ዘፍጥረት 32:7-21

ዘፍጥረት 32:7-21 አዲሱ መደበኛ ትርጒም (NASV)

ያዕቆብም በታላቅ ፍርሀትና ጭንቀት ተውጦ፣ ዐብረውት የነበሩትን ሰዎች ሁለት ቦታ ከፈላቸው፤ በጎቹን፣ ፍየሎቹን፣ ከብቶቹንና ግመሎቹን ሁለት ቦታ ከፈላቸው። “ዔሳው መጥቶ በአንደኛው ላይ አደጋ ቢጥል፣ ሌላው ክፍል ሊያመልጥ ይችላል” ብሎ ዐስቦ ነበር። ያዕቆብ እንዲህ ሲል ጸለየ፤ “የአባቴ የአብርሃም አምላክ፣ የአባቴ የይሥሐቅ አምላክ ሆይ፤ ‘ወደ አገርህና ወደ ዘመዶችህ ተመለስ፤ እኔም በጎ ነገር አደርግልሃለሁ’ ያልኸኝ እግዚአብሔር ሆይ፤ እኔ ባሪያህ እስካሁን ላደረግህልኝ ቸርነትና ታማኝነት ብቁ አይደለሁም፤ ዮርዳኖስን ስሻገር በእጄ ላይ ከነበረው በትር በቀር ምንም አልነበረኝም፤ አሁን ግን ይኸው ሁለት ሰራዊት ሆኛለሁ። ከወንድሜ ከዔሳው እጅ እንድታድነኝ እለምንሃለሁ፤ መጥቶ እኔንም ሆነ እነዚህን እናቶች ከነልጆቻቸው ያጠፋናል ብዬ ፈርቻለሁና፤ ነገር ግን፣ አንተ ራስህ፣ ‘አበለጽግሃለሁ፤ ዘርህንም ሊቈጠር እንደማይቻል እንደ ባሕር አሸዋ አበዛዋለሁ’ ብለኸኛል።” በዚያችም ሌሊት ያዕቆብ እዚያው ዐደረ፤ ካለው ሀብት ለወንድሙ ለዔሳው እጅ መንሻ እነዚህን መረጠ፦ ሁለት መቶ እንስት ፍየሎችና ሃያ አውራ ፍየሎች፣ ሁለት መቶ እንስት በጎችና ሃያ አውራ በጎች፣ ሠላሳ የሚያጠቡ ግመሎች ከነግልገሎቻቸው፣ አርባ ላሞችና ዐሥር ኰርማዎች፣ ሃያ እንስት አህዮችና ዐሥር ተባዕት አህዮች። እነዚህንም በየመንጋው ለይቶ፣ የሚነዷቸውን ጠባቂዎች መደበላቸው፤ ጠባቂዎቹንም፣ “እናንተ ቀድማችሁኝ ሂዱ፣ መንጋዎቹንም አራርቃችሁ ንዷቸው” አላቸው። ቀድሞ የሚሄደውንም እንዲህ ሲል አዘዘው፤ “ዔሳው አግኝቶህ፣ ‘የማን ነህ? ወዴትስ ትሄዳለህ? የምትነዳውስ ይህ ሁሉ ከብት የማን ነው?’ ብሎ ቢጠይቅህ፣ ‘የአገልጋይህ የያዕቆብ ናቸው፤ ለጌታዬ ለዔሳው እጅ መንሻ የሰደዳቸው ናቸው፤ እርሱም ከበስተኋላችን እየመጣ ነው’ ብለህ ንገረው።” እንዲሁም ሁለተኛውን፣ ሦስተኛውንና መንጎችን የሚነዱትን ሌሎቹንም ሁሉ እንዲህ ሲል አዘዛቸው፤ “ዔሳውን ስታገኙት ይህንኑ ትነግሩታላችሁ፤ በተለይም ‘አገልጋይህ ያዕቆብ ከኋላችን እየመጣ ነው’ ማለትን አትዘንጉ።” ይህንም ያዘዘው፣ “ዔሳው ከእኔ ጋራ ከመገናኘቱ በፊት እጅ መንሻዬ አስቀድሞ ቢደርሰው ምናልባት ልቡ ይራራና በሰላም ይቀበለኛል” ብሎ ስላሰበ ነበር። ስለዚህ የያዕቆብ እጅ መንሻ ከርሱ አስቀድሞ ተላከ፤ እርሱ ራሱ ግን እዚያው በሰፈሩበት ቦታ ዐደረ።

