውያንም በርሱ መሪነት ከኰረብታው ላይ ዐብረውት ወረዱ።

መሳፍንት 3:1-27 አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም (አማ05)

በከነዓን ምድር ጦርነት ያልተለማመዱ እስራኤላውያንን ለመፈተን እግዚአብሔር በምድሪቱ የተዋቸው ሕዝቦች እነዚህ ናቸው። ይህንንም ማድረጉ ቀድሞ የጦርነት ልምድ ያልነበራቸውን የእስራኤልን ትውልድ የጦርነት ስልት ለማስተማር ብሎ ብቻ ነው። በምድሪቱ ላይ የቀሩትም፥ አምስቱ የፍልስጥኤማውያን መሪዎች፥ ከነዓናውያን በሙሉ፥ ሲዶናውያንና ከባዓልሔርሞን ተራራ አንሥቶ እስከ ሐማት ድረስ በሊባኖስ ተራራዎች የሚኖሩት ሒዋውያን ነበሩ። እነርሱም እግዚአብሔር በሙሴ አማካይነት ለቀድሞ አባቶቻቸው የሰጣቸውን ትእዛዞች እስራኤላውያን ያከብሩ ወይም አያከብሩ እንደ ሆነ ለማወቅ ለእስራኤል መፈተኛዎች ነበሩ። በዚህም ዐይነት የእስራኤል ሕዝብ በከነዓናውያን፥ በሒታውያን፥ በአሞራውያን፥ በፈሪዛውያን፥ በሒዋውያንና በኢያቡሳውያን መካከል ኖሩ። የእነርሱን ሴቶች ልጆች አገቡ፤ እነርሱም ሴቶች ልጆቻቸውን ለወንዶች ልጆቻቸው ሰጡ፤ አማልክታቸውንም አመለኩ። የእስራኤል ሕዝብ በእግዚአብሔር ፊት ክፉ ነገር አደረጉ፤ አምላካቸውን እግዚአብሔርንም ትተው በዓልና አሼራን አመለኩ፤ ከዚህም የተነሣ የእግዚአብሔር ቊጣ በእስራኤል ሕዝብ ላይ ነደደ፤ ለመስጴጦምያው ንጉሥ ለኩሻን ፊሽዓታይም አሳልፎ ሰጣቸው፤ እነርሱም ለኩሻን ሪሽዓታይም ስምንት ዓመት ተገዙለት፤ ከዚህ በኋላ እስራኤላውያን ወደ እግዚአብሔር ጮኹ፤ እግዚአብሔርም የሚያድናቸውን አዳኝ የካሌብ ታናሽ ወንድም ልጅ የሆነውን የቄኔዝን ልጅ ዖትኒኤልን አስነሣቸው። የእግዚአብሔርም መንፈስ በእርሱ ላይ ዐደረ፤ በእስራኤልም ላይ መሪ ሆነ፤ ለጦርነት በወጣ ጊዜ እግዚአብሔር የመስጴጦምያውን ንጉሥ ኩሻን ፊሽዓታይምን አሳልፎ ሰጠው፤ እርሱም ኩሻን ሪሽዓታይምን ድል አደረገው። በምድሪቱም ላይ ለአርባ ዓመት ያኽል ሰላም ሰፍኖ ከቈየ በኋላ የቄኔዝ ልጅ ዖትኒኤል ሞተ። የእስራኤል ሕዝብ እንደገና በእግዚአብሔር ፊት ክፉ ነገር አደረጉ፤ በዚህም ምክንያት እግዚአብሔር የሞአቡን ንጉሥ ዔግሎንን ከእስራኤል ይበልጥ የበረታ እንዲሆን አደረገው። ዔግሎንም ዐሞናውያንንና ዐማሌቃውያንን አስተባብሮ እስራኤልን ወጋ፤ የተምር ዛፍ የሞላባትንም የኢያሪኮን ከተማ በቊጥጥራቸው ሥር አደረጉ። የእስራኤል ሕዝብ ለዐሥራ ስምንት ዓመት ለሞአብ ንጉሥ ለዔግሎን ተገዢዎች ሆኑ። ከዚህ በኋላ የእስራኤል ሕዝብ ወደ እግዚአብሔር ጮኹ፤ እግዚአብሔርም ከብንያም ነገድ ግራኝ የነበረውን የጌራን ልጅ ኤሁድን አዳኝ አድርጎ አስነሣቸው፤ የእስራኤል ሕዝብ ኤሁድን ግብር አስይዘው ወደ ሞአብ ንጉሥ ወደ ዔግሎን ላኩት። ኤሁድ ኀምሳ ሳንቲ ሜትር የሚያኽል ርዝመት ያለው በሁለት በኩል ስለ ታም የሆነ ሰይፍ ለራሱ አሠራ፤ እርሱንም በቀኝ ጭኑ በኩል በልብሱ ውስጥ ታጠቀው፤ ከዚያን በኋላ ሰውነቱ በጣም ወፍራም ለነበረው ለዔግሎን ግብሩን ይዞ ሄደ። ኤሁድ ግብሩን ለንጉሡ ካቀረበ በኋላ ግብሩን ተሸክመው የነበሩትን ሰዎች ወደ ቤታቸው ተመልሰው እንዲሄዱ አደረገ፤ ኤሁድ ራሱ ግን በጌልገላ አጠገብ ወዳሉት ተጠርበው ወደ ተተከሉ የጣዖት ድንጋዮች ዞር ብሎ ቈየ፤ ወደ ዔግሎንም ተመልሶ “ንጉሥ ሆይ! በግል ለአንተ የምነግርህ አንድ ምሥጢር አለኝ” አለው። እርሱም “ዝም በል” አለው። ስለዚህም ንጉሡ ባለሟሎቹን “እስቲ አንድ ጊዜ ውጪ ቈዩልን!” አላቸው፥ እነርሱም በሙሉ ወጡ። በዚያን ጊዜ ንጉሡ በጣራው ላይ ባለው ነፋሻ ክፍል