የYouVersion አርማ
የፍለጋ አዶ

ዕዝራ 5:6-17

ዕዝራ 5:6-17 የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) (አማ2000)

በወ​ንዙ ማዶ የነ​በ​ረው ገዥ ተን​ት​ናይ፥ ደግሞ አስ​ተ​ር​ቡ​ዝ​ናይ፥ ተባ​ባ​ሪ​ዎ​ቻ​ቸ​ውም፥ በወ​ንዙ ማዶ የነ​በ​ሩት አፈ​ር​ስ​ካ​ው​ያ​ንም ወደ ንጉሡ ወደ ዳር​ዮስ የላ​ኩት የደ​ብ​ዳ​ቤው ቃል ይህ ነበረ። እን​ዲ​ህም የሚል ደብ​ዳቤ ላኩ​ለት፥ “ለን​ጉሡ ለዳ​ር​ዮስ ሙሉ ሰላም ይሁን፤ ወደ ይሁዳ ሀገር ወደ ታላ​ቁም አም​ላክ ቤት እንደ ሄድን ንጉሡ ይወቅ፤ እር​ሱም በጥሩ ድን​ጋይ ይሠ​ራል፤ በቅ​ጥ​ሩም ውስጥ ልዩ እን​ጨት ይደ​ረ​ጋል፤ ያም ሥራ በት​ጋት ይሠ​ራል፤ በእ​ጃ​ቸ​ውም ይከ​ና​ወ​ናል። እነ​ዚ​ያ​ንም ሽማ​ግ​ሌ​ዎች፦ ‘ይህን ቤት ትሠሩ ዘንድ ማን አዘ​ዛ​ችሁ? የም​ት​ሠ​ሩ​በ​ት​ንስ ሥል​ጣን ማን ሰጣ​ችሁ?’ ብለን ጠየ​ቅ​ና​ቸው። ደግ​ሞም እና​ስ​ታ​ው​ቅህ ዘንድ፥ በእ​ነ​ር​ሱም ያሉ​ትን ሹሞች ስም እን​ጽ​ፍ​ልህ ዘንድ ስማ​ቸ​ውን ጠየ​ቅን። እን​ደ​ዚ​ህም ብለው መለ​ሱ​ልን፦ እኛ የሰ​ማ​ይና የም​ድር አም​ላክ ባሪ​ያ​ዎች ነን፥ ከብ​ዙም ዘመን ጀምሮ ተሠ​ርቶ የነ​በ​ረ​ውን፥ ታላ​ቁም የእ​ስ​ራ​ኤል ንጉሥ ሠርቶ ፈጽ​ሞ​ላ​ቸው የነ​በ​ረ​ውን ቤት እን​ሠ​ራ​ለን። አባ​ቶ​ቻ​ች​ንም የሰ​ማ​ይን አም​ላክ ከአ​ስ​ቈጡ በኋላ በከ​ለ​ዳ​ዊው በባ​ቢ​ሎን ንጉሥ በና​ቡ​ከ​ደ​ነ​ፆር እጅ አሳ​ልፎ ሰጣ​ቸው፤ እር​ሱም ይህን ቤት አፈ​ረሰ፤ ሕዝ​ቡ​ንም ወደ ባቢ​ሎን አፈ​ለሰ። ነገር ግን በባ​ቢ​ሎን ንጉሥ በቂ​ሮስ በመ​ጀ​መ​ሪ​ያው ዓመት ንጉሡ ቂሮስ ይህን የእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርን ቤት ይሠሩ ዘንድ አዘዘ። ናቡ​ከ​ደ​ነ​ፆ​ርም በኢ​የ​ሩ​ሳ​ሌም ከነ​በ​ረው መቅ​ደስ የወ​ሰ​ደ​ውን፥ ወደ ባቢ​ሎ​ንም መቅ​ደስ ያፈ​ለ​ሰ​ውን የእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርን ቤት የወ​ር​ቁ​ንና የብ​ሩን ዕቃ ንጉሡ ቂሮስ ከባ​ቢ​ሎን መቅ​ደስ አው​ጥቶ ለቤተ መዛ​ግ​ብቱ ሹም ለሲ​ሳ​ብ​ሳር ሰጠ​ውና፦ ‘ይህን ዕቃ ይዘህ ሂድ፤ በኢ​የ​ሩ​ሳ​ሌ​ምም ባለው መቅ​ደስ በቦ​ታው አኑ​ረው፤ የእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርም ቤት በስ​ፍ​ራው ይሠራ’ አለው። በዚያ ጊዜም ይህ ሲሳ​ብ​ሳር መጣ፤ በኢ​የ​ሩ​ሳ​ሌ​ምም ያለ​ውን የእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርን ቤት መሠ​ረተ፤ ከዚ​ያም ጊዜ ጀምሮ እስከ ዛሬ ድረስ እየ​ተ​ሠራ አል​ተ​ጨ​ረ​ሰም። አሁ​ንም ይህ ነገር በን​ጉሡ ዐይን መል​ካም ቢሆን ይህ የእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ቤት በኢ​የ​ሩ​ሳ​ሌም ይሠራ ዘንድ ከን​ጉሡ ከቂ​ሮስ ታዝዞ እንደ ሆነ በባ​ቢ​ሎን ባለው በን​ጉሡ ቤተ መዛ​ግ​ብት ይመ​ር​መር፤ ስለ​ዚ​ህም ነገር ንጉሡ ፈቃ​ዱን ይላ​ክ​ልን።”