ዘፍጥረት 32:7-21 የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) (አማ2000)

ያዕ​ቆ​ብም እጅግ ፈራ፤ የሚ​ያ​ደ​ር​ገ​ው​ንም አጣ። ከእ​ር​ሱም ጋር ያሉ​ትን ሰዎች ላሞ​ች​ንም፥ ግመ​ሎ​ች​ንም፥ በጎ​ች​ንም ሁለት ወገን አድ​ርጎ ከፈ​ላ​ቸው፤ ያዕ​ቆ​ብም እን​ዲህ አለ፥ “ዔሳው መጥቶ አን​ዱን ወገን የመታ እንደ ሆነ የቀ​ረው ወገን ይድ​ናል።” ያዕ​ቆ​ብም አለ፥ “የአ​ባቴ የአ​ብ​ር​ሃም አም​ላክ ሆይ፥ የአ​ባቴ የይ​ስ​ሐቅ አም​ላክ ሆይ፥ ‘ወደ ምድ​ርህ ወደ ተወ​ለ​ድ​ህ​በ​ትም ስፍራ ተመ​ለስ፤ በጎ​ነ​ት​ንም አደ​ር​ግ​ል​ሃ​ለሁ’ ያል​ኸኝ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ሆይ፥ ለባ​ሪ​ያህ በአ​ደ​ረ​ግ​ኸው በም​ሕ​ረ​ት​ህና በእ​ው​ነ​ት​ህም ሁሉ በጎ​ውን አድ​ር​ግ​ልኝ፤ በት​ሬን ብቻ ይዤ ይህን ዮር​ዳ​ኖ​ስን ተሻ​ግሬ ነበ​ርና፥ አሁን ግን የሁ​ለት ክፍል ሠራ​ዊት ሆንሁ። አቤቱ ከወ​ን​ድሜ ከዔ​ሳው እጅ አድ​ነኝ፤ መጥቶ እን​ዳ​ያ​ጠ​ፋኝ፥ እና​ትን ከል​ጆ​ችዋ ጋር እን​ዳ​ያ​ጠፋ እኔ እፈ​ራ​ዋ​ለ​ሁና። አን​ተም፦ ‘በር​ግጥ መል​ካም አደ​ር​ግ​ል​ሃ​ለሁ፥ ዘር​ህ​ንም ከብ​ዛቱ የተ​ነሣ እን​ደ​ማ​ይ​ቈ​ጠር እንደ ባሕር አሸዋ አደ​ር​ጋ​ለሁ ብለህ ነበር።’ ” በዚ​ያ​ችም ሌሊት በዚ​ያው አደረ። ለወ​ን​ድሙ ለዔ​ሳ​ውም የሚ​ወ​ስ​ደ​ውን እጅ መንሻ አወጣ፤ ሁለት መቶ እን​ስት ፍየ​ሎ​ች​ንና ሃያ የፍ​የል አው​ራ​ዎ​ችን፥ ሁለት መቶ እን​ስት በጎ​ች​ንና ሃያ የበግ አው​ራ​ዎ​ችን፥ ሃምሳ የሚ​ያ​ጠቡ ግመ​ሎ​ችን ከግ​ል​ገ​ሎ​ቻ​ቸው ጋር፥ አርባ ላም፥ ዐሥር በሬ፥ ሃያ እን​ስት አህያ፥ ዐሥ​ርም የአ​ህያ ውር​ን​ጫ​ዎች፤ መን​ጎ​ቹ​ንም ለየ​ብቻ ከፍሎ ለብ​ላ​ቴ​ኖቹ ሰጣ​ቸው፤ ብላ​ቴ​ኖ​ቹ​ንም፥ “በፊቴ እለፉ፤ መን​ጋ​ውን ከመ​ን​ጋው አርቁ” አላ​ቸው። የፊ​ተ​ኛ​ው​ንም እን​ዲህ ብሎ አዘ​ዘው፥ “ወን​ድሜ ዔሳው ያገ​ኘህ እንደ ሆነ፦ ‘አንተ የማን ነህ? ወዴ​ትስ ትሄ​ዳ​ለሀ? በፊ​ትህ ያለው ይህስ መንጋ የማን ነው?’ ብሎ የጠ​የ​ቀ​ህም እን​ደ​ሆነ፥ በዚያ ጊዜ አንተ፦ ‘ለጌ​ታዬ ለዔ​ሳው እጅ መንሻ የላ​ከው የአ​ገ​ል​ጋ​ይህ የያ​ዕ​ቆብ ነው፤ እር​ሱም ደግሞ እነሆ ከኋ​ላ​ችን ተከ​ት​ሎ​ናል’ በለው።” እን​ዲ​ሁም ሁለ​ተ​ኛ​ው​ንና ሦስ​ተ​ኛ​ውን፥ በፊቱ የሚ​ሄ​ዱ​ት​ንና መን​ጋ​ውን የሚ​ነ​ዱ​ትን ሁሉ እን​ዲሁ ብሎ አዘዘ፦“ ወን​ድሜ ዔሳ​ውን ባገ​ኛ​ች​ሁት ጊዜ ይህ​ንኑ ነገር ንገ​ሩት፤ እን​ዲ​ህም በሉ፦ እነሆ አገ​ል​ጋ​ይህ ያዕ​ቆብ ከኋ​ላ​ችን ነው። በፊቴ በሚ​ሄ​ደው እጅ መንሻ እታ​ረ​ቀ​ዋ​ለሁ፤ ከዚ​ያም በኋላ ምና​ል​ባት ይራ​ራ​ል​ኛል፤ ፊቱ​ንም አያ​ለሁ ብሎ​አ​ልና።” እጅ መን​ሻ​ውን ከእ​ርሱ አስ​ቀ​ድሞ ላከ፤ እርሱ ግን በዚ​ያች ሌሊት በሰ​ፈር አደረ።

ዘፍጥረት 32:7-21 አዲሱ መደበኛ ትርጒም (NASV)

ያዕቆብም በታላቅ ፍርሀትና ጭንቀት ተውጦ፣ ዐብረውት የነበሩትን ሰዎች ሁለት ቦታ ከፈላቸው፤ በጎቹን፣ ፍየሎቹን፣ ከብቶቹንና ግመሎቹን ሁለት ቦታ ከፈላቸው። “ዔሳው መጥቶ በአንደኛው ላይ አደጋ ቢጥል፣ ሌላው ክፍል ሊያመልጥ ይችላል” ብሎ ዐስቦ ነበር። ያዕቆብ እንዲህ ሲል ጸለየ፤ “የአባቴ የአብርሃም አምላክ፣ የአባቴ የይሥሐቅ አምላክ ሆይ፤ ‘ወደ አገርህና ወደ ዘመዶችህ ተመለስ፤ እኔም በጎ ነገር አደርግልሃለሁ’ ያልኸኝ እግዚአብሔር ሆይ፤ እኔ ባሪያህ እስካሁን ላደረግህልኝ ቸርነትና ታማኝነት ብቁ አይደለሁም፤ ዮርዳኖስን ስሻገር በእጄ ላይ ከነበረው በትር በቀር ምንም አልነበረኝም፤ አሁን ግን ይኸው ሁለት ሰራዊት ሆኛለሁ። ከወንድሜ ከዔሳው እጅ እንድታድነኝ እለምንሃለሁ፤ መጥቶ እኔንም ሆነ እነዚህን እናቶች ከነልጆቻቸው ያጠፋናል ብዬ ፈርቻለሁና፤ ነገር ግን፣ አንተ ራስህ፣ ‘አበለጽግሃለሁ፤ ዘርህንም ሊቈጠር እንደማይቻል እንደ ባሕር አሸዋ አበዛዋለሁ’ ብለኸኛል።” በዚያችም ሌሊት ያዕቆብ እዚያው ዐደረ፤ ካለው ሀብት ለወንድሙ ለዔሳው እጅ መንሻ እነዚህን መረጠ፦ ሁለት መቶ እንስት ፍየሎችና ሃያ አውራ ፍየሎች፣ ሁለት መቶ እንስት በጎችና ሃያ አውራ በጎች፣ ሠላሳ የሚያጠቡ ግመሎች ከነግልገሎቻቸው፣ አርባ ላሞችና ዐሥር ኰርማዎች፣ ሃያ እንስት አህዮችና ዐሥር ተባዕት አህዮች። እነዚህንም በየመንጋው ለይቶ፣ የሚነዷቸውን ጠባቂዎች መደበላቸው፤ ጠባቂዎቹንም፣ “እናንተ ቀድማችሁኝ ሂዱ፣ መንጋዎቹንም አራርቃችሁ ንዷቸው” አላቸው። ቀድሞ የሚሄደውንም እንዲህ ሲል አዘዘው፤ “ዔሳው አግኝቶህ፣ ‘የማን ነህ? ወዴትስ ትሄዳለህ? የምትነዳውስ ይህ ሁሉ ከብት የማን ነው?’ ብሎ ቢጠይቅህ፣ ‘የአገልጋይህ የያዕቆብ ናቸው፤ ለጌታዬ ለዔሳው እጅ መንሻ የሰደዳቸው ናቸው፤ እርሱም ከበስተኋላችን እየመጣ ነው’ ብለህ ንገረው።” እንዲሁም ሁለተኛውን፣ ሦስተኛውንና መንጎችን የሚነዱትን ሌሎቹንም ሁሉ እንዲህ ሲል አዘዛቸው፤ “ዔሳውን ስታገኙት ይህንኑ ትነግሩታላችሁ፤ በተለይም ‘አገልጋይህ ያዕቆብ ከኋላችን እየመጣ ነው’ ማለትን አትዘንጉ።” ይህንም ያዘዘው፣ “ዔሳው ከእኔ ጋራ ከመገናኘቱ በፊት እጅ መንሻዬ አስቀድሞ ቢደርሰው ምናልባት ልቡ ይራራና በሰላም ይቀበለኛል” ብሎ ስላሰበ ነበር። ስለዚህ የያዕቆብ እጅ መንሻ ከርሱ አስቀድሞ ተላከ፤ እርሱ ራሱ ግን እዚያው በሰፈሩበት ቦታ ዐደረ።

ዘፍጥረት 32:7-21 መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) (አማ54)

ያዕቆብም እጅግ ፈርቶ ተጨነቀ ከእርሱም ጋር ያሉትን ሰዎች መንጎችንም ላሞችንም ግመሎችንም በሁለት ወገን ከፈላቸው እንዲህም አለ፦ ዔሳው መጥቶ አንድን ወገን የመታ እንደ ሆነ የቀረው ወገን ያመልጣል። ያዕቆብም አለ፦ የአባቴ የአብርሃም አምላክ ሆይ፦ ወደ ምድርህ ወደ ተወለድህበትም ስፍራ ተመለስ በጎነትንም አደርግልሃለሁ ያልኸኝ እግዚአብሔር ሆይ ለባሪያህ ከሠራኸው ከምሕረትህን ከእውነትህም ሁሉ ትንሽ ስ ስንኳ የማይገባኝ ነኝ፤ በትሬን ብቻ ይዤ ይህን ዮርዳኖስን ተሻግሬ ነበርና አሁን ግን የሁለት ክፍል ሠራዊት ሆንሁ። ከወንድሜ ከዔሳው እጅ አድነኝ፤ መጥቶ እንዳያጠፋኝ እናቶችንም ከልጆች ጋር እንዳያጠፋ እኔ እፈራዋለሁና። አንተም፦ በእርግጥ መልካም አደርግልሃለሁ፥ ዘርህንም ከብዛቱ የተንሣ እንድማይቈጠር እንደ ባሕር አሸዋ አደርጋለሁ ብለህ ነበር። በዚይችም ሌሊት ከዚያው አደረ። ከያዘውም ሁሉ ለወንድሙ ለዔሳ እጅ መንሻን አወጣ፤ ሁለት መቶ እንስት ፍየሎችንና ሀያ የፍየል አውራዎችም ሁለት መቶ እንስት በጎችንና ሀያ የበግ አውራዎችን ሠላሳ የሚያጠቡ ግመሎችም ከግልገሎቻቸው ጋር አርባ ላም አሥር በሬ ሀያ እንስት አህያ አሥርም የእህያ ግልገሎችን። መንጎቹን፥ በየወገኑ ከፍሎ በባሪያዎቹ እጅ አደረጋቸ ባሪያዎቹን፦ በፊቴ እለፉ መንጋውንና መንጋውንም አራርቁት አለ። የፊተኛውንም እንዲህ ብሎ አዘዘው፦ ወንድሜ ዔሳው ያገኘህ እንደሆነ፦ አንተ የማን ነህ? ወዴትስ ትሄዳለህ? በፊትህ ያለው ይህስ የማን ነው? ብሎ የጠየቀህም እንደ ሆነ፥ በዚያን ጊዜ አንተ ለጌታዬ ለዔሳው እጅ መንሻ የሰደደው የባሪያህ የያዕቆብ ነው እርሱም ደግሞ እነሆ ከኍላችን ነው በለው። እንዲሁም ሁለተኛውንና ሦስተኛውን ከመንጎችም በኍላ የሚሄዱትን ሁሉ እንዱሁ ብሎ አዘዘ፦ ዔሳውን ባገኛችሁት ጊዜ ይህንኑ ነገር ንገሩት እንዲህም በሉት፦ እነሆ ባሪያህ ያዕቆብ ከኍላችን ነው። በፊቴ በሚሄደው እጅ መንሻ እታረቀዋለሁ፤ ከዚያም በኍላ ምናልባት ይራራልኛል ፊቱንም አያለሁ ብሎአልና። እጅ መንሻው ከእርሱ ቀድሞ አለፈ እርሱ ግን በዚያች ሌሊት በሰፈር አደረ።

ዘፍጥረት 32:7-21 አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም (አማ05)

በዚህ ጊዜ ያዕቆብ እጅግ በመፍራት ተጨነቀ፤ አብረውት የነበሩትንም ሰዎች በሁለት ክፍል መደባቸው፤ እንዲሁም በጎቹን፥ ፍየሎቹን፥ ከብቶቹንና ግመሎቹን በሁለት በሁለት መደባቸው። ይህንንም ያደረገው “ዔሳው መጥቶ በድንገተኛ አደጋ የመጀመሪያውን ክፍል ቢያጠቃ፥ ሌላው ክፍል ሊያመልጥ ይችላል” ብሎ በማሰብ ነው። ከዚህ በኋላ ያዕቆብ እንዲህ ብሎ ጸለየ፤ “የአባቶቼ የአብርሃምና የይስሐቅ አምላክ ሆይ! ልመናዬን አድምጥ፤ አምላክ ሆይ፥ ‘ወደ ትውልድ አገርህና ወደ ዘመዶችህ ተመለስ፤ እዚያም መልካም ነገር እንዲሆንልህ አደርጋለሁ’ ብለኸኝ ነበር። እኔ ባሪያህ ይህን ያኽል ቸርነትና ታማኝነት ልታሳየኝ የሚገባኝ አልነበርኩም፤ ዮርዳኖስን ተሻግሬ ስመጣ ከምመረኰዘው በትር በቀር ምንም አልነበረኝም፤ አሁን ግን እነዚህን በሁለት ቡድን የተከፈሉ ወገኖች ይዤ ተመልሻለሁ። በእኔ ላይ አደጋ በመጣል ሴቶችና ሕፃናት እንኳ ሳይቀሩ ያጠፋናል ብዬ ስለ ፈራሁ ከወንድሜ ከዔሳው እጅ እንድታድነኝ እለምንሃለሁ፤ ‘መልካም ነገር አደርጋለሁ፤ ዘርህንም ሊቈጠር እንደማይቻል እንደ ባሕር ዳር አሸዋ አበዛልሃለሁ’ ያልከውን አስታውስ።” እዚያም ዐደረ፤ በማግስቱም ካለው ነገር ሁሉ ለወንድሙ ለዔሳው ስጦታ የሚሆን ነገር መርጦ አዘጋጀ፤ በዚህ ዐይነት ሁለት መቶ እንስት ፍየሎች፥ ኻያ ተባዕት ፍየሎች፥ ሁለት መቶ እንስት በጎች፥ ኻያ ተባዕት በጎች፤ ሠላሳ የሚያጠቡ ግመሎች ከነግልገሎቻቸው፥ አርባ ላሞች፥ ዐሥር ኰርማዎች፥ ኻያ እንስት አህዮችና ዐሥር ተባዕት አህዮች መረጠ፤ እነዚህንም በየመንጋው ከፈለና ለእያንዳንዳቸው እረኞች መደበላቸው፤ እረኞቹንም “ከእኔ ቀድማችሁ ሂዱ፤ በየመንጋው መካከል ርቀት እንዲኖር አድርጋችሁ፥ በመከታተል ሂዱ” አላቸው። የመጀመሪያዎቹንም እረኞች እንዲህ በማለት አዘዛቸው፤ “ወንድሜ ዔሳው በመንገድ አግኝቶ ‘የማን ሰዎች ናችሁ? ወዴትስ ትሄዳላችሁ? እነዚህ የምትነዱአቸው ከብቶች የማን ናቸው?’ ብሎ የጠየቃችሁ እንደ ሆነ፥ ‘እነዚህ ከብቶች የአገልጋይህ የያዕቆብ ናቸው፤ እርሱ እነዚህን የላከው ለጌታዬ ለዔሳው ስጦታ የሚሆን ነው፤ እነሆ ያዕቆብ ከኋላችን ነው’ ብላችሁ ንገሩት።” ለሁለተኛውም ለሦስተኛውም ክፍል እረኞችና ለቀሩትም የመንጋ ጠባቂዎች “እናንተም ዔሳውን ስታገኙት እንደዚሁ ንገሩት፤ ‘በተለይም አገልጋይህ ያዕቆብ ከበስተኋላ እየመጣ ነው’ ብላችሁ ንገሩት” አላቸው። ይህንንም ያለበት ምክንያት “እኔ ከመድረሴ በፊት በሚደርስለት ስጦታ ቊጣውን አበርድ ይሆናል፤ በኋላም በማገኘው ጊዜ በደስታ ይቀበለኛል” በሚል ሐሳብ ነው። በዚህ ዐይነት ስጦታውን አስቀድሞ ከላከ በኋላ፥ እዚያው በሰፈሩበት ቦታ ዐደረ።

ዘፍጥረት 32:7-21 መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) (መቅካእኤ)

