ኢሳይያስ 29:11-24

ኢሳይያስ 29:11-24 የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) (አማ2000)

ይህም ሁሉ ነገር እንደ ታተመ መጽ​ሐፍ ቃል ሆኖ​ባ​ቸ​ዋል፤ ማን​በ​ብ​ንም ለሚ​ያ​ውቅ፥ “ይህን አን​ብብ” ብለው በሰ​ጡት ጊዜ እርሱ፥ “ታት​ሟ​ልና ማን​በብ አል​ች​ልም” ይላ​ቸ​ዋል፤ ደግ​ሞም መጽ​ሐ​ፉን ማን​በ​ብን ለማ​ያ​ውቅ፥ “ይህን አን​ብብ” ብለው በሰ​ጡት ጊዜ እርሱ፥ “ማን​በብ አላ​ው​ቅም” ይላ​ቸ​ዋል። ጌታም አለ፥ “ይህ ሕዝብ በከ​ን​ፈ​ሮቹ ያከ​ብ​ረ​ኛ​ልና፥ ልቡ ግን ከእኔ የራቀ ነውና፥ በከ​ንቱ ያመ​ል​ኩ​ኛል፤ ሰው ሠራሽ ትም​ህ​ር​ትም ያስ​ተ​ም​ራሉ፤ ስለ​ዚህ፥ እነሆ፥ ይህ ሕዝብ በድ​ጋሚ እን​ዲ​ፈ​ልስ አደ​ር​ጋ​ለሁ፤ አፈ​ል​ሳ​ቸ​ዋ​ለ​ሁም፤ የጥ​በ​በ​ኞ​ች​ንም ጥበብ አጠ​ፋ​ለሁ፤ የአ​ስ​ተ​ዋ​ዮ​ች​ንም ማስ​ተ​ዋል እሰ​ው​ራ​ለሁ።” ምክ​ራ​ቸ​ውን ጥልቅ አድ​ር​ገው ከእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ለሚ​ሰ​ውሩ ወዮ​ላ​ቸው! ሥራ​ቸ​ው​ንም በጨ​ለማ ውስጥ አድ​ር​ገው፥ “ማን ያየ​ናል? ወይስ ማን ያው​ቀ​ናል?” ለሚሉ ወዮ​ላ​ቸው! ይህ የእ​ና​ንተ ጠማ​ም​ነት ነው፤ እንደ ሸክላ ሠሪ ጭቃ የም​ት​ቈ​ጠሩ አይ​ደ​ላ​ች​ሁ​ምን? በውኑ ሥራ ሠሪ​ውን፥ “አል​ሠ​ራ​ኸ​ኝም” ይለ​ዋ​ልን? ወይስ የተ​ደ​ረገ አድ​ራ​ጊ​ውን፥ “በማ​ስ​ተ​ዋል አላ​ሳ​መ​ር​ኸ​ኝም” ይለ​ዋ​ልን? ሊባ​ኖስ እንደ ፍሬ​ያማ እርሻ ሊለ​ወጥ፥ ፍሬ​ያ​ማ​ውም እርሻ እንደ ዱር ሊቈ​ጠር ጥቂት ዘመን የቀረ አይ​ይ​ደ​ለ​ምን? በዚ​ያም ቀን ደን​ቆ​ሮች የመ​ጽ​ሐ​ፍን ቃል ይሰ​ማሉ፤ በጨ​ለ​ማና በጭ​ጋግ ውስ​ጥም የዕ​ው​ሮች ዐይ​ኖች ያያሉ። ነዳ​ያን ደስ​ታ​ቸ​ውን በእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ያበ​ዛሉ፤ በሰ​ዎች መካ​ከል ተስፋ የሌ​ላ​ቸ​ውም ሐሤ​ትን በእ​ስ​ራ​ኤል ቅዱስ ያደ​ር​ጋሉ። ኃጥእ ሰው አል​ቆ​አ​ልና፥ ትዕ​ቢ​ተ​ኛ​ውም ጠፍ​ቶ​አ​ልና፥ በክ​ፋት የበ​ደ​ሉም ሁሉ ይነ​ቀ​ላ​ሉና፤ እነ​ዚ​ህም ሰውን በነ​ገር በደ​ለኛ የሚ​ያ​ደ​ርጉ፥ በበ​ርም ለሚ​ገ​ሥ​ጸው አሽ​ክላ የሚ​ያ​ኖሩ፥ ጻድ​ቁ​ንም በከ​ንቱ ነገር የሚ​ያ​ስቱ ናቸው። ስለ​ዚህ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ከአ​ብ​ር​ሃም ስለ ለየው ስለ ያዕ​ቆብ ቤት እን​ዲህ ይላል፥ “ያዕ​ቆብ አሁን አታ​ፍ​ርም፤ ፊት​ህም አሁን አይ​ለ​ወ​ጥም። ነገር ግን ልጆ​ቻ​ቸው የእ​ጄን ሥራ ባዩ ጊዜ ስለ እኔ ስሜን ይቀ​ድ​ሳሉ፤ የያ​ዕ​ቆ​ብ​ንም ቅዱስ ይቀ​ድ​ሳሉ፤ የእ​ስ​ራ​ኤ​ል​ንም አም​ላክ ይፈ​ራሉ። በመ​ን​ፈ​ስም የሳቱ ማስ​ተ​ዋ​ልን ያው​ቃሉ፤ የሚ​ያ​ጕ​ረ​መ​ር​ሙም መታ​ዘ​ዝን ይማ​ራሉ፤ ዲዳ አን​ደ​በ​ትም ሰላም መና​ገ​ርን ይማ​ራል።”

