በዚያም ቀን ይህን ቅኔ በይሁዳ ምድር ይዘምራሉ፤ እነሆም፥ የጸናችና የምታድን፥ ቅጥርንና ምሽግንም የምታደርግ ከተማ አለችን። ፍትሕን የሚጠብቅና ጽድቅን የሚያደርግ ሕዝብ ይገባ ዘንድ በሮችን ክፈቱ። በአንተ ላይ ታምናለችና በአንተ የምትደገፍ ነፍስን ፈጽመህ በሰላም ትጠብቃታለህ። ጌታ እግዚአብሔር የዘለዓለም አንባ ነውና ለዘለዓለም በእግዚአብሔር ታመኑ። በከፍታ የሚኖሩትን ሰዎች ዝቅ ታደርጋለህ፤ የተመሸጉትንም ከተሞች ትጥላለህ፤ እስከ ምድርም ድረስ ታወርዳቸዋለህ። የየዋሃንና የትሑታን እግሮች ይረግጡአቸዋል። የጻድቃን መንገድ የቀና ትሆናለች፤ የቅኖችም መንገድ ትጠረጋለች። የእግዚአብሔር መንገድ የቀና ነው፤ በቅዱስ ስሙም ታመን፤ ነፍሳችን የተመኘችውንም አገኘን። አቤቱ፥ አምላኬ ሆይ፥ ትእዛዝህ በምድር ላይ ብርሃን ነውና ነፍሴ በሌሊት ወደ አንተ ትገሠግሣለች። በምድር የምትኖሩም ጽድቅ መሥራትን ተማሩ። በምድር ጽድቅን የማይማርና መልካምን የማያደርግ ኃጥእ አልቆአልና፥ የእግዚአብሔርን ክብር እንዳያይ ኀጢአተኛን ያስወግዱታል። አቤቱ፥ ከፍ ያለች ክንድህን አላወቁም፤ ካወቁ ግን ያፍራሉ። አላዋቆች ሰዎችን ቅንአት ያዛቸው፤ አሁንም እሳት ጠላቶችን ትበላለች።
ትንቢተ ኢሳይያስ 26 ያንብቡ
Share
ሁሉንም ሥሪቶች ያነጻጽሩ: ትንቢተ ኢሳይያስ 26:1-11
ጥቅሶችን ያስቀምጡ፣ ያለበይነመረብ ያንብቡ፣ አጫጭር የትምህርት ቪዲዮዎችን ይመልከቱ እና ሌሎችም!
Home
Bible
Plans
Videos