ዘፍጥረት 46:1-27

ዘፍጥረት 46:1-27 የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) (አማ2000)

እስ​ራ​ኤ​ልም ለእ​ርሱ ያለ​ውን ሁሉ ይዞ ተነሣ፤ ወደ ዐዘ​ቅተ መሐ​ላም መጣ፤ መሥ​ዋ​ዕ​ት​ንም ለአ​ባቱ ለይ​ስ​ሐቅ አም​ላክ ሠዋ። እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርም በሌ​ሊት ራእይ፥ “ያዕ​ቆብ ያዕ​ቆብ” ብሎ ለእ​ስ​ራ​ኤል ተና​ገ​ረው። እር​ሱም “ምን​ድን ነው?” አለ። አለ​ውም፥ “የአ​ባ​ቶ​ችህ አም​ላክ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር እኔ ነኝ፤ ወደ ግብፅ መው​ረ​ድን አት​ፍራ፤ በዚያ ትልቅ ሕዝብ አደ​ር​ግ​ሃ​ለ​ሁና። እኔ ወደ ግብፅ አብ​ሬህ እወ​ር​ዳ​ለሁ፤ ከዚ​ያም ደግሞ እኔ አወ​ጣ​ሃ​ለሁ፤ ልጅህ ዮሴ​ፍም እጁን በዐ​ይ​ንህ ላይ ያኖ​ራል።” ያዕ​ቆ​ብም ከዐ​ዘ​ቅተ መሐላ ተነሣ፤ የእ​ስ​ራ​ኤ​ልም ልጆች አባ​ታ​ቸ​ውን፥ ገን​ዘ​ባ​ቸ​ውን፥ ሚስ​ቶ​ቻ​ቸ​ው​ንም እነ​ር​ሱን ያመ​ጡ​ባ​ቸው ዘንድ ዮሴፍ በላ​ካ​ቸው ሰረ​ገ​ሎች ጭነው ወሰዱ። ጓዛ​ቸ​ውን፥ በከ​ነ​ዓን ሀገ​ርም ያገ​ኙ​ትን ጥሪ​ታ​ቸ​ውን ሁሉ ይዘው ያዕ​ቆ​ብና ዘሩ ሁሉ ከእ​ርሱ ጋር ወደ ግብፅ መጡ፤ ወን​ዶች ልጆ​ቹ​ንና የወ​ን​ዶች ልጆ​ቹን ወን​ዶች ልጆች፥ ሴቶች ልጆ​ቹ​ንና የሴ​ቶች ልጆ​ቹን ሴቶች ልጆች፥ ዘሩ​ንም ሁሉ ከእ​ርሱ ጋር ወደ ግብፅ አስ​ገ​ባ​ቸው። ከአ​ባ​ታ​ቸው ከያ​ዕ​ቆብ ጋር ወደ ግብፅ የገ​ቡት የእ​ስ​ራ​ኤል ልጆች ስም ይህ ነው፤ ያዕ​ቆ​ብና ልጆቹ፤ የያ​ዕ​ቆብ በኵር ሮቤል። የሮ​ቤ​ልም ልጆች፤ ሄኖኅ፥ ፍሉስ፥ አስ​ሮን፥ ከርሜ። የስ​ም​ዖን ልጆች፤ ይሙ​ኤል፥ ያሚን፥ አኡድ፥ ያኪን፥ ሱሐር፥ የከ​ነ​ዓ​ና​ዊት ልጅ ሳዑል። የሌ​ዊም ልጆች፤ ጌድ​ሶን፥ ቀዓት፥ ሜራሪ። የይ​ሁ​ዳም ልጆች፤ ዔር፥ አው​ናን፥ ሴሎም፥ ፋሬስ፥ ዛራ፤ ዔርና አው​ናን በከ​ነ​ዓን ምድር ሞቱ። የፋ​ሬ​ስም ልጆች እኒህ ናቸው፤ ኤስ​ሮም፥ ይሞ​ሔል፤ የይ​ሳ​ኮ​ርም ልጆች፤ ቶላዕ፥ ፎሓ፥ ያሱብ፥ ስምራ። የዛ​ብ​ሎ​ንም ልጆች፤ ሳሬድ፥ አሎን፥ አሌል። ልያ በመ​ስ​ጴ​ጦ​ምያ በሶ​ርያ ለያ​ዕ​ቆብ የወ​ለ​ደ​ቻ​ቸው ልጆ​ችና ሴቲቱ ልጅዋ ዲና እነ​ዚህ ናቸው፤ ወን​ዶ​ችም ሴቶ​ችም ልጆ​ችዋ ሁሉ ሠላሳ አራት ነፍስ ናቸው። የጋ​ድም ልጆች፤ ስፎን፥ ሐጊ፥ ሱኒ፥ አዜን፥ አድ፥ አሮ​ሐድ፥ አር​ሔል። የአ​ሴ​ርም ልጆች፤ ኢያ​ምን፥ ኢያሱ፥ኢዩል፥ በሪዓ፥ እኅ​ታ​ቸው ሳራ፤ የበ​ሪዓ ልጆ​ችም፤ ኮቦር፥ መል​ኪ​ኤል። ላባ ለልጁ ለልያ የሰ​ጣት የዘ​ለፋ ልጆች እነ​ዚህ ናቸው፤ እር​ስ​ዋም እነ​ዚ​ህን ዐሥራ ስድ​ስ​ቱን ነፍስ ለያ​ዕ​ቆብ ወለ​ደች። የያ​ዕ​ቆብ ሚስት የራ​ሔል ልጆች ዮሴ​ፍና ብን​ያም ናቸው። ለዮ​ሴ​ፍም በግ​ብፅ ምድር ልጆች ተወ​ለ​ዱ​ለት፤ እነ​ር​ሱም የሄ​ል​ዮቱ ከተማ ካህን የጴ​ጤ​ፌራ ልጅ አስ​ኔት የወ​ለ​ደ​ች​ለት ምና​ሴና ኤፍ​ሬም ናቸው። ሶር​ያ​ዊት ዕቅ​ብቱ የወ​ለ​ደ​ች​ለት የም​ና​ሴም ልጅ ማኪር ነው። ማኪ​ርም ገለ​ዓ​ድን ወለደ፤ የም​ና​ሴም ወን​ድም የኤ​ፍ​ሬም ልጆች ሱታ​ላና ጠኀን ናቸው። የሱ​ታላ ልጅም ኤዴን ነው። የብ​ን​ያ​ምም ልጆች፤ ቤላ፥ ቦኮር፥ አስ​ቤር፤ የቤላ ልጆ​ችም፤ ጌራ፥ ኖሔ​ማን፥ አሒ፥ ሮስ፥ ማን​ፌን፥ ሑፈም፤ ጌራም አራ​ድን ወለደ። ለያ​ዕ​ቆብ የተ​ወ​ለ​ዱ​ለት የራ​ሔል ልጆ​ችም እነ​ዚህ ናቸው፤ ሁሉም ዐሥራ አራት ነፍስ ናቸው። የዳ​ንም ልጅ አሳ ነው። የን​ፍ​ታ​ሌ​ምም ልጆች፤ አሴ​ሔል፥ ጎሂን፥ ዮሴር ሴሌም። ላባ ለልጁ ለራ​ሔል የሰ​ጣት የባላ ልጆች እነ​ዚህ ናቸው፤ እነ​ዚ​ህ​ንም ለያ​ዕ​ቆብ ወለ​ደ​ች​ለት፤ ባላ የወ​ለ​ደ​ቻ​ቸው ሁሉም ሰባት ነፍስ ናቸው። ከያ​ዕ​ቆብ ጋር ወደ ግብፅ የገ​ቡት ሰዎች ሁሉ ከጕ​ል​በቱ የወ​ጡት፥ ከል​ጆቹ ሚስ​ቶች ሌላ፥ ሁላ​ቸው ስድሳ ሰባት ናቸው። በግ​ብፅ ምድር የተ​ወ​ለ​ዱ​ለት የዮ​ሴ​ፍም ልጆች ሁለት ናቸው፤ ወደ ግብፅ የገ​ቡት የያ​ዕ​ቆብ ቤተ ሰዎች ሁሉ ሰባ ናቸው።