ኢሳይያስ 29:11-24 አዲሱ መደበኛ ትርጒም (NASV)

ይህ ሁሉ ራእይ በጥቅልል መጽሐፍ ውስጥ እንደ ታሸገ ቃል ሆኖባችኋል። ጥቅልሉንም መጽሐፍ ማንበብ ለሚችል ሰው፣ “እባክህ አንብብልን” ብላችሁ ብትሰጡት፣ “ታሽጓልና አልችልም” ይላችኋል። ደግሞም ጥቅልሉን መጽሐፍ ማንበብ ለማይችል ሰው፣ “እባክህን አንብብልን” ብላችሁ ብትሰጡ፣ “ማንበብ አልችልም” ይላችኋል። እግዚአብሔር እንዲህ ይላል፤ “ይህ ሕዝብ በአፉ ወደ እኔ ይቀርባል፤ በከንፈሩም ያከብረኛል፤ ልቡ ግን ከእኔ የራቀ ነው፤ የሚያመልከኝም፣ ሰው ባስተማረው ሰው ሠራሽ ሥርዐት ነው። ስለዚህ ይህን ሕዝብ በድንቅ ላይ ድንቅ ነገር እያደረግሁ፣ ዳግመኛ አስገርመዋለሁ፤ የጥበበኞችን ጥበብ አጠፋለሁ፤ የአስተዋዮችም ማስተዋል ትሰወራለች።” ሐሳባቸውን ከእግዚአብሔር ለመደበቅ፣ ወደ ጥልቅ ጕድጓድ ለሚወርዱ ሥራቸውንም በጨለማ ለሚያከናውኑ፣ “ማን ያየናል? ማንስ ያውቅብናል” ለሚሉ ወዮላቸው! እናንተ ነገሮችን ትገለብጣላችሁ ሸክላ ሠሪውን እንደ ሸክላ ትመለከታላችሁ! ለመሆኑ፣ ተሠሪ ሠሪውን፣ “እርሱ አልሠራኝም” ይለዋልን? ሸክላ የሠራውን፣ “እርሱ ምንም አያውቅም” ይለዋልን? ሊባኖስ ወደ ለም ዕርሻነት ለመለወጥ፣ ለም የሆነውም መሬት ወደ ዱርነት ለመለወጥ ጥቂት ጊዜ አልቀረውምን? በዚያ ጊዜ ደንቈሮ የጥቅልሉን መጽሐፍ ቃል ይሰማል፤ የዐይነ ስውሩም ዐይኖች ከጭጋግና ከጨለማ ተላቀው ያያሉ። ትሑታን በእግዚአብሔር፣ ምስኪኖችም በእስራኤል ቅዱስ እንደ ገና ሐሤት ያደርጋሉ። ጨካኞች እንዳልነበሩ ይሆናሉ፤ ፌዘኞችም በንነው ይጠፋሉ፤ ለክፋት ያደፈጡ ሁሉ ይወገዳሉ። ሰውን በነገር በደለኛ የሚያደርጉ፣ በተከሳሽ ላይ ወጥመድ የሚዘረጉ፣ በሐሰት ምስክር ፍትሕን ከንጹሓን የሚቀሙ ይቈረጣሉ። ስለዚህ አብርሃምን የተቤዠው እግዚአብሔር ለያዕቆብ ቤት እንዲህ ይላል፤ “ያዕቆብ ከእንግዲህ ወዲያ አያፍርም፤ ፊቱም ከእንግዲህ አይለዋወጥም። በመካከላቸው የእጄ ሥራ የሆኑ፣ ልጆቻቸውን ሲያዩ፣ ስሜን ይቀድሳሉ፤ የያዕቆብን ቅዱስ ቅድስና ያውቃሉ፤ በእስራኤልም አምላክ ፊት በፍርሀት ይቆማሉ። በመንፈስ የሳቱ ያስተውላሉ፤ የሚያጕረመርሙም ምክር ይቀበላሉ።”

