2 ነገሥት 8:1-6

2 ነገሥት 8:1-6 የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) (አማ2000)

ኤል​ሳ​ዕም ልጅ​ዋን ያስ​ነ​ሣ​ላ​ትን ሴት፥ “አንቺ ከቤተ ሰብሽ ጋር ተነ​ሥ​ተሽ ሂጂ፤ በም​ታ​ገ​ኚ​ውም ስፍራ ተቀ​መጪ፤ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር በም​ድር ራብን ጠር​ቶ​አ​ልና፤ ሰባት ዓመ​ትም በም​ድር ላይ ይቆ​ያል” ብሎ ተና​ገ​ራት። ሴቲ​ቱም ተነ​ሥታ ኤል​ሳዕ እንደ ነገ​ራት አደ​ረ​ገች፤ ከቤተ ሰብ​ዋም ጋር ሄዳ በፍ​ል​ስ​ጥ​ኤም ሀገር ሰባት ዓመት ተቀ​መ​ጠች። ሰባ​ቱም ዓመት ካለፈ በኋላ ያች ሴት ከፍ​ል​ስ​ጥ​ኤም ሀገር ተመ​ለ​ሰች፤ ሄዳም ስለ ቤቷና ስለ መሬቷ ልት​ጮህ ወደ ንጉሡ ወጣች። ንጉ​ሡም የእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ሰው የኤ​ል​ሳዕ ሎሌ ግያ​ዝን፥ “ኤል​ሳዕ ያደ​ረ​ገ​ውን ታላ​ላቅ ተአ​ም​ራት ሁሉ ንገ​ረኝ” እያለ ይነ​ጋ​ገር ነበር። እር​ሱም የሞ​ተ​ውን ሕፃን እንደ አስ​ነሣ ለን​ጉሡ ሲና​ገር፥ እነሆ፥ ልጅ​ዋን ያስ​ነ​ሣ​ላት ያች ሴት መጥታ ስለ ቤቷና ስለ መሬቷ ወደ ንጉሥ ጮኸች፥ ግያ​ዝም፥ “ጌታዬ ንጉሥ ሆይ፥ ሴቲቱ ይህች ናት፤ ኤል​ሳ​ዕም ያስ​ነ​ሣው ልጅዋ ይህ ነው፤” አለ። ንጉ​ሡም ሴቲ​ቱን ጠየ​ቃት፤ እር​ስ​ዋም ነገ​ረ​ችው። ንጉ​ሡም ከባ​ለ​ሟ​ሎቹ አን​ዱን ሰጣት፤ “እህ​ል​ዋ​ንና ገን​ዘ​ብ​ዋን ሁሉ ሀገ​ሩን ከተ​ወች ጀምሮ እስከ ዛሬ ድረስ የሄደ ቦታ​ዋን ሁሉ መል​ስ​ላት” አለው።

2 ነገሥት 8:1-6 አዲሱ መደበኛ ትርጒም (NASV)

በዚህ ጊዜ ኤልሳዕ፣ ልጇ ከሞት ያስነሣላትን ሴት፣ “እግዚአብሔር በምድሪቱ ላይ የሰባት ዓመት ራብ ስለ ወሰነ፣ ተነሺና ለጊዜው መቈየት ወደምትችዪበት ቦታ ከቤተ ሰብሽ ጋራ ሂጂ” አላት። ሴቲቱም ተነሥታ የእግዚአብሔር ሰው እንደ ነገራት አደረገች፤ ከነቤተ ሰቧም ሄዳ፣ በፍልስጥኤም ምድር ሰባት ዓመት ተቀመጠች። ከሰባት ዓመት በኋላም፣ ከፍልስጥኤም ምድር ተመልሳ መጣች፤ ስለ ቤቷና ስለ መሬቷ አቤቱታ ለማቅረብም ወደ ንጉሡ ሄደች። በዚህ ጊዜ ንጉሡ የእግዚአብሔርን ሰው አገልጋይ ግያዝን፣ “ኤልሳዕ ያደረጋቸውን ታላላቅ ሥራዎች ሁሉ እስኪ ንገረኝ” እያለው ነበር። ኤልሳዕ ልጇን ከሞት ያስነሣላት ሴት ስለ ቤቷና ስለ መሬቷ ለማመልከት ወደ ንጉሡ ዘንድ የቀረበችውም፣ ኤልሳዕ የሞተውን ልጅ እንዴት እንዳስነሣ ግያዝ ለንጉሡ በሚነግርበት ወቅት ነበር። ግያዝም፣ “ንጉሥ ጌታዬ ሆይ፤ ሴቲቱ ይህች ናት፤ ኤልሳዕ ከሞት ያስነሣው ልጇም ይህ ነው” አለ። ንጉሡም ስለ ስለዚሁ ጕዳይ ጠየቃትና ነገረችው። ከዚያም ንጉሡ፣ “የነበራትን ሁሉ እንዲሁም ትታ ከሄደችበት ጊዜ አንሥቶ እስካሁን ድረስ ያለውን የዕርሻዋን ሰብል በሙሉ እንድትመልስላት” ሲል አንድ ሹም አዘዘላት።

