መሳፍንት 15:1-12

መሳፍንት 15:1-12 መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) (አማ54)

ከዚህም በኋላ በስንዴ መከር ጊዜ ሶምሶን የፍየል ጠቦት ይዞ ሚስቱን ሊጠይቅ ሄደና፦ ወደ ጫጉላ ቤት ወደ ሚስቴ ልግባ አለ፥ አባትዋ ግን እንዳይገባ ከለከለው። አባትዋም፦ ፈጽመህ የጠላሃት መስሎኝ ለሚዜህ አጋባኋት፥ ታናሽ እኅትዋ ከርስዋ ይልቅ የተዋበች አይደለችምን? እባክህ፥ በእርስዋ ፋንታ አግባት አለው። ሶምሶንም፦ ከእንግዲህ ወዲህ በፍልስጥኤማውያን ላይ ክፉ ባደርግ እኔ ንጹሕ ነኝ አላቸው። ሶምሶንም ሄዶ ሦስት መቶ ቀበሮች ያዘ፥ ችቦም ወስዶ ሁለት ሁለቱንም ቀበሮዎች በጅራታቸው አሰረ፥ በሁለቱም ጅራቶች መካከል አንድ ችቦ አደረገ። ችቦውንም አንድዶ በቆመው በፍልስጥኤማውያን እህል መካከል ሰደዳቸው፥ ነዶውንም የቆመውንም እህል ወይኑንም ወይራውንም አቃጠለ። ፍልስጥኤማውያንም፦ ይህን ያደረገው ማን ነው? አሉ። እነርሱም፦ ሚስቱን ወስዶ ለሚዜው አጋብቶበታልና የተምናዊው አማች ሶምሶን ነው አሉ። ፍልስጥኤማያንም ወጥተው ሴቲቱንና አባትዋን በእሳት አቃጠሉ። ሶምሶንም፦ እናንተ እንዲሁ ብታደርጉ እኔ እበቀላችኋለሁ፥ ከዚያም በኋላ ዐርፋለሁ አላቸው። እርሱም ጭን ጭናቸውን ብሎ በታላቅ አገዳደል መታቸው፥ ወርዶም በኤጣም ዓለት ባለው ዋሻ ውስጥ ተቀመጠ። ፍልስጥኤማውያንም ወጡ፥ በይሁዳም ሰፈሩ፥ በሌሒ ላይም ተበታትነው ተቀመጡ። የይሁዳም ሰዎች፦ በእኛ ላይ የወጣችሁት ለምንድር ነው? አሉ። እነርሱም፦ ሶምሶንን ልናስር፥ እንዳደረገብንም ልናደርግበት መጥተናል አሉ። ከይሁዳም ሰዎች ሦስት ሺህ የሚያህሉ በኤጣም ዓለት ወዳለው ዋሻ ወርደው ሶምሶንን፦ ገዦቻችን ፍልስጥኤማውያን እንደ ሆኑ አታውቅምን? ያደረግህብን ይህ ምንድር ነው? አሉት። እርሱም፦ እንዳደረጉብኝ እንዲሁ አደረግሁባቸው አላቸው። እነርሱም፦ አስረን በፍልስጥኤማውያን እጅ አሳልፈን ልንሰጥህ መጥተናል አሉት። ሶምሶንም፦ እናንተ እንዳትገሉኝ ማሉልኝ አላቸው።

መሳፍንት 15:1-12 አዲሱ መደበኛ ትርጒም (NASV)