ዕዝራ 5:6-17 አዲሱ መደበኛ ትርጒም (NASV)

በኤፍራጥስ ማዶ ገዥ የነበረው ተንትናይ፣ ሰተርቡዝናይ፣ ተባባሪዎቻቸውና በኤፍራጥስ ማዶ የነበሩ ሹማምት ለንጉሥ ዳርዮስ የላኩት ደብዳቤ ቅጅ ይህ ነው፤ የላኩትም ደብዳቤ እንዲህ የሚል ነበር፤ ለንጉሥ ዳርዮስ፣ የከበረ ሰላምታ እናቀርባለን። የታላቁ አምላክ ቤተ መቅደስ ወደሚገኝበት ወደ ይሁዳ አውራጃ ሄደን እንደ ነበር በንጉሡ ዘንድ የታወቀ ይሁን። ሕዝቡ ቤተ መቅደሱን በታላላቅ ድንጋዮች እየገነቡና ቅጥሩንም በወፍራም ምሰሶዎች እየሠሩ ነው፤ ሥራው በትጋት በመከናወንና በእነርሱም አመራር በመፋጠን ላይ ይገኛል። እኛም መሪዎቹን፣ “ይህን ቤተ መቅደስ እንደ ገና ለመሥራትና ይህንም ውቅር ለመጠገን የፈቀደላችሁ ማን ነው?” ብለን ጠየቅናቸው። የመሪዎቻቸውን ስም በጽሑፍ እናሳውቅህ ዘንድ ስማቸውን ደግሞ ጠየቅን። የሰጡን መልስ ይህ ነው፤ “እኛ የሰማይና የምድር አምላክ አገልጋዮች ነን፤ አሁንም እንደ ገና የምንሠራው ቤተ መቅደስ፣ ከብዙ ዘመናት በፊት ታላቁ የእስራኤል ንጉሥ ሠርቶ የጨረሰውን ነው። ነገር ግን አባቶቻችን የሰማይን አምላክ አስቈጥተውት ስለ ነበር፣ ለባቢሎኑ ንጉሥ ለከለዳዊው ናቡከደነፆር አሳልፎ ሰጣቸው፤ እርሱም ይህን ቤተ መቅደስ አፈራርሶ ሕዝቡን ወደ ባቢሎን አፈለሰ። “ይሁንና ቂሮስ፣ የባቢሎን ንጉሥ በሆነ በመጀመሪያው ዓመት ይህን የእግዚአብሔር ቤት እንደ ገና እንዲሠሩ ንጉሥ ቂሮስ ትእዛዝ ሰጠ። ናቡከደነፆር ከኢየሩሳሌም ቤተ መቅደስ አውጥቶ ባቢሎን በሚገኘው ቤተ መቅደስ ውስጥ ያኖራቸውን የእግዚአብሔርን ቤት የወርቅና የብር ዕቃዎች ከባቢሎን ቤተ መቅደስ አስመጣ። ከዚያም ንጉሥ ቂሮስ፣ አገረ ገዥ አድርጎ ለሾመውና ሰሳብሳር ተብሎ ለሚጠራው ሰው ሰጠው፤ ቀጥሎም፣ ‘እነዚህን ዕቃዎች ይዘህ ሂድና በኢየሩሳሌም ቤተ መቅደስ ውስጥ አኑራቸው፤ የእግዚአብሔር ቤት ቀድሞ በነበረበት ቦታ እንደ ገና ይሠራ’ አለው። “ስለዚህ ይህ ሰሳብሳር መጥቶ በኢየሩሳሌም የሚገኘውን የእግዚአብሔርን ቤተ መቅደስ መሠረት ጣለ፤ ከዚያን ቀን ጀምሮ እስከ ዛሬ ድረስ እነሆ በመሠራት ላይ ነው፤ ሆኖም ገና አላለቀም።” አሁንም ንጉሡን ደስ የሚያሰኘው ቢሆን፣ ይህ የእግዚአብሔር ቤት በኢየሩሳሌም እንዲሠራ ንጉሥ ቂሮስ በርግጥ ትእዛዝ ሰጥቶ እንደ ሆነ በባቢሎን ቤተ መንግሥት ግምጃ ቤት የተቀመጡት መዛግብት እንዲመረመሩ ያድርግ፤ ከዚያም ንጉሡ ስለዚህ ጕዳይ የወሰነውን ይላክልን።

