መጽ​ሐፈ ዕዝራ 5

5
የቤተ መቅ​ደሱ ሥራ እንደ ገና መቀ​ጠሉ
1ነቢ​ያቱ ሐጌና የአዶ ልጅ ዘካ​ር​ያስ በይ​ሁ​ዳና በኢ​የ​ሩ​ሳ​ሌም ለነ​በሩ አይ​ሁድ በእ​ስ​ራ​ኤል አም​ላክ ስም ትን​ቢት ተና​ገ​ሩ​ላ​ቸው። 2በዚ​ያን ጊዜም የሰ​ላ​ት​ያል ልጅ ዘሩ​ባ​ቤል የኢ​ዮ​ሴ​ዴ​ቅም ልጅ ኢያሱ ተነ​ሥ​ተው በኢ​የ​ሩ​ሳ​ሌም ያለ​ውን የእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርን ቤት መሥ​ራት ጀመሩ፤ የሚ​ያ​ግ​ዙ​አ​ቸ​ውም የእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ነቢ​ያት ከእ​ነ​ርሱ ጋር ነበሩ። 3በዚ​ያም ጊዜ በወ​ንዝ ማዶ የነ​በ​ረው ገዥ ተን​ት​ናይ፥ ደግሞ አስ​ተ​ር​ቡ​ዝ​ናይ ተባ​ባ​ሪ​ዎ​ቻ​ቸ​ውም ወደ እነ​ርሱ መጥ​ተው፥ “ይህን ቤት ትሠሩ ዘንድ ማን አዘ​ዛ​ችሁ? የም​ት​ሠ​ሩ​በ​ት​ንስ ሥል​ጣን ማን ሰጣ​ችሁ?” አሉ​አ​ቸው። 4ደግ​ሞም፥ “ይህ​ችን ከተ​ማስ የሚ​ሠሩ ሰዎች ስም ማን ማን ነው?” ብለው ጠየ​ቁ​አ​ቸው። 5የእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ዐይን ግን በይ​ሁዳ ምር​ኮ​ኞች#ዕብ. “ሽማ​ግ​ሌ​ዎች” ይላል። ላይ ነበረ፤ ይህም ነገር ወደ ዳር​ዮስ እስ​ኪ​ደ​ርስ ድረስ፥ መል​ሱም በመ​ል​እ​ክ​ተኛ እስ​ኪ​መጣ ድረስ አል​ከ​ለ​ከ​ሉ​አ​ቸ​ውም።
6በወ​ንዙ ማዶ የነ​በ​ረው ገዥ ተን​ት​ናይ፥ ደግሞ አስ​ተ​ር​ቡ​ዝ​ናይ፥ ተባ​ባ​ሪ​ዎ​ቻ​ቸ​ውም፥ በወ​ንዙ ማዶ የነ​በ​ሩት አፈ​ር​ስ​ካ​ው​ያ​ንም ወደ ንጉሡ ወደ ዳር​ዮስ የላ​ኩት የደ​ብ​ዳ​ቤው ቃል ይህ ነበረ። 7እን​ዲ​ህም የሚል ደብ​ዳቤ ላኩ​ለት፥ “ለን​ጉሡ ለዳ​ር​ዮስ ሙሉ ሰላም ይሁን፤ 8ወደ ይሁዳ ሀገር ወደ ታላ​ቁም አም​ላክ ቤት እንደ ሄድን ንጉሡ ይወቅ፤ እር​ሱም በጥሩ ድን​ጋይ ይሠ​ራል፤ በቅ​ጥ​ሩም ውስጥ ልዩ እን​ጨት ይደ​ረ​ጋል፤ ያም ሥራ በት​ጋት ይሠ​ራል፤ በእ​ጃ​ቸ​ውም ይከ​ና​ወ​ናል። 9እነ​ዚ​ያ​ንም ሽማ​ግ​ሌ​ዎች፦ ‘ይህን ቤት ትሠሩ ዘንድ ማን አዘ​ዛ​ችሁ? የም​ት​ሠ​ሩ​በ​ት​ንስ ሥል​ጣን ማን ሰጣ​ችሁ?’ ብለን ጠየ​ቅ​ና​ቸው። 