መክብብ 4:1-12

መክብብ 4:1-12 የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) (አማ2000)

እኔም ተመ​ለ​ስሁ፥ ከፀ​ሓይ በታ​ችም የሚ​ደ​ረ​ገ​ውን ግፍ ሁሉ አየሁ፤ እነ​ሆም፥ የተ​ገ​ፉት ሰዎች እንባ ነበረ፤ የሚ​ያ​ጽ​ና​ና​ቸ​ውም አል​ነ​በ​ረም፤ በሚ​ገ​ፉ​አ​ቸ​ውም እጅ ኀይል ነበረ። እነ​ር​ሱን ግን የሚ​ያ​ጽ​ና​ና​ቸው አል​ነ​በ​ረም። እኔም እስከ ዛሬ በሕ​ይ​ወት ካሉት ሕያ​ዋን ይልቅ በቀ​ድሞ ዘመን የሞ​ቱ​ትን አመ​ሰ​ገ​ን​ኋ​ቸው። ከእ​ነ​ዚ​ህም ከሁ​ለቱ ይልቅ ገና ያል​ተ​ወ​ለ​ደው ከፀ​ሓ​ይም በታች የሚ​ደ​ረ​ገ​ውን ክፉ ሥራ ሁሉ ያላየ ይሻ​ላል። እኔ ድካ​ምን ሁሉና የብ​ል​ሃት ሥራ​ውን ተመ​ለ​ከ​ትሁ፥ ለሰ​ውም በባ​ል​ን​ጀ​ራው ዘንድ ቅን​አ​ትን እን​ዲ​ያ​ስ​ነሣ አየሁ፤ ይህም ደግሞ ከንቱ ነፋ​ስ​ንም እንደ መከ​ተል ነው። ሰነፍ እጆ​ቹን ኰር​ትሞ ይቀ​መ​ጣል፥ የገዛ ሥጋ​ው​ንም ይበ​ላል። በድ​ካ​ምና ነፋ​ስን በመ​ከ​ተል ከሁ​ለት እጅ ሙሉ ይልቅ አንድ እጅ ሙሉ በዕ​ረ​ፍት ይሻ​ላል። እኔም ተመ​ለ​ስሁ፥ ከፀ​ሓይ በታ​ችም ከንቱ ነገ​ርን አየሁ። አንድ ሰው ብቻ​ውን አለ፥ ሁለ​ተ​ኛም የለ​ውም፥ ልጅም ሆነ ወን​ድም የለ​ውም፤ ለድ​ካሙ ግን መጨ​ረሻ የለ​ውም፥ ዐይ​ኖ​ቹም ከባ​ለ​ጠ​ግ​ነት አይ​ጠ​ግ​ቡም። ለማን እደ​ክ​ማ​ለሁ? ሰው​ነ​ቴ​ንስ ከደ​ስታ ለምን እነ​ፍ​ጋ​ታ​ለሁ? ይላል። ይህም ደግሞ ከንቱ ነገር፥ ክፉም ጥረት ነው። ድካ​ማ​ቸው መል​ካም ዋጋ አለ​ውና አንድ ብቻ ከመ​ሆን ሁለት መሆን ይሻ​ላል። አንዱ ቢወ​ድቅ ሁለ​ተ​ኛው ያነ​ሣ​ዋ​ልና፥ አንድ ብቻ​ውን ሆኖ በወ​ደቀ ጊዜ ግን የሚ​ያ​ነ​ሣው ሁለ​ተኛ የለ​ው​ምና ወዮ​ለት። ሁለ​ቱም በአ​ን​ድ​ነት ቢተኙ ይሞ​ቃ​ቸ​ዋል፤ አንድ ብቻ​ውን ግን እን​ዴት ይሞ​ቀ​ዋል? አን​ዱም ሌላ​ውን ቢያ​ሸ​ንፍ ሁለቱ በፊቱ ይቆ​ማሉ፤ በሦ​ስ​ትም የተ​ገ​መደ ገመድ ፈጥኖ አይ​በ​ጠ​ስም።

