ኢሳይያስ 65:20-25

ኢሳይያስ 65:20-25 አዲሱ መደበኛ ትርጒም (NASV)

“ከእንግዲህም በዚያ፣ ለጥቂት ጊዜ ብቻ በሕይወት የሚኖር ሕፃን፣ ወይም ዕድሜ ያልጠገበ አረጋዊ አይኖርም፤ አንድ መቶ ዓመት የሞላው ሰው ቢሞት፣ በዐጭር እንደ ተቀጨ ይቈጠራል፤ አንድ ሰው መቶ ዓመት ሳይሞላው ቢሞት፣ እንደ ተቀሠፈ ይገመታል። ሰዎች ቤት ይሠራሉ፤ በውስጡም ይኖራሉ፤ ወይንን ይተክላሉ፤ ፍሬውንም ይበላሉ። ከእንግዲህ ለሌሎች መኖሪያ ቤት አይሠሩም፤ ወይም ሌላው እንዲበላው አይተክሉም፤ የሕዝቤ ዕድሜ፣ እንደ ዛፍ ዕድሜ ይረዝማል፤ እኔ የመረጥኋቸው፣ በእጃቸው ሥራ ለረዥም ዘመን ደስ ይላቸዋል። ድካማቸው በከንቱ አይቀርም፤ ዕድለ ቢስ ልጆችም አይወልዱም፤ እነርሱና ዘራቸው፣ እግዚአብሔር የባረከው ሕዝብ ይሆናሉ። ገና ሳይጣሩ እመልስላቸዋለሁ፤ ተናግረው ሳይጨርሱ እሰማለሁ። ተኵላና የበግ ጠቦት በአንድነት ይበላሉ፤ አንበሳ እንደ በሬ ሣር ይበላል፤ እባብ ትቢያ ይልሳል፤ በተቀደሰው ተራራዬም፣ ጕዳት አያደርሱም፤ ጥፋት አያመጡም፤” ይላል እግዚአብሔር።

ኢሳይያስ 65:20-25 የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) (አማ2000)

ከዚ​ያም ወዲያ ጥቂት ዘመን ብቻ የሚ​ኖር ሕፃን፥ ወይም ዕድ​ሜ​ውን ያል​ፈ​ጸመ ሽማ​ግሌ አይ​ገ​ኝም፤ ጐል​ማ​ሳው የመቶ ዓመት ሆኖት ይሞ​ታ​ልና፥ ኀጢ​አ​ተ​ኛ​ውም የመቶ ዓመት ሆኖት የተ​ረ​ገመ ይሆ​ና​ልና። ቤቶ​ች​ንም ይሠ​ራሉ፤ ይቀ​መ​ጡ​ባ​ቸ​ው​ማል፤ ወይ​ኑን ይተ​ክ​ላሉ፤ ፍሬ​ው​ንም ይበ​ላሉ። ሌላ እን​ዲ​ቀ​መ​ጥ​በት አይ​ሠ​ሩም፤ ሌላም እን​ዲ​በ​ላው አይ​ተ​ክ​ሉም፤ የሕ​ዝቤ ዕድሜ እንደ ሕይ​ወት ዛፍ ዕድሜ ይሆ​ና​ልና፥ እኔም የመ​ረ​ጥ​ኋ​ቸው በእ​ጃ​ቸው ሥራ ረዥም ዘመን ደስ ይላ​ቸ​ዋል። እነ​ርሱ ከእ​ነ​ል​ጆ​ቻ​ቸው የእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ቡሩ​ካን ዘር ናቸ​ውና በከ​ንቱ አይ​ደ​ክ​ሙም፤ ለር​ግ​ማ​ንም አይ​ወ​ል​ዱም። “እን​ዲ​ህም ይሆ​ናል፤ ሳይ​ጠሩ እመ​ል​ስ​ላ​ቸ​ዋ​ለሁ፤ ገናም ሲና​ገሩ እነሆ፥ አለሁ እላ​ቸ​ዋ​ለሁ። ያን​ጊዜ ተኵ​ላና በግ በአ​ን​ድ​ነት ይሰ​ማ​ራሉ፤ አን​በ​ሳም እንደ በሬ ገለባ ይበ​ላል፤ የእ​ባ​ብም መብል ትቢያ ይሆ​ናል። በተ​ቀ​ደ​ሰው ተራ​ራዬ ሁሉ አይ​ጐ​ዱም፤ አያ​ጠ​ፉ​ምም፥” ይላል እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር።