ከጥቂት ጊዜ በኋላ በስንዴ መከር ወራት ሳምሶን አንድ የፍየል ጠቦት ይዞ ሚስቱን ለማየት ሄደ፤ እርሱም፣ “ሚስቴ ወዳለችበት ጫጕላው ቤት ልግባ” አለ፤ አባቷ ግን እንዲገባ አልፈቀደለትም። አባትየውም፣ “ፈጽሞ የጠላሃት መሆንህን ስለ ተረዳሁ ለሚዜህ ድሬለታለሁ፤ ታናሽ እኅቷ ከርሷ ይልቅ ውብ አይደለችምን? እርሷን አግባት” አለው። ሳምሶንም መልሶ፣ “ከእንግዲህ በፍልስጥኤማውያን ላይ በሚደርሰው ጕዳት ተጠያቂ አልሆንም” አላቸው። ከዚያም ወጥቶ በመሄድ ሦስት መቶ ቀበሮች ያዘ፤ የሁለት ሁለቱን ጭራ አንድ ላይ ካሰረ በኋላ ችቦ ወስዶ ጥንድ ሆኖ ከተያያዘው ጭራ ጋራ አሰረው። ችቦውን በእሳት አቀጣጥሎ ቀበሮቹን በፍልስጥኤማውያን የእህል አዝመራ ላይ ለቀቃቸው፤ ነዶውንና የቆመውን አዝመራ እንዲሁም የወይኑንና የወይራውን ተክል አቃጠለ። ፍልስጥኤማውያን፣ “ይህን ያደረገው ማን ነው?” ብለው ሲጠይቁ፣ “ሚስቱ ለሚዜው ስለ ተሰጠችበት የተምናዊው ዐማች ሳምሶን ነው” የሚል መልስ አገኙ። ስለዚህም ፍልስጥኤማውያን ወጥተው ሴቲቱንና አባቷን በእሳት አቃጥለው ገደሏቸው። ሳምሶንም፣ “እንግዲህ እናንተ ይህን ካደረጋችሁ እኔ ደግሞ ሳልበቀላችሁ አልመለስም” አለ። ክፉኛ መታቸው፤ ከእነርሱም ብዙዎችን ገደለ፤ ከዚያም ወርዶ በኤጣም ዐለት ዋሻ ተቀመጠ። ፍልስጥኤማውያን ወጥተው በይሁዳ ሰፈሩ፤ ከዚያም በሌሒ አጠገብ ተበታትነው አደፈጡ። የይሁዳም ሰዎች፣ “ልትወጉን የመጣችሁት ለምንድን ነው?” ሲሉ ጠየቋቸው። እነርሱም “እኛ የመጣነው ሳምሶንን ልናስርና ያደረገብንን ልናደርግበት ነው” ብለው መለሱላቸው። ከዚያም ሦስት ሺሕ ሰዎች ከይሁዳ ተነሥተው በኤጣም ዐለት ወዳለው ዋሻ ወርደው ሳምሶንን፣ “ፍልስጥኤማውያን ገዦቻችን መሆናቸውን አታውቅምን? ያደረግህብንስ ነገር ምንድን ነው?” ብለው ጠየቁት። ሳምሶንም፣ “ያደረግሁት እነርሱ ያደረጉብኝን ነው” በማለት መለሰላቸው። እነርሱም፣ “አስረን ለፍልስጥኤማውያን ልንሰጥህ ይኸው መጥተናል” አሉት። ሳምሶንም፣ “እናንተ ራሳችሁ ላትገድሉኝ ማሉልኝ” አላቸው።

መሳፍንት 15:1-12 አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም (አማ05)

