በዚያም ቀን ይህ ቅኔ በይሁዳ ምድር ይዘመራል፦ የጸናች ከተማ አለችን፥ ለቅጥርና ለምሽግ መድኃኒትን ያኖርባታል። እውነትን የሚጠብቅ ጻድቅ ሕዝብ ይገባ ዘንድ በሮችን ክፈቱ። በአንተ ላይ ታምናለችና በአንተ ለምትደገፍ ነፍስ ፈጽመህ በሰላም ትጠብቃታለህ። ጌታ እግዚአብሔር የዘላለም አምባ ነውና ለዘላለም በእግዚአብሔር ታመኑ። በከፍታ የሚኖሩትን ሰዎች ዝቅ ያደርጋል፥ ከፍ ያለችውን ከተማ ያዋርዳል፥ እስከ መሬትም ድረስ ያወርዳታል፥ እስከ አፈርም ድረስ ይጥላታል። እግር፥ የድሀ እግርም የችግረኛም አረጋገጥ፥ ትረግጣታለች። የጻድቃን መንገድ ቅን ናት፥ አንተ ቅን የሆንህ የጻድቃንን መንገድ ታቀናለህ። አቤቱ፥ በፍርድህ መንገድ ተስፋ አድርገንሃል፥ ስምህንም መታሰቢያህም የነፍሳችን ምኞት ነው። ፍርድህን በምድር ባደረግህ ጊዜ በዓለም የሚኖሩ ጽድቅን ይማራሉና ነፍሴ በሌሊት ትናፍቅሃለች፥ መንፈሴም በውስጤ ወደ አንተ ትገሠግሣለች። ለኃጢአተኛ ሞገስ ቢደረግለት ጽድቅን አይማርም፥ በቅኖች ምድር ክፉን ነገር ያደርጋል፥ የእግዚአብሔርንም ግርማ አያይም። አቤቱ፥ እጅህ ከፍ ከፍ አለች አላዩምም፥ ነገር ግን በሕዝብህ ላይ ያለህን ቅንዓት አይተው ያፍራሉ፥ እሳትም ጠላቶችህን ትበላለች።
ትንቢተ ኢሳይያስ 26 ያንብቡ
ያጋሩ
ሁሉንም ሥሪቶች ያነጻጽሩ: ትንቢተ ኢሳይያስ 26:1-11
ጥቅሶችን ያስቀምጡ፣ ያለበይነመረብ ያንብቡ፣ አጫጭር የትምህርት ቪዲዮዎችን ይመልከቱ እና ሌሎችም!
ቤት
መጽሐፍ ቅዱስ
እቅዶች
ቪዲዮዎች