ሐዋርያት ሥራ 12:20-25
ሐዋርያት ሥራ 12:20-25 መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) (አማ54)
ከጢሮስና ከሲዶና ሰዎችም ጋር ተጣልቶ ነበር፤ በአንድ ልብ ሆነውም ወደ እርሱ መጡ፥ የንጉሥንም ቢትወደድ ብላስጦስን እሺ አሰኝተው ዕርቅ ለመኑ፥ አገራቸው ከንጉሥ አገር ምግብ ያገኝ ነበረና። በተቀጠረ ቀንም ሄሮድስ ልብሰ መንግሥቱን ለብሶ በዙፋን ተቀመጠ እነርሱንም ተናገራቸው፤ ሕዝቡም፦ “የእግዚአብሔር ድምፅ ነው የሰውም አይደለም” ብለው ጮኹ። ለእግዚአብሔርም ክብር ስላልሰጠ ያን ጊዜ የጌታ መልአክ መታው በትልም ተበልቶ ሞተ። የእግዚአብሔር ቃል ግን ያድግና ይበዛ ነበር። በርናባስና ሳውልም አገልግሎታቸውን ፈጽመው ከኢየሩሳሌም ተመለሱ፥ ማርቆስ የተባለውን ዮሐንስንም ከእነርሱ ጋር ይዘውት መጡ።
ሐዋርያት ሥራ 12:20-25 የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) (አማ2000)
ሄሮድስም በጢሮስና በሲዶና ሰዎች ተቈጥቶ ነበር፤ በአንድነትም ወደ እርሱ መጥተው የንጉሡን ቢትወደድ በላስጦስን እንዲያስታርቃቸው ማለዱት፤ የሀገራቸው ምግብ ከንጉሥ ሄርድስ ነበርና። ከዚህም በኋላ አንድ ቀን ሄሮድስ ልብሰ መንግሥቱን ለብሶ፥ በአደባባይ ተገኝቶ ይፈርድ ጀመረ። ሕዝቡም፥ “የእግዚአብሔር ቃል ነው፤ የሰው ቃልም አይደለም” እያሉ ጮኹ። ለእግዚአብሔርም ክብር ስለ አልሰጠ ያንጊዜ የእግዚአብሔር መልአክ ቀሠፈው፤ ተልቶም ሞተ። የእግዚአብሔርም ቃል ከፍ አለ፤ በዛም። በርናባስና ሳውልም አገልግሎታቸውን ፈጽመው ከኢየሩሳሌም ተመለሱ፤ ማርቆስ የተባለውን ዮሐንስንም አስከትለውት መጡ።
ሐዋርያት ሥራ 12:20-25 አዲሱ መደበኛ ትርጒም (NASV)
እርሱም ከጢሮስና ከሲዶና ሰዎች ጋራ ጥለኛ ነበር፤ አገራቸው ምግብ የሚያገኘው ከንጉሡ ግዛት ስለ ነበር፣ የንጉሡን ባለሟል የብላስጦስን ድጋፍ ካገኙ በኋላ፣ አንድ ላይ ሆነው ከንጉሡ ጋራ ለመታረቅ ጠየቁ። በቀጠሮውም ቀን ሄሮድስ ልብሰ መንግሥቱን ለብሶ በዙፋኑ ላይ ተቀመጠ፤ ለሕዝቡም ንግግር አደረገ። ሕዝቡም፣ “ይህስ የአምላክ ድምፅ እንጂ የሰው አይደለም” ብለው ጮኹ። ሄሮድስም ለእግዚአብሔር ክብር ስላልሰጠ የጌታ መልአክ ወዲያው መታው፤ በትልም ተበልቶ ሞተ። የእግዚአብሔር ቃል ግን እያደገና እየሰፋ ሄደ። በርናባስና ሳውልም ተልእኳቸውን ፈጽመው ከኢየሩሳሌም ተመለሱ፤ ማርቆስ የተባለውን ዮሐንስንም ከእነርሱ ጋራ ይዘውት መጡ።
ሐዋርያት ሥራ 12:20-25 መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) (አማ54)