ከጥቂት ጊዜ በኋላ በስንዴ መከር ወራት ሶምሶን ሚስቱን ለመጐብኘት አንድ የፍየል ጠቦት ይዞ ሄደ፤ አባትዋንም “ሚስቴ ወዳለችበት ክፍል መግባት እፈልጋለሁ” አለው። አባትዋ ግን እንዲገባ አልፈቀደለትም፤ ሶምሶንንም “አንተ የጠላሃት ስለ መሰለኝ ሚዜህ ለነበረው ሰው ዳርኳት፤ የሆነ ሆኖ የእርስዋ ታናሽ ይበልጥ ውብ አይደለችምን? እባክህ እርስዋን አግባት” አለው። ሶምሶንም “ከእንግዲህ ወዲህ በፍልስጥኤማውያን ላይ ክፉ ነገር ባደርግ አልወቀስበትም!” አለ። ሄዶም ሦስት መቶ ቀበሮዎችን በማደን ያዘ፤ ጥንድ ጥንድ አድርጎ ጭራቸውን በማያያዝ በገመድ አሰረ፤ ችቦዎችም አምጥቶ በጭራቸው መካከል አሰረ። ከዚያም በኋላ በችቦዎቹ ላይ እሳት በማቀጣጠል ቀበሮዎቹን ገና ወዳልታጨደው ወደ ፍልስጥኤማውያን የስንዴ ሰብል ውስጥ ለቀቃቸው፤ በዚህም ዐይነት ታጭዶ የተከመረውን ብቻ ሳይሆን ገና በማሳ ላይ ያለውን ስንዴ፥ የወይራና የወይን ተክል ጭምር አቃጠለ። ፍልስጥኤማውያን ይህን ያደረገው ማን እንደሆን በጠየቁ ጊዜ፥ ሶምሶን መሆኑን ተረዱ፤ የቲምና ተወላጅ የሆነው ዐማቱ የሶምሶንን ሚስት ሚዜው ለነበረ ሌላ ሰው ሰጥቶበት ነበር፤ ስለዚህ ፍልስጥኤማውያን ሄደው ሴቲቱንና አባቷን በእሳት አቃጠሉ። ሶምሶንም “እንግዲህ እናንተ ይህን አድርጋችኋል፤ እኔ ደግሞ እናንተን ሳልበቀል አልተዋችሁም!” ብሎ ማለ። ወዲያውም ብርቱ አደጋ ጥሎባቸው ከእነርሱ ብዙዎችን ገደለ፤ ከዚህም በኋላ ሄዶ ዔጣም ተብላ በምትጠራ ስፍራ በዋሻ ውስጥ ተቀመጠ። ፍልስጥኤማውያን መጥተው በይሁዳ ሰፈሩ፤ ሌሒ ተብላ የምትጠራውንም ከተማ ወረሩአት፤ የይሁዳም ሰዎች “በእኛ ላይ አደጋ የምትጥሉት ስለምንድነው?” ሲሉ ጠየቁአቸው። እነርሱም “እኛ የመጣነው ሶምሶንን ልንይዝና እስረኛ አድርገን ወስደን በእኛ ላይ ያደረገውን ሁሉ በእርሱም ላይ ልንፈጽምበት ነው” ሲሉ መለሱላቸው። ስለዚህም ሦስት ሺህ የሚሆኑ የይሁዳ ሰዎች በዔጣም ወዳለው ዋሻ ሄደው “ፍልስጥኤማውያን ገዢዎቻችን እንደ ሆኑ አታውቅምን? ታዲያ ይህ ያደረግህብን ምንድን ነው?” ሲሉ ሶምሶንን ጠየቁት። እርሱም “እኔ በእነርሱ ላይ ያደረግኹት ልክ እነርሱ በእኔ ላይ ያደረጉትን ነው” አላቸው። እነርሱም “እኛ አሁን ወደዚህ የመጣነው አንተን አስረን ለእነርሱ አሳልፈን ልንሰጥህ ነው” አሉት። ሶምሶንም “እናንተ ራሳችሁ እንደማትገድሉኝ ማሉልኝ” አላቸው።

መሳፍንት 15:1-12 የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) (አማ2000)