ለብቻው ተቀምጦ ሳለ፥ ኤሁድ ወደ እርሱ ቀረብ ብሎ “ከእግዚአብሔር ለአንተ የተላከ መልእክት አለኝ” አለው፤ ንጉሡም ብድግ ብሎ ቆመ። ኤሁድም ሰይፉን ከቀኝ ጭኑ በግራ እጁ መዞ በንጉሡ ሆድ ውስጥ ሻጠ፤ እጀታው ሳይቀር ሰይፉ በሙሉ ወደ ሆድ ዕቃው ገባ፤ እስከ ጀርባውም ዘለቀ፤ ሞራውም ሰይፉን ሸፈነው፤ ኤሁድም ሰይፉን ከንጉሡ ሆድ አላወጣውም። ከዚያን በኋላ ኤሁድ ወደ ውጪ ወጣ፤ በሮቹንም ዘግቶ ቈለፈበት። ኤሁድ ከሄደ በኋላ የንጉሡ አገልጋዮች መጥተው በሮቹ እንደ ተቈለፉ አዩ፤ ነገር ግን ንጉሡ ከውስጥ በኩል በመጸዳዳት የዘገየ መሰላቸው፤ መቈየት የሚገባቸውን ያኽል በውጪ ቈዩ፤ ነገር ግን አሁንም በሩ እንዳልተከፈተ ባዩ ጊዜ ቊልፉን ወስደው በሩን ከፈቱ፤ እዚያም ጌታቸው ሞቶ በወለል ላይ መዘርጋቱን ተመለከቱ። እነርሱ እዚያው ቆመው በሚጠባበቁበት ጊዜ ኤሁድ ርቆ ሄዶ ነበር፤ ተጠርበው የተተከሉ የጣዖት ድንጋዮችን አልፎ ወደ ሰዒራ አመለጠ፤ እዚያም ወደ ኮረብታማው ወደ ኤፍሬም አገር እንደ ደረሰ በኤፍሬም ተራራማው አገር የክተት እምቢልታ ነፋ፤ የእስራኤልም ሕዝብ በእርሱ መሪነት ተከትለውት ወረዱ።

መሳፍንት 3:1-27 የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) (አማ2000)

የከ​ነ​ዓ​ና​ው​ያ​ን​ንም ጦር​ነት ሁሉ ያላ​ወ​ቁ​ትን እስ​ራ​ኤ​ልን በእ​ነ​ርሱ ይፈ​ት​ና​ቸው ዘንድ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር እነ​ዚ​ህን አሕ​ዛብ ተዋ​ቸው። ይህም ጦር​ነ​ትን ያስ​ተ​ም​ሩ​አ​ቸው ዘንድ ስለ እስ​ራ​ኤል ልጆች ትው​ልድ ብቻ ነው፤ ነገር ግን ከእ​ነ​ርሱ በፊት የነ​በ​ሩት እነ​ዚ​ህን አላ​ወ​ቋ​ቸ​ውም ነበር፤ እነ​ር​ሱም አም​ስቱ የፍ​ል​ስ​ጥ​ኤ​ማ​ው​ያን መኳ​ን​ንት፥ ከነ​ዓ​ና​ው​ያ​ንም ሁሉ ፥ ሲዶ​ና​ው​ያ​ንም፥ ከበ​ዓ​ል​ሄ​ር​ሞን ተራራ ጀምሮ እስከ ኤማት መግ​ቢያ ድረስ በሊ​ባ​ኖስ ተራራ የሚ​ኖ​ሩ​ትም ኤዌ​ዎ​ና​ው​ያን፤ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር በሙሴ እጅ ለአ​ባ​ቶ​ቻ​ቸው ያዘ​ዘ​ውን ትእ​ዛዝ መስ​ማ​ታ​ቸው እን​ዲ​ታ​ወቅ እስ​ራ​ኤል ይፈ​ተ​ኑ​ባ​ቸው ዘንድ እነ​ዚህ ቀሩ። የእ​ስ​ራ​ኤ​ልም ልጆች በከ​ነ​ዓ​ና​ው​ያን፥ በኬ​ጤ​ዎ​ና​ው​ያን፥ በአ​ሞ​ሬ​ዎ​ና​ው​ያን፥ በፌ​ር​ዜ​ዎ​ና​ው​ያን፥ በኤ​ዌ​ዎ​ና​ው​ያን፥ በኢ​ያ​ቡ​ሴ​ዎ​ና​ው​ያ​ንም መካ​ከል ተቀ​መጡ። ሴቶች ልጆ​ቻ​ቸ​ው​ንም አገ​ቡ​አ​ቸው፤ እነ​ር​ሱም ሴቶች ልጆ​ቻ​ቸ​ውን ለወ​ን​ዶች ልጆ​ቻ​ቸው ሰጡ፤ አማ​ል​ክ​ቶ​ቻ​ቸ​ው​ንም አመ​ለኩ። የእ​ስ​ራ​ኤ​ልም ልጆች በእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ፊት ክፉ አደ​ረጉ፤ አም​ላ​ካ​ቸ​ው​ንም እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርን ረስ​ተው በዓ​ሊ​ም​ንና አስ​ታ​ሮ​ትን አመ​ለኩ። ስለ​ዚህ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር በእ​ስ​ራ​ኤል ላይ ፈጽሞ ተቈጣ፤ በወ​ን​ዞ​ችም መካ​ከል ባለች በሶ​ርያ ንጉሥ በኩ​ሳ​ር​ሳ​ቴም እጅ አሳ​ልፎ ሰጣ​ቸው፤ የእ​ስ​ራ​ኤ​ልም ልጆች ለኩ​ሳ​ር​ሳ​ቴም ስም​ንት ዓመት ተገ​ዙ​ለት። የእ​ስ​ራ​ኤ​ልም ልጆች ወደ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ጮኹ። እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርም ለእ​ስ​ራ​ኤል መድ​ኀ​ኒ​ትን አስ​ነ​ሣ​ላ​ቸው። የካ​ሌብ የታ​ናሽ ወን​ድሙ የቄ​ኔዝ ልጅ ጎቶ​ን​ያ​ልም አዳ​ና​ቸው፤ ለእ​ር​ሱም ታዘ​ዙ​ለት። የእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርም መን​ፈስ በእ​ርሱ ላይ አደረ፤ በእ​ስ​ራ​ኤ​ልም ላይ ይፈ​ርድ ነበር፤ ለጦ​ር​ነ​ትም ወጣ፤ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርም በወ​ን​ዞች መካ​ከል ያለች የሶ​ርያ ንጉሥ ኩሳ​ር​ሳ​ቴ​ምን በእጁ አሳ​ልፎ ሰጠው፤ እጁም በኩ​ሳ​ር​ሳ​ቴም ላይ በረ​ታች። ምድ​ሪ​ቱም አርባ ዓመት ዐረ​ፈች፤ የቄ​ኔ​ዝም ልጅ ጎቶ​ን​ያል ሞተ። የእ​ስ​ራ​ኤ​ልም ልጆች በእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ፊት እንደ ገና ክፉ ሥራ ሠሩ፤ በእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርም ፊት ክፉ ስለ ሠሩ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር የሞ​ዓ​ብን ንጉሥ ዔግ​ሎ​ምን በእ​ስ​ራ​ኤል ላይ አበ​ረ​ታ​ባ​ቸው። የአ​ሞ​ንን ልጆ​ችና አማ​ሌ​ቅን ወደ እርሱ ሰበ​ሰበ፤ ሄዶም እስ​ራ​ኤ​ልን መታ፤ ዘን​ባባ ያለ​ባ​ት​ንም ከተማ ያዘ። የእ​ስ​ራ​ኤ​ልም ልጆች ለሞ​ዓብ ንጉሥ ለዔ​ግ​ሎም ዐሥራ ስም​ንት ዓመት ተገዙ። የእ​ስ​ራ​ኤ​ልም ልጆች ወደ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ጮኹ፤ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርም ብን​ያ​ማ​ዊ​ውን የጌ​ራን ልጅ ናዖ​ድን ሁለቱ እጆቹ ቀኝ የሆ​ኑ​ለ​ትን ሰው አዳኝ አስ​ነ​ሣ​ላ​ቸው፤ የእ​ስ​ራ​ኤ​ልም ልጆች በእ​ርሱ እጅ ወደ ሞዓብ ንጉሥ ወደ ዔግ​ሎም እጅ መንሻ ላኩ። ናዖ​ድም ሁለት አፍ ያላት ርዝ​መቷ አንድ ስን​ዝር የሆ​ነች ሰይፍ አበጀ፤ ከል​ብ​ሱም በታች በቀኝ በኩል በወ​ገቡ ታጠ​ቃት። ለሞ​ዓ​ብም ንጉሥ ለዔ​ግ​ሎም እጅ መን​ሻ​ውን አቀ​ረበ፤ ዔግ​ሎ​ምም እጅግ ወፍ​ራም ሰው ነበረ። እጅ መን​ሻ​ው​ንም ማቅ​ረብ በጨ​ረሰ ጊዜ፥ እጅ መንሻ የተ​ሸ​ከ​ሙ​ትን ሰዎች አሰ​ና​በ​ታ​ቸው። ዔግ​ሎ​ምም ከገ​ል​ገል ከጣ​ዖ​ታቱ ቤት ተመ​ለሰ። ናዖ​ድም፥ “ንጉሥ ሆይ፥ ለብ​ቻህ የም​ነ​ግ​ርህ የም​ሥ​ጢር ነገር አለኝ” አለ፤ ዔግ​ሎ​ምም ሁሉ ከእ​ርሱ ዘንድ እን​ዲ​ወጣ አዘዘ፤ በእ​ር​ሱም ዘንድ የቆ​ሙት ሁሉ ወጡ ። ናዖ​ድም ወደ እርሱ ገባ፤ እር​ሱም በበጋ ቤቱ ሰገ​ነት ለብ​ቻው ተቀ​ምጦ ነበር። ናዖ​ድም፥ “ንጉሥ ሆይ! የእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር መል​እ​ክት ለአ​ንተ አለኝ” አለው። ዔግ​ሎ​ምም ከዙ​ፋኑ ተነሣ፥ ቀረ​በ​ውም። ናዖ​ድም በተ​ነሣ ጊዜ ግራ እጁን ዘር​ግቶ ከቀኝ ጎኑ ሰይ​ፉን መዘዘ፤ ዔግ​ሎ​ም​ንም ሆዱን ወጋው፤ እስከ ውላ​ጋ​ዋም አስ​ገ​ባት፤ እስከ ጀር​ባ​ውም በረ​በ​ረው፥ ሰይ​ፉ​ንም ከሆዱ መልሶ አላ​ወ​ጣ​ትም። ናዖ​ድም የእ​ል​ፍ​ኙን ደጅ ዘግ​ቶና ቈልፎ ወደ ውጭ ወጣ። ናዖ​ድም ከሄደ በኋላ አገ​ል​ጋ​ዮቹ መጡ፤ የሰ​ገ​ነ​ቱም ደጅ ተቈ​ልፎ ባዩ ጊዜ፥ “ምና​ል​ባት በበጋ ሰገ​ነቱ ውስጥ ወገ​ቡን ይሞ​ክር ይሆ​ናል” አሉ። እስ​ኪ​ያ​ፍ​ሩም ድረስ ቈዩ፤ የሰ​ገ​ነ​ቱ​ንም ደጅ እን​ዳ​ል​ከ​ፈተ ባዩ ጊዜ መክ​ፈ​ቻ​ውን ወስ​ደው ከፈቱ፤ እነ​ሆም፥ ጌታ​ቸው በም​ድር ላይ ወድቆ ሞቶም አገ​ኙት። እስ​ከ​ሚ​ታ​ወ​ኩም ድረስ ናዖድ አመ​ለጠ፤ ያወ​ቀ​ውም የለም፤ ከጣ​ዖ​ቶ​ቻ​ቸ​ውም አልፎ ወደ ሴይ​ሮታ አመ​ለጠ። ከዚ​ህም በኋላ ወደ እስ​ራ​ኤል ምድር በደ​ረሰ ጊዜ በተ​ራ​ራ​ማው በኤ​ፍ​ራም ሀገር ቀንደ መለ​ከት ነፋ፤ የእ​ስ​ራ​ኤ​ልም ልጆች ከእ​ርሱ ጋር ከተ​ራ​ራ​ማው ሀገር ወረዱ፤ እር​ሱም በፊ​ታ​ቸው ሄደ።