ዘፍጥረት 46:1-27 አዲሱ መደበኛ ትርጒም (NASV)

እስራኤልም ጓዙን ሁሉ ጠቅልሎ ተነሣ፤ ቤርሳቤህም ሲደርስ፣ ለአባቱ ለይሥሐቅ አምላክ መሥዋዕት ሠዋ። እግዚአብሔርም ሌሊት በራእይ ለእስራኤል ተገልጦ “ያዕቆብ ያዕቆብ” ብሎ ጠራው። እርሱም፣ “እነሆ፤ አለሁ” አለ። እግዚአብሔርም እንዲህ አለው፤ “እኔ እግዚአብሔር ነኝ፤ የአባትህ አምላክ ነኝ፤ ወደ ግብጽ ለመውረድ አትፍራ፤ በዚያ ታላቅ ሕዝብ አደርግሃለሁና፤ ዐብሬህ ወደ ግብጽ እወርዳለሁ፤ ከዚያም መልሼ አወጣሃለሁ፤ የዮሴፍ የራሱ እጆችም ዐይኖችህን ይገጥሟቸዋል።” ከዚህ በኋላ ያዕቆብ ከቤርሳቤህ ተነሣ፤ የእስራኤል ወንዶች ልጆችም አባታቸውን ያዕቆብን፣ ልጆቻቸውንና ሚስቶቻቸውን ፈርዖን ለያዕቆብ በላካቸው ሠረገላዎች ላይ አወጧቸው። ከብቶቻቸውንና በከነዓን ምድር ያፈሩትን ሀብት ንብረታቸውን ይዘው፣ ያዕቆብና ዘሮቹ በሙሉ ወደ ግብጽ ወረዱ። ወደ ግብጽም የወረደው፣ ወንዶች ልጆቹንና ወንዶች የልጅ ልጆቹን፣ ሴቶች ልጆቹንና ሴቶች የልጅ ልጆቹን፣ ማለትም ዘሮቹን ሁሉ ይዞ ነው። ወደ ግብጽ የወረዱት የእስራኤል ልጆች፣ ያዕቆብና ዘሮቹ እነዚህ ናቸው፦ የያዕቆብ የበኵር ልጅ ሮቤል። የሮቤል ልጆች፦ ሄኖኅ፣ ፈሉስ፣ አስሮን እና ከርሚ ናቸው። የስምዖን ልጆች፦ ይሙኤል፣ ያሚን፣ ኦሃድ፣ ያኪን፣ ጾሐርና ከከነዓናዊቷ ሴት የተወለደው ሳኡል ናቸው። የሌዊ ልጆች፦ ጌርሶን፣ ቀዓት እና ሜራሪ ናቸው። የይሁዳ ልጆች፦ ዔር፣ አውናን፣ ሴሎም፣ ፋሬስ እና ዛራ ናቸው። ነገር ግን ዔርና አውናን በከነዓን ምድር ሞቱ። የፋሬስ ልጆች፦ ኤስሮምና ሐሙል ናቸው። የይሳኮር ልጆች፦ ቶላ፣ ፉዋ፣ ዮብና ሺምሮን ናቸው፤ የዛብሎን ልጆች፦ ሴሬድ፣ ኤሎንና ያሕልኤል ናቸው፤ እነዚህ ወንዶች ልጆች ያዕቆብ በሰሜን ምዕራብ መስጴጦምያ ሳለ፣ ልያ የወለደችለት ናቸው። ሴቷን ዲናን ጨምሮ፣ የወንዶችና የሴቶች ልጆቹ ቍጥር ሠላሳ ሦስት ነው። የጋድ ልጆች፦ ጽፎን፣ ሐጊ፣ ሹኒ፣ ኤስቦን፣ ዔሪ፣ አሮዲና አርኤሊ ናቸው፤ የአሴር ልጆች፦ ዪምና፣ የሱዋ፣ የሱዊና በሪዓ ናቸው፤ እኅታቸውም ሤራሕ ናት፤ የበሪዓ ልጆች፦ ሔቤርና