የYouVersion አርማ
የፍለጋ አዶ

ኢሳይያስ 26:1-11

ኢሳይያስ 26:1-11 አዲሱ መደበኛ ትርጒም (NASV)

በዚያ ቀን ይህ መዝሙር በይሁዳ ምድር ይዘመራል፤ ብርቱ ከተማ አለችን፤ አምላካችን ቅጥሮቿንና ምሽጎቿን፣ ለድነት አድርጓል። በእምነቱ የጸና ጻድቅ የሆነ ሕዝብ ይገባ ዘንድ፣ በሮቿን ክፈቱ። በአንተ ላይ ታምናለችና፣ በአንተ የምትደገፈውን ነፍስ ፈጽመህ በሰላም ትጠብቃታለህ። በእግዚአብሔር ለዘላለም ታመኑ፤ ጌታ እግዚአብሔር የዘላለም ዐለት ነውና። በከፍታ የሚኖሩትን ዝቅ ዝቅ ያደርጋል፤ ከፍ ከፍ ያለችውን ከተማ ያዋርዳል፤ ወደ ምድር ይጥላታል፤ ከትቢያም ጋራ ይደባልቃታል። እግር፣ የተጨቋኞች እግር፣ የድኾች ኮቴ ይረግጣታል። የጻድቃን መንገድ ቅን ናት፤ አንተ ቅን የሆንህ ሆይ፤ የጻድቃንን መንገድ ታቃናለህ። እግዚአብሔር ሆይ፤ በሕግህ ጐዳና በመሄድ፣ አንተን ተስፋ አድርገናል፤ ስምህና ዝናህ፣ የልባችን ምኞት ነው። ነፍሴ በሌሊት ትናፍቅሃለች፤ መንፈሴም በውስጤ ትፈልግሃለች። ፍርድህ ወደ ምድር በመጣ ጊዜ፣ የዓለም ሕዝቦች ጽድቅን ይማራሉ። ክፉዎች ርኅራኄ ቢደረግላቸው እንኳ፣ ጽድቅን አይማሩም፤ በቅንነት ምድር እንኳ ክፋትን ያደርጋሉ፤ የእግዚአብሔርንም ግርማ አያስተውሉም። እግዚአብሔር ሆይ፤ ክንድህ ከፍ ከፍ ብሏል፤ እነርሱ ግን አላስተዋሉም፤ ለሕዝብህ ያለህን ቅናት ይዩ፤ ይፈሩም፤ ለጠላቶችህም የተዘጋጀው እሳት ይብላቸው።

ኢሳይያስ 26:1-11 የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) (አማ2000)

በዚ​ያም ቀን ይህን ቅኔ በይ​ሁዳ ምድር ይዘ​ም​ራሉ፤ እነ​ሆም፥ የጸ​ና​ችና የም​ታ​ድን፥ ቅጥ​ር​ንና ምሽ​ግ​ንም የም​ታ​ደ​ርግ ከተማ አለ​ችን። ፍት​ሕን የሚ​ጠ​ብ​ቅና ጽድ​ቅን የሚ​ያ​ደ​ርግ ሕዝብ ይገባ ዘንድ በሮ​ችን ክፈቱ። በአ​ንተ ላይ ታም​ና​ለ​ችና በአ​ንተ የም​ት​ደ​ገፍ ነፍ​ስን ፈጽ​መህ በሰ​ላም ትጠ​ብ​ቃ​ታ​ለህ። ጌታ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር የዘ​ለ​ዓ​ለም አንባ ነውና ለዘ​ለ​ዓ​ለም በእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ታመኑ። በከ​ፍታ የሚ​ኖ​ሩ​ትን ሰዎች ዝቅ ታደ​ር​ጋ​ለህ፤ የተ​መ​ሸ​ጉ​ት​ንም ከተ​ሞች ትጥ​ላ​ለህ፤ እስከ ምድ​ርም ድረስ ታወ​ር​ዳ​ቸ​ዋ​ለህ። የየ​ዋ​ሃ​ንና የት​ሑ​ታን እግ​ሮች ይረ​ግ​ጡ​አ​ቸ​ዋል። የጻ​ድ​ቃን መን​ገድ የቀና ትሆ​ና​ለች፤ የቅ​ኖ​ችም መን​ገድ ትጠ​ረ​ጋ​ለች። የእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር መን​ገድ የቀና ነው፤ በቅ​ዱስ ስሙም ታመን፤ ነፍ​ሳ​ችን የተ​መ​ኘ​ች​ው​ንም አገ​ኘን። አቤቱ፥ አም​ላኬ ሆይ፥ ትእ​ዛ​ዝህ በም​ድር ላይ ብር​ሃን ነውና ነፍሴ በሌ​ሊት ወደ አንተ ትገ​ሠ​ግ​ሣ​ለች። በም​ድር የም​ት​ኖ​ሩም ጽድቅ መሥ​ራ​ትን ተማሩ። በም​ድር ጽድ​ቅን የማ​ይ​ማ​ርና መል​ካ​ምን የማ​ያ​ደ​ርግ ኃጥእ አል​ቆ​አ​ልና፥ የእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርን ክብር እን​ዳ​ያይ ኀጢ​አ​ተ​ኛን ያስ​ወ​ግ​ዱ​ታል። አቤቱ፥ ከፍ ያለች ክን​ድ​ህን አላ​ወ​ቁም፤ ካወቁ ግን ያፍ​ራሉ። አላ​ዋ​ቆች ሰዎ​ችን ቅን​አት ያዛ​ቸው፤ አሁ​ንም እሳት ጠላ​ቶ​ችን ትበ​ላ​ለች።