10ደግ​ሞም እና​ስ​ታ​ው​ቅህ ዘንድ፥ በእ​ነ​ር​ሱም ያሉ​ትን ሹሞች ስም እን​ጽ​ፍ​ልህ ዘንድ ስማ​ቸ​ውን ጠየ​ቅን። 11እን​ደ​ዚ​ህም ብለው መለ​ሱ​ልን፦ እኛ የሰ​ማ​ይና የም​ድር አም​ላክ ባሪ​ያ​ዎች ነን፥ ከብ​ዙም ዘመን ጀምሮ ተሠ​ርቶ የነ​በ​ረ​ውን፥ ታላ​ቁም የእ​ስ​ራ​ኤል ንጉሥ ሠርቶ ፈጽ​ሞ​ላ​ቸው የነ​በ​ረ​ውን ቤት እን​ሠ​ራ​ለን። 12አባ​ቶ​ቻ​ች​ንም የሰ​ማ​ይን አም​ላክ ከአ​ስ​ቈጡ በኋላ በከ​ለ​ዳ​ዊው በባ​ቢ​ሎን ንጉሥ በና​ቡ​ከ​ደ​ነ​ፆር እጅ አሳ​ልፎ ሰጣ​ቸው፤ እር​ሱም ይህን ቤት አፈ​ረሰ፤ ሕዝ​ቡ​ንም ወደ ባቢ​ሎን አፈ​ለሰ። 13ነገር ግን በባ​ቢ​ሎን ንጉሥ በቂ​ሮስ በመ​ጀ​መ​ሪ​ያው ዓመት ንጉሡ ቂሮስ ይህን የእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርን ቤት ይሠሩ ዘንድ አዘዘ። 14ናቡ​ከ​ደ​ነ​ፆ​ርም በኢ​የ​ሩ​ሳ​ሌም ከነ​በ​ረው መቅ​ደስ የወ​ሰ​ደ​ውን፥ ወደ ባቢ​ሎ​ንም መቅ​ደስ ያፈ​ለ​ሰ​ውን የእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርን ቤት የወ​ር​ቁ​ንና የብ​ሩን ዕቃ ንጉሡ ቂሮስ ከባ​ቢ​ሎን መቅ​ደስ አው​ጥቶ ለቤተ መዛ​ግ​ብቱ ሹም ለሲ​ሳ​ብ​ሳር ሰጠ​ውና፦ 15‘ይህን ዕቃ ይዘህ ሂድ፤ በኢ​የ​ሩ​ሳ​ሌ​ምም ባለው መቅ​ደስ በቦ​ታው አኑ​ረው፤ የእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርም ቤት በስ​ፍ​ራው ይሠራ’ አለው። 16በዚያ ጊዜም ይህ ሲሳ​ብ​ሳር መጣ፤ በኢ​የ​ሩ​ሳ​ሌ​ምም ያለ​ውን የእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርን ቤት መሠ​ረተ፤ ከዚ​ያም ጊዜ ጀምሮ እስከ ዛሬ ድረስ እየ​ተ​ሠራ አል​ተ​ጨ​ረ​ሰም። 17አሁ​ንም ይህ ነገር በን​ጉሡ ዐይን መል​ካም ቢሆን ይህ የእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ቤት በኢ​የ​ሩ​ሳ​ሌም ይሠራ ዘንድ ከን​ጉሡ ከቂ​ሮስ ታዝዞ እንደ ሆነ በባ​ቢ​ሎን ባለው በን​ጉሡ ቤተ መዛ​ግ​ብት ይመ​ር​መር፤ ስለ​ዚ​ህም ነገር ንጉሡ ፈቃ​ዱን ይላ​ክ​ልን።”

ማድመቅ

ያጋሩ

ኮፒ

None

ያደመቋቸው ምንባቦች በሁሉም መሣሪያዎችዎ ላይ እንዲቀመጡ ይፈልጋሉ? ይመዝገቡ ወይም ይግቡ