ዕዝራ 5:6-17 መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) (አማ54)

በወንዙ ማዶ የነበረው ገዥ ተንትናይ፥ ደግሞ ሰተርቡዝናይ፥ ተባባሪዎቹና በወንዙ ማዶ የነበሩት አፈርስካውያን ወደ ንጉሡ ወዳ ዳርዮስ የላኩት የደብዳቤው ግልባጭ ይህ ነበረ። እንዲህም የሚል ደብዳቤ ላኩለት፦ “ለንጉሡ ለዳርዮስ ሙሉ ሰላም ይሁን፤ ወደ ይሁዳ አገር ወደ ታላቁም አምላክ ቤት እንደ ሄድን ንጉሡ ይወቅ፤ እርሱም በትልቅ ድንጋይ ተሠራ፤ በቅጥሩም ውስጥ እንጨት ተደረገ፤ ያም ሥራ በትጋት ይሠራል፤ በእጃቸውም ይከናወናል። እነዚያንም ሽማግሌዎች፦ ‘ይህን ቤት ትሠሩ ዘንድ፥ ይህንስ ቅጥር ታድሱ ዘንድ ያዘዛችሁ ማን ነው?’ ብለን ጠየቅናቸው። ደግሞም እናስታውቅህ ዘንድ፥ በእነርሱም ያሉትን ሹሞች ስም እንጽፍልህ ዘንድ ስማቸውን ጠየቅን። እንደዚህም ብለው መለሱልን፦ ‘እኛ የሰማይና የምድር አምላክ ባሪያዎች ነን፤ ከብዙም ዘመን ጀምሮ ተሠርቶ የነበረውን፥ ታላቁም የእሥራኤል ንጉሥ ሠርቶ የፈጸመውን ቤት እንሠራለን። አባቶቻችንም የሰማይን አምላክ ካስቈጡ በኋላ በከለዳዊው በባቢሎን ንጉሥ በናቡከደነፆር እጅ አሳልፎ ሰጣቸው፤ እርሱም ይህን ቤት አፈረሰ፤ ሕዝቡንም ወደ ባቢሎን አፈለሰ። ነገር ግን በባቢሎን ንጉሥ በቂሮስ በመጀመሪያው ዓመት ንጉሡ ቂሮስ ይህን የእግዚአብሔርን ቤት ይሠሩ ዘንድ አዘዘ። ናቡከደነፆርም በኢየሩሳሌም ከነበረው መቅደስ የወሰደውን፥ ወደ ባቢሎንም መቅደስ ያፈለሰውን የእግዚአብሔርን ቤት የወርቅንና የብርን ዕቃ ንጉሡ ቂሮስ ከባቢሎን መቅደስ አውጥቶ ሰሳብሳር ለተባለው ለሹሙ ሰጠውና፦ “ይህን ዕቃ ይዘህ ሂድ፤ በኢየሩሳሌምም ባለው መቅደስ አኑረው፤ የእግዚአብሔርም ቤት በስፍራው ይሠራ” አለው። በዚያ ጊዜም ይህ ሰሳብሳር መጣ፤ በኢየሩሳሌምም ያለውን የእግዚአብሔርን ቤት መሠረተ፤ ከዚያም ጊዜ ጀምሮ እስከ ዛሬ ድረስ እየተሠራ አልተጨረሰም።’ አሁንም ይህ ነገር በንጉሡ ዓይን መልካም ቢሆን ይህ የእግዚአብሔር ቤት በኢየሩሳሌም ይሠራ ዘንድ ከንጉሡ ከቂሮስ ታዝዞ እንደ ሆነ በባቢሎን ባለው በንጉሡ ቤተ መዛግብት ይመርመር፤ ስለዚህም ነገር ንጉሡ ፈቃዱን ይላክልን።”