መሳፍንት 3:1-27 አዲሱ መደበኛ ትርጒም (NASV)

በዚህ ጊዜ በከነዓን ላይ በተደረጉት ጦርነቶች ተሳትፈው የማያውቁትን እስራኤላውያን ለመፈተን፣ እግዚአብሔር ባሉበት የተዋቸው ሕዝቦች እነዚህ ናቸው፤ ይህን ማድረጉ ቀደም ሲል በጦር ሜዳ ውለው የማያውቁትን የእስራኤል ልጆች የጦርነት ልምድ እንዲያገኙ ለማድረግ ብቻ ነው፤ እነዚህም አሕዛብ ዐምስቱ የፍልስጥኤም ገዦች፣ ከነዓናውያን በሙሉ፣ ሲዶናውያንና ከበኣል አርሞንዔም ተራራ እስከ ሐማት መግቢያ ባሉት የሊባኖስ ተራሮች የሚኖሩ ኤዊያውያን ነበሩ። እነዚህ፣ እግዚአብሔር በሙሴ በኩል ለቀደሙ አባቶቻቸው የሰጠውን ትእዛዞች ማክበር አለማክበራቸውን ለማወቅ ለእስራኤል መፈተኛ እንዲሆኑ እዚያው የቀሩ ነበሩ። ስለዚህ እስራኤላውያን ከከነዓናውያን፣ ከኬጢያውያን፣ ከአሞራውያን፣ ከፌርዛውያን፣ ከኤዊያውያንና ከኢያቡሳውያን ጋራ ዐብረው ኖሩ። እስራኤላውያን የእነዚህን ሴቶች ልጆች አገቡ፤ የራሳቸውንም ሴቶች ልጆች ለእነርሱ ወንዶች ልጆች ዳሩ፤ አማልክታቸውንም አመለኩ። እስራኤላውያን በእግዚአብሔር ፊት ክፉ ድርጊት ፈጸሙ፤ እግዚአብሔር አምላካቸውንም ረሱ፤ የበኣልንና የአስታሮትን አማልክት አመለኩ። እግዚአብሔር በእስራኤላውያን ላይ እጅግ ተቈጣ፤ ስለዚህ ለመስጴጦምያ ንጉሥ ለኵስርስቴም አሳልፎ ሰጣቸው፤ እስራኤላውያንም ስምንት ዓመት በባርነት ተገዙለት። እስራኤላውያን ወደ እግዚአብሔር በጮኹ ጊዜ ግን የካሌብን ታናሽ ወንድም የቄኔዝን ልጅ ጎቶንያልን ታዳጊ አድርጎ አስነሣላቸው። የእግዚአብሔር መንፈስ በርሱ ላይ ወረደ፤ የእስራኤል መስፍን ሆኖ ወደ ጦርነትም ወጣ። እግዚአብሔር የአራም ንጉሥ ኵስርስቴምን አሳልፎ ስለ ሰጠው ድል አደረገ። የቄኔዝ ልጅ ጎቶንያል እስከ ሞተበት ጊዜ ድረስ ምድሪቱ ለአርባ ዓመት ሰላም አገኘች። እስራኤላውያን እንደ ገና በእግዚአብሔር ፊት ክፉ ድርጊት ፈጸሙ፤ ይህን በማድረጋቸውም እግዚአብሔር የሞዓብ ንጉሥ ዔግሎን በእስራኤል ላይ እንዲበረታባቸው አደረገ። እርሱም አሞናውያንንና አማሌቃውያንን ካስተባበረ በኋላ እስራኤልን ወግቶ የዘንባባ ዛፎች ከተማ የሆነችውን ኢያሪኮን ያዙ። እስራኤላውያንም ለሞዓብ ንጉሥ ለዔግሎን ዐሥራ ስምንት ዓመት ተገዘሉት። እስራኤላውያን እንደ ገና ወደ እግዚአብሔር ጮኹ፤ እግዚአብሔርም ብንያማዊውን የጌራን ልጅ ግራኙን ናዖድን ነጻ እንዲያወጣቸው አስነሣው። እስራኤላውያን ናዖድን ግብር አስይዘው ወደ ሞዓብ ንጉሥ ወደ ዔግሎን ላኩት። እርሱም በሁለት በኩል ስለታም የሆነና አንድ ክንድ ተኩል ርዝመት ያለው ሰይፍ አዘጋጅቶ በልብሱ ውስጥ በቀኝ ጭኑ ላይ አሰረው። ግብሩንም ወፍራም ለነበረው ለሞዓብ ንጉሥ ለዔግሎን አቀረበ፤ ናዖድም ግብሩን ካቀረበ በኋላ፣ ግብር ተሸክመው የመጡት ሰዎች ተመልሰው እንዲሄዱ አደረገ። እርሱ ራሱ ግን ጌልገላ አጠገብ ድንጋዮች ተጠርበው ከሚወጡበት አካባቢ ሲደርስ ወደ ኋላ በመመለስ ወደ ንጉሡ ሄዶ፣ “ንጉሥ ሆይ፤ በምስጢር የምነግርህ ነገር አለኝ” አለው። ንጉሡም፣ “ጸጥታ” ሲል፤ አጠገቡ የነበሩት