የYouVersion አርማ
የፍለጋ አዶ

ኦሪት ዘፍጥረት 47:1-12

ኦሪት ዘፍጥረት 47:1-12 አማ54

ዮሴፍም ገባ ለፈርዖንም ነገረው እንዲህ ብሎ፦ አባቴና ወንድሞቼ በጎቻቸውም ላሞቻቸውም ያላቸውም ሁሉ ከከነዓን ምድር ወጡ እነርሱም እነሆ በጌሤም ምድር ናቸው። ከወንድሞቹም አምስት ሰዎች ወስዶ በፈርዖን ፊት አቆማቸው። ፈርዖንም ወንድሞቹም፦ ሥራችሁ ምንድር ነው? አላቸው። እነርሱም ፈርዖንን፦ እኛ ባሪያዎችን እኝም አባቶቻችንም በግ አርቢዎች ነን አሉት። ፈርዖንንም እንዲህ አሉት፦ በምድር ልንቀመጥ በእንግድነት መጣን የባርያዎችህ በጎች የሚስማሩበት ስፍራ የለምና ራብ በከነዓን ምድር እጅግ ጸንቶቸልና አሁንም ባርያዎችህ በጌሤም ምድር እንድንቀመጥ እንለምንሃለን። ፈርዖንም ዮሴፍን ተናገረው እንዲህ ብሎ፦ አባትህና ወንድሞችን መጥተውልሃል የግብፅ ምድር በፊትህ ናት በመልካሙ ምድር አባትህንና ወንድሞችህን አኑራቸው በጌሤም ምድር ይኑሩ ከእነርሱም ውስጥ እውቀት ያላቸውን ሰዎች ታውቅ እንደ ሆነ በእንስሶቼ ላይ አለቆች አድርጋቸው ዮሴፍም ያዕቆብን አባቱን አስገብቶ በፈርዖን ፊት አቆመው ያዕቆብም ፈርዖንን ባረከው። ፈርዖንም ያዕቆብን፦ የዕድሜህ ዘመን ስንት ዓመት ነው? አለው ያዕቆብም ለፈርዖን አለው፦ የእንግድነቴ ዘመን መቶ ሠላሳ ዓመት ነው የሕይወቴ ዘመኖች ጥቂትም ክፋም ሆኑብኝ አባቶቼ በእንግነት የተቀመጡበትንም ዘመን አያህሉም። ያዕቆብም ፈርዖንን ባረከው ከፈርዖንም ፊት ወጣ። ዮሴፍም አባቱንና ወንድሞቹን አኖረ ፈርዖን እንዳዘዘው በግብፅ ምድር በተሻለችው በራምሴ ምድር ጉልትን ሰጣቸው። ዮሴፍም ለአባቱና ለወንድሞቹ ለአባቱም ቤተስዎች ሁሉ እንደ ልጆቻቸው መጠን እህል ሰጣቸው።

ቪዲዮ ለ {{ዋቢ_ሰዉ}}