መክብብ 4:1-12 አዲሱ መደበኛ ትርጒም (NASV)

እንደ ገና ከፀሓይ በታች የሚደረገውን ግፍ ሁሉ አየሁ፤ አስተዋልሁም፤ የተገፉትን ሰዎች እንባ ተመለከትሁ፤ የሚያጽናናቸውም አልነበረም፤ ኀይል በሚገፏቸው ሰዎች እጅ ነበረ፤ የሚያጽናናቸውም አልነበረም። እኔም የቀድሞ ሙታን፣ ዛሬ በሕይወት ካሉት ሕያዋን ይልቅ፣ ደስተኞች እንደ ሆኑ ተናገርሁ። ነገር ግን ከሁለቱም ይልቅ፣ ገና ያልተወለደው፣ ከፀሓይ በታች የሚደረገውንም፣ ክፋት ያላየው ይሻላል። እንዲሁም ጥረትና የሥራ መከናወን ሁሉ ሰው በባልንጀራው ላይ ካለው ቅናት እንደሚመነጭ ተመለከትሁ፤ ይህም ደግሞ ከንቱ፣ ነፋስንም እንደ መከተል ነው። ሞኝ እጁን አጣጥፎ ይቀመጣል፤ የገዛ ራሱንም ሥጋ ይበላል። በድካምና ነፋስን በመከተል ከሚገኝ ሁለት ዕፍኝ ይልቅ፣ በርጋታ የሚገኝ አንድ ዕፍኝ ይሻላል። ደግሞም ከፀሓይ በታች ከንቱ የሆነን ነገር አየሁ፤ ልጅም ሆነ ወንድም የሌለው፣ ብቸኛ ሰው አለ፤ ጥረቱ ማለቂያ የለውም፤ ዐይኑም ባለው ሀብት ገና አልረካም፤ እርሱም፣ “ለማን ብዬ ነው የምደክመው? ራሴን ከማስደሰትስ የምቈጠበው ለምንድን ነው?” ብሎ ጠየቀ፤ ይህም ደግሞ ከንቱ፣ የጭንቅ ኑሮ ነው። ለሥራቸው መልካም ውጤት ስለሚያገኙ፣ ከአንድ፣ ሁለት መሆን ይሻላል፤ አንዱ ቢወድቅ፣ ባልንጀራው ደግፎ ያነሣዋል። ቢወድቅ የሚያነሣው ረዳት የሌለው ግን፣ እንዴት አሳዛኝ ነው! ደግሞም ሁለቱ ዐብረው ቢተኙ ይሞቃቸዋል፤ ነገር ግን አንዱ ብቻውን እንዴት ሊሞቀው ይችላል? አንድ ሰው ብቸኛውን ቢያጠቃውም፣ ሁለት ከሆኑ ይመክቱታል፤ በሦስት የተገመደ ገመድም ቶሎ አይበጠስም።

መክብብ 4:1-12 መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) (አማ54)