ኢሳይያስ 26:1-11 አዲሱ መደበኛ ትርጒም (NASV)

በዚያ ቀን ይህ መዝሙር በይሁዳ ምድር ይዘመራል፤ ብርቱ ከተማ አለችን፤ አምላካችን ቅጥሮቿንና ምሽጎቿን፣ ለድነት አድርጓል። በእምነቱ የጸና ጻድቅ የሆነ ሕዝብ ይገባ ዘንድ፣ በሮቿን ክፈቱ። በአንተ ላይ ታምናለችና፣ በአንተ የምትደገፈውን ነፍስ ፈጽመህ በሰላም ትጠብቃታለህ። በእግዚአብሔር ለዘላለም ታመኑ፤ ጌታ እግዚአብሔር የዘላለም ዐለት ነውና። በከፍታ የሚኖሩትን ዝቅ ዝቅ ያደርጋል፤ ከፍ ከፍ ያለችውን ከተማ ያዋርዳል፤ ወደ ምድር ይጥላታል፤ ከትቢያም ጋራ ይደባልቃታል። እግር፣ የተጨቋኞች እግር፣ የድኾች ኮቴ ይረግጣታል። የጻድቃን መንገድ ቅን ናት፤ አንተ ቅን የሆንህ ሆይ፤ የጻድቃንን መንገድ ታቃናለህ። እግዚአብሔር ሆይ፤ በሕግህ ጐዳና በመሄድ፣ አንተን ተስፋ አድርገናል፤ ስምህና ዝናህ፣ የልባችን ምኞት ነው። ነፍሴ በሌሊት ትናፍቅሃለች፤ መንፈሴም በውስጤ ትፈልግሃለች። ፍርድህ ወደ ምድር በመጣ ጊዜ፣ የዓለም ሕዝቦች ጽድቅን ይማራሉ። ክፉዎች ርኅራኄ ቢደረግላቸው እንኳ፣ ጽድቅን አይማሩም፤ በቅንነት ምድር እንኳ ክፋትን ያደርጋሉ፤ የእግዚአብሔርንም ግርማ አያስተውሉም። እግዚአብሔር ሆይ፤ ክንድህ ከፍ ከፍ ብሏል፤ እነርሱ ግን አላስተዋሉም፤ ለሕዝብህ ያለህን ቅናት ይዩ፤ ይፈሩም፤ ለጠላቶችህም የተዘጋጀው እሳት ይብላቸው።

ኢሳይያስ 26:1-11 መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) (አማ54)

በዚያም ቀን ይህ ቅኔ በይሁዳ ምድር ይዘመራል፦ የጸናች ከተማ አለችን፥ ለቅጥርና ለምሽግ መድኃኒትን ያኖርባታል። እውነትን የሚጠብቅ ጻድቅ ሕዝብ ይገባ ዘንድ በሮችን ክፈቱ። በአንተ ላይ ታምናለችና በአንተ ለምትደገፍ ነፍስ ፈጽመህ በሰላም ትጠብቃታለህ። ጌታ እግዚአብሔር የዘላለም አምባ ነውና ለዘላለም በእግዚአብሔር ታመኑ። በከፍታ የሚኖሩትን ሰዎች ዝቅ ያደርጋል፥ ከፍ ያለችውን ከተማ ያዋርዳል፥ እስከ መሬትም ድረስ ያወርዳታል፥ እስከ አፈርም ድረስ ይጥላታል። እግር፥ የድሀ እግርም የችግረኛም አረጋገጥ፥ ትረግጣታለች። የጻድቃን መንገድ ቅን ናት፥ አንተ ቅን የሆንህ የጻድቃንን መንገድ ታቀናለህ። አቤቱ፥ በፍርድህ መንገድ ተስፋ አድርገንሃል፥ ስምህንም መታሰቢያህም የነፍሳችን ምኞት ነው። ፍርድህን በምድር ባደረግህ ጊዜ በዓለም የሚኖሩ ጽድቅን ይማራሉና ነፍሴ በሌሊት ትናፍቅሃለች፥ መንፈሴም በውስጤ ወደ አንተ ትገሠግሣለች። ለኃጢአተኛ ሞገስ ቢደረግለት ጽድቅን አይማርም፥ በቅኖች ምድር ክፉን ነገር ያደርጋል፥ የእግዚአብሔርንም ግርማ አያይም። አቤቱ፥ እጅህ ከፍ ከፍ አለች አላዩምም፥ ነገር ግን በሕዝብህ ላይ ያለህን ቅንዓት አይተው ያፍራሉ፥ እሳትም ጠላቶችህን ትበላለች።