መልኪኤል ናቸው፤ እነዚህ ዐሥራ ስድስት ልጆች ሁሉ፣ ላባ ለልጁ ለልያ ከሰጣት ከዘለፋ ላይ ያዕቆብ የወለዳቸው ናቸው። የያዕቆብ ሚስት የራሔል ልጆች፦ ዮሴፍና ብንያም ናቸው፤ በግብጽም የሄልዮቱ ከተማ ካህን የጶጥፌራ ልጅ አስናት፣ ምናሴንና ኤፍሬምን ለዮሴፍ ወለደችለት። የብንያም ልጆች፦ ቤላ፣ ቤኬር፣ አስቤል፣ ጌራ፣ ናዕማን፣ አኪ፣ ሮስ፣ ማንፌን ሑፊምና አርድ ናቸው። እነዚህ ዐሥራ አራቱ፣ ራሔል ለያዕቆብ የወለደችለት ልጆችና የልጅ ልጆች ናቸው። የዳን ልጅ፦ ሑሺም ነው፤ የንፍታሌም ልጆች፦ ያሕጽኤል፣ ጉኒ፣ ዬጽርና ሺሌም ናቸው። እነዚህ ሰባቱ ልጆች ሁሉ ላባ ለልጁ ለራሔል ከሰጣት ከባላ ላይ ያዕቆብ የወለዳቸው ናቸው። ከያዕቆብ ጋራ ወደ ግብጽ የሄዱት የገዛ ዘሮቹ ብዛት ስድሳ ስድስት ሲሆን ይህ ቍጥር ግን የልጆቹን ሚስቶች አይጨምርም። ዮሴፍ በግብጽ የወለዳቸውን ሁለት ልጆች ጨምሮ፣ ወደ ግብጽ የወረደው የያዕቆብ ቤተ ሰብ ቍጥር ሰባ ነበር።

ዘፍጥረት 46:1-27 መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) (አማ54)

እስራኤልም ለእርሱ ያለውን ሁሉ ይዞ ተነሣ ወደ ቤርሳቤህ መጣ መሥዋዕትንም ለአባቱ ለይስሐቅ አምላክ ሠዋ። እግዚአብሔርም በሌሊት ራእይ፦ ያዕቆብ ያዕቆብ ብሎ ለእስራኤል ተናገረው። እርሱም፦ እነሆኝ አለ። አለውም፦ የአባቶችህ አምላክ እግዚአብሔር እኔ ነኝ ወደ ግብፅ መውረድ አትፍራ በዚያ ትልቅ ሕዝብ አደርግሃለሁና። እኔ ወደ ግብፅ አብሬህ እወርዳለሁ ከዚያንም ደግሞ እኔ አወጣሃለሁ፤ ዮሴፍም እጁን በዓይንህ ላይ ያኖራል። ያዕቆብም ከቤርሳቤህ ተነሣ የእስራኤልም ልጆች ያዕቆብም ልጆች ያዕቆብን ይወስዱ ዘንድ ፈርዖን በሰደዳቸው ሰረገሎች አባታቸውን ያዕቆብንና ሕፃናቶቻቸውንም ሴቶቻቸውንም ወሰዱ። እንስሶቻቸውንም በከነዓን አገርም ያገኙትን ከብታቸውን ሁሉ ይዘው ያዕቆብ ዘሩ ሁሉ ከእርሱ ጋር ወደ ግብፅ መጡ ወንዶች ልጆቹንና የልጆቹን ወንዶች ልጆች ሴቶች ልጆቹንና የወንዶች ልጆቹን ሴቶች ልጆች ዘሩንም ሁሉ ከእርሱ ጋር ወደ ግብፅ አስገባቸው። ወደ ግብፅም የገቡት የእስራኤል ልጆች ስም ይህ ነው ያዕቆብና ልጆቹ የያዕቆብ በኵር ሮቤል። የሮቤልም ልጆች ሄኖኅ ፈሉሶ፥ አስሮን፥ ከርሚ። የስሞዖን ልጆች ይሙኤል ያሚን፥ አሃድ ያኪን ጾሐር፥ የከነዓናዊት ልጅ ሳኡል። የሌዊም ልጆች ጌድሶን፥ ቀዓት ሜራሪ። የይሁዳም ልጆች ዔር አውናን፥ ሴሎም፥ ፋሬስ፥ ዛራ፤ ዔርና አውናን በከነዓን ምድር ሞቱ የፋሬስም ልጆች ኤስሮችም ሐሙል። የይሳኮር ልጆች ቶላ፥ ፋዋ፥ ዮብ ሺምሮን። የዛብሎንም ልጆች ሴሬድ ኤሎን ያሕልኤል። ልያ በመስዼጦምያ በሶርያ ለያዕቆብ የወለደቻቸው ልጆችና ሴቲቱ ልጅዋ ዲና እነዚህ ናቸው ወንዶችም ሴቶችም ልጆችዋ ዲና እነዚን ናቸው ወንዶችም ሴቶችም ልጆችዋ ሁሉ ሠላሳ ሦስት ነፍስ ናቸው። የጋድም ልጆች ጽፎን፥ ሐጊ፥ ሹኒ ኤስቦን፥ ዔሪ አሮዲ አርኤሊ የአሲርም ልጆች ዪምና የሱዋ፥ የሱዊ በሪዓ እኅታቸው ሤራሕ የበሪዓ ልጆችም ሔቤር መልኪኤል። ላባ ለልጁ ለልያ የሰጣት የዘለፋ ልጆች እነዚህ ናቸው እነዚህን አሥራ ስድስቱንም ነፍስ ለያዕቆብ ወለደች። የያዕቆብ ሚስት የራሔል ልጆች ዮሴፍና ብንያም ናቸው። ለዮሴፍም በግብፅ ምድር ምነሴና ኤፍሬም ተወለዱለት የሄልዮቱ ከተማ ካህን የዾጥፌራ ልጅ አስናት የወለደቻቸው ናቸው። የብንያም ልጆች ቤላ፥ ቤኬር፥ አስቤል የቤላ ልጆችም ጌራ ናዕማን አኪ ሮስ፥ ማንፌን፥ ሑፊም ጌራም አርድን ወለደ። ለያዕቆብ የተወለዱለት የራሔልም ልጆች እነዚህ ናቸው ሁሉም አሥራ አራት ነፍስ ናቸው። የዳንም ልጆች ሑሺም የንፍታሌምም ልጆች ያሕጽኤል ጊኑ ዮጽር፥ ሺሌም። ላባ ለልጁ ለራሔል የሰጣት የባላ ልጆች እነዚህ ናቸው እነዚህንም ለያዕቆብ ወለደችለት ሁሉም ሰባት ነፍስ ናቸው። ከያዕቆብ ጋር ወደ ግብፅ የገቡት ሰዎች ሁሉ ከጉልበቱ የወጡት ከልጆቹ ሚስቶች ሌላ ሁላቸው ስድሳ ስድስት ናቸው። በግብፅ ምድር የተወለዳለት የዮሴፍም ልጆች ሁለት ናቸኤ ወደ ግብፅ የገቡት የያዕቆብ ቤተስዎች ሁሉ ሰባ ናቸው።

ዘፍጥረት 46:1-27 አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም (አማ05)

