2 ሳሙኤል 12:11-31

2 ሳሙኤል 12:11-31 መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) (አማ54)

እግዚአብሔር እንዲህ ይላል፦ እነሆ፥ ከቤትህ ክፉ ነገር አስነሣብሃለሁ፥ ሚስቶችህንም በዓይንህ ፊት እወስዳለሁ፥ ለዘመድህም እሰጣቸዋለሁ፥ በዚህችም ፀሐይ ዓይን ፊት ከሚስቶችህ ጋር ይተኛል። አንተ ይህን በስውር አድርገኸዋል፥ እኔ ግን ይህን በእስራኤል ሁሉ ፊትና በፀሐይ ፊት አደርገዋለሁ። ዳዊትም ናታንን፦ እግዚአብሔርን በድያለሁ አለው። ናታንም ዳዊትን፦ እግዚአብሔር ደግሞ ኃጢአትህን አርቆልሃል፥ አትሞትም። ነገር ግን በዚህ ነገር ለእግዚአብሔር ጠላቶች ታላቅ የስድብ ምክንያት አድርገሃልና ስለዚህ ደግሞ የተወለደልህ ልጅ ፈጽሞ ይሞታል አለው። ናታንም ወደ ቤቱ ተመለሰ። እግዚአብሔርም የኦርዮ ሚስት ለዳዊት የወለደችውን ሕፃን ቀሠፈ፥ እጅግም ታምሞ ነበር። ዳዊትም ስለ ሕፃኑ እግዚአብሔርን ለመነ፥ ዳዊትም ጾመ፥ ገብቶም በመሬት ላይ ተኛ። የቤቱም ሽማግሌዎች ተነሥተው ከምድር ያነሡት ዘንድ በአጠገቡ ቆሙ፥ እርሱ ግን እንቢ አለ፥ ከእነርሱም ጋር እንጀራ አልበላም። በሰባተኛውም ቀን ሕፃኑ ሞተ። የዳዊትም ባሪያዎች፦ ሕፃኑ በሕይወት ሳለ ብንነግረው አልሰማንም፥ ይልቁንስ ሕፃኑ እንደ ሞተ ብንነግረው እንዴት ይሆን? በነፍሱ ክፉ ያደርጋል ብለው ሕፃኑ እንደ ሞተ ይነግሩት ዘንድ ፈሩ። ዳዊትም ባሪያዎቹ በሹክሹክታ ሲነጋገሩ ባየ ጊዜ ዳዊት ሕፃኑ እንደ ሞተ አወቀ፥ ዳዊትም ባሪያዎቹን፦ ሕፃኑ ሞቶአል? አላቸው። እነርሱም፦ ሞቶአል አሉት። ዳዊትም ከምድር ተነሥቶ ታጠበ፥ ተቀባም፥ ልብሱንም ለወጠ፥ ወደ እግዚአብሔርም ቤት ገብቶ ሰገደ። ወደ ቤቱም መጣ፦ እንጀራ አምጡልኝ አለ፥ በፊቱም አቀረቡለት፥ በላም። ባሪያዎቹም፦ ይህ ያደረግኸው ነገር ምንድር ነው? በሕይወት ሳለ ስለ ሕፃኑ ጾምህና አለቀስህ፥ ከሞተ በኋላ ግን ተነሥተህ እንጀራ በላህ አሉት። እርሱም፦ ሕፃኑ ሕያው ሳለ፦ እግዚአብሔር ይምረኝ፥ ሕፃኑም በሕይወት ይኖር እንደ ሆነ ማን ያውቃል? ብዬ ጾምሁ አለቀስሁም። አሁን ግን ሞቶአል፥ የምጾመው ስለ ምንድር ነው? በውኑ እንግዲህ እመልሰው ዘንድ ይቻለኛልን? እኔ ወደ እርሱ እሄዳለሁ እንጂ እርሱ ወደ እኔ አይመለስም አለ። ዳዊትም ሚስቱን ቤርሳቤህን አጽናናት፥ ወደ እርስዋም ገባ፥ ከእርስዋም ጋር ተኛ፥ ወንድ ልጅም ወለደች፥ ስሙንም ሰሎሞን ብሎ ጠራው። እግዚአብሔርም ወደደው፥ ደግሞም በነቢዩ በናታን እጅ ልኮ ስሙን ስለ እግዚአብሔር ይዲድያ ብሎ ጠራው። ኢዮአብም የአሞንን ልጆች ከተማ ረባትን ወጋ፥ የውኃውንም ከተማ ያዘ። ኢዪአብም ወደ ዳዊት፦ ረባትን ወግቻለሁ፥ የውኃውንም ከተማ ይዤአለሁ። አሁንም ከተማይቱን እንዳልይዝ፥ በስሜም እንዳትጠራ፥ የቀረውን ሕዝብ ሰብስብ፥ ከተማይቱንም ከብበህ ያዝ ብሎ መልእክተኞችን ላከ። ዳዊትም ሕዝቡን ሁሉ ሰብስቦ ወደ ረባት ሄደ፥ ወግቶም ያዛት። የንጉሣቸውንም ዘውድ ከራሱ ላይ ወሰደ። ክብደቱም አንድ መክሊት ወርቅ ያህል ነበር፥ ክቡር ዕንቁም ነበረበት፥ ዳዊትም በራሱ ላይ አደረገው። ከከተማይቱም እጅግ ብዙ ምርኮ አወጣ። በውስጥዋም የነበሩትን ሕዝብ አውጥቶ በመጋዝና በብረት መቆፈሪያና በብረት መጥረቢያ እንዲሠሩ አደረጋቸው፥ የሸክላ ጡብም እንዲያቃጥሉ አደረጋቸው፥ በአሞን ልጆች ከተሞች ሁሉ እንዲህ አደረገ። ዳዊትም ሕዝቡም ሁሉ ወደ ኢየሩሳሌም ተመለሱ።

2 ሳሙኤል 12:11-31 አዲሱ መደበኛ ትርጒም (NASV)

