ኦሪት ዘፍጥረት 46
46
1እስራኤልም ለእርሱ ያለውን ሁሉ ይዞ ተነሣ ወደ ቤርሳቤህ መጣ መሥዋዕትንም ለአባቱ ለይስሐቅ አምላክ ሠዋ። 2እግዚአብሔርም በሌሊት ራእይ፦ ያዕቆብ ያዕቆብ ብሎ ለእስራኤል ተናገረው። እርሱም፦ እነሆኝ አለ። 3አለውም፦ የአባቶችህ አምላክ እግዚአብሔር እኔ ነኝ ወደ ግብፅ መውረድ አትፍራ በዚያ ትልቅ ሕዝብ አደርግሃለሁና። 4እኔ ወደ ግብፅ አብሬህ እወርዳለሁ ከዚያንም ደግሞ እኔ አወጣሃለሁ፤ ዮሴፍም እጁን በዓይንህ ላይ ያኖራል። 5ያዕቆብም ከቤርሳቤህ ተነሣ የእስራኤልም ልጆች ያዕቆብም ልጆች ያዕቆብን ይወስዱ ዘንድ ፈርዖን በሰደዳቸው ሰረገሎች አባታቸውን ያዕቆብንና ሕፃናቶቻቸውንም ሴቶቻቸውንም ወሰዱ። 6እንስሶቻቸውንም በከነዓን አገርም ያገኙትን ከብታቸውን ሁሉ ይዘው ያዕቆብ ዘሩ ሁሉ ከእርሱ ጋር ወደ ግብፅ መጡ 7ወንዶች ልጆቹንና የልጆቹን ወንዶች ልጆች ሴቶች ልጆቹንና የወንዶች ልጆቹን ሴቶች ልጆች ዘሩንም ሁሉ ከእርሱ ጋር ወደ ግብፅ አስገባቸው።
8ወደ ግብፅም የገቡት የእስራኤል ልጆች ስም ይህ ነው ያዕቆብና ልጆቹ የያዕቆብ በኵር ሮቤል። 9የሮቤልም ልጆች ሄኖኅ ፈሉሶ፥ አስሮን፥ ከርሚ። 10የስሞዖን ልጆች ይሙኤል ያሚን፥ አሃድ ያኪን ጾሐር፥ የከነዓናዊት ልጅ ሳኡል። 11የሌዊም ልጆች ጌድሶን፥ ቀዓት ሜራሪ። 12የይሁዳም ልጆች ዔር አውናን፥ ሴሎም፥ ፋሬስ፥ ዛራ፤ ዔርና አውናን በከነዓን ምድር ሞቱ የፋሬስም ልጆች ኤስሮችም ሐሙል። 13የይሳኮር ልጆች ቶላ፥ ፋዋ፥ ዮብ ሺምሮን። 14የዛብሎንም ልጆች ሴሬድ ኤሎን ያሕልኤል። 15ልያ በመስዼጦምያ በሶርያ ለያዕቆብ የወለደቻቸው ልጆችና ሴቲቱ ልጅዋ ዲና እነዚህ ናቸው ወንዶችም ሴቶችም ልጆችዋ ዲና እነዚን ናቸው ወንዶችም ሴቶችም ልጆችዋ ሁሉ ሠላሳ ሦስት ነፍስ ናቸው። 16የጋድም ልጆች ጽፎን፥ ሐጊ፥ ሹኒ ኤስቦን፥ ዔሪ አሮዲ አርኤሊ 17የአሲርም ልጆች ዪምና የሱዋ፥ የሱዊ በሪዓ እኅታቸው ሤራሕ የበሪዓ ልጆችም ሔቤር መልኪኤል። 18ላባ ለልጁ ለልያ የሰጣት የዘለፋ ልጆች እነዚህ ናቸው እነዚህን አሥራ ስድስቱንም ነፍስ ለያዕቆብ ወለደች። 19የያዕቆብ ሚስት የራሔል ልጆች ዮሴፍና ብንያም ናቸው። 20ለዮሴፍም በግብፅ ምድር ምነሴና ኤፍሬም ተወለዱለት የሄልዮቱ ከተማ ካህን የዾጥፌራ ልጅ አስናት የወለደቻቸው ናቸው። 21የብንያም ልጆች ቤላ፥ ቤኬር፥ አስቤል የቤላ ልጆችም ጌራ ናዕማን አኪ ሮስ፥ ማንፌን፥ ሑፊም ጌራም አርድን ወለደ። 22ለያዕቆብ የተወለዱለት የራሔልም ልጆች እነዚህ ናቸው ሁሉም አሥራ አራት ነፍስ ናቸው። 23የዳንም ልጆች ሑሺም 24የንፍታሌምም ልጆች ያሕጽኤል ጊኑ ዮጽር፥ ሺሌም። 25ላባ ለልጁ ለራሔል የሰጣት የባላ ልጆች እነዚህ ናቸው እነዚህንም ለያዕቆብ ወለደችለት ሁሉም ሰባት ነፍስ ናቸው። 26ከያዕቆብ ጋር ወደ ግብፅ የገቡት ሰዎች ሁሉ ከጉልበቱ የወጡት ከልጆቹ ሚስቶች ሌላ ሁላቸው ስድሳ ስድስት ናቸው። 27በግብፅ ምድር የተወለዳለት የዮሴፍም ልጆች ሁለት ናቸኤ ወደ ግብፅ የገቡት የያዕቆብ ቤተስዎች ሁሉ ሰባ ናቸው።
28ይሁዳንም በጌሤም እንዲቀበለው በፊቱ ወደ ዮሴፍም ላከ ወደ ጌሤም ምድርም ደረሱ። 29ዮሴፍም ሰረገላውን አዘጋጀ አባቱንም እስራኤልን ሊገናኘው ወደ ጌሤም ወጣ ባየውም ጊዜ በአንገቱ ላይ ወደቀ አቅፎትም ረጅም ጊዜ አለቀሰ። 30እስራኤልም ዮሴፍን፦ አንተ ገና በሕይወት ሳለህ ፊትህን አይቼአለሁና አሁን ልሙት አለው። 31ዮሴፍም ወንድሞቹንና የአባቱን ቤተ ስዎች እንዲህ አላቸው፦ እኔ መጥቼ ለፈርዖን እንዲህ ብዬ እነግረዋለሁ፦ በከነዓን ምድር የነበሩት ወንድሞቼና የአባቴ ቤተ ሰዎች ወደ እኔ መጥተዋል፤ 32እነርሱም በግ የሚጠብቁ ሰዎች ናቸው እነርስሳ ያረቡ ነበርና በጎቻቸውንና ላሞቻቸውን ያላቸውንም ሁሉ አመጡ። 33ፈርዖንም ቢጠራችሁ፦ ተግባራችሁስ ምንድር ነው? ቢላችሁ፥ በግ ጠባቂ ሁሉ ለግብፅ ሰዎች ርኵስ ነውና በጌሤም እንድ 34ትቀመጡ እንዲህ በሉት፦ እኛ ባሪያዎችህ ከብላቴናነታችን ጀምረን እስለ አሁን ድረስ እኝም አባቶቻችንም እንስሳ አርቢዎች ነን።
Currently Selected:
ኦሪት ዘፍጥረት 46: አማ54
ማድመቅ
Share
Copy
ያደመቋቸው ምንባቦች በሁሉም መሣሪያዎችዎ ላይ እንዲቀመጡ ይፈልጋሉ? ይመዝገቡ ወይም ይግቡ