ያዕቆብ ጓዙን ሁሉ ይዞ ተነሣ፤ ቤርሳቤህም በደረሰ ጊዜ ለአባቱ ለይስሐቅ አምላክ መሥዋዕት አቀረበ። እግዚአብሔር፥ ሌሊት በራእይ ተገለጠለትና “ያዕቆብ! ያዕቆብ!” ብሎ ጠራው። እርሱም “አቤት ጌታ ሆይ፥ እነሆ አለሁ” አለ። እግዚአብሔርም እንዲህ አለው፤ “እኔ የአባትህ አምላክ፥ እግዚአብሔር ነኝ፤ ወደ ግብጽ ለመሄድ አትፍራ፤ እኔ ዘርህን በግብጽ አገር ታላቅ ሕዝብ አደርገዋለሁ፤ እኔ ወደ ግብጽ አብሬህ እሄዳለሁ፤ ወደዚህ ምድርም ትውልድህን መልሼ አመጣለሁ፤ በምትሞትበትም ጊዜ ዮሴፍ በአጠገብህ ይገኛል።” ያዕቆብ ከቤርሳቤህ ተነሥቶ ወደ ግብጽ ጒዞ ጀመረ፤ ልጆቹም አባታቸውን ያዕቆብን፥ ሕፃናት ልጆቻቸውንና ሚስቶቻቸውን የግብጽ ንጉሥ በላካቸው ሠረገሎች አሳፍረው፥ ከብቶቻቸውንና በከነዓን ያፈሩትን ሀብት ሁሉ ይዘው ወደ ግብጽ ሄዱ፤ በዚህ ዐይነት ያዕቆብ ቤተሰቡን ሁሉ ይዞ ወደ ግብጽ ሄደ፤ አብረው የሄዱትም ወንዶች ልጆቹ፥ ሴቶች ልጆቹና የልጅ ልጆቹ ናቸው። ከእስራኤል ጋር ወደ ግብጽ የወረዱት የእስራኤላውያን ስም ዝርዝር የሚከተለው ነው፦ የያዕቆብ የበኲር ልጅ ሮቤል፥ የሮቤል ልጆች፦ ሔኖክ፥ ፋሉ፥ ሔጽሮንና ካርሚ ናቸው። የስምዖን ልጆች፦ ይሙኤል፥ ያሚን፥ ኦሃድ፥ ያኪን፥ ጾሐርና ከከነዓናዊቷ ሴት የተወለደው ሻኡል ናቸው። የሌዊ ልጆች፦ ጌርሾን፥ ቀዓትና መራሪ ናቸው። የይሁዳ ልጆች፦ ዔር፥ ኦናን፥ ሴላ፥ ፋሬስና ዛራሕ ናቸው፤ ዔርና ኦናን ግን በከነዓን ምድር ሞተዋል። የፋሬስ ልጆች ሔጽሮንና ሐሙል ናቸው። የይሳኮር ልጆች፦ ቶላዕ፥ ፉዋ፥ ያሹብና ሺምሮን ናቸው። የዛብሎን ልጆች፦ ሴሬድ፥ ኤሎንና ያሕለኤል ናቸው። እነዚህ ወንዶች ልጆችና ሴቷም ልጅ ዲና በመስጴጦምያ ሳሉ ልያ ለያዕቆብ የወለደችለት ናቸው። ያዕቆብ ከልያ ያፈራቸው ልጆችና የልጅ ልጆች ሠላሳ ሦስት ናቸው። የጋድ ልጆች፦ ጸፎን፥ ሐጊ፥ ሹኒ፥ ኤጽቦን፥ ዔሪ፥ አሮድና አርኤሊ ናቸው። የአሴር ልጆች፦ ይምና፥ ይሽዋ፥ ይሽዊና በሪዓ ናቸው። እኅታቸው ሤራሕ ትባላለች። የበሪዓ ልጆች ደግሞ ሔቤርና ማልኪኤል ናቸው። እነዚህ ዐሥራ ስድስቱ ላባ ለልጁ ለልያ በሞግዚትነት ከሰጣት ከዚልፋ የተወለዱ የያዕቆብ ልጆችና የልጅ ልጆች ናቸው። ያዕቆብ ከራሔል የወለዳቸው ዮሴፍና ብንያም ናቸው። የዮሴፍ ልጆች ምናሴና ኤፍሬም ናቸው፤ እነርሱም ዮሴፍ በግብጽ ምድር ከኦን ከተማ ካህን ከጶጢፌራ ሴት ልጅ ከአስናት የወለዳቸው ናቸው። የብንያም ልጆች፦ ቤላዕ፥ ቤኬር፥ አሽቤል፥ ጌራ፥ ናዕማን፥ ኤሒ፥ ሮሽ፥ ሙፊም፥ ሑፊምና አረድ ናቸው። እነዚህ ዐሥራ አራቱ ያዕቆብ ከራሔል የወለዳቸው ልጆችና የልጅ ልጆች ናቸው። የዳን ልጅ ሑሺም ነው። የንፍታሌም ልጆች፦ ያሕጽኤል፥ ጉኒ፥ ዬጼርና ሺሌም ናቸው። እነዚህ ሰባቱ ላባ ለልጁ ለራሔል ከሰጣት ከባላ የተወለዱ የያዕቆብ ልጆችና የልጅ ልጆች ናቸው። ከያዕቆብ ጋር ወደ ግብጽ የሄዱት የያዕቆብ ቤተሰቦች ሥልሳ ስድስት ናቸው፤ ይህም የልጆቹን ሚስቶች ቊጥር ሳይጨምር ነው። ለዮሴፍ በግብጽ ከተወለዱት ከሁለቱ ወንዶች ልጆች ጋር፥ ከያዕቆብ ጋር ወደ ግብጽ የገቡት የያዕቆብ ልጆችና የልጅ ልጆች ቊጥር በአጠቃላይ ሰባ ነበር።

ዘፍጥረት 46:1-27 መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) (መቅካእኤ)

እስራኤልም ያለውን ሁሉ ይዞ ተነሣ፥ ወደ ቤርሳቤህ ደረሰ፥ መሥዋዕትንም ለአባቱ ለይስሐቅ አምላክ ሠዋ። እግዚአብሔርም በሌሊት ራእይ፦ “ያዕቆብ ያዕቆብ” ብሎ ለእስራኤል ጠራው። እርሱም፦ “እነሆኝ” አለ። እሱም አለው፦ “የአባቶችህ አምላክ እግዚአብሔር እኔ ነኝ፥ ወደ ግብጽ መውረድ አትፍራ፥ በዚያ ትልቅ ሕዝብ አደርግሃለሁና። እኔ ወደ ግብጽ አብሬህ እወርዳለሁ፥ ከዚያም ደግሞ እኔ አወጣሃለሁ፥ የዮሴፍም እጅ ዓይንህን ይሸፍናል።” ያዕቆብም ከቤርሳቤህ ተነሣ፥ የእስራኤልም ልጆች ያዕቆብን ይወስዱ ዘንድ ፈርዖን በሰደዳቸው ሰረገሎች አባታቸውን ያዕቆብንና ሕፃናቶቻቸውን ሴቶቻቸውንም ወሰዱ። እንስሶቻቸውንም በከነዓን አገርም ያገኙትን ከብታቸውን ሁሉ ይዘው ያዕቆብና ዘሩ ሁሉ ከእርሱ ጋር ወደ ግብጽ መጡ፥ ወንዶች ልጆቹንና የልጆቹን ወንዶች ልጆች፥ ሴቶች ልጆቹንና የወንዶች ልጆቹን