“እግዚአብሔር እንዲህ ይላል፤ ‘እነሆ ከራስህ ቤት ክፉ ነገር አስነሣብሃለሁ፤ ዐይንህ እያየም ሚስቶችህን ወስጄ ለአንተ ቅርብ ለሆነ ሰው ለአንዱ እሰጣለሁ፤ እርሱም በቀን ብርሃን ከሚስቶችህ ጋራ ይተኛል። አንተ ይህን በስውር አድርገኸዋል፤ እኔ ግን ይህንኑ ነገር በቀን ብርሃን በእስራኤል ሁሉ ፊት እገልጠዋለሁ።’ ” ከዚያም ዳዊት ለናታን፣ “እግዚአብሔርን በጣም በድያለሁ” አለው። ናታንም እንዲህ አለው፣ “እግዚአብሔር ኀጢአትህን አስወግዶልሃል። አንተ አትሞትም፤ ይህን በመፈጸምህ ግን፣ የእግዚአብሔር ጠላቶች እጅግ እንዲያቃልሉት ስላደረግህ፣ የተወለደልህ ልጅ ይሞታል።” ናታን ወደ ቤቱ ከሄደ በኋላ፣ የኦርዮ ሚስት ለዳዊት የወለደችለትን ሕፃን እግዚአብሔር ከባድ ሕመም ላይ ጣለው። ዳዊት ስለ ሕፃኑ እግዚአብሔርን ለመነ፤ ጾመም፤ ከዚያም ወደ ክፍሉ ገብቶ በተከታታይ ሌሊቱን መሬት ላይ ተኝቶ ዐደረ። የቤተ ሰቡ ሰው፣ ሽማግሌዎችም ከመሬት ሊያስነሡት በአጠገቡ ቆሙ፤ እርሱ ግን እንቢ አለ፤ ዐብሯቸውም አንዳች ነገር አልበላም። በሰባተኛው ቀን ሕፃኑ ሞተ፤ የዳዊት አገልጋዮችም፣ “እነሆ ሕፃኑ በሕይወት እያለ የነገርነውን ዳዊት አልሰማንም፤ ታዲያ አሁን የሕፃኑን መሞት እንዴት አድርገን ልንነግረው እንችላለን? በራሱ ላይ ጕዳት ሊያደርስ ይችላል” ብለው መንገሩን ፈሩ። ዳዊት አገልጋዮቹ በሹክሹክታ ሲነጋገሩ አይቶ፣ ሕፃኑ መሞቱን ዐወቀ፤ ስለዚህ፣ “ሕፃኑ ሞተ?” ብሎ ጠየቃቸው። እነርሱም፣ “አዎን ሞቷል” ብለው መለሱለት። በዚህ ጊዜ ዳዊት ከመሬት ተነሣ፤ ከታጠበ፣ ከተቀባና ልብሱን ከለወጠ በኋላ፣ ወደ እግዚአብሔርም ቤት ሄዶ ሰገደ። ከዚያም ወደ ክፍሉ ገባ፤ በራሱም ጥያቄ ምግብ አቅርበውለት በላ። አገልጋዮቹም፣ “እንደዚህ ያደረግኸው ለምንድን ነው? ሕፃኑ በሕይወት እያለ ጾምህ፤ አለቀስህ፤ ሕፃኑ ከሞተ በኋላ ግን ተነሥተህ በላህ” ብለው ጠየቁት። እርሱም እንዲህ አለ፤ “በርግጥ ሕፃኑ በሕይወት እያለ፣ ‘እግዚአብሔር ይቅር ብሎኝ ሕፃኑን በሕይወት ያኖረው ይሆናል’ ብዬ ጾምሁ፤ አለቀስሁ። አሁን ግን ሕፃኑ ስለ ሞተ፣ የምጾመው ለምንድን ነው? መልሼ ላመጣው እችላለሁን? እኔ ወደ እርሱ እሄዳለሁ እንጂ፣ እርሱ ወደ እኔ አይመለስ!” ከዚያም ዳዊት ሚስቱን ቤርሳቤህን አጽናናት፤ ወደ እርሷም ገብቶ ዐብሯት ተኛ፤ ወንድ ልጅ ወለደች፤ ስሙንም ሰሎሞን አለው። እግዚአብሔርም ወደደው፤ እግዚአብሔር ሕፃኑን ስለ ወደደውም ስሙ ይዲድያ ተብሎ እንዲጠራ በነቢዩ በናታን በኩል ቃል ላከ። በዚያ ጊዜም ኢዮአብ የአሞናውያንን ከተማ ረባትን ወግቶ የቤተ መንግሥቱን ምሽግ ያዘ። ከዚያም ኢዮአብ እንዲህ በማለት ወደ ዳዊት መልክተኞችን ላከ፤ “ረባትን ወግቼ የውሃውን ከተማ ይዤአለሁ፤ እንግዲህ የቀረውን ሰራዊት አሰባስበህ ከተማዪቱን ክበብና ያዛት፤ አለዚያ እኔ ከተማዪቱን እይዛትና በስሜ መጠራቷ ነው።” ስለዚህ ዳዊት መላውን ሰራዊት አሰባስቦ ወደ ረባት በመሄድ ወግቶ ያዛት። የንጉሣቸውንም ዘውድ ከራሱ ላይ ወሰደ፤ የዘውዱ ክብደት አንድ መክሊት ወርቅ የሚመዝን ሲሆን፣ በከበረ ዕንቍም ያጌጠ ነበር፤ ይህም በዳዊት ራስ ላይ ተጫነ። ዳዊትም ከከተማዪቱ እጅግ ብዙ ምርኮ ወሰደ፤ እዚያ የነበሩትንም ሕዝብ አውጥቶ መጋዝ፣ የብረት መቈፈሪያና መጥረቢያ ተጠቅመው ሥራ እንዲሠሩ አደረጋቸው፣ እንዲሁም የሸክላ ጡብ አሠራቸው። እንዲህ ያለውም ሥራ በሌሎቹ የአሞናውያን ከተሞች ሁሉ እንዲፈጸም አደረገ። ከዚያም ዳዊትና ሰራዊቱ በሙሉ ወደ ኢየሩሳሌም ተመለሱ።

2 ሳሙኤል 12:11-31 አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም (አማ05)