ያዕቆብም እጅግ ፈራ ተጨነቀም፤ ከእርሱም ጋር ያሉትን ሰዎች፥ መንጎችን እና ከብቶችን ግመሎችንም፥ በሁለት ወገን ከፈላቸው፥ “ዔሳው መጥቶ አንዱን ወገን የመታ እንደሆነ የቀረው ወገን ያመልጣል።” ብሎም አሰበ። ያዕቆብም አለ፦ “የአባቴ የአብርሃም አምላክ ሆይ፥ የአባቴም የይስሐቅ አምላክ ሆይ፥ ‘ወደ ትውልድ አገርህ ወደ ተወለድህበትም ስፍራ ተመለስ፥ በጎነትንም አደርግልሃለሁ’ ያልኸኝ ጌታ ሆይ፥ ለባርያህ ካሳየኸው ከጽኑ ፍቅርና ከታማኝነትህ ሁሉ ትንሽ ስንኳ የማይገባኝ ነኝ፥ በትሬን ብቻ ይዤ ይህን ዮርዳኖስን ተሻግሬ ነበር፥ አሁን ግን ለሁለት ወገን የተከፈልኩ ሆንሁ። ከወንድሜ ከዔሳው እጅ አድነኝ፥ መጥቶ እንዳያጠፋኝ፥ እናቶችንም ከልጆች ጋር እንዳያጠፋ እኔ እፈራዋለሁና። አንተም፦ ‘በእርግጥ መልካም አደርግልሃለሁ፥ ዘርህንም ከብዛቱ የተነሣ እንደማይቈጠር እንደ ባሕር አሸዋ አደርጋለሁ’ ብለህ ነበር።” በዚያችም ሌሊት ከዚያው ሰፈረ። ከያዘውም ሁሉ ለወንድሙ ለዔሳው ስጦታ የሚሆን አወጣ፥ ሁለት መቶ እንስት ፍየሎችንና ሀያ የፍየል አውራዎችን፥ ሁለት መቶ እንስት በጎችንና ሀያ የበግ አውራዎችን፥ ሠላሳ የሚያጠቡ ግመሎችን ከግልገሎቻቸው ጋር፥ አርባ ላም፥ ዐሥር በሬ፥ ሀያ እንስት አህያ፥ ዐሥርም እህዮችን፤ እነዚህንም መንጎቹ በየወገኑ ከፍሎ በአገልጋዮቹ እጅ አደረጋቸው፥ አገልጋዮቹንም፦ “ከእኔ ቀድማችሁ ሂዱ፥ በመንጋው እና መንጋው መካከልም እርቀት አኑሩ” አለ። የፊተኛውንም እንዲህ ብሎ አዘዘው፦ “ወንድሜ ዔሳው ያገኘህ እንደሆነ፥ ‘አንተ የማን ነህ? ወዴትስ ትሄዳለህ? በፊትህ ያለው ይህስ የማን ነው?’ ብሎ የጠየቀህም እንደሆነ፥ በዚያን ጊዜ አንተ፦ ‘ለጌታዬ ለዔሳው እጅ መንሻ የላከው የባርያህ የያዕቆብ ነው፥ እርሱም ደግሞ እነሆ ከኋላችን ነው’ በለው።” እንዲሁም ሁለተኛውንና ሦስተኛውን ከመንጎችም በኋላ የሚሄዱትን ሁሉ እንዱሁ ብሎ አዘዘ፦ “ዔሳውን ባገኛችሁት ጊዜ ይህንኑ ነገር ንገሩት። ‘እንዲሁም ባርያህ ያዕቆብ ከኋላችን ነው’ እንድትሉት። እሱ ‘በፊቴ በሚሄደው እጅ መንሻ እታረቀዋለሁ፥ ከዚያም በኋላ ምናልባት ይቀበለኛል ፊቱንም አያለሁ’ ብሎ አስቧል።” ስለዚህ እጅ መንሻው ከእርሱ ቀድሞ አለፈ፥ እርሱ ግን በዚያች ሌሊት እዚያው በሰፈሩበት አደረ።