የYouVersion አርማ
የፍለጋ አዶ

ዘፍጥረት 47:1-12

ዘፍጥረት 47:1-12 አዲሱ መደበኛ ትርጒም (NASV)

ዮሴፍም ወደ ፈርዖን ሄዶ፣ “አባቴና ወንድሞቼ በጎቻቸውን፣ ፍየሎቻቸውን እንዲሁም ያላቸውን ሁሉ ይዘው ከከነዓን አገር መጥተው በጌሤም ሰፍረዋል” አለው። ከወንድሞቹም መካከል ዐምስቱን መርጦ፣ ፈርዖን ፊት አቀረባቸው። ፈርዖን የዮሴፍን ወንድሞች፣ “ሥራችሁ ምንድን ነው?” ሲል ጠየቃቸው። እነርሱም ፈርዖንን፣ “እኛ አገልጋዮችህ ልክ እንደ አባቶቻችን ከብት አርቢዎች ነን” አሉት፤ ደግሞም፣ “በከነዓን ምድር ራቡ እጅግ የጸና በመሆኑ በጎችና ፍየሎች የሚሰማሩበት በማጣታቸው፣ ለጊዜው እዚህ ለመኖር መጥተናል፤ አሁንም ባሮችህ በጌሤም ምድር እንድንኖር እንድትፈቅድልን እንለምንሃለን” አሉት። ፈርዖንም ዮሴፍን እንዲህ አለው፤ “አባትህና ወንድሞችህ ወደ አንተ መጥተዋል፤ የግብጽ ምድር እንደ ሆነ በእጅህ ነው፤ አባትህንና ወንድሞችህን ምርጥ በሆነው ምድር አስፍራቸው፤ በጌሤም ይኑሩ። ከመካከላቸው ልዩ ችሎታ ያላቸው መኖራቸውን የምታውቅ ከሆነ፣ የከብቶቼ ኀላፊዎች አድርጋቸው።” ከዚህ በኋላ ዮሴፍ አባቱን ያዕቆብን ቤተ መንግሥት አስገብቶ በፈርዖን ፊት አቀረበው፤ ያዕቆብም ፈርዖንን ከመረቀው በኋላ ፈርዖን፣ “ለመሆኑ ዕድሜህ ምን ያህል ነው?” ሲል ያዕቆብን ጠየቀው። ያዕቆብም ለፈርዖን፣ “በምድር ላይ በእንግድነት ያሳለፍሁት ዘመን 130 ዓመት ነው፤ ይህም አባቶቼ በእንግድነት ከኖሩበት ዘመን ጋራ ሲነጻጸር ዐጭር ነው፤ ችግር የበዛበትም ነበር” ሲል መለሰለት። ከዚያም ያዕቆብ ፈርዖንን መርቆ፣ ተሰናብቶት ወጣ። ዮሴፍም አባቱንና ወንድሞቹን በግብጽ እንዲኖሩ አደረገ፤ ፈርዖን በሰጠውም ትእዛዝ መሠረት ምርጥ ከሆነው ምድር ራምሴን በርስትነት ሰጣቸው። ዮሴፍም ለአባቱ፣ ለወንድሞቹና ለመላው የአባቱ ቤተ ሰዎች በልጆቻቸው ቍጥር ልክ ቀለብ እንዲሰፈርላቸው አደረገ።

ዘፍጥረት 47:1-12 የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) (አማ2000)