ከጊ​ዜም በኋላ በስ​ንዴ መከር ጊዜ ሶም​ሶን የፍ​የል ጠቦት ይዞ ሚስ​ቱን ሊጠ​ይቅ ሄደና፥ “ወደ ጫጕላ ቤት ወደ ሚስቴ ልግባ” አለ፤ አባቷ ግን እን​ዳ​ይ​ገባ ከለ​ከ​ለው። አባ​ቷም፥ “ፈጽ​መህ ጠላ​ህ​ዋት ያልህ መስ​ሎኝ ለሚ​ዜህ አጋ​ባ​ኋት፤ ታናሽ እኅቷ ከእ​ር​ስዋ ይልቅ የተ​ዋ​በች አይ​ደ​ለ​ች​ምን? እባ​ክህ በእ​ር​ስዋ ፋንታ አግ​ባት” አለው። ሶም​ሶ​ንም፥ “ከእ​ን​ግ​ዲህ ወዲህ በፍ​ል​ስ​ጥ​ኤ​ማ​ው​ያን ላይ ክፉ ባደ​ርግ እኔ ንጹሕ ነኝ” አላ​ቸው። ሶም​ሶ​ንም ሄዶ ሦስት መቶ ቀበ​ሮ​ችን ያዘ፤ ችቦም ወስዶ ሁለት ሁለ​ቱን ቀበ​ሮ​ዎች በጅ​ራ​ታ​ቸው አሰረ፤ በሁ​ለ​ቱም ጅራ​ቶች መካ​ከል አንድ ችቦ አደ​ረገ። ችቦ​ው​ንም አን​ድዶ በቆ​መው በፍ​ል​ስ​ጥ​ኤ​ማ​ው​ያን እህል መካ​ከል ሰደ​ዳ​ቸው፤ ነዶ​ው​ንም፥ ክም​ሩ​ንም፥ የቆ​መ​ዉ​ንም እህል፥ ወይ​ኑ​ንም፥ ወይ​ራ​ዉ​ንም አቃ​ጠለ። ፍል​ስ​ጥ​ኤ​ማ​ው​ያ​ንም፥ “ይህን ያደ​ረገ ማን ነው?” አሉ። እነ​ር​ሱም፥ “ሚስ​ቱን ወስዶ ለሚ​ዜው አጋ​ብ​ቶ​በ​ታ​ልና የቴ​ም​ና​ታ​ዊዉ አማች ሶም​ሶን ነው” አሉ​አ​ቸው። ፍል​ስ​ጥ​ኤ​ማ​ው​ያ​ንም ወጥ​ተው የአ​ባ​ቷን ቤትና እር​ስ​ዋን አባ​ቷ​ንም በእ​ሳት አቃ​ጠሉ። ሶም​ሶ​ንም አላ​ቸው- “ይህን ብታ​ደ​ር​ጉም ደስ አይ​ለ​ኝም፤ በቀሌ ከአ​ንድ ሰው ብቻ አይ​ደ​ለም፤ ሁላ​ች​ሁ​ንም እበ​ቀ​ላ​ች​ኋ​ለሁ፤ ከዚ​ያም በኋላ አር​ፋ​ለሁ።” ሶም​ሶ​ንም ጭን ጭና​ቸ​ውን ብሎ በታ​ላቅ አገ​ዳ​ደል መታ​ቸው፤ ወር​ዶም ኢጣም በም​ት​ባል ዋሻ በወ​ንዝ ዳር ተቀ​መጠ። ፍል​ስ​ጥ​ኤ​ማ​ው​ያ​ንም ወጡ፤ በይ​ሁ​ዳም ሰፈሩ፤ የአ​ህያ መን​ጋጋ አጥ​ንት በተ​ባለ ቦታም ተበ​ታ​ት​ነው ተቀ​መጡ። የይ​ሁ​ዳም ሰዎች ሁሉ፥ “በእኛ ላይ የወ​ጣ​ች​ሁት ለም​ን​ድን ነው?” አሉ። እነ​ር​ሱም፥ “ሶም​ሶ​ንን ልና​ስር፥ እን​ዳ​ደ​ረ​ገ​ብ​ንም ልና​ደ​ር​ግ​በት መጥ​ተ​ናል” አሏ​ቸው። ከይ​ሁ​ዳም ሰዎች ሦስት ሺህ የሚ​ያ​ህሉ በኢ​ጣም ዓለት ወዳ​ለው ዋሻ ወር​ደው ሶም​ሶ​ንን፥ “ገዢ​ዎ​ቻ​ችን ፍል​ስ​ጥ​ኤ​ማ​ው​ያን እን​ደ​ሆኑ አታ​ው​ቅ​ምን? ያደ​ረ​ግ​ህ​ብን ይህ ምን​ድን ነው?” አሉት። ሶም​ሶ​ንም፥ “እን​ዳ​ደ​ረ​ጉ​ባ​ችሁ እን​ዲሁ አደ​ረ​ግ​ሁ​ባ​ቸው” አላ​ቸው። እነ​ር​ሱም፥ “አስ​ረን በፍ​ል​ስ​ጥ​ኤ​ማ​ው​ያን እጅ አሳ​ል​ፈን ልን​ሰ​ጥህ መጥ​ተ​ናል” አሉት። ሶም​ሶ​ንም፥ “እና​ንተ እን​ዳ​ት​ገ​ድ​ሉኝ ማሉ​ልኝ፤ ለእ​ነ​ር​ሱም አሳ​ል​ፋ​ችሁ ስጡኝ፤ እና​ንተ ግን ከእኔ ጋር አትዋጉ” አላ​ቸው።

