ኤልሳዕም ልጅዋን ያስነሣላትን ሴት፥ “አንቺ ከቤተ ሰብሽ ጋር ተነሥተሽ ሂጂ፤ በምታገኚውም ስፍራ ተቀመጪ፤ እግዚአብሔር በምድር ራብን ጠርቶአልና፤ ሰባት ዓመትም በምድር ላይ ይቆያል” ብሎ ተናገራት። ሴቲቱም ተነሥታ ኤልሳዕ እንደ ነገራት አደረገች፤ ከቤተ ሰብዋም ጋር ሄዳ በፍልስጥኤም ሀገር ሰባት ዓመት ተቀመጠች። ሰባቱም ዓመት ካለፈ በኋላ ያች ሴት ከፍልስጥኤም ሀገር ተመለሰች፤ ሄዳም ስለ ቤቷና ስለ መሬቷ ልትጮህ ወደ ንጉሡ ወጣች። ንጉሡም የእግዚአብሔር ሰው የኤልሳዕ ሎሌ ግያዝን፥ “ኤልሳዕ ያደረገውን ታላላቅ ተአምራት ሁሉ ንገረኝ” እያለ ይነጋገር ነበር። እርሱም የሞተውን ሕፃን እንደ አስነሣ ለንጉሡ ሲናገር፥ እነሆ፥ ልጅዋን ያስነሣላት ያች ሴት መጥታ ስለ ቤቷና ስለ መሬቷ ወደ ንጉሥ ጮኸች፥ ግያዝም፥ “ጌታዬ ንጉሥ ሆይ፥ ሴቲቱ ይህች ናት፤ ኤልሳዕም ያስነሣው ልጅዋ ይህ ነው፤” አለ። ንጉሡም ሴቲቱን ጠየቃት፤ እርስዋም ነገረችው። ንጉሡም ከባለሟሎቹ አንዱን ሰጣት፤ “እህልዋንና ገንዘብዋን ሁሉ ሀገሩን ከተወች ጀምሮ እስከ ዛሬ ድረስ የሄደ ቦታዋን ሁሉ መልስላት” አለው።
መጽሐፈ ነገሥት ካልእ 8 ያንብቡ
ያጋሩ
ሁሉንም ሥሪቶች ያነጻጽሩ: መጽሐፈ ነገሥት ካልእ 8:1-6
ጥቅሶችን ያስቀምጡ፣ ያለበይነመረብ ያንብቡ፣ አጫጭር የትምህርት ቪዲዮዎችን ይመልከቱ እና ሌሎችም!
ቤት
መጽሐፍ ቅዱስ
እቅዶች
ቪዲዮዎች