ዮሴ​ፍም ገባ፤ ለፈ​ር​ዖ​ንም እን​ዲህ ብሎ ነገ​ረው፥ “አባ​ቴና ወን​ድ​ሞች በጎ​ቻ​ቸ​ውም፥ ላሞ​ቻ​ቸ​ውም፥ ያላ​ቸ​ውም ሁሉ ከከ​ነ​ዓን ምድር መጡ፤ እነ​ር​ሱም እነሆ፥ ወደ ጌሤም ምድር ደረሱ።” ከወ​ን​ድ​ሞ​ቹም አም​ስት ሰዎ​ችን ወስዶ በፈ​ር​ዖን ፊት አቆ​ማ​ቸው። ፈር​ዖ​ንም የዮ​ሴ​ፍን ወን​ድ​ሞች፥ “ሥራ​ችሁ ምን​ድን ነው?” አላ​ቸው። እነ​ር​ሱም ፈር​ዖ​ንን፥ “እኛ አገ​ል​ጋ​ዮ​ችህ፥ አባ​ታ​ች​ንም ከብት ጠባ​ቂ​ዎች ነን” አሉት። ፈር​ዖ​ን​ንም እን​ዲህ አሉት፥ “በም​ድር ልን​ቀ​መጥ በእ​ን​ግ​ድ​ነት መጣን፤ የአ​ገ​ል​ጋ​ዮ​ችህ በጎች የሚ​ሰ​ማ​ሩ​በት ስፍራ የለ​ምና፤ ራብም በከ​ነ​ዓን ምድር እጅግ ጸን​ቶ​አ​ልና፤ አሁ​ንም አገ​ል​ጋ​ዮ​ችህ በጌ​ሤም ምድር እን​ቀ​መጥ።” ፈር​ዖ​ንም ዮሴ​ፍን እን​ዲህ ብሎ ተና​ገ​ረው፥ “አባ​ት​ህና ወን​ድ​ሞ​ችህ መጥ​ተ​ው​ል​ሃል፤ እነሆ፥ የግ​ብፅ ምድር በፊ​ትህ ናት፤ በመ​ል​ካሙ ምድር አባ​ት​ህ​ንና ወን​ድ​ሞ​ች​ህን አኑ​ራ​ቸው፤ ከእ​ነ​ር​ሱም ውስጥ ዕው​ቀት ያላ​ቸ​ውን ሰዎች ታውቅ እን​ደ​ሆነ በእ​ን​ስ​ሶች ጠባ​ቂ​ዎች ላይ አለ​ቆች አድ​ር​ጋ​ቸው።” ዮሴ​ፍም ያዕ​ቆ​ብን አባ​ቱን አስ​ገ​ብቶ በፈ​ር​ዖን ፊት አቆ​መው፤ ያዕ​ቆ​ብም ፈር​ዖ​ንን ባረ​ከው። ፈር​ዖ​ንም ያዕ​ቆ​ብን፥ “የኖ​ር​ኸው ዘመን ስንት ነው?” አለው። ያዕ​ቆ​ብም ለፈ​ር​ዖን አለው፥ “በእ​ን​ግ​ድ​ነት የኖ​ር​ሁት የሕ​ይ​ወቴ ዘመ​ንስ መቶ ሠላሳ ዓመት ነው፤ የሕ​ይ​ወ​ቴም ዘመ​ኖች ጥቂ​ትም ክፉም ሆኑ​ብኝ፤ አባ​ቶች በእ​ን​ግ​ድ​ነት የተ​ቀ​መ​ጡ​በ​ት​ንም ዘመን አያ​ህ​ሉም።” ያዕ​ቆ​ብም ፈር​ዖ​ንን ባረ​ከው፤ ከፈ​ር​ዖ​ንም ፊት ወጣ። ዮሴ​ፍም አባ​ቱ​ንና ወን​ድ​ሞ​ቹን አኖረ፤ ፈር​ዖን እን​ዳ​ዘ​ዘ​ላ​ቸ​ውም በግ​ብፅ ምድር በተ​ሻ​ለ​ችው በራ​ምሴ ምድር ርስ​ትን ሰጣ​ቸው። ዮሴ​ፍም ለአ​ባ​ቱና ለወ​ን​ድ​ሞቹ፥ ለአ​ባ​ቱም ቤተ ሰዎች ሁሉ ለእ​ያ​ን​ዳ​ንዱ ሰው እየ​ሰ​ፈረ እህ​ልን ለም​ግብ ይሰ​ጣ​ቸው ነበር።

ዘፍጥረት 47:1-12 አዲሱ መደበኛ ትርጒም (NASV)

ዮሴፍም ወደ ፈርዖን ሄዶ፣ “አባቴና ወንድሞቼ በጎቻቸውን፣ ፍየሎቻቸውን እንዲሁም ያላቸውን ሁሉ ይዘው ከከነዓን አገር መጥተው በጌሤም ሰፍረዋል” አለው። ከወንድሞቹም መካከል ዐምስቱን መርጦ፣ ፈርዖን ፊት አቀረባቸው። ፈርዖን የዮሴፍን ወንድሞች፣ “ሥራችሁ ምንድን ነው?” ሲል ጠየቃቸው። እነርሱም ፈርዖንን፣ “እኛ አገልጋዮችህ ልክ እንደ አባቶቻችን ከብት አርቢዎች ነን” አሉት፤ ደግሞም፣ “በከነዓን ምድር ራቡ እጅግ የጸና በመሆኑ በጎችና ፍየሎች የሚሰማሩበት በማጣታቸው፣ ለጊዜው እዚህ ለመኖር መጥተናል፤ አሁንም ባሮችህ በጌሤም ምድር እንድንኖር እንድትፈቅድልን እንለምንሃለን” አሉት። ፈርዖንም ዮሴፍን እንዲህ አለው፤ “አባትህና ወንድሞችህ ወደ አንተ መጥተዋል፤ የግብጽ ምድር እንደ ሆነ በእጅህ ነው፤ አባትህንና ወንድሞችህን ምርጥ በሆነው ምድር አስፍራቸው፤ በጌሤም ይኑሩ። ከመካከላቸው ልዩ ችሎታ ያላቸው መኖራቸውን የምታውቅ ከሆነ፣ የከብቶቼ ኀላፊዎች አድርጋቸው።” ከዚህ በኋላ ዮሴፍ አባቱን ያዕቆብን ቤተ መንግሥት አስገብቶ በፈርዖን ፊት አቀረበው፤ ያዕቆብም ፈርዖንን ከመረቀው በኋላ ፈርዖን፣ “ለመሆኑ ዕድሜህ ምን ያህል ነው?” ሲል ያዕቆብን ጠየቀው። ያዕቆብም ለፈርዖን፣ “በምድር ላይ በእንግድነት ያሳለፍሁት ዘመን 130 ዓመት ነው፤ ይህም አባቶቼ በእንግድነት ከኖሩበት ዘመን ጋራ ሲነጻጸር ዐጭር ነው፤ ችግር የበዛበትም ነበር” ሲል መለሰለት። ከዚያም ያዕቆብ ፈርዖንን መርቆ፣ ተሰናብቶት ወጣ። ዮሴፍም አባቱንና ወንድሞቹን በግብጽ እንዲኖሩ አደረገ፤ ፈርዖን በሰጠውም ትእዛዝ መሠረት ምርጥ ከሆነው ምድር ራምሴን በርስትነት ሰጣቸው። ዮሴፍም ለአባቱ፣ ለወንድሞቹና ለመላው የአባቱ ቤተ ሰዎች በልጆቻቸው ቍጥር ልክ ቀለብ እንዲሰፈርላቸው አደረገ።

ዘፍጥረት 47:1-12 መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) (አማ54)