መሳፍንት 15:1-12 አዲሱ መደበኛ ትርጒም (NASV)

ከጥቂት ጊዜ በኋላ በስንዴ መከር ወራት ሳምሶን አንድ የፍየል ጠቦት ይዞ ሚስቱን ለማየት ሄደ፤ እርሱም፣ “ሚስቴ ወዳለችበት ጫጕላው ቤት ልግባ” አለ፤ አባቷ ግን እንዲገባ አልፈቀደለትም። አባትየውም፣ “ፈጽሞ የጠላሃት መሆንህን ስለ ተረዳሁ ለሚዜህ ድሬለታለሁ፤ ታናሽ እኅቷ ከርሷ ይልቅ ውብ አይደለችምን? እርሷን አግባት” አለው። ሳምሶንም መልሶ፣ “ከእንግዲህ በፍልስጥኤማውያን ላይ በሚደርሰው ጕዳት ተጠያቂ አልሆንም” አላቸው። ከዚያም ወጥቶ በመሄድ ሦስት መቶ ቀበሮች ያዘ፤ የሁለት ሁለቱን ጭራ አንድ ላይ ካሰረ በኋላ ችቦ ወስዶ ጥንድ ሆኖ ከተያያዘው ጭራ ጋራ አሰረው። ችቦውን በእሳት አቀጣጥሎ ቀበሮቹን በፍልስጥኤማውያን የእህል አዝመራ ላይ ለቀቃቸው፤ ነዶውንና የቆመውን አዝመራ እንዲሁም የወይኑንና የወይራውን ተክል አቃጠለ። ፍልስጥኤማውያን፣ “ይህን ያደረገው ማን ነው?” ብለው ሲጠይቁ፣ “ሚስቱ ለሚዜው ስለ ተሰጠችበት የተምናዊው ዐማች ሳምሶን ነው” የሚል መልስ አገኙ። ስለዚህም ፍልስጥኤማውያን ወጥተው ሴቲቱንና አባቷን በእሳት አቃጥለው ገደሏቸው። ሳምሶንም፣ “እንግዲህ እናንተ ይህን ካደረጋችሁ እኔ ደግሞ ሳልበቀላችሁ አልመለስም” አለ። ክፉኛ መታቸው፤ ከእነርሱም ብዙዎችን ገደለ፤ ከዚያም ወርዶ በኤጣም ዐለት ዋሻ ተቀመጠ። ፍልስጥኤማውያን ወጥተው በይሁዳ ሰፈሩ፤ ከዚያም በሌሒ አጠገብ ተበታትነው አደፈጡ። የይሁዳም ሰዎች፣ “ልትወጉን የመጣችሁት ለምንድን ነው?” ሲሉ ጠየቋቸው። እነርሱም “እኛ የመጣነው ሳምሶንን ልናስርና ያደረገብንን ልናደርግበት ነው” ብለው መለሱላቸው። ከዚያም ሦስት ሺሕ ሰዎች ከይሁዳ ተነሥተው በኤጣም ዐለት ወዳለው ዋሻ ወርደው ሳምሶንን፣ “ፍልስጥኤማውያን ገዦቻችን መሆናቸውን አታውቅምን? ያደረግህብንስ ነገር ምንድን ነው?” ብለው ጠየቁት። ሳምሶንም፣ “ያደረግሁት እነርሱ ያደረጉብኝን ነው” በማለት መለሰላቸው። እነርሱም፣ “አስረን ለፍልስጥኤማውያን ልንሰጥህ ይኸው መጥተናል” አሉት። ሳምሶንም፣ “እናንተ ራሳችሁ ላትገድሉኝ ማሉልኝ” አላቸው።