እኔም ተመለስሁ፥ ከፀሐይ በታችም የሚደረገውን ግፍ ሁሉ አየሁ፥ እነሆም፥ የተገፉት ሰዎች እንባ ነበረ፥ የሚያጽናናቸውም አልነበረም፥ በሚገፉአቸውም እጅ ኃይል ነበረ፥ እነርሱን ግን የሚያጽናናቸው አልነበረም። እኔም እስከ ዛሬ በሕይወት ካሉት ይልቅ በቀድሞ ዘመን የሞቱትን አመሰገንሁ፥ ከእነዚህም ከሁለቱ ይልቅ ገና ያልተወለደው ከፀሐይም በታች የሚደረገውን ግፍ ያላየው ይሻላል። ደግሞም የሰውን ድካምና የብልሃት ሥራውን ሁሉ ተመለከትሁ፥ በባልንጀራውም ዘንድ ቅንዓት እንዲያስነሣ አየሁ፥ ይህም ደግሞ ከንቱ ነፋስንም እንደ መከተል ነው። ሰነፍ እጆቹን ኮርትሞ ይቀመጣል፥ የገዛ ሥጋውንም ይበላል። በድካምና ነፋስን በመከተል ከሁለት እጅ ሙሉ ይልቅ አንድ እጅ ሙሉ በዕረፍት ይሻላል። እኔም ተመለስሁ፥ ከፀሐይ በታችም ከንቱ ነገር አየሁ። አንድ ሰው ብቻውን አለ፥ ሁለተኛም የለውም፥ ልጅም ሆነ ወንድም የለውም፥ ለድካሙ ግን መጨረሻ የለውም፥ ዓይኖቹም ከባለጠግነት አይጠግቡም። ለማን እደክማለሁ፥ ሰውነቴንስ መልካሙን ነገር ለምን እነፍጋታለሁ? ይላል። ይህም ደግሞ ከንቱ ነገር ክፉም ጥረት ነው። ድካማቸው መልካም ዋጋ አለውና አንድ ብቻ ከመሆን ሁለት መሆን ይሻላል። ቢወድቁ አንዱ ሁለተኛውን ያነሣዋልና፥ አንዱ ብቻውን ሆኖ በወደቀ ጊዜ ግን የሚያነሣው ሁለተኛ የለውምና ወዮለት። ሁለቱም በአንድነት ቢተኙ ይሞቃቸዋል፥ አንድ ብቻውን ግን እንዴት ይሞቀዋል? አንዱም አንዱን ቢያሸንፍ ሁለቱ በፊቱ ይቆማሉ፥ በሦስትም የተገመደ ገመድ ፈጥኖ አይበጠስም።

መክብብ 4:1-12 አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም (አማ05)

እንደገናም በዓለም ያለውን የፍርድ መጓደልና ግፍ ተመለከትኩ፤ የተገፉ ጭቊኖች የሚያጽናናቸው አጥተው ያለቅሱ ነበር፤ የፈላጭ ቈራጭነት ሥልጣን በገዢዎቻቸው እጅ ስለ ሆነ የሚረዳቸው አላገኙም። ስለዚህም እኔ “በዚህ ሁኔታ ላይ በሕይወት ካሉት ይልቅ በቀድሞ ዘመን የሞቱት ይሻላሉ” አልኩ። በተለይም ከነዚህ ከሁለቱ ወገኖች ይልቅ ከቶውኑ ያልተወለዱና በዚህ ዓለም የሚፈጸመውን ግፍና ጭቈና ያላዩ ዕድለኞች ናቸው። ደግሞም ሰዎች የተመኙትን ለማግኘት ተግተው በመሥራት ምን ያኽል እንደሚደክሙ ተመለከትኩ፤ ይህንንም የሚያደርጉት በባልንጀሮቻቸው ላይ በመቅናት መሆኑን ተረዳሁ፤ ይህም ሁሉ ከንቱ ስለ ሆነ ነፋስን ለመጨበጥ እንደ መሞከር ነው። እጆቹን አጥፎ የሚቀመጥ ሞኝ ሰው ራሱን በራብ ይገድላል። ነፋስን እንደ መጨበጥ ከሚቈጠር ላልተጨበጠ ሐሳብ ብዙ አገኛለሁ ብሎ ከመድከም ይልቅ ከኅሊና ዕረፍት ጋር ጥቂት ለማግኘት መሥራት ይሻላል። በዚህ ዓለም ያለውን ሌላውንም ከንቱ ነገር ተመለከትኩ፤ እነሆ፥ ብቻውን የሚኖር አንድ ሰው አለ፤ ልጅም ሆነ ወንድም የለውም፤ ይሁን እንጂ ዘወትር በሥራ ከመድከም አይቦዝንም፤ ባገኘውም ሀብት በቃኝ ማለትን አላወቀም፤ “እርሱም የምደክመው ለማን ነው? ለራሴስ ደስታን የምነፍገው ለምንድን ነው?” ብሎ ራሱን ይጠይቃል፤ ይህ ሁሉ የባሰ ከንቱና የሥቃይ ሕይወት ነው። የሥራቸው ውጤት መልካም ሊሆን ስለሚችል አንድ ብቻ ከመሆን ሁለት መሆን ይሻላል። ከሁለቱ አንዱ ቢወድቅ ሌላው ያነሣዋል፤ ብቻውን የሆነ ሰው ቢወድቅ እንኳ የሚያነሣው ረዳት ስለሌለው ወዮለት። ሁለቱ አብረው ቢተኙ ይሞቃቸዋል፤ ብቻውን የሚተኛ ሰው ግን እንዴት ሊሞቀው ይችላል? አንድ ሰው ብቻውን ሊመልሰው የማይችለውን አደጋ ሁለት ሰዎች ሊቋቋሙት ይችላሉ፤ በሦስት ተሸርቦ የተገመደ ፈትል እንኳ በቀላሉ አይበጠስም።