ከቤተሰብህ አንዱ ተነሥቶ ችግር እንዲያደርስብህ የማደርግ መሆኔን በመሐላ አረጋግጥልሃለሁ፤ ሚስቶችህን ወስጄ ለሌላ ሰው በምሰጥበት ጊዜ ይህ ነገር እንደሚፈጸም ትገነዘባለህ፤ እርሱም ከሚስቶችህ ጋር በቀን ብርሃን ይገናኛል። አንተ ይህን ኃጢአት በስውር ሠርተሃል፤ እኔ ግን እስራኤል ሁሉ ይመለከቱ ዘንድ ይህን ነገር የቀን ብርሃን ባለበት በግልጥ አደርጋለሁ።’ ” ዳዊትም “ኃጢአት በመሥራት እግዚአብሔርን አሳዝኛለሁ” አለ። ናታንም እንዲህ ሲል መለሰለት፦ “እግዚአብሔር ይቅር ስላለህ አትሞትም፤ ነገር ግን ይህን በደል በመፈጸም እግዚአብሔርን ስለ ናቅህ የተወለደልህ ልጅ ይሞታል።” ከዚህ በኋላ ናታን ወደ ቤቱ ሄደ። የኦርዮ ሚስት ለዳዊት የወለደችለትን ልጅ እግዚአብሔር በከባድ ሕመም ቀሠፈው፤ ዳዊትም ሕፃኑን እንዲፈውስለት በጾምና በጸሎት እግዚአብሔርን ለመነ፤ በየሌሊቱም ወደ መኝታ ክፍሉ እየገባ በመሬት ላይ ይተኛ ነበር፤ የቤተ መንግሥቱ ባለሟሎች ወደ እርሱ ቀርበው ከመሬት ላይ ሊያስነሡት ሞከሩ፤ እርሱ ግን ከመሬት ላለመነሣትና ከእነርሱም ጋር ምንም ነገር ላለመቅመስ ወሰነ፤ ከአንድ ሳምንትም በኋላ ሕፃኑ ሞተ፤ የዳዊት ባለሟሎችም መርዶውን ለመንገር ፈርተው “ሕፃኑ በሕይወት በነበረበት ጊዜ እንኳ ዳዊት ስንመክረው አልሰማንም፤ ታዲያ፥ አሁን የልጁን መሞት እንዴት አድርገን ልንነግረው እንችላለን? ምናልባት በራሱ ላይ አንዳች ጒዳት ማድረስ ይችል ይሆናል!” አሉ። ዳዊት እርስ በርሳቸው ሲያንሾካሹኩ በሰማ ጊዜ ሕፃኑ መሞቱን ተረዳ፤ ስለዚህም “ሕፃኑ ሞተ እንዴ?” ሲል ጠየቃቸው። እነርሱም “አዎ ሞቶአል” ሲሉ መለሱለት። ዳዊትም ከተኛበት መሬት ተነሥቶ ሰውነቱን ታጠበ፤ ቅባት ተቀባ፤ ልብሱንም ለወጠ፤ ከዚያም ወደ እግዚአብሔር ቤት ሄዶ ሰገደ፤ ወደ ቤተ መንግሥቱም ሲመለስ ምግብ እንዲያቀርቡለት ጠየቀ፤ እንደ ቀረበለትም ወዲያውኑ ተመገበ፤ ባለሟሎቹም “ይህ ነገር ምን እንደ ሆነ ለማወቅ አልቻልንም፤ ሕፃኑ በሕይወት በነበረበት ጊዜ በመጾም አለቀስክለት፤ እርሱ ከሞተ በኋላ ግን ወዲያውኑ ተነሥተህ ተመገብክ!” አሉት። ዳዊትም እንዲህ ሲል መለሰ፤ “ሕፃኑ በሕይወት ሳለ መጾሜና ማልቀሴ እርግጥ ነው፤ እግዚአብሔር ምሕረት አድርጎልኝ ሕፃኑ እንዳይሞት ያደርግ ይሆናል ብዬ አስቤ ነበር፤ አሁን ግን ከሞተ በኋላ ስለምን እጾማለሁ? ሕፃኑን እንደገና በሕይወት እንዲኖር ማድረግ ይቻለኛልን? እኔ አንድ ቀን ወደ እርሱ እሄዳለሁ እንጂ እርሱ ወደ እኔ ተመልሶ አይመጣም።” ከዚህ በኋላ ዳዊት ሚስቱን ቤርሳቤህን አጽናናት፤ ከእርስዋም ጋር ግንኙነት አደረገ፤ እርስዋም ወንድ ልጅ ወለደችለት፤ ዳዊትም የልጁን ስም “ሰሎሞን” ብሎ ጠራው፤ እግዚአብሔር ሕፃኑን ስለ ወደደው፥ “ይዲድያ” የሚል ስም እንዲያወጣለት ነቢዩ ናታንን አዘዘው፤ ይህም “በእግዚአብሔር የተወደደ” ማለት ነው። በዚያን ጊዜ ኢዮአብ ራባ ተብላ የምትጠራውን የዐሞናውያንን ከተማ ለመያዝ የሚያደርገውን ዘመቻ በመቀጠል የከተማ ውሃ የሚገኝበትን ምሽግ ያዘ። መልእክተኞችንም ልኮ ለዳዊት እንዲህ ብለው እንዲነግሩት አደረገ፤ “በራባ ላይ አደጋ ጥዬ የውሃ ማመንጫውን ምሽግ ይዤአለሁ፤ እነሆ አሁን ከሠራዊትህ ቀሪውን ክፍል አሰባስብና በከተማይቱ ላይ አደጋ በመጣል አንተው ራስህ ያዛት፤ አለበለዚያ እኔ ከተማይቱን ይዤ በስሜ እንድትጠራ አደርጋለሁ።” ስለዚህም ዳዊት ሠራዊቱን ሁሉ አሰባስቦ ወደ ራባ በመዝመት አደጋ ጥሎ ያዛት፤ ዳዊት የዐሞናውያን አምላክ ከሆነው ሚልኮም ተብሎ ከሚጠራው ጣዖት ራስ ላይ ሠላሳ አምስት ኪሎ ግራም የሚመዝነውንና በውስጡም የከበረ ዕንቊ ያለበትን ዘውድ ወስዶ በራሱ ላይ ደፋው፤ እንዲሁም ከከተማይቱ ብዙ ምርኮ ወሰደ፤ ሰዎቹም በመጋዝ፥ በብረት ዶማና በብረት መጥረቢያ እንዲሠሩ አደረጋቸው፤ ጡብ እንዲሠሩለትም አስገደዳቸው፤ በሌሎቹ የዐሞን ከተሞች ሁሉ ያሉትን ሰዎችም እንዲሁ በዚሁ ዐይነት እንዲሠሩ አደረጋቸው፤ ከዚህ በኋላ እርሱና ሠራዊቱ ወደ ኢየሩሳሌም ተመለሱ።

2 ሳሙኤል 12:11-31 የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) (አማ2000)

እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር እን​ዲህ ይላል፦ እነሆ ከቤ​ትህ ክፉ ነገ​ርን አስ​ነ​ሣ​ብ​ሃ​ለሁ፤ ሚስ​ቶ​ች​ህ​ንም በዐ​ይ​ኖ​ችህ እያ​የህ እወ​ስ​ዳ​ለሁ፤ ለዘ​መ​ድ​ህም እሰ​ጣ​ቸ​ዋ​ለሁ፤ በዚ​ችም ፀሐይ ፊት ከሚ​ስ​ቶ​ችህ ጋር ይተ​ኛል። አንተ ይህን በስ​ውር አድ​ር​ገ​ኸ​ዋል፤ እኔ ግን ይህን በእ​ስ​ራ​ኤል ሁሉ ፊትና በፀ​ሐይ ፊት አደ​ር​ገ​ዋ​ለሁ።” ዳዊ​ትም ናታ​ንን፥ “እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርን በድ​ያ​ለሁ” አለው። ናታ​ንም ዳዊ​ትን አለው፥ “እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ደግሞ ኀጢ​አ​ት​ህን አር​ቆ​ል​ሃል፤ አት​ሞ​ት​ምም። ነገር ግን በዚህ ነገር ለእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ጠላ​ቶች መነ​ሣ​ሣት ምክ​ን​ያት አድ​ር​ገ​ሃ​ልና ስለ​ዚህ ደግሞ የተ​ወ​ለ​ደ​ልህ ልጅ ፈጽሞ ይሞ​ታል” አለው። ናታ​ንም ወደ ቤቱ ተመ​ለሰ። እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርም የኦ​ርዮ ሚስት ለዳ​ዊት የወ​ለ​ደ​ች​ውን ሕፃን ቀሠ​ፈው፤ እጅ​ግም ታምሞ ነበር። ዳዊ​ትም ስለ ሕፃኑ እግ​ዚ​አ​ሔ​ርን ለመነ፤ ዳዊ​ትም ጾመ፤ ገብ​ቶም በመ​ሬት ላይ ተኛ። የቤ​ቱም ሽማ​ግ​ሌ​ዎች ተነ​ሥ​ተው ከም​ድር ያነ​ሡት ዘንድ በአ​ጠ​ገቡ ቆሙ፤ እርሱ ግን እንቢ አለ፤ ከእ​ነ​ር​ሱም ጋር እን​ጀራ አል​በ​ላም። በሰ​ባ​ተ​ኛ​ውም ቀን ሕፃኑ ሞተ። የዳ​ዊ​ትም ብላ​ቴ​ኖች፥ “ሕፃኑ በሕ​ይ​ወት ሳለ ብን​ነ​ግ​ረው አል​ሰ​ማ​ንም፤ ይል​ቁ​ንስ ሕፃኑ እንደ ሞተ ብን​ነ​ግ​ረው እን​ዴት ይሆን? በራሱ ላይ ክፉ ያደ​ር​ጋል” ብለው ሕፃኑ እንደ ሞተ ይነ​ግ​ሩት ዘንድ ፈሩ። ዳዊ​ትም ብላ​ቴ​ኖቹ በሹ​ክ​ሹ​ክታ ሲነ​ጋ​ገሩ ባየ ጊዜ ዳዊት ሕፃኑ እንደ ሞተ ዐወቀ፤ ዳዊ​ትም ብላ​ቴ​ኖ​ቹን፥ “ሕፃኑ ሞቶ​አል?” አላ​ቸው። እነ​ር​ሱም፥ “ሞቶ​አል” አሉት። ዳዊ​ትም ከም​ድር ተነ​ሥቶ ታጠበ፤ ተቀ​ባም፤ ልብ​ሱ​ንም ለወጠ፤ ወደ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርም ቤት ገብቶ ሰገደ። ወደ ቤቱም መጣ፦ እን​ጀ​ራም አም​ጡ​ልኝ አለ፤ በፊ​ቱም እን​ጀራ አቀ​ረ​ቡ​ለት፤ በላም። ብላ​ቴ​ኖ​ቹም፥ “ይህ ስለ ሕፃኑ ያደ​ረ​ግ​ኸው ነገር ምን​ድን ነው? እርሱ በሕ​ይ​ወት ሳለ ጾም​ህና አለ​ቀ​ስህ፤ እን​ቅ​ል​ፍም አጣህ፤ ሕፃኑ ከሞተ በኋላ ግን ተነ​ሥ​ተህ እን​ጀራ በላህ፤ ጠጣ​ህም” አሉት። ዳዊ​ትም፥ “ሕፃኑ ሕያው ሳለ፤ ምና​ል​ባት እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ይም​ረኝ፥ ሕፃ​ኑም በሕ​ይ​ወት ይኖር እንደ ሆነ ማን ያው​ቃል? ብዬ ጾምሁ፤ አለ​ቀ​ስ​ሁም። አሁን ግን ሞቶ​አል፤ የም​ጾ​መው ስለ ምን​ድን ነው? በውኑ እን​ግ​ዲህ እመ​ል​ሰው ዘንድ ይቻ​ለ​ኛ​ልን? እኔ ወደ እርሱ እሄ​ዳ​ለሁ እንጂ እርሱ ወደ እኔ አይ​መ​ለ​ስም” አለ። ዳዊ​ትም ሚስ​ቱን ቤር​ሳ​ቤ​ህን አጽ​ና​ናት፤ ወደ እር​ስ​ዋም ገባ፤ ከእ​ር​ስ​ዋም ጋር ተኛ፤ ፀነ​ሰ​ችም፤ ወንድ ልጅም ወለ​ደች፤ ስሙ​ንም ሰሎ​ሞን ብሎ ጠራው። እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርም ወደ​ደው። ደግ​ሞም በነ​ቢዩ በና​ታን እጅ ልኮ ስሙን ስለ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ፍቁረ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ብሎ ጠራው። ኢዮ​አ​ብም የአ​ሞ​ንን ልጆች ከተማ ራባ​ትን ወጋ፤ የመ​ን​ግ​ሥ​ታ​ቸ​ው​ንም ከተማ ያዘ። ኢዮ​አ​ብም ወደ ዳዊት እን​ዲህ ብሎ መል​እ​ክ​ተ​ኞ​ችን ላከ፥ “ራባ​ትን ወግ​ቻ​ለሁ፤ የው​ኃ​ው​ንም ከተማ ይዤ​አ​ለሁ። አሁ​ንም ከተ​ማ​ዪ​ቱን እኔ ቀድሜ እን​ዳ​ል​ይዝ፥ በስ​ሜም እን​ዳ​ት​ጠራ፥ የቀ​ረ​ውን ሕዝብ ሰብ​ስብ፥ ከተ​ማ​ዪ​ቱ​ንም ከብ​በህ ቀድ​መህ ያዛት።” ዳዊ​ትም ሕዝ​ቡን ሁሉ ሰብ​ስቦ ወደ ራባት ሄደ፤ ወግ​ቶም ያዛት። የን​ጉ​ሣ​ቸ​ው​ንም የሜ​ል​ኮ​ምን ዘውድ ከራሱ ላይ ወሰደ። ክብ​ደ​ቱም አንድ መክ​ሊት ወርቅ ያህል ነበር፤ ክቡር ዕን​ቍም ነበ​ረ​በት፤ ዳዊ​ትም በራሱ ላይ አደ​ረ​ገው። ከከ​ተ​ማ​ዪ​ቱም እጅግ ብዙ ምርኮ አወጣ። በው​ስ​ጥ​ዋም የነ​በ​ሩ​ትን ሕዝብ አው​ጥቶ በመ​ጋ​ዝና በብ​ረት መቈ​ፈ​ሪያ በብ​ረት መጥ​ረ​ቢ​ያም ሥር አኖ​ራ​ቸው፤ በሸ​ክላ ጡብ እቶ​ንም አሳ​ለ​ፋ​ቸው። በአ​ሞን ልጆች ከተ​ሞች ሁሉ እን​ዲሁ አደ​ረገ። ዳዊ​ትም፥ ሕዝ​ቡም ሁሉ ወደ ኢየ​ሩ​ሳ​ሌም ተመ​ለሱ።