መሳፍንት 15:1-12 መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) (አማ54)

ከዚህም በኋላ በስንዴ መከር ጊዜ ሶምሶን የፍየል ጠቦት ይዞ ሚስቱን ሊጠይቅ ሄደና፦ ወደ ጫጉላ ቤት ወደ ሚስቴ ልግባ አለ፥ አባትዋ ግን እንዳይገባ ከለከለው። አባትዋም፦ ፈጽመህ የጠላሃት መስሎኝ ለሚዜህ አጋባኋት፥ ታናሽ እኅትዋ ከርስዋ ይልቅ የተዋበች አይደለችምን? እባክህ፥ በእርስዋ ፋንታ አግባት አለው። ሶምሶንም፦ ከእንግዲህ ወዲህ በፍልስጥኤማውያን ላይ ክፉ ባደርግ እኔ ንጹሕ ነኝ አላቸው። ሶምሶንም ሄዶ ሦስት መቶ ቀበሮች ያዘ፥ ችቦም ወስዶ ሁለት ሁለቱንም ቀበሮዎች በጅራታቸው አሰረ፥ በሁለቱም ጅራቶች መካከል አንድ ችቦ አደረገ። ችቦውንም አንድዶ በቆመው በፍልስጥኤማውያን እህል መካከል ሰደዳቸው፥ ነዶውንም የቆመውንም እህል ወይኑንም ወይራውንም አቃጠለ። ፍልስጥኤማውያንም፦ ይህን ያደረገው ማን ነው? አሉ። እነርሱም፦ ሚስቱን ወስዶ ለሚዜው አጋብቶበታልና የተምናዊው አማች ሶምሶን ነው አሉ። ፍልስጥኤማያንም ወጥተው ሴቲቱንና አባትዋን በእሳት አቃጠሉ። ሶምሶንም፦ እናንተ እንዲሁ ብታደርጉ እኔ እበቀላችኋለሁ፥ ከዚያም በኋላ ዐርፋለሁ አላቸው። እርሱም ጭን ጭናቸውን ብሎ በታላቅ አገዳደል መታቸው፥ ወርዶም በኤጣም ዓለት ባለው ዋሻ ውስጥ ተቀመጠ። ፍልስጥኤማውያንም ወጡ፥ በይሁዳም ሰፈሩ፥ በሌሒ ላይም ተበታትነው ተቀመጡ። የይሁዳም ሰዎች፦ በእኛ ላይ የወጣችሁት ለምንድር ነው? አሉ። እነርሱም፦ ሶምሶንን ልናስር፥ እንዳደረገብንም ልናደርግበት መጥተናል አሉ። ከይሁዳም ሰዎች ሦስት ሺህ የሚያህሉ በኤጣም ዓለት ወዳለው ዋሻ ወርደው ሶምሶንን፦ ገዦቻችን ፍልስጥኤማውያን እንደ ሆኑ አታውቅምን? ያደረግህብን ይህ ምንድር ነው? አሉት። እርሱም፦ እንዳደረጉብኝ እንዲሁ አደረግሁባቸው አላቸው። እነርሱም፦ አስረን በፍልስጥኤማውያን እጅ አሳልፈን ልንሰጥህ መጥተናል አሉት። ሶምሶንም፦ እናንተ እንዳትገሉኝ ማሉልኝ አላቸው።