መክብብ 4:1-12 መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) (መቅካእኤ)

እኔም ተመለስሁ፥ ከፀሐይ በታችም የሚደረገውን ግፍ ሁሉ አየሁ፥ እነሆም፥ የተገፉት ሰዎች እንባ፥ የሚያጽናናቸውም አልነበረም፥ በሚገፉአቸውም እጅ ኃይል ነበረ፥ እነርሱን ግን የሚያጽናናቸው አልነበረም። እኔም እስከ ዛሬ በሕይወት ካሉት ይልቅ በቀድሞ ዘመን የሞቱትን አመሰገንሁ፥ ከእነዚህም ከሁለቱ ይልቅ ገና ያልተወለደው ከፀሐይም በታች የሚደረገውን ግፍ ያላየው ይሻላል። ደግሞም የሰውን ድካምና የብልሃት ሥራውን ሁሉ ተመለከትሁ፥ በባልንጀራም ዘንድ ቅንዓት እንደሚያስነሣ አየሁ፥ ይህም ደግሞ ከንቱ ነፋስንም እንደ መከተል ነው። አላዋቂ እጆቹን አጥፎ ይቀመጣል፥ የገዛ ሥጋውንም ይበላል። በድካምና ነፋስን በመከተል ከሚገኝ ሁለት እፍኝ ይልቅ፥ በእርጋታ የሚገኝ አንድ እፍኝ ይሻላል። እንደገና፥ ከፀሐይ በታችም ከንቱ ነገር አየሁ። አንድ ሰው ብቻውን ይኖራል፥ ማንም አብሮት የለም፥ ልጅም ሆነ ወንድም የለውም፥ ለድካሙም መጨረሻ የለውም፥ ዐይኖቹም ሳይቀሩ ሀብትን አይጠግቡም። እንግዲህ ለማን እደክማለሁ፥ ሰውነቴንስ መልካሙን ነገር ለምን እነፍጋታለሁ? ይላል። ይህም ደግሞ ከንቱ ነገር ክፉም ጥረት ነው። ድካማቸው መልካም ዋጋ አለውና አንድ ብቻ ከመሆን ሁለት መሆን ይሻላል። ቢወድቁ አንዱ ሁለተኛውን ያነሣዋልና፥ አንዱ ብቻውን ሆኖ በወደቀ ጊዜ ግን የሚያነሣው ሁለተኛ የለውምና ወዮለት። ሁለቱም በአንድነት ቢተኙ ይሞቃቸዋል፥ አንድ ብቻውን ግን እንዴት ይሞቀዋል? አንዱም አንድን ሰው ቢያሸንፍ፥ ሁለቱ ግን ይቋቋሙታል፥ በሦስትም የተገመደ ገመድ በፍጥነት አይበጠስም።