ዮሴፍም ገባ ለፈርዖንም ነገረው እንዲህ ብሎ፦ አባቴና ወንድሞቼ በጎቻቸውም ላሞቻቸውም ያላቸውም ሁሉ ከከነዓን ምድር ወጡ እነርሱም እነሆ በጌሤም ምድር ናቸው። ከወንድሞቹም አምስት ሰዎች ወስዶ በፈርዖን ፊት አቆማቸው። ፈርዖንም ወንድሞቹም፦ ሥራችሁ ምንድር ነው? አላቸው። እነርሱም ፈርዖንን፦ እኛ ባሪያዎችን እኝም አባቶቻችንም በግ አርቢዎች ነን አሉት። ፈርዖንንም እንዲህ አሉት፦ በምድር ልንቀመጥ በእንግድነት መጣን የባርያዎችህ በጎች የሚስማሩበት ስፍራ የለምና ራብ በከነዓን ምድር እጅግ ጸንቶቸልና አሁንም ባርያዎችህ በጌሤም ምድር እንድንቀመጥ እንለምንሃለን። ፈርዖንም ዮሴፍን ተናገረው እንዲህ ብሎ፦ አባትህና ወንድሞችን መጥተውልሃል የግብፅ ምድር በፊትህ ናት በመልካሙ ምድር አባትህንና ወንድሞችህን አኑራቸው በጌሤም ምድር ይኑሩ ከእነርሱም ውስጥ እውቀት ያላቸውን ሰዎች ታውቅ እንደ ሆነ በእንስሶቼ ላይ አለቆች አድርጋቸው ዮሴፍም ያዕቆብን አባቱን አስገብቶ በፈርዖን ፊት አቆመው ያዕቆብም ፈርዖንን ባረከው። ፈርዖንም ያዕቆብን፦ የዕድሜህ ዘመን ስንት ዓመት ነው? አለው ያዕቆብም ለፈርዖን አለው፦ የእንግድነቴ ዘመን መቶ ሠላሳ ዓመት ነው የሕይወቴ ዘመኖች ጥቂትም ክፋም ሆኑብኝ አባቶቼ በእንግነት የተቀመጡበትንም ዘመን አያህሉም። ያዕቆብም ፈርዖንን ባረከው ከፈርዖንም ፊት ወጣ። ዮሴፍም አባቱንና ወንድሞቹን አኖረ ፈርዖን እንዳዘዘው በግብፅ ምድር በተሻለችው በራምሴ ምድር ጉልትን ሰጣቸው። ዮሴፍም ለአባቱና ለወንድሞቹ ለአባቱም ቤተስዎች ሁሉ እንደ ልጆቻቸው መጠን እህል ሰጣቸው።

ዘፍጥረት 47:1-12 አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም (አማ05)

ዮሴፍም ወደ ፈርዖን ሄዶ “አባቴና ወንድሞቼ በጎቻቸውንና ፍየሎቻቸውን ከብቶቻቸውንና ሌላም ያላቸውን ነገር ሁሉ ይዘው ከከነዓን ወደዚህ መጥተዋል፤ አሁንም በጌሴም ምድር ይገኛሉ” አለው። ከወንድሞቹ መካከል መርጦ ያመጣቸውንም አምስቱን ወንድሞቹን ወደ ፈርዖን አቀረባቸው። ፈርዖንም የዮሴፍን ወንድሞች፦ “የምትተዳደሩበት ሥራ ምንድን ነው?” ብሎ ጠየቃቸው። እነርሱም እንዲህ ብለው መለሱለት፥ “እኛ አገልጋዮችህ በግ አርቢዎች ነን፤ አባቶቻቸንም ይተዳደሩበት የነበረ ሥራ ይኸው ነበር። በከነዓን ምድር ራብ እጅግ ከመበርታቱ የተነሣ ለእንስሶቻችን ግጦሽ ስላጣን ለጊዜው በዚህች አገር ለመኖር መጥተናል፤ ስለዚህ አገልጋዮችህ በጌሴም ምድር እንድንኖር ፍቀድልን።” ፈርዖንም ዮሴፍን እንዲህ አለው፥ “አባትህና ወንድሞችህ ከመጡልህ፤ እነሆ፥ መላው የግብጽ ምድር የአንተ ነው፤ ስለዚህ አባትህና ወንድሞችህ ምርጥ በሆነችው በጌሴም ምድር እንዲኖሩ አድርግ። ከእነርሱ መካከል ልዩ ችሎታ ያላቸው ሰዎች ካሉ፥ በእኔ እንስሶች ላይ የበላይ ኀላፊዎች አድርገህ ሹማቸው።” ከዚህ በኋላ ዮሴፍ አባቱን ያዕቆብን ወደ ፈርዖን አቀረበው፤ ያዕቆብም ፈርዖንን ባረከው፤ ፈርዖንም “ዕድሜህ ስንት ነው?” በማለት ያዕቆብን ጠየቀው። ያዕቆብም “በመንከራተት ያሳለፍኳቸው ዘመናት መቶ ሠላሳ ናቸው። እነርሱም የቀድሞ አባቶቼ በመንከራተት ካሳለፉአቸው ዘመናት እጅግ ያነሡና ችግር የበዛባቸው ናቸው” አለ። ያዕቆብ ፈርዖንን ባረከውና ተሰናብቶት ወጣ። ከዚህ በኋላ ዮሴፍ አባቱና ወንድሞቹ በግብጽ ምድር እንዲቀመጡ አደረገ፤ ፈርዖን ባዘዘው መሠረት በግብጽ ምድር ምርጥ የሆነውን፥ በራምሴ ከተማ አጠገብ ያለውን ቦታ በይዞታ ሰጣቸው። ዮሴፍ ለአባቱና ለወንድሞቹ በልጆቻቸው ቊጥር ልክ እህል ይሰጣቸው ነበር።