መሳፍንት 15:1-12 አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም (አማ05)

ከጥቂት ጊዜ በኋላ በስንዴ መከር ወራት ሶምሶን ሚስቱን ለመጐብኘት አንድ የፍየል ጠቦት ይዞ ሄደ፤ አባትዋንም “ሚስቴ ወዳለችበት ክፍል መግባት እፈልጋለሁ” አለው። አባትዋ ግን እንዲገባ አልፈቀደለትም፤ ሶምሶንንም “አንተ የጠላሃት ስለ መሰለኝ ሚዜህ ለነበረው ሰው ዳርኳት፤ የሆነ ሆኖ የእርስዋ ታናሽ ይበልጥ ውብ አይደለችምን? እባክህ እርስዋን አግባት” አለው። ሶምሶንም “ከእንግዲህ ወዲህ በፍልስጥኤማውያን ላይ ክፉ ነገር ባደርግ አልወቀስበትም!” አለ። ሄዶም ሦስት መቶ ቀበሮዎችን በማደን ያዘ፤ ጥንድ ጥንድ አድርጎ ጭራቸውን በማያያዝ በገመድ አሰረ፤ ችቦዎችም አምጥቶ በጭራቸው መካከል አሰረ። ከዚያም በኋላ በችቦዎቹ ላይ እሳት በማቀጣጠል ቀበሮዎቹን ገና ወዳልታጨደው ወደ ፍልስጥኤማውያን የስንዴ ሰብል ውስጥ ለቀቃቸው፤ በዚህም ዐይነት ታጭዶ የተከመረውን ብቻ ሳይሆን ገና በማሳ ላይ ያለውን ስንዴ፥ የወይራና የወይን ተክል ጭምር አቃጠለ። ፍልስጥኤማውያን ይህን ያደረገው ማን እንደሆን በጠየቁ ጊዜ፥ ሶምሶን መሆኑን ተረዱ፤ የቲምና ተወላጅ የሆነው ዐማቱ የሶምሶንን ሚስት ሚዜው ለነበረ ሌላ ሰው ሰጥቶበት ነበር፤ ስለዚህ ፍልስጥኤማውያን ሄደው ሴቲቱንና አባቷን በእሳት አቃጠሉ። ሶምሶንም “እንግዲህ እናንተ ይህን አድርጋችኋል፤ እኔ ደግሞ እናንተን ሳልበቀል አልተዋችሁም!” ብሎ ማለ። ወዲያውም ብርቱ አደጋ ጥሎባቸው ከእነርሱ ብዙዎችን ገደለ፤ ከዚህም በኋላ ሄዶ ዔጣም ተብላ በምትጠራ ስፍራ በዋሻ ውስጥ ተቀመጠ። ፍልስጥኤማውያን መጥተው በይሁዳ ሰፈሩ፤ ሌሒ ተብላ የምትጠራውንም ከተማ ወረሩአት፤ የይሁዳም ሰዎች “በእኛ ላይ አደጋ የምትጥሉት ስለምንድነው?” ሲሉ ጠየቁአቸው። እነርሱም “እኛ የመጣነው ሶምሶንን ልንይዝና እስረኛ አድርገን ወስደን በእኛ ላይ ያደረገውን ሁሉ በእርሱም ላይ ልንፈጽምበት ነው” ሲሉ መለሱላቸው። ስለዚህም ሦስት ሺህ የሚሆኑ የይሁዳ ሰዎች በዔጣም ወዳለው ዋሻ ሄደው “ፍልስጥኤማውያን ገዢዎቻችን እንደ ሆኑ አታውቅምን? ታዲያ ይህ ያደረግህብን ምንድን ነው?” ሲሉ ሶምሶንን ጠየቁት። እርሱም “እኔ በእነርሱ ላይ ያደረግኹት ልክ እነርሱ በእኔ ላይ ያደረጉትን ነው” አላቸው። እነርሱም “እኛ አሁን ወደዚህ የመጣነው አንተን አስረን ለእነርሱ አሳልፈን ልንሰጥህ ነው” አሉት። ሶምሶንም “እናንተ ራሳችሁ እንደማትገድሉኝ ማሉልኝ” አላቸው።