2 ነገሥት 8:1-6 መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) (አማ54)

ኤልሳዕም ልጅዋን ያስነሥላትን ሴት “አንቺ ከቤተ ሰብሽ ጋር ተነሥተሽ ሂጂ፤ በምታገኚውም ስፍራ ተቀመጪ፤ እግዚአብሔር ራብ ጠርቶአል፤ ሰባት ዓመትም በምድር ላይ ይመጣል፤” ብሎ ተናገራት። ሴቲቱም ተነሥታ እንደ እግዚአብሔር ሰው ቃል አደረገች፤ ከቤተሰብዋም ጋር ሄዳ በፍልስጥኤም አገር ሰባት ዓመት ተቀመጠች። ሰባቱም ዓመት በተፈጸመ ጊዜ ሴቲቱ ከፍልስጥኤም አገር ተመለሰች፤ ስለ ቤትዋና ስለ መሬትዋ ልትጮኽ ወደ ንጉሡ ወጣች። ንጉሡም ከእግዚአብሔር ሰው ሎሌ ከግያዝ ጋር “ኤልሳዕ ያደረገውን ተአምራት ሁሉ ንገረኝ፤” እያለ ይጫወት ነበር። እርሱም የሞተውን እንደ አስነሣ ለንጉሡ ሲናገር፥ እነሆ፥ ልጅዋን ያስነሣላት ሴት ስለ ቤትዋና ስለ መሬትዋ ወደ ንጉሥ ጮኸች፤ ግያዝም “ጌታዬ ንጉሥ ሆይ! ሴቲቱ ይህች ናት፤ ኤልሳዕም ያስነሣው ልጅዋ ይህ ነው፤” አለ። ንጉሡም ሴቲቱን ጠየቀ፤ ነገረችውም። ንጉሡም “የነበረላትን ሁሉ፥ መሬትዋንም ከተወች ጀምራ እስከ ዛሬ ድረስ ያለውን የእርሻዋን ፍሬ ሁሉ መልስላት፤” ብሎ ስለ እርስዋ ጃንደረባውን አዘዘ።

2 ነገሥት 8:1-6 አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም (አማ05)