ኢሳይያስ 65:20-25 አዲሱ መደበኛ ትርጒም (NASV)

“ከእንግዲህም በዚያ፣ ለጥቂት ጊዜ ብቻ በሕይወት የሚኖር ሕፃን፣ ወይም ዕድሜ ያልጠገበ አረጋዊ አይኖርም፤ አንድ መቶ ዓመት የሞላው ሰው ቢሞት፣ በዐጭር እንደ ተቀጨ ይቈጠራል፤ አንድ ሰው መቶ ዓመት ሳይሞላው ቢሞት፣ እንደ ተቀሠፈ ይገመታል። ሰዎች ቤት ይሠራሉ፤ በውስጡም ይኖራሉ፤ ወይንን ይተክላሉ፤ ፍሬውንም ይበላሉ። ከእንግዲህ ለሌሎች መኖሪያ ቤት አይሠሩም፤ ወይም ሌላው እንዲበላው አይተክሉም፤ የሕዝቤ ዕድሜ፣ እንደ ዛፍ ዕድሜ ይረዝማል፤ እኔ የመረጥኋቸው፣ በእጃቸው ሥራ ለረዥም ዘመን ደስ ይላቸዋል። ድካማቸው በከንቱ አይቀርም፤ ዕድለ ቢስ ልጆችም አይወልዱም፤ እነርሱና ዘራቸው፣ እግዚአብሔር የባረከው ሕዝብ ይሆናሉ። ገና ሳይጣሩ እመልስላቸዋለሁ፤ ተናግረው ሳይጨርሱ እሰማለሁ። ተኵላና የበግ ጠቦት በአንድነት ይበላሉ፤ አንበሳ እንደ በሬ ሣር ይበላል፤ እባብ ትቢያ ይልሳል፤ በተቀደሰው ተራራዬም፣ ጕዳት አያደርሱም፤ ጥፋት አያመጡም፤” ይላል እግዚአብሔር።

ኢሳይያስ 65:20-25 አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም (አማ05)

በሕፃንነቱ የሚሞት ከቶ አይኖርም፤ ዕድሜውንም የማይፈጽም ሽማግሌ አይኖርም፤ በመቶ ዓመቱ የሚሞት ሰው በወጣትነቱ እንደ ሞተ ወጣት ከመቶ ዓመት በታች የሚሞት ሰው እንደ ተረገመ ይቈጠራል። ሕዝቤ ቤት ሠርተው ይኖሩበታል፤ ወይን ተክለው ፍሬውን ይበላሉ፤ እነርሱ የሠሩትን ቤት ሌሎች አይገቡበትም፤ የተከሉትንም ማንኛውንም ነገር ባዕዳን አይበሉትም፤ ሕዝቤ እንደ ዛፍ ለረጅም ዘመናት ይኖራሉ፤ የመረጥኳቸውም ሰዎች የደከሙበትን ነገር ለረጅም ጊዜ ይደሰቱበታል። ሥራቸው ከንቱ አይሆንም፤ የወለዱአቸው ልጆችና የልጅ ልጆቻቸው በእግዚአብሔር የተባረኩ ስለሚሆኑ ልጆቹን የሚወልዱት ጥፋት እንዲደርስባቸው አይደለም። እኔን በልመና ከመጥራታቸው በፊት እመልስላቸዋለሁ፤ እየጸለዩም ሳለ እሰማቸዋለሁ። ተኲላና ጠቦት አብረው ይመገባሉ፤ አንበሳ እንደ በሬ ገለባ ይበላል፤ የእባብ ምግብ ትቢያ ይሆናል፤ እነርሱም በተቀደሰው ተራራዬ ሁሉ አይጐዱም፤ አያጠፉምም” ይህን የተናገርኩ እኔ እግዚአብሔር ነኝ።