ሴቶች ልጆች፥ ዘሩንም ሁሉ ከእርሱ ጋር ወደ ግብጽ ወሰደ። ወደ ግብጽም የገቡት የእስራኤል ልጆች ስም ይህ ነው፥ ያዕቆብና ልጆቹ፥ የያዕቆብ በኩር ሮቤል። የሮቤልም ልጆች፥ ሄኖኅ፥ ፈሉሶ፥ አስሮን፥ ካርሚ። የስሞዖን ልጆች፥ ይሙኤል፥ ያሚን፥ አሃድ፥ ያኪን፥ ጾሐር፥ የከነዓናዊት ልጅ ሳኡል። የሌዊም ልጆች፥ ጌድሾን፥ ቀዓት፥ ሜራሪ። የይሁዳም ልጆች፥ ዔር፥ ኦውናን፥ ሴላ፥ ፋሬስ፥ ዛራሕ፥ ዔርና አውናን በከነዓን ምድር ሞቱ፥ የፋሬስም ልጆች ኤስሮም፥ ሐሙል። የይሳኮር ልጆች፥ ቶላዕ፥ ፉዋ፥ ዮብ፥ ሺምሮን። የዛብሎንም ልጆች፥ ሴሬድ፥ ኤሎን፥ ያሕልኤል። ልያ በፓዳን-ኣሪም በሶርያ ለያዕቆብ የወለደቻቸው ልጆችና፥ ሴቲቱ ልጇ ዲና እነዚህ ናቸው፥ ወንዶችም ሴቶችም ልጆችዋ ሁሉ ሠላሳ ሦስት ናቸው። የጋድም ልጆች፥ ጽፎን፥ ሐጊ፥ ሹኒ፥ ኤጽቦን፥ ዔሪ፥ አሮዲ፥ አርኤሊ። የአሴር ልጆች፦ ይምና፥ ይሽዋ፥ ይሽዊና በሪዓ ናቸው። እኅታቸው ሤራሕ ትባላለች። የበሪዓ ልጆች ደግሞ ሔቤርና ማልኪኤል ናቸው። እነዚህ ዐሥራ ስድስቱ ላባ ለልጁ ለልያ በሞግዚትነት ከሰጣት ከዚልፋ የተወለዱ የያዕቆብ ልጆችና የልጅ ልጆች ናቸው። ያዕቆብ ከራሔል የወለዳቸው ዮሴፍና ብንያም ናቸው። የዮሴፍ ልጆች ምናሴና ኤፍሬም ናቸው፤ እነርሱም ዮሴፍ በግብጽ ምድር ከኦን ከተማ ካህን ከጶጢፌራ ሴት ልጅ ከአስናት የወለዳቸው ናቸው። የብንያም ልጆች፦ ቤላዕ፥ ቤኬር፥ አሽቤል፥ ጌራ፥ ናዕማን፥ ኤሒ፥ ሮሽ፥ ሙፊም፥ ሑፊምና አረድ ናቸው። እነዚህ ዐሥራ አራቱ ያዕቆብ ከራሔል የወለዳቸው ልጆችና የልጅ ልጆች ናቸው። የዳን ልጅ ሑሺም ነው። የንፍታሌም ልጆች፦ ያሕጽኤል፥ ጉኒ፥ ዬጼርና ሺሌም ናቸው። እነዚህ ሰባቱ ላባ ለልጁ ለራሔል ከሰጣት ከባላ የተወለዱ የያዕቆብ ልጆችና የልጅ ልጆች ናቸው። ከያዕቆብ ጋር ወደ ግብጽ የሄዱት የያዕቆብ ቤተሰቦች ሥልሳ ስድስት ናቸው፤ ይህም የልጆቹን ሚስቶች ቊጥር ሳይጨምር ነው። ለዮሴፍ በግብጽ ከተወለዱት ከሁለቱ ወንዶች ልጆች ጋር፥ ከያዕቆብ ጋር ወደ ግብጽ የገቡት የያዕቆብ ልጆችና የልጅ ልጆች ቊጥር በአጠቃላይ ሰባ ነበር።