የYouVersion አርማ
የፍለጋ አዶ

መክብብ 3:1-9

መክብብ 3:1-9 የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) (አማ2000)

ለሁሉ ዘመን አለው፥ ከፀ​ሐይ በታ​ችም ለሆነ ነገር ሁሉ ጊዜ አለው። ለመ​ፅ​ነስ ጊዜ አለው፥ ለመ​ው​ለ​ድም ጊዜ አለው፤ ለመ​ኖር ጊዜ አለው፥ ለመ​ሞ​ትም ጊዜ አለው፤ ለመ​ት​ከል ጊዜ አለው፥ የተ​ተ​ከ​ለ​ው​ንም ለመ​ን​ቀል ጊዜ አለው። ለመ​ግ​ደል ጊዜ አለው፥ ለመ​ፈ​ወ​ስም ጊዜ አለው፤ ለማ​ፍ​ረስ ጊዜ አለው፥ ለመ​ሥ​ራ​ትም ጊዜ አለው፤ ለማ​ል​ቀስ ጊዜ አለው፥ ለመ​ሣ​ቅም ጊዜ አለው፤ ዋይ ለማ​ለት ጊዜ አለው፥ ለመ​ዝ​ፈ​ንም ጊዜ አለው። ድን​ጋ​ይን ለመ​ወ​ር​ወር ጊዜ አለው፥ ድን​ጋ​ይ​ንም ለመ​ሰ​ብ​ሰብ ጊዜ አለው፤ ለመ​ተ​ቃ​ቀፍ ጊዜ አለው፥ ከመ​ተ​ቃ​ቀ​ፍም ለመ​ራቅ ጊዜ አለው፤ ለመ​ፈ​ለግ ጊዜ አለው፥ ለማ​ጥ​ፋ​ትም ጊዜ አለው፤ ለመ​ጠ​በቅ ጊዜ አለው፥ ለመ​ጣ​ልም ጊዜ አለው፤ ለመ​ቅ​ደድ ጊዜ አለው፥ ለመ​ስ​ፋ​ትም ጊዜ አለው፤ ዝም ለማ​ለት ጊዜ አለው፥ ለመ​ና​ገ​ርም ጊዜ አለው፤ ለመ​ው​ደድ ጊዜ አለው፥ ለመ​ጥ​ላ​ትም ጊዜ አለው፤ ለጦ​ር​ነት ጊዜ አለው፥ ለሰ​ላ​ምም ጊዜ አለው። ለሠ​ራ​ተኛ የድ​ካሙ ትርፍ ምን​ድን ነው?