መሳፍንት 15:1-12 መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) (መቅካእኤ)

ከጥቂት ጊዜ በኋላ በስንዴ መከር ወራት ሳምሶን አንድ የፍየል ጠቦት ይዞ ሚስቱን ለማየት ሄደ፤ እርሱም፥ “ሚስቴ ወዳለችበት ጫጉላው ቤት ልግባ” አለ፤ አባቷ ግን እንዲገባ አልፈቀደለትም። አባትየውም፥ “ፈጽሞ የጠላሃት መሆንህን ስለ ተረዳሁ ለሚዜህ ድሬለታለሁ፤ ታናሽ እኅቷ ከእርሷ ይልቅ ውብ አይደለችምን? እርሷን አግባት” አለው። ሳምሶንም መልሶ፥ “ከእንግዲህ በፍልስጥኤማውያን ላይ በሚደርሰው ጉዳት ተጠያቂ አልሆንም” አላቸው። ከዚያም ወጥቶ በመሄድ ሦስት መቶ ቀበሮች ያዘ፤ የሁለት ሁለቱን ጭራ አንድ ላይ ካሰረ በኋላ ችቦ ወስዶ ጥንድ ሆኖ ከተያያዘው ጭራ ጋር አሰረው። ችቦውን በእሳት አቀጣጥሎ ቀበሮቹን በፍልስጥኤማውያን የእህል አዝመራ ላይ ለቀቃቸው፤ ነዶውንና የቆመውን አዝመራ እንዲሁም የወይኑንና የወይራውን ተክል አቃጠለ። ፍልስጥኤማውያን፥ “ይህን ያደረገው ማን ነው?” ብለው ሲጠይቁ፥ “ሚስተ ለሚዜው ስለ ተሰጠችበት የቲምናዊው ዐማች ሳምሶን ነው” የሚል መልስ አገኙ። ስለዚህም ፍልስጥኤማውያን ወጥተው ሴቲቱንና አባቷን በእሳት አቃጥለው ገደሏቸው። ሳምሶንም፥ “እንግዲህ እናንተ ይህን ካደረጋችሁ እኔ ደግሞ ሳልበቀላችሁ አልመለስም” አለ። ክፉኛ መታቸው፤ ከነርሱም ብዙዎችን ገደለ፤ ከዚያም ወርዶ በኢታም ዐለት ዋሻ ተቀመጠ። ፍልስጥኤማውያን ወጥተው በይሁዳ ሰፈሩ፤ ከዚያም በሌሒ አጠገብ ተበታትነው አደፈጡ። የይሁዳም ሰዎች፥ “ልትወጉን የመጣችሁት ለምንድን ነው?” ሲሉ ጠየቋቸው። እነርሱም “እኛ የመጣነው ሳምሶንን ልና ስርና ያደረገብንን ልናደርግበት ነው” ብለው መለሱላቸው። ከዚያም ሦስት ሺህ ሰዎች ከይሁዳ ተነሥተው በኤታም ዐለት ወዳለው ዋሻ ወርደው ሳምሶንን፥ “ፍልስጥኤማውያን ገዦቻችን መሆናቸውን አታውቅምን? ያደረግህብንስ ነገር ምንድነው?” ብለው ጠየቁት። ሳምሶንም፥ “ያደረግሁት እነርሱ ያደረ ጉብኝን ነው” በማለት መለሰላቸው። እነርሱም፥ “አስረን ለፍልስጥአማውያን ልንሰጥህ ይኸው መጥተናል” አሉት። ሳምሶንም፥ “እናንተ ራሳችሁ ላትገድሉኝ ማሉልኝ” አላቸው።