የYouVersion አርማ
የፍለጋ አዶ

መጽ​ሐፈ መክ​ብብ 4

4
1እኔም ተመ​ለ​ስሁ፥ ከፀ​ሓይ በታ​ችም የሚ​ደ​ረ​ገ​ውን ግፍ ሁሉ አየሁ፤ እነ​ሆም፥ የተ​ገ​ፉት ሰዎች እንባ ነበረ፤ የሚ​ያ​ጽ​ና​ና​ቸ​ውም አል​ነ​በ​ረም፤ በሚ​ገ​ፉ​አ​ቸ​ውም እጅ ኀይል ነበረ። እነ​ር​ሱን ግን የሚ​ያ​ጽ​ና​ና​ቸው አል​ነ​በ​ረም። 2እኔም እስከ ዛሬ በሕ​ይ​ወት ካሉት ሕያ​ዋን ይልቅ በቀ​ድሞ ዘመን የሞ​ቱ​ትን አመ​ሰ​ገ​ን​ኋ​ቸው። 3ከእ​ነ​ዚ​ህም ከሁ​ለቱ ይልቅ ገና ያል​ተ​ወ​ለ​ደው ከፀ​ሓ​ይም በታች የሚ​ደ​ረ​ገ​ውን ክፉ ሥራ ሁሉ ያላየ ይሻ​ላል።
4እኔ ድካ​ምን ሁሉና የብ​ል​ሃት ሥራ​ውን ተመ​ለ​ከ​ትሁ፥ ለሰ​ውም በባ​ል​ን​ጀ​ራው ዘንድ ቅን​አ​ትን እን​ዲ​ያ​ስ​ነሣ አየሁ፤ ይህም ደግሞ ከንቱ ነፋ​ስ​ንም እንደ መከ​ተል ነው። 5ሰነፍ እጆ​ቹን ኰር​ትሞ ይቀ​መ​ጣል፥ የገዛ ሥጋ​ው​ንም ይበ​ላል። 6በድ​ካ​ምና ነፋ​ስን በመ​ከ​ተል ከሁ​ለት እጅ ሙሉ ይልቅ አንድ እጅ ሙሉ በዕ​ረ​ፍት ይሻ​ላል።
7እኔም ተመ​ለ​ስሁ፥ ከፀ​ሓይ በታ​ችም ከንቱ ነገ​ርን አየሁ። 8አንድ ሰው ብቻ​ውን አለ፥ ሁለ​ተ​ኛም የለ​ውም፥ ልጅም ሆነ ወን​ድም የለ​ውም፤ ለድ​ካሙ ግን መጨ​ረሻ የለ​ውም፥ ዐይ​ኖ​ቹም ከባ​ለ​ጠ​ግ​ነት አይ​ጠ​ግ​ቡም። ለማን እደ​ክ​ማ​ለሁ? ሰው​ነ​ቴ​ንስ ከደ​ስታ ለምን እነ​ፍ​ጋ​ታ​ለሁ? ይላል። ይህም ደግሞ ከንቱ ነገር፥ ክፉም ጥረት ነው። 9ድካ​ማ​ቸው መል​ካም ዋጋ አለ​ውና አንድ ብቻ ከመ​ሆን ሁለት መሆን ይሻ​ላል። 10አንዱ ቢወ​ድቅ ሁለ​ተ​ኛው ያነ​ሣ​ዋ​ልና፥ አንድ ብቻ​ውን ሆኖ በወ​ደቀ ጊዜ ግን የሚ​ያ​ነ​ሣው ሁለ​ተኛ የለ​ው​ምና ወዮ​ለት። 11ሁለ​ቱም በአ​ን​ድ​ነት ቢተኙ ይሞ​ቃ​ቸ​ዋል፤ አንድ ብቻ​ውን ግን እን​ዴት ይሞ​ቀ​ዋል? 12አን​ዱም ሌላ​ውን ቢያ​ሸ​ንፍ ሁለቱ በፊቱ ይቆ​ማሉ፤ በሦ​ስ​ትም የተ​ገ​መደ ገመድ ፈጥኖ አይ​በ​ጠ​ስም።
13ድሃና ጠቢብ ብላ​ቴና ከእ​ን​ግ​ዲህ ወዲህ ተግ​ሣ​ጽን መቀ​በል ከማ​ያ​ውቅ ከሰ​ነፍ ሽማ​ግሌ ንጉሥ ይሻ​ላል። 14በመ​ን​ግ​ሥቱ ችግ​ረኛ ቢሆ​ንም ከግ​ዞት ቤት ለመ​ን​ገሥ ወጥ​ቶ​አ​ልና። 15ከፀ​ሓይ በታች የሚ​ሄ​ዱ​ትን ሕያ​ዋን ሁሉ በእ​ርሱ ፋንታ ከሚ​ነ​ሣው ከሌ​ላው ጐል​ማሳ ጋር ሆነው አየሁ። 16ከእ​ርሱ በፊት የነ​በ​ሩት ሕዝብ ሁሉ ቍጥር የላ​ቸ​ውም፤ በኋላ የሚ​መ​ጡት ግን በእ​ርሱ ደስ አይ​ላ​ቸ​ውም። ይህ ደግሞ ከንቱ ነው፥ ነፋ​ስ​ንም እንደ መከ​ተል ነው።

ማድመቅ

Share

Copy

None

ያደመቋቸው ምንባቦች በሁሉም መሣሪያዎችዎ ላይ እንዲቀመጡ ይፈልጋሉ? ይመዝገቡ ወይም ይግቡ