ኢሳይያስ 29:11-24 መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) (አማ54)

ራእዩም ሁሉ እንደ ታተመ መጽሐፍ ቃል ሆኖባችኋል፥ ማንበብንም ለሚያውቅ፦ ይህን አንብብ ብለው በሰጡት ጊዜ እርሱ፦ ታትሞአልና አልችልም ይላቸዋል፥ ደግሞም መጽሐፉን ማንበብን ለማያውቅ፦ ይህን አንብብ ብለው በሰጡት ጊዜ እርሱ፦ ማንበብ አላውቅም ይላቸዋል። ጌታም፦ ይህ ሕዝብ በአፉ ወደ እኔ ይቀርባልና፥ በከንፈሮቹም ያከብረኛልና፥ ልቡ ግን ከእኔ የራቀ ነውና፥ በሰዎች ሥርዓትና ትምህርት ብቻ ይፈራኛልና ስለዚህ፥ እነሆ፥ ድንቅ ነገርን በዚህ ሕዝብ መካከል፥ ድንቅ ነገርን ተአምራትንም፥ እንደ ገና አደርጋለሁ፥ የጥበበኞችም ጥበብ ትጠፋለች፥ የአስተዋዮችም ማስተዋል ትሰወራለች። ምክራቸውን ጥልቅ አድርገው ከእግዚአብሔር ለሚሰውሩ፥ ሥራቸውንም በጨለማ ውስጥ አድርገው፦ ማን ያየናል? ወይስ ማን ያውቀናል? ለሚሉ ወዮላቸው! ይህ የእናንተ ጠማምነት ነው፥ እንደ ሸክላ ሠሪ ጭቃ የምትቈጠሩ አይደላችሁምን? በውኑ ሥራ ሠሪውን፦ አልሠራኸኝም ይለዋልን? ወይስ የተደረገው አድራጊውን፦ አታስተውልም ይለዋልን? ሊባኖስ እንደ ፍሬያማ እርሻ ሊለወጥ ፍሬያማውም እርሻ እንደ ዱር ሊቆጠር ጥቂት ዘመን የቀረ አይደለምን? በዚያም ቀን ደንቆሮች የመጽሐፍን ቃል ይሰማሉ፥ የዕውሮችም ዓይኖች ከጭጋግና ከጨለማ ተለይተው ያያሉ። የዋሃን ደስታቸውን በእግዚአብሔር ያበዛሉ፥ በሰዎች መካከል ያሉ ችግረኞችም ሐሤትን በእስራኤል ቅዱስ ያደርጋሉ። ጨካኙ ሰው አልቆአልና፥ ፌዘኛውም ጠፍቷልና፥ ለኃጢአትም የደፈጡ ሁሉ ይቈረጣሉና፥ እነዚህም ሰውን በነገር በደለኛ የሚያደርጉ፥ በበርም ለሚገሥጸው አሽክላ የሚያኖሩ፥ ጻድቁንም በከንቱ ነገር የሚያስቱ ናቸው። ስለዚህ አብርሃምን የተቤዠ እግዚአብሔር ስለ ያዕቆብ ቤት እንዲህ ይላል፦ ያዕቆብ አሁን አያፍርም፥ ፊቱም አሁን አይለወጥም። ነገር ግን የእጄን ሥራ ልጆቹን በመካከሉ ባያቸው ጊዜ ስሜን ይቀድሳሉ፥ የያዕቆብንም ቅዱስ ይቀድሳሉ፥ የእስራኤልንም አምላክ ይፈራሉ። በመንፈስም የሳቱ ማስተዋልን ያውቃሉ፥ የሚያጕረመርሙ ትምህርትን ይቀበላሉ።