2 ሳሙኤል 12:11-31 አዲሱ መደበኛ ትርጒም (NASV)

“እግዚአብሔር እንዲህ ይላል፤ ‘እነሆ ከራስህ ቤት ክፉ ነገር አስነሣብሃለሁ፤ ዐይንህ እያየም ሚስቶችህን ወስጄ ለአንተ ቅርብ ለሆነ ሰው ለአንዱ እሰጣለሁ፤ እርሱም በቀን ብርሃን ከሚስቶችህ ጋራ ይተኛል። አንተ ይህን በስውር አድርገኸዋል፤ እኔ ግን ይህንኑ ነገር በቀን ብርሃን በእስራኤል ሁሉ ፊት እገልጠዋለሁ።’ ” ከዚያም ዳዊት ለናታን፣ “እግዚአብሔርን በጣም በድያለሁ” አለው። ናታንም እንዲህ አለው፣ “እግዚአብሔር ኀጢአትህን አስወግዶልሃል። አንተ አትሞትም፤ ይህን በመፈጸምህ ግን፣ የእግዚአብሔር ጠላቶች እጅግ እንዲያቃልሉት ስላደረግህ፣ የተወለደልህ ልጅ ይሞታል።” ናታን ወደ ቤቱ ከሄደ በኋላ፣ የኦርዮ ሚስት ለዳዊት የወለደችለትን ሕፃን እግዚአብሔር ከባድ ሕመም ላይ ጣለው። ዳዊት ስለ ሕፃኑ እግዚአብሔርን ለመነ፤ ጾመም፤ ከዚያም ወደ ክፍሉ ገብቶ በተከታታይ ሌሊቱን መሬት ላይ ተኝቶ ዐደረ። የቤተ ሰቡ ሰው፣ ሽማግሌዎችም ከመሬት ሊያስነሡት በአጠገቡ ቆሙ፤ እርሱ ግን እንቢ አለ፤ ዐብሯቸውም አንዳች ነገር አልበላም። በሰባተኛው ቀን ሕፃኑ ሞተ፤ የዳዊት አገልጋዮችም፣ “እነሆ ሕፃኑ በሕይወት እያለ የነገርነውን ዳዊት አልሰማንም፤ ታዲያ አሁን የሕፃኑን መሞት እንዴት አድርገን ልንነግረው እንችላለን? በራሱ ላይ ጕዳት ሊያደርስ ይችላል” ብለው መንገሩን ፈሩ። ዳዊት አገልጋዮቹ በሹክሹክታ ሲነጋገሩ አይቶ፣ ሕፃኑ መሞቱን ዐወቀ፤ ስለዚህ፣ “ሕፃኑ ሞተ?” ብሎ ጠየቃቸው። እነርሱም፣ “አዎን ሞቷል” ብለው መለሱለት። በዚህ ጊዜ ዳዊት ከመሬት ተነሣ፤ ከታጠበ፣ ከተቀባና ልብሱን ከለወጠ በኋላ፣ ወደ እግዚአብሔርም ቤት ሄዶ ሰገደ። ከዚያም ወደ ክፍሉ ገባ፤ በራሱም ጥያቄ ምግብ አቅርበውለት በላ። አገልጋዮቹም፣ “እንደዚህ ያደረግኸው ለምንድን ነው? ሕፃኑ በሕይወት እያለ ጾምህ፤ አለቀስህ፤ ሕፃኑ ከሞተ በኋላ ግን ተነሥተህ በላህ” ብለው ጠየቁት። እርሱም እንዲህ አለ፤ “በርግጥ ሕፃኑ በሕይወት እያለ፣ ‘እግዚአብሔር ይቅር ብሎኝ ሕፃኑን በሕይወት ያኖረው ይሆናል’ ብዬ ጾምሁ፤ አለቀስሁ። አሁን ግን ሕፃኑ ስለ ሞተ፣ የምጾመው ለምንድን ነው? መልሼ ላመጣው እችላለሁን? እኔ ወደ እርሱ እሄዳለሁ እንጂ፣ እርሱ ወደ እኔ አይመለስ!” ከዚያም ዳዊት ሚስቱን ቤርሳቤህን አጽናናት፤ ወደ እርሷም ገብቶ ዐብሯት ተኛ፤ ወንድ ልጅ ወለደች፤ ስሙንም ሰሎሞን አለው። እግዚአብሔርም ወደደው፤ እግዚአብሔር ሕፃኑን ስለ ወደደውም ስሙ ይዲድያ ተብሎ እንዲጠራ በነቢዩ በናታን በኩል ቃል ላከ። በዚያ ጊዜም ኢዮአብ የአሞናውያንን ከተማ ረባትን ወግቶ የቤተ መንግሥቱን ምሽግ ያዘ። ከዚያም ኢዮአብ እንዲህ በማለት ወደ ዳዊት መልክተኞችን ላከ፤ “ረባትን ወግቼ የውሃውን ከተማ ይዤአለሁ፤ እንግዲህ የቀረውን ሰራዊት አሰባስበህ ከተማዪቱን ክበብና ያዛት፤ አለዚያ እኔ ከተማዪቱን እይዛትና በስሜ መጠራቷ ነው።” ስለዚህ ዳዊት መላውን ሰራዊት አሰባስቦ ወደ ረባት በመሄድ ወግቶ ያዛት። የንጉሣቸውንም ዘውድ ከራሱ ላይ ወሰደ፤ የዘውዱ ክብደት አንድ መክሊት ወርቅ የሚመዝን ሲሆን፣ በከበረ ዕንቍም ያጌጠ ነበር፤ ይህም በዳዊት ራስ ላይ ተጫነ። ዳዊትም ከከተማዪቱ እጅግ ብዙ ምርኮ ወሰደ፤ እዚያ የነበሩትንም ሕዝብ አውጥቶ መጋዝ፣ የብረት መቈፈሪያና መጥረቢያ ተጠቅመው ሥራ እንዲሠሩ አደረጋቸው፣ እንዲሁም የሸክላ ጡብ አሠራቸው። እንዲህ ያለውም ሥራ በሌሎቹ የአሞናውያን ከተሞች ሁሉ እንዲፈጸም አደረገ። ከዚያም ዳዊትና ሰራዊቱ በሙሉ ወደ ኢየሩሳሌም ተመለሱ።