ዕዝራ 5:6-17 አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም (አማ05)

የኤፍራጥስ ምዕራባዊ ክፍል ገዢ የነበረው ታተናይና ሽታርቦዝናይ እንዲሁም ተባባሪዎቻቸው የሆኑ ለንጉሥ ዳርዮስ የጻፉት ደብዳቤ የሚከተለው ነው፦ “ለግርማዊ ንጉሠ ነገሥት ዳርዮስ! ግዛትዎ ሰላም ይሁን፤ ወደ ይሁዳ ምድር ሄደን የታላቁ አምላክ ቤተ መቅደስ በድንጋይና በጠርብ እንጨት ሲሠራ ማየታችን ለግርማዊነትዎ የታወቀ ይሁን፤ ሥራውም በሽማግሌዎቹ መሪነት በጥንቃቄና በፍጥነት እየተሠራ ነው። “እኛም የሕዝቡን መሪዎች ‘ይህን ቤተ መቅደስ እንደገና መልሳችሁ ለመሥራትና ቅጽሮቹንም ለማደስ ማን ፈቀደላችሁ?’ ብለን ጠየቅናቸው፤ የዚህ ሥራ መሪዎችም እነማን እንደ ሆኑ እንገልጥልህ ዘንድ የስም ዝርዝራቸውን ጠይቀናል። “እነርሱም እንዲህ ሲሉ አስረድተውናል፤ ‘እኛ ሰማይንና ምድርን የፈጠረ የታላቁ እግዚአብሔር አገልጋዮች ነን፤ ስለዚህም ለእርሱ ከብዙ ዘመን በፊት በአንድ ታላቅ የእስራኤል ንጉሥ ተሠርቶለት የነበረውን ቤተ መቅደስና ቅጽር እንደገና መልሰን በመሥራት ላይ እንገኛለን፤ ነገር ግን የቀድሞ አባቶቻችን ይህን የሰማይ አምላክ በማስቈጣታቸው ምክንያት በከለዳውያን ሥርወ መንግሥት የባቢሎን ንጉሠ ነገሥት በሆነው በናቡከደነፆር ጦር እንዲሸነፉ አደረገ፤ ቤተ መቅደሱ ፈራረሰ፤ ሕዝቡም ተማርኮ ወደ ባቢሎን ተወሰደ። ከዚህም በኋላ ቂሮስ የባቢሎን ንጉሠ ነገሥት በሆነ በመጀመሪያው ዓመት ይህን ቤተ መቅደስ መልሰን መሥራት እንድንችል በዐዋጅ የፈቀደልን ንጉሠ ነገሥቱ ቂሮስ ራሱ ነው። ናቡከደነፆር በዚሁ በኢየሩሳሌም ተሠርቶ ከነበረው ከቀድሞው ቤተ መቅደስ ማርኮ የወሰዳቸውንና በባቢሎን ማምለኪያ ስፍራው ውስጥ ያኖራቸውን ከወርቅና ከብር የተሠሩ ንዋያተ ቅድሳትም ሁሉ ቂሮስ መልሶ አስረክቦናል፤ ንዋያተ ቅድሳቱንም ያስረከበን የይሁዳ ገዢ አድርጎ በሾመው ሼሽባጻር ተብሎ በሚጠራው ሰው አማካይነት ነው። ይኸው አገረ ገዢው ሼሽባጻር እነዚህን ንዋያተ ቅድሳት መልሶ በማምጣት በኢየሩሳሌም ከነበረው ቤተ መቅደስ ውስጥ ያኖር ዘንድ፥ እንዲሁም ቤተ መቅደሱ ቀድሞ በነበረበት ስፍራ ላይ ተመልሶ እንዲሠራ ያደርግ ዘንድ፥ ንጉሠ ነገሥቱ ቂሮስ አዞታል። ስለዚህም ሼሽባጻር መጥቶ መሠረቱን ጣለ፤ ከዚያም በኋላ የሕንጻው ሥራ እንዲቀጥል ተደርጎ፥ ይኸው እስከ አሁን በመሠራት ላይ ነው፤ ነገር ግን የቤተ መቅደሱ ሕንጻ ገና አልተፈጸመም።’ “ንጉሥ ሆይ! እንግዲህ በእርግጥ ይህ ቤተ መቅደስ በኢየሩሳሌም ይሠራ ዘንድ ንጉሥ ቂሮስ የሰጠው ትእዛዝ መኖር አለመኖሩን ለማረጋገጥ በባቢሎን ቤተ መንግሥት የጽሑፍ ማስረጃዎችን አስመርምረህ በዚህ ጉዳይ ላይ ምን ዐይነት ውሳኔ ቢሰጥ እንደምትፈቅድ ታስታውቀን ዘንድ እንለምናለን።”

ዕዝራ 5:6-17 መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) (መቅካእኤ)

የደብዳቤውንም ግልባጭ በወንዝ ማዶ ያለ አካባቢ ገዢ ታትናይ፥ ሽታርቦዝናይና ተባባሪዎቻቸው በወንዙ ማዶ የነበሩ ባለ ሥልጣናት ወደ ንጉሡ ዳርዮስ ላኩለት፤ እንዲህም የሚል ደብዳቤ ላኩለት፦ “ለንጉሡ ዳርዮስ ሙሉ ሰላም ይሁን፤ ወደ ይሁዳ አገር ወደ ታላቁ አምላክ ቤትም እንደ ሄድን በንጉሡ ዘንድ ይታወቅ፥ እርሱም በትልቅ ድንጋይ ተሠራ፥ በቅጥሩም ውስጥ እንጨት ተደረገ፥ ያም ሥራ በጥንቃቄ ይሠራል፥ በእጃቸውም ይከናወናል። እኛም ሽማግሌዎቹን፦ ‘ይህን ቤት እንድትሠሩ፥ ይህንንም ቅጥር እንድታድሱ ማን አዘዛችሁ?’ ብለን ጠየቅናቸው። ደግሞም እንድታውቅ፥ በእነርሱ ላይ ያሉትን መሪዎች ስም እንድንጽፍልህ ስማቸውን ጠየቅን። የመለሱልን መልስ ይህ ነው፦ ‘እኛ የሰማያትና የምድር አምላክ አገልጋዮች ነን፥ ከብዙም ዘመን ጀምሮ ተሠርቶ የነበረ፥ ታላቅ የእሥራኤል ንጉሥ ሠርቶ የፈጸመውን ቤት እንሠራለን። ነገር ግን አባቶቻችን የሰማያትን አምላክ ስላስቆጡት በከለዳዊው በባቢሎን ንጉሥ በናቡከደነፆር እጅ አሳልፎ ሰጣቸው፥ እርሱም ይህን ቤት አፈረሰ፥ ሕዝቡንም ወደ ባቢሎን አፈለሰ። ነገር ግን በባቢሎን ንጉሥ በቂሮስ በመጀመሪያው ዓመት ንጉሡ ቂሮስ ይህን የእግዚአብሔርን ቤት እንዲሠሩ አዘዘ። ናቡከደነፆር በኢየሩሳሌም ከነበረው መቅደስ የወሰደውን፥ ወደ ባቢሎንም መቅደስ ያመጣውን የእግዚአብሔርን ቤት የወርቅንና የብርን ዕቃዎች ንጉሡ ቂሮስ ከባቢሎን መቅደስ አውጥቶ ሼሽባጻር ለተባለው፥ ገዢ ላደረገው ሰጠው፤ እነዚህን ዕቃዎች ውሰድ፥ በኢየሩሳሌምም ባለው መቅደስ አስቀምጠው የእግዚአብሔርም ቤት በስፍራው ይሠራ’” አለው። በዚያን ጊዜ ይህ ሼሽባጻር መጣ፥ በኢየሩሳሌምም ያለውን የእግዚአብሔርን ቤት መሠረተ፤ ከዚያም ጊዜ ጀምሮ እስከ ዛሬ ድረስ እየተሠራ ነው አላለቀምም። “አሁንም ይህ ነገር በንጉሡ ዐይን መልካም ቢሆን ይህ የእግዚአብሔር ቤት በኢየሩሳሌም እንዲሠራ ከንጉሡ ከቂሮስ ታዝዞ እንደሆነ በባቢሎን ባለው በንጉሡ ቤተ መዛግብት ይመርመር፥ ስለዚህም ነገር ንጉሡ ፈቃዱን ይላክልን።”