ኢሳይያስ 26:1-11 አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም (አማ05)

በዚያን ጊዜ በይሁዳ ምድር የሚከተለው መዝሙር ይዘመራል፦ ጠንካራ ከተማ አለን፤ እንደ ቅጥርና እንደ ምሽግ የጸና መዳኛም አድርጎላታል። እምነቱን የጠበቀ እውነተኛ ሕዝብ እንዲገባ የከተማይቱን በሮች ክፈቱ፤ ጌታ ሆይ! በእምነታቸው ለጸኑ ሰዎች ፍጹም ሰላምን ትሰጣቸዋለህ። ለዘለዓለሙም በእግዚአብሔር ታምናችሁ ኑሩ፤ ጌታ እግዚአብሔር የዘለዓለም መጠጊያ አምባችን ነውና። በከፍተኛ ቦታ ላይ የሚኖሩትን ሰዎች ያዋርዳል፤ ከፍ ከፍ ያለችውን ከተማ ያፈራርሳታል። አፈራርሶም ከትቢያ ጋር ይቀላቅላታል። ጭቊኖች ይረማመዱባታል፤ በእግራቸውም ይረጋግጡአታል። አምላክ ሆይ! አንተ የጻድቃንን ጎዳና ታስተካክላለህ፤ መንገዳቸውም እንዲለሰልስ ታደርጋለህ። አምላክ ሆይ፥ ሕግህን እየጠበቅን በአንተ ተስፋ እናደርጋለን። የልባችንም ምኞት የአንተ ገናናነት በሕዝቦች ዘንድ እንዲታወቅ ማድረግ ነው። ፍርድህ በምድር ላይ በሚሰፍን ጊዜ የዓለም ሕዝቦች እውነትን ይማራሉ። ነፍሴ በሌሊት አንተን ትናፍቃለች፤ በውስጤም ያለው መንፈስ አንተን ትሻለች። ክፉ ሰዎች ቸርነት ብታደርግላቸው እንኳ መልካም መሥራትን አይማሩም፤ በዚህ ጽድቅ በሰፈነበት ምድር እያሉ እንኳ ክፋት ከማድረግ አይቈጠቡም፤ ታላቅነትህንም አይገነዘቡም። አምላክ ሆይ፥ ክንድህ ለመቅጣት ተነሥቶአል፤ አንተን የሚጠሉ ሰዎች አያዩትም፤ ለሕዝብህ ምን ያኽል ቅናት እንዳለህ አይተው ይፈሩ፤ ለጠላቶችህ ባዘጋጀኸው ቅጣት ይጥፉ።

ኢሳይያስ 26:1-11 መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) (መቅካእኤ)

በዚያም ቀን ይህ መዝሙር በይሁዳ ምድር ይዘመራል፦ የጸናች ከተማ አለችን፤ ቅጥሯንና ምሽጓን ለደኅንነታችን አኑሮታል። በእምነቱ የጸና ጻድቅ ሕዝብ ይገባ ዘንድ በሮችን ክፈቱ። በአንተ ለምትደገፍ ነፍስ በአንተ ላይ ታምናለችና በሰላም ትጠብቃታለህ። ጌታ እግዚአብሔር የዘለዓለም ዐለት ነውና ለዘለዓለም በጌታ ታመኑ። በከፍታ የሚኖሩትን ሰዎች ዝቅ ያደርጋል፤ ከፍ ያለችውን ከተማ ያዋርዳል፥ እስከ መሬትም ድረስ ያወርዳታል፥ እስከ ትቢያም ድረስ ይጥላታል። እግር፥ የድሀ እግርም የችግረኛም ኮቴ፥ ትረግጣታለች። የጻድቃን መንገድ ቅን ናት፤ አንተ ቅን የሆንክ የጻድቃንን መንገድ ታቀናለህ። አቤቱ ጌታ፥ በፍርድህ መንገድ ተስፋ አድርገንሃል፥ ስምህም መታሰቢያህም የነፍሳችን ምኞት ነው። ፍርድህን በምድር ላይ በፈረድክ ጊዜ በዓለም የሚኖሩ ጽድቅን ይማራሉና ነፍሴ በሌሊት ትናፍቅሃለች፥ መንፈሴም በውስጤ ወደ አንተ ትገሠግሣለች። ክፉዎች እድል ቢሰጣቸው እንኳን ጽድቅን አይማሩም፤ በቅኖች ምድር ክፉን ነገር ያደርጋሉ፥ የጌታንም ግርማ አያዩም። አቤቱ ጌታ፥ እጅህ ከፍ ከፍ አለች አላዩም፤ ነገር ግን በሕዝብህ ላይ ያለህን ቅንዓት አይተው ያፍራሉ፤ እሳትም ጠላቶችህን ትበላለች።