ከጢሮስና ከሲዶና ሰዎችም ጋር ተጣልቶ ነበር፤ በአንድ ልብ ሆነውም ወደ እርሱ መጡ፥ የንጉሥንም ቢትወደድ ብላስጦስን እሺ አሰኝተው ዕርቅ ለመኑ፥ አገራቸው ከንጉሥ አገር ምግብ ያገኝ ነበረና። በተቀጠረ ቀንም ሄሮድስ ልብሰ መንግሥቱን ለብሶ በዙፋን ተቀመጠ እነርሱንም ተናገራቸው፤ ሕዝቡም፦ “የእግዚአብሔር ድምፅ ነው የሰውም አይደለም” ብለው ጮኹ። ለእግዚአብሔርም ክብር ስላልሰጠ ያን ጊዜ የጌታ መልአክ መታው በትልም ተበልቶ ሞተ። የእግዚአብሔር ቃል ግን ያድግና ይበዛ ነበር። በርናባስና ሳውልም አገልግሎታቸውን ፈጽመው ከኢየሩሳሌም ተመለሱ፥ ማርቆስ የተባለውን ዮሐንስንም ከእነርሱ ጋር ይዘውት መጡ።
ሐዋርያት ሥራ 12:20-25 አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም (አማ05)
ሄሮድስ በጢሮስና በሲዶና ሰዎች ላይ በጣም ተቈጥቶ ነበር፤ እነርሱም በአንድነት መጡና፤ የንጉሥ ባለሟል ብላስጦስ እንዲተባበራቸው ለምነው እሺ ካሰኙትም በኋላ ንጉሡን ዕርቅ ጠየቁ፤ ይህንንም ያደረጉት አገራቸው ምግብ የምታገኘው ከንጉሡ ግዛት ስለ ነበረ ነው። በተቀጠረው ቀን ሄሮድስ ልብሰ መንግሥቱን ለበሰና በዙፋኑ ላይ ተቀምጦ ለሕዝቡ ንግግር አደረገ። ሕዝቡም “ይህ የአምላክ ድምፅ ነው እንጂ የሰው ድምፅ አይደለም!” እያሉ ጮኹ። ሄሮድስ ለእግዚአብሔር ክብር ሳይሰጥ በመቅረቱ ወዲያውኑ የጌታ መልአክ ቀሠፈውና ተልቶ ሞተ። የእግዚአብሔር ቃል ግን ዘወትር እያደገና እየተስፋፋ ይሄድ ነበር። በርናባስና ሳውል አገልግሎታቸውን ፈጽመው ከኢየሩሳሌም ወደ አንጾኪያ ተመለሱ፤ ማርቆስ የተባለውን ዮሐንስንም ከእነርሱ ጋር ይዘውት መጡ።
ሐዋርያት ሥራ 12:20-25 መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) (መቅካእኤ)
ከጢሮስና ከሲዶና ሰዎችም ጋር ተጣልቶ ነበር፤ በአንድ ልብ ሆነውም ወደ እርሱ መጡ፤ የንጉሥንም ቢትወደድ ብላስጦስን እሺ አሰኝተው ዕርቅ ለመኑ፤ አገራቸው ከንጉሥ አገር ምግብ ያገኝ ነበረና። በተቀጠረ ቀንም ሄሮድስ ልብሰ መንግሥቱን ለብሶ በዙፋን ተቀመጠ፤ እነርሱንም ተናገራቸው፤ ሕዝቡም “የእግዚአብሔር ድምፅ ነው፤ የሰውም አይደለም፤” ብለው ጮኹ። ለእግዚአብሔርም ክብር ስላልሰጠ ያንጊዜ የጌታ መልአክ መታው፤ በትልም ተበልቶ ሞተ። የእግዚአብሔር ቃል ግን ያድግና ይበዛ ነበር። በርናባስና ሳውልም አገልግሎታቸውን ፈጽመው ከኢየሩሳሌም ተመለሱ፤ ማርቆስ የተባለውን ዮሐንስንም ከእነርሱ ጋር ይዘውት መጡ።