አገልጋዮች በሙሉ ትተዉት ወጡ። ንጉሡ ሰገነት ላይ ባለው ነፋሻ ዕልፍኝ ውስጥ ብቻውን ተቀምጦ ሳለ ናዖድ ቀረብ ብሎ፣ “ከእግዚአብሔር ዘንድ ለአንተ ያመጣሁት መልእክት አለኝ” አለው፤ ንጉሡም ከዙፋኑ ተነሣ። ናዖድ ግራ እጁን ሰደድ በማድረግ ሰይፉን ከደበቀበት ከቀኝ ጭኑ መዝዞ በንጉሡ ሆድ ሻጠው። እጀታው ሳይቀር ሰይፉ እንዳለ ሆዱ ውስጥ ገባ፤ ስለቱም በጀርባው ወጣ፤ ሞራም ስለቱን ሸፈነው፤ ናዖድ ሰይፉን ስላልነቀለው አንጀቱ ተዘረገፈ። ከዚያም በኋላ ናዖድ በዕልፍኙ መግቢያ ወጣ፤ የዕልፍኙንም በር በንጉሡ ላይ ዘግቶ ቈለፈው። ናዖድ ከሄደ በኋላ፣ የንጉሡ አገልጋዮች ሲመጡ፣ የዕልፍኙ በር ተቈልፎ አገኙት፤ እነርሱም፣ “በውስጠኛው ክፍል እየተጸዳዳ ይሆናል” አሉ፤ እስኪደክማቸውም ድረስ ጠበቁ፤ ነገር ግን ንጉሡ የዕልፍኙን በሮች ባለመክፈቱ ቍልፍ ወስደው ከፈቱ፤ በዚያም ጌታቸው ሞቶ፣ በወለሉም ላይ ተዘርግቶ አገኙት። የንጉሡ አገልጋዮች በዕልፍኙ በር ላይ ቆመው ሲጠባበቁ ናዖድ ርቆ ሄደ፤ ድንጋዮች ተጠርበው በሚወጡበት በኩል ወደ ሴርታይም አመለጠ። እዚያም እንደ ደረሰ፣ በኰረብታማው በኤፍሬም ምድር ቀንደ መለከቱን ነፋ፤ እስራኤላውያንም በርሱ መሪነት ከኰረብታው ላይ ዐብረውት ወረዱ።

መሳፍንት 3:1-27 መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) (አማ54)

ከከነዓናውያንም ጋር መዋጋት ያላወቁትን እስራኤልን በእነርሱ ይፈትናቸው ዘንድ፥ በፊትም ሰልፍን ያልለመዱ የእስራኤል ልጆች ትውልድ መዋጋትን ያውቁና ይማሩ ዘንድ እግዚአብሔር ያስቀራቸው አሕዛብ እነዚህ ናቸው፥ አምስቱ የፍልስጥኤማውያን መኳንንት፥ ከነዓናውያንም ሁሉ፥ ሲዶናውያንም፥ ከበኣልአርሞንዔም ተራራ ጀምሮ እስከ ሐማት መግቢያ ድረስ በሊባኖስ ተራራ የሚኖሩትም ኤዊያውያን። እግዚአብሔር በሙሴ እጅ ለአባቶቻቸው ያዘዘውን ትእዛዝ መስማታቸው እንዲታወቅ እስራኤል ይፈተኑባቸው ዘንድ እነዚህ ቀሩ። የእስራኤልም ልጆች በከነዓናውያን በኬጢያውያንም በአሞራውያንም በፌርዛውያንም በኤዊያውያንም በኢያቡሳውያንም መካከል ተቀመጡ። ሴት ልጆቻቸውንም አገቡአቸው፥ እነርሱም ሴቶች ልጆቻቸውን ለወንዶች ልጆቻቸው ሰጡ፥ አማልክቶቻቸውንም አመለኩ። የእስራኤልም ልጆች በእግዚአብሔር ፊት ክፉ የሆነውን ነገር አደረጉ፥ አምላካቸውንም እግዚአብሔርን ረስተው በኣሊምንና አስታሮትን አመለኩ። ስለዚህ የእግዚአብሔር ቁጣ በእስራኤል ላይ ነደደ፥ በመስጴጦምያ ንጉሥ በኩሰርሰቴም እጅ አሳልፎ ሰጣቸው፥ የእስራኤልም ልጆች ለኩሰርሰቴም ስምንት ዓመት ተገዙለት። የእስራኤልም ልጆች ወደ እግዚአብሔር ጮኹ፥ እግዚአብሔርም የሚያድናቸውን አዳኝ የካሌብን የታናሽ ውንድሙን የቄኔዝን ልጅ ጎቶንያልን አስነሣላቸው። የእግዚአብሔርም መንፈስ በእርሱ ላይ መጣ፥ በእስራኤልም ላይ ይፈርድ ነበር፥ ለሰልፍ ወጣ፥ እግዚአብሔርም የመሰጴጦምያን ንጉሥ ኩሰርሰቴምን በእጁ አሳልፎ ሰጠው፥ እጁም በኩሰርሰቴም ላይ አሸነፈች። ምድሪቱም አርባ ዓመት ዐረፈች፥ የቄኔዝም ልጅ ጎቶንያል ሞተ። የእስራኤልም ልጆች በእግዚአብሔር ፊት እንደ ገና ክፉ ሥራ ሠሩ፥ በእግዚአብሔርም ፊት ክፉ ስለ ሠሩ እግዚአብሔር የሞዓብን ንጉሥ ዔግሎምን በእስራኤል ላይ አበረታባቸው። የአሞንን ልጆችና አማሌቅን ወደ እርሱ ሰበሰበ፥ ሄዶም እስራኤልን መታ፥ ዘንባባም ያለባትን ከተማ ያዙአት። የእስራኤልም ልጆች ለሞዓብ ንጉሥ ለዔግሎም አሥራ ስምንት ዓመት ተገዙለት። የእስራኤልም ልጆች ወደ እግዚአብሔር ጮኹ፥ እግዚአብሔርም ብንያማዊውን የጌራን ልጅ ናዖድን