2 ሳሙኤል 12:11-31 መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) (አማ54)

እግዚአብሔር እንዲህ ይላል፦ እነሆ፥ ከቤትህ ክፉ ነገር አስነሣብሃለሁ፥ ሚስቶችህንም በዓይንህ ፊት እወስዳለሁ፥ ለዘመድህም እሰጣቸዋለሁ፥ በዚህችም ፀሐይ ዓይን ፊት ከሚስቶችህ ጋር ይተኛል። አንተ ይህን በስውር አድርገኸዋል፥ እኔ ግን ይህን በእስራኤል ሁሉ ፊትና በፀሐይ ፊት አደርገዋለሁ። ዳዊትም ናታንን፦ እግዚአብሔርን በድያለሁ አለው። ናታንም ዳዊትን፦ እግዚአብሔር ደግሞ ኃጢአትህን አርቆልሃል፥ አትሞትም። ነገር ግን በዚህ ነገር ለእግዚአብሔር ጠላቶች ታላቅ የስድብ ምክንያት አድርገሃልና ስለዚህ ደግሞ የተወለደልህ ልጅ ፈጽሞ ይሞታል አለው። ናታንም ወደ ቤቱ ተመለሰ። እግዚአብሔርም የኦርዮ ሚስት ለዳዊት የወለደችውን ሕፃን ቀሠፈ፥ እጅግም ታምሞ ነበር። ዳዊትም ስለ ሕፃኑ እግዚአብሔርን ለመነ፥ ዳዊትም ጾመ፥ ገብቶም በመሬት ላይ ተኛ። የቤቱም ሽማግሌዎች ተነሥተው ከምድር ያነሡት ዘንድ በአጠገቡ ቆሙ፥ እርሱ ግን እንቢ አለ፥ ከእነርሱም ጋር እንጀራ አልበላም። በሰባተኛውም ቀን ሕፃኑ ሞተ። የዳዊትም ባሪያዎች፦ ሕፃኑ በሕይወት ሳለ ብንነግረው አልሰማንም፥ ይልቁንስ ሕፃኑ እንደ ሞተ ብንነግረው እንዴት ይሆን? በነፍሱ ክፉ ያደርጋል ብለው ሕፃኑ እንደ ሞተ ይነግሩት ዘንድ ፈሩ። ዳዊትም ባሪያዎቹ በሹክሹክታ ሲነጋገሩ ባየ ጊዜ ዳዊት ሕፃኑ እንደ ሞተ አወቀ፥ ዳዊትም ባሪያዎቹን፦ ሕፃኑ ሞቶአል? አላቸው። እነርሱም፦ ሞቶአል አሉት። ዳዊትም ከምድር ተነሥቶ ታጠበ፥ ተቀባም፥ ልብሱንም ለወጠ፥ ወደ እግዚአብሔርም ቤት ገብቶ ሰገደ። ወደ ቤቱም መጣ፦ እንጀራ አምጡልኝ አለ፥ በፊቱም አቀረቡለት፥ በላም። ባሪያዎቹም፦ ይህ ያደረግኸው ነገር ምንድር ነው? በሕይወት ሳለ ስለ ሕፃኑ ጾምህና አለቀስህ፥ ከሞተ በኋላ ግን ተነሥተህ እንጀራ በላህ አሉት። እርሱም፦ ሕፃኑ ሕያው ሳለ፦ እግዚአብሔር ይምረኝ፥ ሕፃኑም በሕይወት ይኖር እንደ ሆነ ማን ያውቃል? ብዬ ጾምሁ አለቀስሁም። አሁን ግን ሞቶአል፥ የምጾመው ስለ ምንድር ነው? በውኑ እንግዲህ እመልሰው ዘንድ ይቻለኛልን? እኔ ወደ እርሱ እሄዳለሁ እንጂ እርሱ ወደ እኔ አይመለስም አለ። ዳዊትም ሚስቱን ቤርሳቤህን አጽናናት፥ ወደ እርስዋም ገባ፥ ከእርስዋም ጋር ተኛ፥ ወንድ ልጅም ወለደች፥ ስሙንም ሰሎሞን ብሎ ጠራው። እግዚአብሔርም ወደደው፥ ደግሞም በነቢዩ በናታን እጅ ልኮ ስሙን ስለ እግዚአብሔር ይዲድያ ብሎ ጠራው። ኢዮአብም የአሞንን ልጆች ከተማ ረባትን ወጋ፥ የውኃውንም ከተማ ያዘ። ኢዪአብም ወደ ዳዊት፦ ረባትን ወግቻለሁ፥ የውኃውንም ከተማ ይዤአለሁ። አሁንም ከተማይቱን እንዳልይዝ፥ በስሜም እንዳትጠራ፥ የቀረውን ሕዝብ ሰብስብ፥ ከተማይቱንም ከብበህ ያዝ ብሎ መልእክተኞችን ላከ። ዳዊትም ሕዝቡን ሁሉ ሰብስቦ ወደ ረባት ሄደ፥ ወግቶም ያዛት። የንጉሣቸውንም ዘውድ ከራሱ ላይ ወሰደ። ክብደቱም አንድ መክሊት ወርቅ ያህል ነበር፥ ክቡር ዕንቁም ነበረበት፥ ዳዊትም በራሱ ላይ አደረገው። ከከተማይቱም እጅግ ብዙ ምርኮ አወጣ። በውስጥዋም የነበሩትን ሕዝብ አውጥቶ በመጋዝና በብረት መቆፈሪያና በብረት መጥረቢያ እንዲሠሩ አደረጋቸው፥ የሸክላ ጡብም እንዲያቃጥሉ አደረጋቸው፥ በአሞን ልጆች ከተሞች ሁሉ እንዲህ አደረገ። ዳዊትም ሕዝቡም ሁሉ ወደ ኢየሩሳሌም ተመለሱ።

