ከጊዜም በኋላ በስንዴ መከር ጊዜ ሶምሶን የፍየል ጠቦት ይዞ ሚስቱን ሊጠይቅ ሄደና፥ “ወደ ጫጕላ ቤት ወደ ሚስቴ ልግባ” አለ፤ አባቷ ግን እንዳይገባ ከለከለው። አባቷም፥ “ፈጽመህ ጠላህዋት ያልህ መስሎኝ ለሚዜህ አጋባኋት፤ ታናሽ እኅቷ ከእርስዋ ይልቅ የተዋበች አይደለችምን? እባክህ በእርስዋ ፋንታ አግባት” አለው። ሶምሶንም፥ “ከእንግዲህ ወዲህ በፍልስጥኤማውያን ላይ ክፉ ባደርግ እኔ ንጹሕ ነኝ” አላቸው። ሶምሶንም ሄዶ ሦስት መቶ ቀበሮችን ያዘ፤ ችቦም ወስዶ ሁለት ሁለቱን ቀበሮዎች በጅራታቸው አሰረ፤ በሁለቱም ጅራቶች መካከል አንድ ችቦ አደረገ። ችቦውንም አንድዶ በቆመው በፍልስጥኤማውያን እህል መካከል ሰደዳቸው፤ ነዶውንም፥ ክምሩንም፥ የቆመዉንም እህል፥ ወይኑንም፥ ወይራዉንም አቃጠለ። ፍልስጥኤማውያንም፥ “ይህን ያደረገ ማን ነው?” አሉ። እነርሱም፥ “ሚስቱን ወስዶ ለሚዜው አጋብቶበታልና የቴምናታዊዉ አማች ሶምሶን ነው” አሉአቸው። ፍልስጥኤማውያንም ወጥተው የአባቷን ቤትና እርስዋን አባቷንም በእሳት አቃጠሉ። ሶምሶንም አላቸው- “ይህን ብታደርጉም ደስ አይለኝም፤ በቀሌ ከአንድ ሰው ብቻ አይደለም፤ ሁላችሁንም እበቀላችኋለሁ፤ ከዚያም በኋላ አርፋለሁ።” ሶምሶንም ጭን ጭናቸውን ብሎ በታላቅ አገዳደል መታቸው፤ ወርዶም ኢጣም በምትባል ዋሻ በወንዝ ዳር ተቀመጠ። ፍልስጥኤማውያንም ወጡ፤ በይሁዳም ሰፈሩ፤ የአህያ መንጋጋ አጥንት በተባለ ቦታም ተበታትነው ተቀመጡ። የይሁዳም ሰዎች ሁሉ፥ “በእኛ ላይ የወጣችሁት ለምንድን ነው?” አሉ። እነርሱም፥ “ሶምሶንን ልናስር፥ እንዳደረገብንም ልናደርግበት መጥተናል” አሏቸው። ከይሁዳም ሰዎች ሦስት ሺህ የሚያህሉ በኢጣም ዓለት ወዳለው ዋሻ ወርደው ሶምሶንን፥ “ገዢዎቻችን ፍልስጥኤማውያን እንደሆኑ አታውቅምን? ያደረግህብን ይህ ምንድን ነው?” አሉት። ሶምሶንም፥ “እንዳደረጉባችሁ እንዲሁ አደረግሁባቸው” አላቸው። እነርሱም፥ “አስረን በፍልስጥኤማውያን እጅ አሳልፈን ልንሰጥህ መጥተናል” አሉት። ሶምሶንም፥ “እናንተ እንዳትገድሉኝ ማሉልኝ፤ ለእነርሱም አሳልፋችሁ ስጡኝ፤ እናንተ ግን ከእኔ ጋር አትዋጉ” አላቸው።
መጽሐፈ መሳፍንት 15 ያንብቡ
ያጋሩ
ሁሉንም ሥሪቶች ያነጻጽሩ: መጽሐፈ መሳፍንት 15:1-12
ጥቅሶችን ያስቀምጡ፣ ያለበይነመረብ ያንብቡ፣ አጫጭር የትምህርት ቪዲዮዎችን ይመልከቱ እና ሌሎችም!
ቤት
መጽሐፍ ቅዱስ
እቅዶች
ቪዲዮዎች