ዕዝራ 5:3-4
ዕዝራ 5:3-4 የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) (አማ2000)
በዚያም ጊዜ በወንዝ ማዶ የነበረው ገዥ ተንትናይ፥ ደግሞ አስተርቡዝናይ ተባባሪዎቻቸውም ወደ እነርሱ መጥተው፥ “ይህን ቤት ትሠሩ ዘንድ ማን አዘዛችሁ? የምትሠሩበትንስ ሥልጣን ማን ሰጣችሁ?” አሉአቸው። ደግሞም፥ “ይህችን ከተማስ የሚሠሩ ሰዎች ስም ማን ማን ነው?” ብለው ጠየቁአቸው።
Share
ዕዝራ 5 ያንብቡዕዝራ 5:3-4 አዲሱ መደበኛ ትርጒም (NASV)
በዚህ ጊዜ በኤፍራጥስ ማዶ ገዥ የነበረው ተንትናይ፣ ሰተርቡዝናይና ተባባሪዎቻቸው ሄደው፣ “ይህን ቤተ መቅደስ እንደ ገና ለመሥራትና ውቅሩንም ለመጠገን የፈቀደላችሁ ማን ነው?” ሲሉ ጠየቋቸው። ደግሞም፣ “ይህን ሕንጻ የሚገነቡት ሰዎች ስም ማን ይባላል?” በማለት ጠየቋቸው።
Share
ዕዝራ 5 ያንብቡዕዝራ 5:3-4 መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) (አማ54)
በዚያም ዘመን በወንዝ ማዶ የነበረው ገዥ ተንትናይ፥ ደግሞ ሰተርቡዝናይ፥ ተባባሪዎቻቸውም ወደ እነርሱ መጥተው “ይህን ቤት ትሠሩ ዘንድ፥ ይህንኑም ቅጥር ታድሱ ዘንድ ያዘዛችሁ ማን ነው?” አሉአቸው። ደግሞም፦ “ይህንስ ሥራ የሚሠሩት ሰዎች ስም ማን ነው?” ብለው ጠየቁአቸው።
Share
ዕዝራ 5 ያንብቡ