2 ሳሙኤል 12:11-31 አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም (አማ05)

ከቤተሰብህ አንዱ ተነሥቶ ችግር እንዲያደርስብህ የማደርግ መሆኔን በመሐላ አረጋግጥልሃለሁ፤ ሚስቶችህን ወስጄ ለሌላ ሰው በምሰጥበት ጊዜ ይህ ነገር እንደሚፈጸም ትገነዘባለህ፤ እርሱም ከሚስቶችህ ጋር በቀን ብርሃን ይገናኛል። አንተ ይህን ኃጢአት በስውር ሠርተሃል፤ እኔ ግን እስራኤል ሁሉ ይመለከቱ ዘንድ ይህን ነገር የቀን ብርሃን ባለበት በግልጥ አደርጋለሁ።’ ” ዳዊትም “ኃጢአት በመሥራት እግዚአብሔርን አሳዝኛለሁ” አለ። ናታንም እንዲህ ሲል መለሰለት፦ “እግዚአብሔር ይቅር ስላለህ አትሞትም፤ ነገር ግን ይህን በደል በመፈጸም እግዚአብሔርን ስለ ናቅህ የተወለደልህ ልጅ ይሞታል።” ከዚህ በኋላ ናታን ወደ ቤቱ ሄደ። የኦርዮ ሚስት ለዳዊት የወለደችለትን ልጅ እግዚአብሔር በከባድ ሕመም ቀሠፈው፤ ዳዊትም ሕፃኑን እንዲፈውስለት በጾምና በጸሎት እግዚአብሔርን ለመነ፤ በየሌሊቱም ወደ መኝታ ክፍሉ እየገባ በመሬት ላይ ይተኛ ነበር፤ የቤተ መንግሥቱ ባለሟሎች ወደ እርሱ ቀርበው ከመሬት ላይ ሊያስነሡት ሞከሩ፤ እርሱ ግን ከመሬት ላለመነሣትና ከእነርሱም ጋር ምንም ነገር ላለመቅመስ ወሰነ፤ ከአንድ ሳምንትም በኋላ ሕፃኑ ሞተ፤ የዳዊት ባለሟሎችም መርዶውን ለመንገር ፈርተው “ሕፃኑ በሕይወት በነበረበት ጊዜ እንኳ ዳዊት ስንመክረው አልሰማንም፤ ታዲያ፥ አሁን የልጁን መሞት እንዴት አድርገን ልንነግረው እንችላለን? ምናልባት በራሱ ላይ አንዳች ጒዳት ማድረስ ይችል ይሆናል!” አሉ። ዳዊት እርስ በርሳቸው ሲያንሾካሹኩ በሰማ ጊዜ ሕፃኑ መሞቱን ተረዳ፤ ስለዚህም “ሕፃኑ ሞተ እንዴ?” ሲል ጠየቃቸው። እነርሱም “አዎ ሞቶአል” ሲሉ መለሱለት። ዳዊትም ከተኛበት መሬት ተነሥቶ ሰውነቱን ታጠበ፤ ቅባት ተቀባ፤ ልብሱንም ለወጠ፤ ከዚያም ወደ እግዚአብሔር ቤት ሄዶ ሰገደ፤ ወደ ቤተ መንግሥቱም ሲመለስ ምግብ እንዲያቀርቡለት ጠየቀ፤ እንደ ቀረበለትም ወዲያውኑ ተመገበ፤ ባለሟሎቹም “ይህ ነገር ምን እንደ ሆነ ለማወቅ አልቻልንም፤ ሕፃኑ በሕይወት በነበረበት ጊዜ በመጾም አለቀስክለት፤ እርሱ ከሞተ በኋላ ግን ወዲያውኑ ተነሥተህ ተመገብክ!” አሉት። ዳዊትም እንዲህ ሲል መለሰ፤ “ሕፃኑ በሕይወት ሳለ መጾሜና ማልቀሴ እርግጥ ነው፤ እግዚአብሔር ምሕረት አድርጎልኝ ሕፃኑ እንዳይሞት ያደርግ ይሆናል ብዬ አስቤ ነበር፤ አሁን ግን ከሞተ በኋላ ስለምን እጾማለሁ? ሕፃኑን እንደገና በሕይወት እንዲኖር ማድረግ ይቻለኛልን? እኔ አንድ ቀን ወደ እርሱ እሄዳለሁ እንጂ እርሱ ወደ እኔ ተመልሶ አይመጣም።” ከዚህ በኋላ ዳዊት ሚስቱን ቤርሳቤህን አጽናናት፤ ከእርስዋም ጋር ግንኙነት አደረገ፤ እርስዋም ወንድ ልጅ ወለደችለት፤ ዳዊትም የልጁን ስም “ሰሎሞን” ብሎ ጠራው፤ እግዚአብሔር ሕፃኑን ስለ ወደደው፥ “ይዲድያ” የሚል ስም እንዲያወጣለት ነቢዩ ናታንን አዘዘው፤ ይህም “በእግዚአብሔር የተወደደ” ማለት ነው። በዚያን ጊዜ ኢዮአብ ራባ ተብላ የምትጠራውን የዐሞናውያንን ከተማ ለመያዝ የሚያደርገውን ዘመቻ በመቀጠል የከተማ ውሃ የሚገኝበትን ምሽግ ያዘ። መልእክተኞችንም ልኮ ለዳዊት እንዲህ ብለው እንዲነግሩት አደረገ፤ “በራባ ላይ አደጋ ጥዬ የውሃ ማመንጫውን ምሽግ ይዤአለሁ፤ እነሆ አሁን ከሠራዊትህ ቀሪውን ክፍል አሰባስብና በከተማይቱ ላይ አደጋ በመጣል አንተው ራስህ ያዛት፤ አለበለዚያ እኔ ከተማይቱን ይዤ በስሜ እንድትጠራ አደርጋለሁ።” ስለዚህም ዳዊት ሠራዊቱን ሁሉ አሰባስቦ ወደ ራባ በመዝመት አደጋ ጥሎ ያዛት፤ ዳዊት የዐሞናውያን አምላክ ከሆነው ሚልኮም ተብሎ ከሚጠራው ጣዖት ራስ ላይ ሠላሳ አምስት ኪሎ ግራም የሚመዝነውንና በውስጡም የከበረ ዕንቊ ያለበትን ዘውድ ወስዶ በራሱ ላይ ደፋው፤ እንዲሁም ከከተማይቱ ብዙ ምርኮ ወሰደ፤ ሰዎቹም በመጋዝ፥ በብረት ዶማና በብረት መጥረቢያ እንዲሠሩ አደረጋቸው፤ ጡብ እንዲሠሩለትም አስገደዳቸው፤ በሌሎቹ የዐሞን ከተሞች ሁሉ ያሉትን ሰዎችም እንዲሁ በዚሁ ዐይነት እንዲሠሩ አደረጋቸው፤ ከዚህ በኋላ እርሱና ሠራዊቱ ወደ ኢየሩሳሌም ተመለሱ።