ግራኙን ሰው አዳኝ አስነሣላቸው፥ የእስራኤልም ልጆች በእርሱ እጅ ወደ ሞዓብ ንጉሥ ወደ ዔግሎም ግብር ላኩ። ናዖድም ሁለት አፍ ያለው ርዝመቱ አንድ ክንድ የሆነ ሰይፍ አበጀ፥ ከልብሱም በታች በቀኝ ጭኑ በኩል አደረገው። ለሞዓብም ንጉሥ ለዔግሎም ግብሩን አቀረበ፥ ዔግሎምም እጅግ ወፍራም ሰው ነበረ። ግብሩንም ማቅረብ በጨረሰ ጊዜ፥ ግብር የተሸከሙትን ሰዎች ሰደደ። ናዖድ ግን በጌልገላ ከነበሩት ትክል ድንጋዮች ዘንድ ተመልሶ፦ ንጉሥ ሆይ፥ የምሥጢር ነገር አለኝ አለ፥ ንጉሡም፦ ዝም በል አለ፥ በዙሪያውም የቆሙት ሁሉ ወጡ። ናዖድም ወደ እርሱ ቀረበ፥ እርሱም በሰገነት ቤት ለብቻው ተቀምጦ ነበር። ናዖድም፦ የእግዚአብሔር መልእክት ለአንተ አለኝ አለ። ከዙፋኑም ተነሣ። ናዖድም ግራ እጁን ዘርግቶ ከቀኝ ጭኑ ሰይፉን ወሰደ፥ ሆዱንም ወጋው፥ የሰይፉም እጀታው ደግሞ ከስለቱ በኋላ ገባ፥ ስቡም ስለቱን ከደነው፥ ሰይፉንም ከሆዱ መልሶ አላወጣውም፥ በኋላውም ወጣ። ናዖድም ወደ ደርቡ ወጣ፥ የሰገነቱንም ደጅ ዘግቶ ቈለፈው። ናዖድም ከሄደ በኋላ ባሪያዎቹ መጡ፥ የሰገነቱም ደጅ ተቈልፎ ባዩ ጊዜ፦ ማናልባት በሰገነቱ ውስጥ ወገቡን ይሞክር ይሆናል አሉ። እስኪያፍሩም ድረስ እጅግ ዘገዩ፥ የሰገነቱንም ደጅ እንዳልከፈተ ባዩ ጊዜ መክፈቻውን ወስደው ከፈቱ፥ እነሆም፥ ጌታቸው በምድር ወድቆ ሞቶም አገኙት። በዘገዩበትም ጊዜያት ናዖድ ሸሸ፥ ትክል ድንጋዮቹንም አለፈ፥ ወደ ሴይሮታም አመለጠ። በመጣም ጊዜ በተራራማው በኤፍሬም አገር ቀንደ መለከት ነፋ፥ የእስራኤልም ልጆች ከእርሱ ጋር ከተራራማው አገር ወረዱ፥ እርሱም በፊታቸው ሄደ።

መሳፍንት 3:1-27 አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም (አማ05)

በከነዓን ምድር ጦርነት ያልተለማመዱ እስራኤላውያንን ለመፈተን እግዚአብሔር በምድሪቱ የተዋቸው ሕዝቦች እነዚህ ናቸው። ይህንንም ማድረጉ ቀድሞ የጦርነት ልምድ ያልነበራቸውን የእስራኤልን ትውልድ የጦርነት ስልት ለማስተማር ብሎ ብቻ ነው። በምድሪቱ ላይ የቀሩትም፥ አምስቱ የፍልስጥኤማውያን መሪዎች፥ ከነዓናውያን በሙሉ፥ ሲዶናውያንና ከባዓልሔርሞን ተራራ አንሥቶ እስከ ሐማት ድረስ በሊባኖስ ተራራዎች የሚኖሩት ሒዋውያን ነበሩ። እነርሱም እግዚአብሔር በሙሴ አማካይነት ለቀድሞ አባቶቻቸው የሰጣቸውን ትእዛዞች እስራኤላውያን ያከብሩ ወይም አያከብሩ እንደ ሆነ ለማወቅ ለእስራኤል መፈተኛዎች ነበሩ። በዚህም ዐይነት የእስራኤል ሕዝብ በከነዓናውያን፥ በሒታውያን፥ በአሞራውያን፥ በፈሪዛውያን፥ በሒዋውያንና በኢያቡሳውያን መካከል ኖሩ። የእነርሱን ሴቶች ልጆች አገቡ፤ እነርሱም ሴቶች ልጆቻቸውን ለወንዶች ልጆቻቸው ሰጡ፤ አማልክታቸውንም አመለኩ። የእስራኤል ሕዝብ በእግዚአብሔር ፊት ክፉ ነገር አደረጉ፤ አምላካቸውን እግዚአብሔርንም ትተው በዓልና አሼራን አመለኩ፤ ከዚህም የተነሣ የእግዚአብሔር ቊጣ በእስራኤል ሕዝብ ላይ ነደደ፤ ለመስጴጦምያው ንጉሥ ለኩሻን ፊሽዓታይም አሳልፎ ሰጣቸው፤ እነርሱም ለኩሻን ሪሽዓታይም ስምንት ዓመት ተገዙለት፤ ከዚህ በኋላ እስራኤላውያን ወደ እግዚአብሔር ጮኹ፤ እግዚአብሔርም የሚያድናቸውን አዳኝ የካሌብ ታናሽ ወንድም ልጅ የሆነውን የቄኔዝን ልጅ ዖትኒኤልን አስነሣቸው። የእግዚአብሔርም መንፈስ በእርሱ ላይ ዐደረ፤ በእስራኤልም ላይ መሪ ሆነ፤ ለጦርነት በወጣ ጊዜ እግዚአብሔር የመስጴጦምያውን ንጉሥ ኩሻን ፊሽዓታይምን አሳልፎ ሰጠው፤ እርሱም ኩሻን ሪሽዓታይምን ድል አደረገው። በምድሪቱም ላይ ለአርባ ዓመት ያኽል ሰላም ሰፍኖ ከቈየ በኋላ የቄኔዝ ልጅ ዖትኒኤል ሞተ። የእስራኤል ሕዝብ እንደገና በእግዚአብሔር ፊት ክፉ ነገር አደረጉ፤ በዚህም ምክንያት እግዚአብሔር የሞአቡን ንጉሥ ዔግሎንን ከእስራኤል ይበልጥ የበረታ እንዲሆን አደረገው። ዔግሎንም ዐሞናውያንንና ዐማሌቃውያንን አስተባብሮ እስራኤልን ወጋ፤ የተምር ዛፍ የሞላባትንም የኢያሪኮን ከተማ በቊጥጥራቸው ሥር አደረጉ። የእስራኤል ሕዝብ ለዐሥራ ስምንት ዓመት ለሞአብ ንጉሥ ለዔግሎን ተገዢዎች ሆኑ። ከዚህ በኋላ የእስራኤል ሕዝብ ወደ እግዚአብሔር ጮኹ፤ እግዚአብሔርም ከብንያም ነገድ ግራኝ የነበረውን የጌራን ልጅ ኤሁድን አዳኝ አድርጎ አስነሣቸው፤ የእስራኤል ሕዝብ ኤሁድን ግብር አስይዘው ወደ ሞአብ ንጉሥ ወደ ዔግሎን ላኩት። ኤሁድ ኀምሳ ሳንቲ ሜትር የሚያኽል ርዝመት ያለው በሁለት በኩል ስለ ታም የሆነ ሰይፍ ለራሱ አሠራ፤ እርሱንም በቀኝ ጭኑ በኩል በልብሱ ውስጥ ታጠቀው፤ ከዚያን በኋላ ሰውነቱ በጣም ወፍራም ለነበረው ለዔግሎን ግብሩን ይዞ ሄደ። ኤሁድ ግብሩን ለንጉሡ ካቀረበ በኋላ ግብሩን ተሸክመው የነበሩትን ሰዎች ወደ ቤታቸው ተመልሰው እንዲሄዱ አደረገ፤ ኤሁድ ራሱ ግን በጌልገላ አጠገብ ወዳሉት ተጠርበው ወደ ተተከሉ የጣዖት ድንጋዮች ዞር ብሎ ቈየ፤ ወደ ዔግሎንም ተመልሶ “ንጉሥ ሆይ! በግል ለአንተ የምነግርህ አንድ ምሥጢር አለኝ” አለው። እርሱም “ዝም በል” አለው። ስለዚህም ንጉሡ ባለሟሎቹን “እስቲ አንድ ጊዜ ውጪ ቈዩልን!” አላቸው፥ እነርሱም በሙሉ ወጡ። በዚያን ጊዜ ንጉሡ በጣራው ላይ ባለው ነፋሻ ክፍል ለብቻው ተቀምጦ ሳለ፥ ኤሁድ ወደ እርሱ ቀረብ ብሎ “ከእግዚአብሔር ለአንተ የተላከ መልእክት አለኝ” አለው፤ ንጉሡም ብድግ ብሎ ቆመ። ኤሁድም ሰይፉን ከቀኝ ጭኑ በግራ እጁ መዞ በንጉሡ ሆድ ውስጥ ሻጠ፤ እጀታው ሳይቀር ሰይፉ በሙሉ ወደ ሆድ ዕቃው ገባ፤ እስከ ጀርባውም ዘለቀ፤ ሞራውም ሰይፉን ሸፈነው፤ ኤሁድም ሰይፉን ከንጉሡ ሆድ አላወጣውም። ከዚያን በኋላ ኤሁድ ወደ ውጪ ወጣ፤ በሮቹንም ዘግቶ ቈለፈበት። ኤሁድ ከሄደ በኋላ የንጉሡ አገልጋዮች መጥተው በሮቹ እንደ ተቈለፉ አዩ፤ ነገር ግን ንጉሡ ከውስጥ በኩል በመጸዳዳት የዘገየ መሰላቸው፤ መቈየት የሚገባቸውን ያኽል በውጪ ቈዩ፤ ነገር ግን አሁንም በሩ እንዳልተከፈተ ባዩ ጊዜ ቊልፉን ወስደው በሩን ከፈቱ፤ እዚያም ጌታቸው ሞቶ በወለል ላይ መዘርጋቱን ተመለከቱ። እነርሱ እዚያው ቆመው በሚጠባበቁበት ጊዜ ኤሁድ ርቆ ሄዶ ነበር፤ ተጠርበው የተተከሉ የጣዖት ድንጋዮችን አልፎ ወደ ሰዒራ አመለጠ፤ እዚያም ወደ ኮረብታማው ወደ ኤፍሬም አገር እንደ ደረሰ በኤፍሬም ተራራማው አገር የክተት እምቢልታ ነፋ፤ የእስራኤልም ሕዝብ በእርሱ መሪነት ተከትለውት ወረዱ።

መሳፍንት 3:1-27 መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) (መቅካእኤ)

በዚህ ጊዜ በከነዓን ላይ በተደረጉት ጦርነቶች ተሳትፈው የማያውቁትን እስራኤላውያን ለመፈተን፥ ጌታ ባሉበት የተዋቸው ሕዝቦች እነዚህ ናቸው። ይህን ማድረጉ ቀደም ሲል በጦር ሜዳ ውለው የማያውቁትን የእስራኤል ልጆች የጦርነት ልምድ እንዲያገኙ ለማድረግ ብቻ ነው። እነዚህም አሕዛብ አምስቱ የፍልስጥኤም ገዦች፥ ከነዓናውያን በሙሉ፥ ሲዶናውያንና ከበኣል አርሞንዔም ተራራ እስከ ሐማትስ መግቢያ ባሉት የሊባኖስ ተራሮች የሚኖሩ ኤዊያውያን ነበሩ። እነርሱም ጌታ በሙሴ አማካይነት ለቀድሞ አባቶቻቸው የሰጣቸውን ትእዛዞች እስራኤላውያን ያከብሩ ወይም አያከብሩ እንደሆነ ለማወቅ ለእስራኤል መፈተኛዎች