የYouVersion አርማ
የፍለጋ አዶ

መጽ​ሐፈ መክ​ብብ 3

3
ለሁሉ ጊዜ አለው
1ለሁሉ ዘመን አለው፥ ከፀ​ሐይ#ዕብ. እና ግሪክ ሰባ. ሊ. “ከሰ​ማይ” ይላል። በታ​ችም ለሆነ ነገር ሁሉ ጊዜ አለው። 2ለመ​ፅ​ነስ ጊዜ አለው፥#“ለመ​ፅ​ነስ ጊዜ አለው” የሚ​ለው በግ​እዝ ብቻ። ለመ​ው​ለ​ድም ጊዜ አለው፤ ለመ​ኖር ጊዜ አለው፥ ለመ​ሞ​ትም ጊዜ አለው፤ ለመ​ት​ከል ጊዜ አለው፥ የተ​ተ​ከ​ለ​ው​ንም ለመ​ን​ቀል ጊዜ አለው። 3ለመ​ግ​ደል ጊዜ አለው፥ ለመ​ፈ​ወ​ስም ጊዜ አለው፤ ለማ​ፍ​ረስ ጊዜ አለው፥ ለመ​ሥ​ራ​ትም ጊዜ አለው፤ 4ለማ​ል​ቀስ ጊዜ አለው፥ ለመ​ሣ​ቅም ጊዜ አለው፤ ዋይ ለማ​ለት ጊዜ አለው፥ ለመ​ዝ​ፈ​ንም ጊዜ አለው። 5ድን​ጋ​ይን ለመ​ወ​ር​ወር ጊዜ አለው፥ ድን​ጋ​ይ​ንም ለመ​ሰ​ብ​ሰብ ጊዜ አለው፤ ለመ​ተ​ቃ​ቀፍ ጊዜ አለው፥ ከመ​ተ​ቃ​ቀ​ፍም ለመ​ራቅ ጊዜ አለው፤ 6ለመ​ፈ​ለግ ጊዜ አለው፥ ለማ​ጥ​ፋ​ትም ጊዜ አለው፤ ለመ​ጠ​በቅ ጊዜ አለው፥ ለመ​ጣ​ልም ጊዜ አለው፤ 7ለመ​ቅ​ደድ ጊዜ አለው፥ ለመ​ስ​ፋ​ትም ጊዜ አለው፤ ዝም ለማ​ለት ጊዜ አለው፥ ለመ​ና​ገ​ርም ጊዜ አለው፤ 8ለመ​ው​ደድ ጊዜ አለው፥ ለመ​ጥ​ላ​ትም ጊዜ አለው፤ ለጦ​ር​ነት ጊዜ አለው፥ ለሰ​ላ​ምም ጊዜ አለው። 9ለሠ​ራ​ተኛ የድ​ካሙ ትርፍ ምን​ድን ነው?
10እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ለሰው ልጆች ይደ​ክ​ሙ​በት ዘንድ የሰ​ጣ​ቸ​ውን ድካም ሁሉ አይ​ቻ​ለሁ። 11የሠ​ራው ሥራ ሁሉ በጊ​ዜው መል​ካም ነው፤ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርም ከጥ​ንት ጀምሮ እስከ ፍጻሜ ድረስ የሠ​ራ​ውን ሥራ ሰው መር​ምሮ እን​ዳ​ያ​ገኝ ዘለ​ዓ​ለ​ም​ነ​ትን በልቡ ሰጠው። 12ሰው ደስ ከሚ​ለ​ውና በሕ​ይ​ወቱ ሳለ መል​ካ​ምን ነገር ከሚ​ያ​ደ​ርግ በቀር በው​ስ​ጣ​ቸው መል​ካም ነገር እን​ደ​ሌለ ዐወ​ቅሁ። 13ደግ​ሞም ሰው ሁሉ ይበ​ላና ይጠጣ ዘንድ በድ​ካ​ሙም ሁሉ መል​ካ​ምን ያይ ዘንድ የእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ስጦታ ነው። 14እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ያደ​ረ​ገው ሁሉ ለዘ​ለ​ዓ​ለም እን​ዲ​ኖር ዐወ​ቅሁ፤ በእ​ነ​ር​ሱም ላይ መጨ​መር ከእ​ነ​ር​ሱም ማጕ​ደል አይ​ቻ​ልም፤ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርም በፊቱ ይፈሩ ዘንድ አደ​ረገ። 15በፊት የተ​ደ​ረ​ገው አሁን አለ። ይደ​ረግ ዘንድ ያለ​ውም እነሆ ተደ​ር​ጓል፤ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርም ያለ​ፈ​ውን መልሶ ይሻ​ዋል።
16ደግ​ሞም ከፀ​ሐይ በታች በጻ​ድቅ ስፍራ ኃጥእ፥ በኃ​ጥ​እም ስፍራ ጻድቅ እን​ዳለ አየሁ። 17እኔም በልቤ፥ “በዚያ ለነ​ገር ሁሉና ለሥራ ሁሉ ጊዜ አለ​ውና በጻ​ድ​ቁና በኀ​ጢ​አ​ተ​ኛው ላይ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ይፈ​ር​ዳል” አልሁ። 18እኔ በልቤ ስለ ሰው ልጆች ነገር፥ “እንደ እን​ስሳ መሆ​ና​ቸ​ውን ያሳይ ዘንድ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ይፈ​ር​ድ​ባ​ቸ​ዋል” አልሁ። 19ለሰው ልጆች ሞት አለ​ባ​ቸው፥ ለእ​ን​ስ​ሳም ሞት አለ​ባ​ቸው፤ አንድ ሞት አለ​ባ​ቸው፤ አንዱ እን​ደ​ሚ​ሞት ሌላ​ውም እን​ዲሁ ይሞ​ታል፤ ለሁ​ሉም አንድ እስ​ት​ን​ፋስ አላ​ቸው፥ ሰው ከእ​ን​ስሳ ብል​ጫው ምን​ድን ነው? ሁሉም ከንቱ ነውና ምንም የለ​ውም። 20ሁሉም ወደ አንድ ቦታ ይሄ​ዳል፤ ሁሉ ከአ​ፈር ተገኘ፥ ሁሉም ወደ አፈር ይመ​ለ​ሳል። 21የሰው ልጆች ነፍስ ወደ ላይ እን​ደ​ም​ት​ወጣ፥ የእ​ን​ስ​ሳም ነፍስ ወደ ታች ወደ ምድር እን​ደ​ም​ት​ወ​ርድ የሚ​ያ​ውቅ ማን ነው? 22ያም ዕድል ፋን​ታው ነውና ሰው በሥ​ራው ደስ ከሚ​ለው በቀር ሌላ መል​ካም ነገር እን​ደ​ሌ​ለው አየሁ፤ ከእ​ርሱ በኋ​ላስ የሚ​ሆ​ነ​ውን ያይ ዘንድ የሚ​ያ​መ​ጣው ማን ነው?

ማድመቅ

Share

Copy

None

ያደመቋቸው ምንባቦች በሁሉም መሣሪያዎችዎ ላይ እንዲቀመጡ ይፈልጋሉ? ይመዝገቡ ወይም ይግቡ