2 ሳሙኤል 12:11-31 መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) (መቅካእኤ)

ጌታ እንዲህ ይላል፤ “እነሆ ከራስህ ቤት ክፉ ነገር አስነሣብሃለሁ፤ ዐይንህ እያየም ሚስቶችህን ወስጄ ለአንተ ቅርብ ለሆነ ሰው ለአንዱ እሰጣለሁ፤ እርሱም በቀን ብርሃን ከሚስቶችህ ጋር ይተኛል። አንተ ይህን በስውር አድርገኸዋል፤ እኔ ግን ይህንኑ ነገር በቀን ብርሃን በእስራኤል ሁሉ ፊት እገልጠዋለሁ።” ከዚያም ዳዊት ለናታን፥ “ጌታን በድያለሁ” አለው። ናታንም እንዲህ አለው፥ “ጌታ ኃጢአትህን አስወግዶልሃል። አንተ አትሞትም፤ ይህን በመፈጸምህ ግን፥ የጌታ ጠላቶች እጅግ እንዲያቃልሉት ስላደረግህ፥ የተወለደልህ ልጅ ይሞታል።” ናታን ወደ ቤቱ ከሄደ በኋላ፥ የኦርዮን ሚስት ለዳዊት የወለደችለትን ሕፃን ጌታ ከባድ ሕመም ላይ ጣለው። ዳዊት ስለ ሕፃኑ እግዚአብሔርን ለመነ፤ ጾመም፤ ወደ ክፍሉ ገብቶም ሌሊቱን መሬት ላይ ተኝቶ ዐደረ። የቤተሰቡ ሽማግሌዎችም ከመሬት ሊያሰነሡት በአጠገቡ ቆሙ፤ እርሱ ግን እምቢ አለ፤ አብሮአቸውም አንዳች ምግብ አልበላም። በሰባተኛው ቀን ሕፃኑ ሞተ፤ የዳዊት አገልጋዮችም፥ “እነሆ ሕፃኑ በሕይወት እያለ የነገርነውን ዳዊት አልሰማንም ታዲያ አሁን የሕፃኑን መሞት እንዴት አድርገን ልንነግረው እንችላለን? በራሱ ላይ ጉዳት ሊያደርስ ይችላል” ብለው መንገሩን ፈሩ። ዳዊት አገልጋዮቹ በሹክሹክታ ሲነጋገሩ አይቶ፥ ሕፃኑ መሞቱን ዐወቀ፤ ስለዚህ፥ “ሕፃኑ ሞተ?” ብሎ ጠየቃቸው። እነርሱም፥ “አዎን ሞቷል” ብለው መለሱለት። በዚህ ጊዜ ዳዊት ከመሬት ተነሣ፤ ከታጠበ፥ ከተቀባና ልብሱን ከለወጠ በኋላ ወደ ጌታ ቤት ሄዶ ሰገደ። ከዚያም ወደ ክፍሉ ገባ፤ በራሱም ጥያቄ ምግብ አቅርበውለት በላ። አገልጋዮቹም፥ “እንደዚህ ያደረግኸው ለምንድን ነው? ሕፃኑ በሕይወት እያለ ጾምህ፤ አለቀስህ፤ ሕፃኑ ከሞተ በኋላ ግን ተነሥተህ በላህ” ብለው ጠየቁት። እርሱም እንዲህ አለ፤ “በእርግጥ ሕፃኑ በሕይወት እያለ፥ ‘ጌታ ይቅር ብሎኝ ሕፃኑን በሕይወት ያኖረው ይሆናል’ ብዬ ጾምሁ፤ አለቀስሁ። አሁን ግን ሕፃኑ ስለ ሞተ፥ የምጾመው ለምንድን ነው? መልሼ ላመጣው እችላለሁን? እኔ ወደ እርሱ እሄዳለሁ እንጂ፥ እርሱ ወደ እኔ አይመለስም” አለ። ከዚያም ዳዊት ሚስቱን ቤርሳቤህን አጽናናት፤ ወደ እርሷም ገብቶ አብሮአት ተኛ፤ ወንድ ልጅ ወለደች፤ ስሙንም ሰሎሞን አለው። ጌታም ወደደው፤ ጌታ ሕፃኑን ስለ ወደደም ስሙ ይዲድያ ተብሎ እንዲጠራ በነቢዩ በናታን በኩል ቃል ላከ። በዚያን ጊዜም ኢዮአብ የአሞናውያንን ከተማ ራባትን ወግቶ የቤተ መንግሥቱን ምሽግ ያዘ። ከዚያም ኢዮአብ እንዲህ በማለት ወደ ዳዊት መልክተኞችን ላከ፤ “ራባን ወግቼ የውሃውንም ከተማ ይዤአለሁ፤ እንግዲህ የቀረውን ሠራዊት አሰባስበህ ከተማዪቱን ክበብና ያዛት፤ ያለበለዚያ እኔ ከተማዪቱን እይዛትና በስሜ መጠራቷ ነው።” ስለዚህ ዳዊት መላውን ሠራዊት አሰባስቦ ወደ ራባ በመሄድ ወግቶ ያዛት። የንጉሣቸውንም ዘውድ ከራሱ ላይ ወሰደ፤ የዘውዱ ክብደት የሚመዝነው አንድ መክሊት ወርቅ ሲሆን፥ በከበረ ዕንቁም ያጌጠ ነበር፤ ይህም በዳዊት ራስ ላይ ተጫነ። ዳዊትም ከከተማዪቱ እጅግ ብዙ ምርኮ ወሰደ፤ እዚያ የነበሩትንም ሕዝብ አውጥቶ መጋዝ፥ የብረት መቆፈሪያና መጥረቢያ ተጠቅመው ሥራ እንዲሠሩ አደረጋቸው፤ እንዲሁም የሸክላ ጡብ አሠራቸው። እንዲህ ያለውም ሥራ በአሞናውያን ከተሞች ሁሉ እንዲፈጸም አደረገ። ከዚያም ዳዊትና ሠራዊቱ በሙሉ ወደ ኢየሩሳሌም ተመለሱ።