ነበሩ። ስለዚህ እስራኤላውያን ከከነዓናውያን፥ ከኬጢያውያን፥ ከአሞራውያን፥ ከፌርዛውያን፥ ከኤዊያውያንና ከኢያቡሳውያን ጋር አብረው ኖሩ። እስራኤላውያን የእነዚህን ሴቶች ልጆች አገቡ፤ የራሳቸውንም ሴቶች ልጆች ለእነርሱ ወንዶች ልጆች ዳሩ፤ አማልክቶቻቸውንም አመለኩ። እስራኤላውያን በጌታ ፊት ክፉ ድርጊት ፈጸሙ፤ አምላካቸውን ጌታንም ረሱ፤ በኣልንና አስታሮትን አመለኩ። ጌታ በእስራኤላውያን ላይ እጅግ ተቈጣ፤ ስለዚህ ለመስጴጦምያ ንጉሥ ለኩሽን-ሪሽዓታይም አሳልፎ ሰጣቸው፤ እስራኤላውያንም ለኩሽን-ሪሽዓታይም ስምንት ዓመት በባርነት ተገዙለት። እስራኤላውያን ወደ ጌታ በጮኹ ጊዜ ግን፥ ጌታ የካሌብን ታናሽ ወንድም የቄኔዝን ልጅ ዖትኒኤልን ታዳጊ አድርጎ አስነሣላቸው። የጌታም መንፈስ በእርሱ ላይ ዐደረ፤ በእስራኤልም ላይ መሪ ሆነ፤ ለጦርነት በወጣ ጊዜ ጌታ የመስጴጦምያውን ንጉሥ ኩሽን ሪሽዓታይምን አሳልፎ ሰጠው፤ እርሱም ኩሽን-ሪሽዓታይምን ድል አደረገው። የቄኔዝ ልጅ ዖትኒኤል እስከሞተበት ጊዜ ድረስ ምድሪቱ ለአርባ ዓመት ሰላም አገኘች። እስራኤላውያን እንደገና በጌታ ፊት ክፉ ድርጊት ፈጸሙ፤ ይህን ክፋት በጌታ ፊት በማድረጋቸው፥ ጌታ የሞዓብ ንጉሥ ዔግሎን በእስራኤል ላይ እንዲበረታባቸው አደረገ። እርሱም አሞናውያንንና አማሌቃውያንን ካስተባበረ በኋላ እስራኤልን ወግቶ የዘንባባ ዛፎችበ ከተማ የሆነችውን ኢያሪኮን ያዙ። እስራኤላውያንም ለሞዓብ ንጉሥ ለዔግሎን ዐሥራ ስምንት ዓመት ተገዘሉት። እስራኤላውያን እንደገና ወደ ጌታ ጮኹ፤ ጌታም ብንያማዊውን የጌራን ልጅ፥ ግራኙን፥ ኤሁድን ነጻ እንዲያወጣቸው አስነሣው። እስራኤላውያን ኤሁድን ግብር አስይዘው ወደ ሞዓብ ንጉሥ ወደ ዔግሎን ላኩት። እርሱም በሁለት በኩል ስለታም የሆነና አንድ ክንድ ተኩል ርዝመትተ ያለው ሰይፍ አዘጋጅቶ በልብሱ ውስጥ በቀኝ ጭኑ ላይ አሰረው። ግብሩንም ወፍራም ለነበረው ለሞዓብ ንጉሥ ለዔግሎን አቀረበ። ኤሁድ ግብሩን ካቀረበ በኋላ፥ ግብር ተሸክመው የመጡትን ሰዎች ተመልሰው እንዲሄዱ አደረገ። እርሱ ራሱ ግን ጌልጌላ አጠገብ ድንጋዮች ተጠርበው ከሚወጡበት አካባቢ ሲደርስ ወደ ኋላ በመመለስ ወደ ንጉሡ ሄዶ፥ “ንጉሥ ሆይ፤ በምስጢር የምነግርህ ነገር አለኝ” አለው። ንጉሡም፥ “ጸጥታ” ሲል፤ አጠገቡ የነበሩትአገልጋዮች በሙሉ ትተውት ወጡ። ንጉሡ ሰገነት ላይ ባለው ነፋሻ ዕልፍኝ ውስጥ ብቻውን ተቀምጦ ሳለ ኤሁድ ቀረብ ብሎ፥ “ከእግዚአብሔር ዘንድ ለአንተ ያመጣሁት መልእክት አለኝ” አለው፤ ንጉሡም ከዙፋኑ ተነሣ። ኤሁድ ግራ እጁን ሰደድ በማድረግ ሰይፉን ከደበቀበት ከቀኝ ጭኑ መዝዞ በንጉሡ ሆድ ሻጠው። እጀታው ሳይቀር ሰይፉ እንዳለ ሆዱ ውስጥ ገባ፤ ሞራውም ስለቱን ሸፈነው፤ ስለቱም በጀርባው ወጣ፤ ኤሁድ ሰይፉን ስላልነቀለው አንጀቱ ተዘረገፈ። ከዚያም በኋላ ኤሁድ በዕልፍኙ መግቢያ ወጣ፤ የዕልፍኙንም በር በንጉሡ ላይ ዘግቶ ቈለፈው። ኤሁድ ከሄደ በኋላ፥ የንጉሡ አገልጋዮች ሲመጡ፥ የዕልፍኙ በር ተቈልፎ አገኙት፤ እነርሱም፥ “በውስጠኛው ክፍል እየተጸዳዳ ይሆናል” አሉ፤ እስኪደክማቸውም ድረስ ጠበቁ፤ ነገር ግን ንጉሡ የእልፍኙን በሮች ባለመክፈቱ ቊልፍ ወስደው ከፈቱ፤ በዚያም ጌታቸው ሞቶ፥ በወለሉም ላይ ተዘርግቶ አገኙት። የንጉሡ አገልጋዮች በዕልፍኙ በር ላይ ቆመው ሲጠባበቁ ኤሁድ ርቆ ሄደ፤ ድንጋዮች ተጠርበው በሚወጡበት በኩል ወደ ሴርታ ይም አመለጠ። እዚያም እንደ ደረሰ፥ በኰረብታማው በኤፍሬም ምድር ቀንደ መለከቱን ነፋ፤ እስራኤላውያንም በእርሱ መሪነት ከኰረብታው ላይ አብረውት ወረዱ።