ዘፍጥረት 47:1-12 መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) (መቅካእኤ)

ዮሴፍም ወደ ፈርዖን ሄዶ “አባቴና ወንድሞቼ በጎቻቸውንና ፍየሎቻቸውን ከብቶቻቸውንና ሌላም ያላቸውን ነገር ሁሉ ይዘው ከከነዓን ወደዚህ መጥተዋል፤ አሁንም በጌሴም ምድር ይገኛሉ” አለው። ከወንድሞቹ መካከል መርጦ ያመጣቸውንም አምስቱን ወንድሞቹን ወደ ፈርዖን አቀረባቸው። ፈርዖንም ወንድሞቹን፦ “ሥራችሁ ምንድነው?” አላቸው። እነርሱም ፈርዖንን፦ “እኛ አገልጋዮችህ፥ እኝም አባቶቻችንም፥ በግ አርቢዎች ነን” አሉት። “በምድር ልንቀመጥ በእንግድነት መጣን፥ ራብ በከነዓን ምድር እጅግ ጸንቶአልና፥ የአገልጋዮችህ በጎች የሚሰማሩበት ስፍራ የለም፥ አሁንም አገልጋዮችህ በጌሤም ምድር እንድንቀመጥ እንለምንሃለን።” አሉት ፈርዖንን። ፈርዖንም ዮሴፍን እንዲህ አለው፦ “አባትህና ወንድሞችህ መጥተውልሃል፥ የግብጽ ምድር በፊትህ ናት፥ በመልካሙ ምድር አባትህንና ወንድሞችህን አኑራቸው፥ በጌሤም ምድር ይኑሩ፤ ከእነርሱ መካከል ችሎታ ያላቸው ሰዎች ካሉ፥ በእኔ እንስሶች ላይ የበላይ ኀላፊዎች አድርገህ ሹማቸው።” ዮሴፍም ያዕቆብን አባቱን አስገብቶ በፈርዖን ፊት አቆመው፥ ያዕቆብም ፈርዖንን ባረከው። ፈርዖንም ያዕቆብን፦ “የዕድሜህ ዘመን ስንት ዓመት ነው?” አለው። ያዕቆብም ለፈርዖን አለው፦ “የእንግድነቴ ዘመን መቶ ሠላሳ ዓመት ነው፥ የሕይወቴ ዘመኖች ጥቂትም ክፋም ሆኑብኝ፥ አባቶቼ በእንግድነት የተቀመጡበትንም ዘመን አያህሉም።” ፈርዖንን ባርኮም ያዕቆብ ከፈርዖንም ፊት ወጣ። ዮሴፍም አባቱንና ወንድሞቹን አኖረ፥ ፈርዖን እንዳዘዘም በግብጽ ምድር በተሻለችው የራምሴ ምድር በይዞታ ሰጣቸው። ዮሴፍም ለአባቱና ለወንድሞቹ ለአባቱም ቤተ ሰዎች ሁሉ እንደ ልጆቻቸው መጠን እህል ሰጣቸው።