ኢሳይያስ 29:11-24 አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም (አማ05)

የትንቢት ራእይ ሁሉ ትርጒም ከእናንተ ተሰውሮ እንደ ታሸገ መጽሐፍ ይሆናል፤ ወደሚያነብ ሰው ወስዳችሁ “አንብብልን” ብላችሁ ብትጠይቁት እንኳ “ስለ ታሸገ ላነበው አልችልም” ይላችኋል። ማንበብ ወደማይችል ሰው ወስዳችሁ “አንብብልን” ብትሉት፥ “እኔ ማንበብ አልችልም” ይላችኋል። ጌታ እንዲህ ይላል፦ “ይህ ሕዝብ በአፉ ያከብረኛል፤ ልቡ ግን ከእኔ የራቀ ነው፤ እኔንም የሚያመልከኝ ሰው ሠራሽ ወግና ሥርዓትን እያስተማረ በከንቱ ነው። አስደናቂ ተአምርን አከታትዬ በማምጣት ይህ ሕዝብ እንዲገረም አደርገዋለሁ፤ የጥበበኞች ጥበብ ትሰወራለች፤ የአስተዋዮችም ማስተዋል ትረሳለች።” ዕቅዳቸውን ከእግዚአብሔር ለመደበቅ ወደ ጥልቅ ቦታ ለሚሄዱ በጨለማ የሠሩትንም ሥራ “ማን ያይብናል? ማን ያውቅብናል?” ለሚሉ ሰዎች ወዮላቸው! እናንተ ሁሉን ነገር ትገለባብጣላችሁ። ሸክላ ሠሪው ከሸክላው አይበልጥምን? አንድ የተሠራ ሥራ ሠሪውን “አንተ አልሠራኸኝም” ይለዋልን? ወይስ ደግሞ የሸክላ ዕቃ ሸክላ ሠሪውን “ሥራህን አታውቅም” ይለዋልን? በጥቂት ጊዜ ውስጥ የሊባኖስ ጫካ የእርሻ ቦታ ይሆናል፤ የእርሻው ቦታ ወደ ጫካነት ይለወጣል። ደንቆሮዎች የሚነበብላቸውን መጽሐፍ መስማት የሚችሉበት ጊዜና በጨለማ የሚኖሩ ዕውሮችም ዐይኖቻቸው በርተው የሚያዩበት ጊዜ ይመጣል። ትሑታንና ችግረኞች በእስራኤል ቅዱስ በእግዚአብሔር ይደሰታሉ። ጨካኞችና ፌዘኞች ይጠፋሉ፤ ክፉ አድራጊዎችም ሁሉ ይደመሰሳሉ። ሰውን በነገር ወንጀለኛ የሚያደርጉ፥ ተከሳሽንም በፍርድ ሸንጎ የሚያጠምዱ፥ በሐሰተኛ ምስክር ንጹሕ ሰው ፍትሕ እንዳያገኝ በሐሰት የሚመሰክሩትን ሁሉ እግዚአብሔር ያጠፋቸዋል። ስለዚህ አብርሃምን ከችግሩ ያዳነ እግዚአብሔር ለእስራኤል ሕዝብ እንዲህ ይላል፦ “ሕዝቤ ሆይ! ከእንግዲህ ወዲህ ውርደትና ኀፍረት አይደርስባችሁም። የእጄ ሥራ የሆኑትን ልጆቻቸውን በመካከላቸው ባዩ ጊዜ ስሜን ይቀድሳሉ፤ የእስራኤልን ቅዱስ ያከብራሉ፤ በእስራኤልም አምላክ ፊት በፍርሃት ይቆማሉ። በመንፈስም የሚሳሳቱ ማስተዋልን ይገበያሉ፤ ዘወትር የሚያጒረመርሙ ትምህርትን ይቀበላሉ።”

