የሐ​ዋ​ር​ያት ሥራ 12:20-25

የሐ​ዋ​ር​ያት ሥራ 12:20-25 አማ2000

ሄሮ​ድ​ስም በጢ​ሮ​ስና በሲ​ዶና ሰዎች ተቈ​ጥቶ ነበር፤ በአ​ን​ድ​ነ​ትም ወደ እርሱ መጥ​ተው የን​ጉ​ሡን ቢት​ወ​ደድ በላ​ስ​ጦ​ስን እን​ዲ​ያ​ስ​ታ​ር​ቃ​ቸው ማለ​ዱት፤ የሀ​ገ​ራ​ቸው ምግብ ከን​ጉሥ ሄር​ድስ ነበ​ርና። ከዚ​ህም በኋላ አንድ ቀን ሄሮ​ድስ ልብሰ መን​ግ​ሥ​ቱን ለብሶ፥ በአ​ደ​ባ​ባይ ተገ​ኝቶ ይፈ​ርድ ጀመረ። ሕዝ​ቡም፥ “የእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ቃል ነው፤ የሰው ቃልም አይ​ደ​ለም” እያሉ ጮኹ። ለእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርም ክብር ስለ አል​ሰጠ ያን​ጊዜ የእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር መል​አክ ቀሠ​ፈው፤ ተል​ቶም ሞተ። የእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርም ቃል ከፍ አለ፤ በዛም። በር​ና​ባ​ስና ሳው​ልም አገ​ል​ግ​ሎ​ታ​ቸ​ውን ፈጽ​መው ከኢ​የ​ሩ​ሳ​ሌም ተመ​ለሱ፤ ማር​ቆስ የተ​ባ​ለ​ውን ዮሐ​ን​ስ​ንም አስ​ከ​ት​ለ​ውት መጡ።