ልጅዋን ከሞት ያስነሣላትን፥ በሱነም ትኖር የነበረችውን ሴት እነሆ፥ ኤልሳዕ አስቀድሞ እንዲህ ሲል ነግሮአት ነበር፥ “እግዚአብሔር እስከ ሰባት ዓመት የሚቈይ ራብ በዚህች ምድር ላይ ልኮአል፤ ከቤተሰብሽ ጋር በሕይወት ለመትረፍ ከዚህ ተነሥተሽ ወደ ሌላ ስፍራ ሂጂ።” ስለዚህም የኤልሳዕን ምክር ሰምታ ከነቤተሰብዋ ወደ ፍልስጥኤም አገር በመሰደድ እስከ ሰባት ዓመት ቈየች። ከሰባቱም የራብ ዓመቶች ፍጻሜ በኋላ ወደ እስራኤል ተመለሰች፤ መኖሪያ ቤትዋና የእርሻ መሬትዋ እንዲመለስላት ለመጠየቅ ወደ ንጉሡ ቀረበች። ንጉሡንም የኤልሳዕ አገልጋይ ከሆነው ከግያዝ ጋር ሲነጋገር አገኘችው፤ ንጉሡ ከግያዝ ጋር የሚነጋገረውም ኤልሳዕ ስላደረጋቸው ተአምራት ለማወቅ ፈልጎ ነበር፤ ኤልሳዕ የሞተ ሰው ማስነሣቱን ግያዝ ለንጉሡ በሚነግርበት ጊዜ ሴቲቱ መጥታ አቤቱታዋን ለንጉሡ አቀረበች፤ ግያዝ “ንጉሥ ሆይ! ሴትዮዋ እነሆ፥ ይህች ናት፤ ኤልሳዕ ከሞት ያስነሣውም ልጅዋ ይሄ ነው!” በማለት ለንጉሡ አስረዳ። ግያዝ ለንጉሡ የሰጠውን መልስ ሴትዮዋ ለንጉሡ እውነት መሆኑን አረጋገጠችለት፤ ስለዚህም ንጉሡ አንድ ባለሥልጣን ጠርቶ፥ የእርስዋ የሆነው ማናቸውም ነገርና እንዲሁም የእርሻ መሬትዋ በሰባት ዓመት ጊዜ ውስጥ ያስገኘው የእህል ሰብል ጭምር እንዲመለስላት ትእዛዝ ሰጠላት።

2 ነገሥት 8:1-6 መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) (መቅካእኤ)

ልጇን ከሞት ያስነሣላትን፥ በሱነም ትኖር የነበረችውን ሴት እነሆ፥ ኤልሳዕ አስቀድሞ እንዲህ ሲል ነግሮአት ነበር፥ “እግዚአብሔር እስከ ሰባት ዓመት የሚቆይ ራብ በዚህች ምድር ላይ ልኮአል፤ ከቤተሰብሽ ጋር በሕይወት ለመትረፍ ከዚህ ተነሥተሽ ወደ ሌላ ስፍራ ሂጂ።” ስለዚህም የኤልሳዕን ምክር ሰምታ ከነቤተሰብዋ ወደ ፍልስጥኤም አገር በመሰደድ እስከ ሰባት ዓመት ቆየች። ከሰባቱም የራብ ዓመቶች ፍጻሜ በኋላ ወደ እስራኤል ተመለሰች፤ መኖሪያ ቤትዋና የእርሻ መሬትዋ እንዲመለስላት ለመጠየቅ ወደ ንጉሡ ቀረበች። ንጉሡንም የኤልሳዕ አገልጋይ ከሆነው ከግያዝ ጋር ሲነጋገር አገኘችው፤ ንጉሡ ከግያዝ ጋር የሚነጋገረውም ኤልሳዕ ስላደረጋቸው ተአምራት ለማወቅ ፈልጎ ነበር፤ ኤልሳዕ የሞተ ሰው ማስነሣቱን ግያዝ ለንጉሡ በሚነግርበት ጊዜ ሴቲቱ መጥታ አቤቱታዋን ለንጉሡ አቀረበች፤ ግያዝ “ንጉሥ ሆይ! ሴትዮዋ እነሆ፥ ይህች ናት፤ ኤልሳዕ ከሞት ያስነሣውም ልጇ ይሄ ነው!” በማለት ለንጉሡ አስረዳ። ግያዝ ለንጉሡ የሰጠውን መልስ ሴትዮዋ ለንጉሡ እውነት መሆኑን አረጋገጠችለት፤ ስለዚህም ንጉሡ አንድ ባለ ሥልጣን ጠርቶ፥ የእርሷ የሆነው ማናቸውም ነገርና እንዲሁም የእርሻ መሬትዋ በሰባት ዓመት ጊዜ ውስጥ ያስገኘው የእህል ሰብል ጭምር እንዲመለስላት ትእዛዝ ሰጠላት።