ኢሳይያስ 29:11-24 መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) (መቅካእኤ)

ይህ ሁሉ ራእይ እንደ ታተመ የመጽሐፍ ቃል ሆኖባችኋል፤ ማንበብንም ለሚያውቅ፦ “ይህን አንብብ” ብለው ባዘዙት ጊዜ እርሱ፦ “ታሽጓልና አልችልም” ይላቸዋል፤ ደግሞም መጽሐፉን ማንበብን ለማያውቅ፦ “ይህን አንብብ” ብለው በሰጡት ጊዜ እርሱ፦ “ማንበብ አላውቅም” ይላቸዋል። ጌታም፦ ይህ ሕዝብ በአፉ ወደ እኔ ይቀርባል፥ በከንፈሮቹም ያከብረኛል፥ ልቡ ግን ከእኔ የራቀ ነው፤ በሰዎች ሥርዓትና ትምህርት ብቻ ይፈራኛል። ስለዚህ፥ እነሆ፥ ድንቅ ነገርን በዚህ ሕዝብ መካከል፥ አስደማሚ ነገርን ተአምራትንም እንደገና አደርጋለሁ፤ የጥበበኞችም ጥበብ ትጠፋለች፥ የአስተዋዮችም ማስተዋል ትሰወራለች። ምክራቸውን ጥልቅ አድርገው ከጌታ ለሚሰውሩ፥ ሥራቸውንም በጨለማ ውስጥ አድርገው፦ “ማን ያየናል? ወይስ ማን ያውቀናል?” ለሚሉ ወዮላቸው! ይህ የእናንተ ጠማምነት ነው፤ እንደ ሸክላ ሠሪ ጭቃ የምትቈጠሩ አይደላችሁምን? በውኑ ሥራ ሠሪውን፦ “አልሠራኸኝም” ይለዋልን? ወይስ የተደረገው አድራጊውን፦ “አታስተውልም” ይለዋልን? ሊባኖስ እንደ ፍሬያማ እርሻ ሊለወጥ ፍሬያማውም እርሻ እንደ ዱር ሊቆጠር ጥቂት ዘመን ቀርቶት የለምን? በዚያም ቀን ደንቆሮዎች የመጽሐፍን ቃል ይሰማሉ፥ የዕውሮችም ዐይኖች ጭጋግና ጨለማው ተገፎላቸው ያያሉ። የዋሃን ደስታቸውን በጌታ ያበዛሉ፥ በሰዎች መካከል ያሉ ችግረኞችም ሐሤትን በእስራኤል ቅዱስ ያደርጋሉ። ጨካኙ ሰው አልቆአልና፥ ፌዘኛውም ጠፍቷልና፥ ለኃጢአትም ያደፈጡ ሁሉ ይቈረጣሉ፤ እነርሱም ሰውን በነገር በደለኛ የሚያደርጉ፥ በበርም ለሚገሥጸው አሽክላ የሚያኖሩ፥ ጻድቁንም በከንቱ ነገር የሚያስቱ ናቸው። ስለዚህ አብርሃምን የተቤዠ ጌታ ስለ ያዕቆብ ቤት እንዲህ ይላል፦ ያዕቆብ አሁን አያፍርም፥ ፊቱም አሁን አይለወጥም። ነገር ግን የእጄን ሥራ ልጆቹን በመካከሉ ባያቸው ጊዜ ስሜን ይቀድሳሉ፤ የያዕቆብንም ቅዱስ ይቀድሳሉ፥ የእስራኤልንም አምላክ ይፈራሉ። በመንፈስም የሳቱ ወደ ማስተዋል ይደርሳሉ፤ የሚያጉረመርሙም ምክርን ይቀበላሉ።